Thursday, February 26, 2015

እምቢተኝነት

በአዋጅ የተደነገጉ የሕዝብን አሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመደራጀትና የመሰብሰብ እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን እየሸረሸሩና አዋጅን በተራ መመሪያ እየሻሩ የስቃይ ቀንበሩን ያከብዱበታል ፡፡በየትኛውም ሁኔታ ማለትም የሰብአዊ መብቱ የተረገጠውን፣ የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል ስላለ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታየ የሚሰቃየውን የነፃነት ታጋይ፣ በስርዓቱ ብልሹና የተዝረከረከ አሰራር በኑሮ ውድነት እየማቀቀ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለጥያቄው ተገቢውን መልስ ወይ መፈትሄ ከመስጠት ይልቅ በተራ ካድሬያዊ ዲስኩር ከላይ ለዘረኛው ስርዓት ቃል አቀባይ ከሆነው ጠ/ሚ ተብዬው እስከ ልማታዊ ጋዜጠኛ ነን እስከሚሉት ድረስ በርሃብ ለጠወለገው ምስኪን ሕዝብ ጥጋብን፣ በገዛ ሃገሩ ፍትህ አጥቶ ለሚሰቃየው ፍትሃዊነትን እንዲሁም ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ነፃነቱን ለተነጠቀው ሕዝብ ዴሞክራሲን ነጋ ጠባ ይሰብኩታል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን ጭቆና ጨምሮ ለመወያየትና መፍትሔዎችን ለመለዋወጥ የምንችልበት መድረክ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ራድዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ውስጥ ይኖረን ነበር፤ ስንት ሰው ሥራ ያገኝ ነበር፡፡

በኬኒያ የተያዙት ኢትዮጲያዊያን ተቀጡ

ከትናንት በስቲያ በኬኒያ ታሲያ በተባለ ግዛት መያዛቸው የተነገረው 101 ኢትዮጲያዊያኑን ስደተኞች በህደገወጥ መንገድ ወደኬኒያ ገብተዋል በሚል እስከ 50 ሺህ የኬኒያ ሽልንግ ቅጣት ተጣለባቸው፡፡ ኢትዮጲያዊያኑ ቅጣቱን ካልከፈሉ የአንድ አመት እስር ይጠብቃቸዋል ሲል ነው የኬኒያው እለታዊ ዴይሊ ኔሽን የጻፈው፡፡
ከኢትዮጲያዊያኑ ጋር ሶስት ኬንያዊያንም ፍርድ ቤት ቀርበው ለቅጣት መዳረጋቸው ተነግሯል፡፡ ኢትዮጲያዊያኑ ቅጣታቸውን እንደጨረሱ ወደሀገራቸው ይጋዛሉ። 
============= ወይኔ የሀገር ሰው ኬንያም በኛ ላይ እንዲህ ትዛበትብን ።
ባለቤት ያቀለለውን ባለዕዳ አይቀበለውም የሚባለው ተረት እንዲህ ነው ።
የኢትዮጵያውያን ሞት
የኢትዮጵያውያን ስደት ባሁኑ ጊዜ እንኳ ለማይመለከተው ለባዕዳን ለኛው ለራሳችን የተለማመድነው ከዓምላክ የወረደብን ነው ብለን የተቀበልነው ይመስላል ። በቁጭት ለምን ብለን ራሳችን አንጠይቅም ።
ማነው የሚሰደድ ፣ ?
ማነው የሚያሰድድ ?
ብለን ጠይቀናል?

የኤፈርት ባለቤት ማን ይሁን??

ምን አልባትም ከምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የኢኮኖሚ ኢምፓየር ኤፈርት ሳይሆን አይቀርም:: ማስተካከያ አለን ባዮች አስተያየት መስጫው ጋር ጠብቁኝ:: አዲሱ የትግራይ ብሄርተኝነት እንደየትኛውም ብሄር ተኮር ብሄርተኝነት የዘውጉን ጥቅም እስካስጠበቀ ድረስ በየትኛውም አይነት ሃገራዊ ኪሳራ ላይ ቢሆን ይደራደራል.......በአብሮነት ውስጥ ያሉትን መተሳሰሪያ ገመዶችን ቢገዘግዝ እንኩዋን ጠባብ የብሄርተኝነት ባህሪው ያንን እንዲያደርግ አይፈቅድለትም:: አንዱ በኦሮሞ ፈርስት አመንክዮ ላይ ያንጫጫን ይኅው ለብሄር ጥቅም የሚኬድበት መንገድ ሌሎችን አደጋ ላይ የማያስቀምጥ ለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ አለመቻሉ ነበር....(ይህ ማለት በሃገራዊነት ላይ ስላለው ስለማንቆጣጠረው የማንነትና ስሜት ቅድሚያ ሳይሆን ይህንን የኦሮሞ ቅድሚያነትን ለማረጋገጥ የሚኬድበት መንገድ ትግበራ(practicality) አነጋጋሪ የሚሆንበት አገባብ ስለሚኖር ነው...ቅድሚያ ለኔ የሚለው የዳርዌንያንን አስተምህሮ ስናስተውል) ::

ሐየሎም አረአያን ማን ገደለዉ?

አርአያ ተስፋማሪያም
“ኩሹፍ” ሲገለጥ
ጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም፣ ባለቤታቸውና ሌሎች አንገታቸው ላይ
ስላጠለቁት በተመለከተ አንድ የቀድሞ አንጋፋ የድርጅቱ ታጋይ
በግል ያደረሱኝ መልእክት እንዲህ ሲል ይጀምራል « በታጋዮች
ዘንድ “ኩሹፍ” ተብሎ ይጠራል። ታጋዩ ከሞተ በኋላ የሚገነዝበት
ጨርቅ ነው። ድርጅቱ አላማ ያለው የመሰለው አብዛኛው ታጋይ
ያን ጨርቅ አንገቱ ላይ በማጥለቅ ለመሰዋት (ለመሞት)
ቁርጠኝነቱን የሚያሳይበት ነበር። 98 በመቶ የሚሆነው ተዋጊ
ያልተማረ ስለነበረ የድርጅቱ አላማና አካሄድ ሊያውቅበት የሚችል
አንድም መንገድ አልነበረም። በእሱ ደምና አጥንት ተረማምደው
ሲያበቁ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ አስፈፀሙ።

ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፣ከኤርሚያስ ለገሰ /የመለስ ትሩፋቶች /የተሰጠ ምላሽ

ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ የፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ርግጥ በሐይማኖት ጉዳዬች ላይ መናገር ከባድ እንደሆነና ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንቅቄ አውቃለሁ ። በሌላ በኩል የሚያውቁትን አለመግለጵም የፀፀት ዋጋ አለው። በመሆኑም ባለመናገሬ ከሚሰማኝ ሙግት መናገሩን ስለመረጥኩ የሚከተለውን አጭር አስተያየት ለመስጠት ተገደድኩ።
1• ያቀረብከውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም። በተለይም በድህረና ቅድመ ምርጫ 97 ባሉት ሶስት አመታት( ከኃላም ከፊትም) ያቀረብካቸውን መረጃዎች ምንጭ ማወቅ እፈልጋለሁ ። ይህን ጥያቄ የማነሳበት መሰረታዊ ምክንያቶች ስላሉኝ ነው።

ስበር ዜና ፡ – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በተወረወረ ጫማ ተመቱ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ትላንት ፣ መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቤተ መቅደስ ከምእመናን አቅጣጫ በተወረወረ ቀይ ሸራ ጫማ መመታታቸው ታወቀ ፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩን ጫማ በመወርወር የመታው ግለሰብ አስቻለው ግቢ አናጋው ሲባል ፤ የወረወራቸው የኹለት እግሩ ጫማዎች አንዱ ቅዱስነታቸውን ሲመታ ሌላው የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ የኾኑትን ንቡረ እድ አባተ ጠምቀን መምታቱን በሥፍራው የነበረው ምንጫችን መመልከት ችሏል ፡፡
እንደምንጫችን ዘገባ ከኾነ ቅዱስ ፓትርያርኩን ጫማውን በመርወር የመታው አስቻለው ጫማውን እየወረወረ ‹‹ ሌባ ፤ የሌባ ወዳጅ ፤›› ሲል ተደምጧል ፡፡ ቅዱስነታቸውም በድንጋጤ ሲያማትቡ ታይተዋል ፡፡

Saturday, February 21, 2015

በስልጢ ለሳምንት የዘለቀው ቃጠሎ በደን ላይ ውድመት አደረሰ

አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው
በደቡብ ክልል ስልጢ ዞን ስልጢ ወረዳ ውስጥ በተፈጥሮ ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ ውድመት እየደረሰ መሆኑን ምንጮቻችን የጠቆሙ ሲሆን የወረዳው ግብርና ላይ በበኩሉ እሣቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቅሶ የአደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ ነው ብሏል፡፡

ምርጫ ቦርድ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ሰረዘ

ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ እንዲቆይ አይፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ እንደተሰረዙበት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በጋሞጎፋ፣ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ጎንደርና ጉጅን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ አንድን ዕጩ ለመሰረዝ የሚያበቃ ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር ‹‹ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ታዘናል›› በማለት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለክልል ምክር ቤቶች ያስመዘገብናቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎቹን በመሰረዝ ከምርጫው ውድድር ውጪ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ

ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡

Thursday, February 19, 2015

በሳውዲ የኢትዮጵያዊቷ የደመወዝ ጥያቄ ሽጉጥ አስመዘዘ የኢህአዴግ ዲፕሎማቶች መረጃ የላቸውም

eth woman in saudi1

ሳውዲ አረቢያ ቢሻ እየተባለ የሚጠራ አነስተኛ ከተማ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ በሳውዲያዊ አሰሪዋ ከተተኮሰባት ጥይት ከሞት መትረፏን ምንጮች አረጋገጡ። በዚህች ኢትዮጵያዊት ላይ ስለደረሰው የነፍስ ማጥፋት ጥቃት በኢህአዴግ ተመልምለው የተሰየሙት ዲፕሎማቶች ምንም ዓይነት መረጃ የላቸውም፡፡
አደጋው የደረሰባት ወጣት በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆኗን የሚናገሩ የዜናው አቀባዮች ወጣቷ  እንደተራራ የገዘፈውን ህይወት በመጋፈጥ ቤተስቦቿን ከችግር ለመታደግ በወቅቱ ከነበሩ የኤጀንሲ ደላላዎች ጋር ተዋውላ ሳውዲ አረቢያ ለስራ መምጣቷን ይናገራሉ።

“ይድረስ ከየካቲት ለግንቦት” የዶ/ር ነገደ ጎበዜ አዲስ መጽሐፍ

negede book

“. . . ይህንን የትግሉን ህዝባዊ ገፅታ ችላ ብለን እነዚህን ሚሊዮኖች የሚያካትት ህዝባዊ የትግል ማእበል ለመቀስቀስ፣ መቀስቀስ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችለን የጋራ ስትራቴጂ አውጥተን ካልተንቀሳቀስን በስተቀር “በእኛና በእነሱ” መሃከል negede bookበተወሰነ የትግል ክፈፍ ከብረት ድስትና ከሸክላ ድስት ፍልሚያ፤ ሸክላ በአሸናፊነት ይወጣል በሚል የአጉል ህልም ዓለም ውስጥ ነን ማለት ይሆናል፡፡” ዶ/ር ነገደ ጎበዜ
በምርጫ 97 ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ በፓርላማቸው ውስጥ ተቃዋሚዎችን ለመወንጀል እየተንጨረጨሩ ያነሱት ስም ነገደ ጎበዜ የሚለውን ነበር። ያ ስም እንደገና ተመልሶ መጥቷል። አሁንም ከመጽሐፍ ጋር ነው የመጣው። ዶ/ር ነገደ ጎበዜ “ይድረስ ከየካቲት ለግንቦት” የሚል አዲስ መጽሐፍ ይዘው መጥተዋል።

አኖሌ ሃውልት ፖለቲከኞችና የታሪክ ምሁራንን እያወዛገበ ነው

politicians and scholars
በምኒልክ ዘመን በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ተፈፅሟል የተባለውን የጡትና እጅ መቁረጥ ኢ-ሰብአዊ ድርጊትና ጭፍጨፋ ለማስታወስ በሚል በአርሲ አኖሌ አካባቢ በ20 ሚሊዮን ብር የተሰራው ሃውልት፣ በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድርን ጨምሮ በርካታ የኦህዴድ ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቋል፡፡
ሃውልቱን ያሰራው አካል ያለፈን ታሪክ መዞ ቂም በቀልን ለማውረስ ሳይሆን ቀጣዩ ትውልድ ከአስከፊው ድርጊት እንዲማርና ወደፊት ድርጊቱ እንዳይደገም ነው ሃውልቱ የተገነባው ብሏል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ምሁራን በበኩላቸው ለሁለት ተከፍለዋል፡፡ አንደኛው ወገን  ሃውልቱ በህዝቦች መካከል ቅራኔና ቂም በቀል የሚፈጥር ነው በማለት ሲቃወም ሌላው ወገን በበኩሉ ድርጊቱ ዳግመኛ እንዳይከሰት መማርያ እንጂ የበቀል አይደለም ሲሉ የሃውልቱን መቆም ይደግፋሉ፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፣ አወዛጋቢ በሆነው የአኖሌ ሃውልት ዙሪያ የታሪክ ምሁራንንና ፖለቲከኞችን አነጋግሮ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል፡፡

“ተፌ!”

tefera w

ታጋይ፣ ከንቲባ፣ መከላከያ ሚ/ር፣ ምክትል ጠ/ሚ/ር፣ አቅም ገንቢ፣ አቅም ተገንቢ … ከዚህ ሁሉ አልፈው አሁን አቅማቸው ተገንብቶ የስፔስ (ሕዋ) ሳይንስ “አቅም ግንባታ” ለመሆን የበቁት ጡረተኛው ተፈራ ዋልዋ “የኢትዮጵያን የሕዋ (ስፔስ) ሳይንስ ሶሳይቲን” ገንብተው በሪፖርተር በኩል ብቅ ብለዋል፡፡
“አቅም ገንቢ ሚ/ር” በነበሩበት ወቅት “ሂድና ከአባዱላ ተማር የአንተ አቅም ግንባታ እንኳን አቅም ሊገነባ ያለውንም ሊያስቀጥል አልቻለም” ተብለው በአቶ መለስ የተገመገሙት አቶ ተፈራ አቅማቸው ተገንብቶ ለስፔስ መድረሱን “ባለራዕዩ መሪ” ሳያዩና ሪፖርተር ላይ ሳያነቡ መሰዋታቸው አቶ ተፈራን እጀ ሰባራ አድርጓቸዋል፡፡

“ስኳር ለባለካርድ ብቻ” – ምርጫ ቦርድ

sugar and election board

የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ይሁን ባላንጣዎቻቸውን ወይም ከእርሳቸው የተለየ ሃሳብ የሚያመነጩትን “ስኳር ወዳድ”፣ “በስኳር የተታለለ”፣ … እያሉ ለእስር ሲዳርጉ የነበሩት አቶ መለስ፤ ሞት ሳይቀድማቸው በፊት ራሳቸው ያቋቋሙትና እርሳቸውን ደግሞ ደጋግሞ እያገላበጠ አንዴ ፕሬዚዳንት ሌላ ጊዜም ጠቅላይ እያደረገ ሲሾማቸው የኖረው “የምርጫ ቦርድ” ሕዝቡን በስኳር እየፈተነ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ “ስኳር” ቀምሰው ሳያውቁ ስለ ስኳር “አስከፊነት” ዘለግ ያለ መግለጫ በመስጠት ይታወቁ የነበሩት መለስ ለፓርቲያቸው መለያ “ንብ” መምረጣቸው በስኳር ላይ ያላቸውን ጥላቻ በትጋት ያሳየ እንደሆነ ታሪካቸው አሁንም ይመሰክራል፡፡ የሆነው ሆኖ ጓዶቻቸውን “በስኳር ወዳጅነት” ለእስር የዳረጉት መለስ እርሳቸው እየመላለሰ እንዲያነግሥ የመሠረቱት “የምርጫ ቦርድ” ሰሞኑን በ“አፍቅሮተ ስኳር” መጠመዱን ቢሰሙ ኖሮ ምን ይሉ ይሆን? ለማንኛውም እስካሁን በ“ስኳር” ተጠርጥሮ እስርቤት ያልወረደው “ምርጫ ቦርድ” ብቻ መሆኑ ሰሞኑን ነገረ ኢትዮጵያ በፌስቡክ ገጹ ላይ “የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች ስኳር እንዳይወስዱ ተከለከሉ” በሚል ያስነበበው ዜና ያስረዳል፡፡ እንዲህ ቀርቧል፡-

ሀብታችን ነጻነት እንጂ ባቡር አይደለም! (ቢንያም ግዛው)

አሁን አሁን እጅግ እየከፋ የመጣው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ፀረ ዴሞክራሲ እና ፀረ ሰላም መሆኑ በይበልጥ ግልጥ እየሆነ ከቀን ወደ ቀን እየተሰፈረ ያለው የግፍ ፅዋ ሞልቶ የመፍሰሱ ጉዳይ አለም ሁሉ የሚያውቀው የወቅቱ ዘገባ ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየጋመ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ መከራና ግፍ እየተቀበለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ወያኔ ባቡር አሳይቶ ህዝብን ለማሳቅ መሞከሩ ትውልድን እንደህጻን ቆጥሮ በብልጭልጭ ነገር እያባበሉ ማስተኛትን ይመስላል። መጽሀፍ ስለ ሰይጣን ሲናገር እንደ ብርሀን መልዐክ ለመግደልና ለማሳሳት ራሱን ይለውጣል ይላል። ታዲያ ቢያብለጨልጭ ለመግደል ብቻ መሆኑ ደግሞ ሊታሰብበት ይገባል።
ስለ ሶርያ ጥቂት ነገር እናንሳ። ጥንታዊ እና ስልጣኔ የጀመረባት ሀገር እንደነበረች በከብት እርባታ እና በእርሻ ዘመናዊ ሁኔታዎች የበቀሉባት ስለመሆንዋ ተወስቶላታል። ቀደምት ተብላ እንደመጠራቷም ሀገሪቷ ከ100 አመታት በፊት በቱርክ ግዛት ስር ሆና ደማስቆን እና የቤሩትን የወደብ ከተሞች የሚያካልል ሀዲድ ተዘርግቶ የባቡር መጓጓዣ አገልግሎት ተጠቃሚም ሆናለች። ከዚያም በመነሳት ነጻነቷን አውጃ ራስዋን ማስተዳደር ስትጀምር የዛሬ 60 አመት በፊት 1956 እ.ኤ.አ ሞደርን ሲኤፍኤስ ፓሴንጀር ትሬን በማለት አዲስ መዋቅር አበጅታ እስከ 2012 ተገልግላበታለች። አሁን ያ ያላት መልካም ገጽታ እና ታሪኳ እንዲሁም ከሁሉ በፊት ባቡር ነጂ መሆናዋ ከመሰባበር አላዳናትም።

ኢትዮጵያ ውስጥ የስፖርት ጋዜጠኛ ወይስ ተርጓሚ ነው ያለው? (ሁኔ አቢሲኒያ)

Addis-Ababa-Stadium
“የምን ማራዶና የምን ፔሌ ፔሌ 
እኛም አገር አለ ገብረመድኅን ኃይሌ”
ደምሴ ዳምጤ ጎልታ የምትጠቀስለት መንቶ ግጥሙ ነበረች፡፡ ለአገሪቱ ስፖርት ዕድገት በተለይም እግር ኳሱ እንዲያብብ በሙያው ያደረገው ጥረት ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ክሂላቸው ከማንም እንደማያንስ በማንፀባረቅ ነበር፡፡ በ1970ዎቹ መጨረሻና በ80ዎቹ መጀመርያ ጎልተው ወጥተው የነበሩት እነሙሉጌታ ከበደ፣ ሙሉጌታ ወልደየስ፣ ገብረመድኅን ኃይሌን ሲያወድስ ገጣሚ ሆኖ በመገኘት ነበር፡፡
ስፖርት እንደ አንድ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ምጣኔ-ሃብታዊ ጉዳይ ራሱን የቻለ ሰፊ ርዕሰ ጉዳይ እየሆነ የመጣ ሲሆን ሊሰጠው የሚገባው ግምትም ያን ያህል እየከበደ መጥቷል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ምጣኔ-ሃብታዊ ጉዳዮች ብቻ የሚተነትኑ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዳሉ ሁሉ ስፖርታዊ ጉዳዮችን ብቻ የሚተነትኑ ጋዜጦች፣ ሬድዮኖች፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ ድረ-ገጾች እና ሌሎች መገናኛ ብዙሃን በርካታ ናቸው፡፡

ላልቀረልን ሀገርንና ሕዝብን የመታደግ ትግል ተነሡ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ሥልጣንን ይዞ ሀገርንና ሕዝብን ለማሥተዳደር ሁለት የትግል አማራጮች አሉ፡፡ በሀገራችን ሁለቱም ዓይነቶች በሚገባ ይታወቃሉ ተሞክረዋልም፡፡  አንደኛው ሕዝብ በሚያደርገው ምርጫ የመንግሥትነት ሥልጣንን መያዝ መሠረቱ ያደረገው ሰላማዊ የትግል አማራጭ ሲሆን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ይህ ሰላማዊ የትግል አማራጭ ዝግ ሲሆን ወይም ሊሠራ በማይችልበት ጊዜ በሕዝብ ላይ በኃይል የተጫነን አንባገነን አገዛዝን በኃይል ለማስወገድ የሚደረግ የኃይል እንቅስቃሴዎችን መሠረቱ ያደረገ የትጥቅ ወይም የዐመፅ የትግል አማራጭ ነው፡፡ እስኪ ሰላማዊው የትግል አማራጭ በዘመነ ወያኔ ምን እንደሚመስል በአጭሩ ዕንይ፡፡
ወያኔና ምርጫ፡-
በዘመነ ወያኔ ምርጫ እየተባለ ለአራት ጊዜያት ያህል በሕዝብና በሀገር ላይ ከባድ ቀልድና ሹፈት ሲቀለድና ሲሾፍ ሲፌዝ ተቆይቷል አሁን ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ እየተሾፈና እየተቀለደ ይገኛል፡፡ በዘመነ ወያኔ ምርጫ ተደርጎ አያውቅም፡፡ ይህ ሐቅ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (State department) እስከ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ድረስ በሚሰጧቸው መግለጫዎች በተደጋጋሚ ያረጋገጡት ሀቅ ነው፡፡ ዐይኑን ጨፍኖ ለመሞኘት የፈቀደ ካልሆነ በስተቀር በሁሉም ዜጋም በሚገባ ይታወቃል፡፡ አገዛዙ ፍትሐዊና ትክክለኛ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አቅም ፍላጎትና ተፈጥሮ ከቶውንም ኖሮት አያውቅም መቸምም ደግሞ አይኖረውም፡፡

እውን ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚደነቅ የሚከበር ነገር አለውን? (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

tplf addis

በእስካሁኑ ግፍ ያልጠፋኸው ነገር ግን ለማይቀርልህ ወገኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! እንኳን ለአጥፊህ ለወያኔ ሐርነት ትግራይ 40ኛ ዓመት የልደት በዓል አደረሰህ! የዚህች ሀገር ነቀርሳ በውስጧ የበቀለበት 40ኛ ዓመት እነሆ ከነገ ወዲያ እሮብ የካቲት 11 2007ዓ.ም. ይከበራል፡፡
ግን ወያኔ ማን ነው? እውን የሚከበር የሚያኮራ ማንነት አለው? ነው ወይስ የሚረገምና የሚያሳፍር? ከዚህ ቡድን ውስጣዊ ታሪክ እንደምንረዳው ይህ ቡድን በርዕዮተ ዓለምና በአስተሳሰብ ልዩነት በግል ጥቅምና በሥልጣን ሽኩቻ አንዱ ሌላውን እየበላ አንዱ በሌላው እየተበላ እርስ በእርስ እንደ አውሬ እየተባላ እየተጠፋፋ በመጨረሻ በአውሬነቱ የበረታው የበረታው አስከፊው አስከፊው ቀርቶና ተቧድኖ ለዚህ የደረሰ እኩይ ሰይጣናዊ ቡድን ነው፡፡

“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” ይላል​ የአባ ማትያስ የግብፅ ጉብኝት:- የፖለቲካ ተልእኮ ክፍል አንድ

Ethiopia-Mathias-I-Egypt-Pope-Tawadros-II-meet-in-Cairo
“ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል” የሚለው ጥሬ ንባብ፤ ስለ ጅብና ስለ ቁርበት መልእክት ለማስተላለፍ አይደለም። ጅቡ የሚወክለው አካል አለ። ቁርበቱ የሚወክለው ነገር አለ። በቁርበቱና በጅቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ሳያውቁ ቁርበቱን ለጅቡ ያነጠፉለትም የሚወክሉት አለ። ይህ አገላለጽ በኢትዮጵያዊው ቅኔ ትምህርት፣ ቀመር፣ ስልት ሲመዘን፤ ጅቡ ሰም ነው። ቆርበቱም ሰም ነው። ሁሉም ሰም ነው። ወርቁ ከሰሙ ጋራ ጎን ለጎን ባለመቀመጡ፤ ወርቅ የጎደለው ‘ሰማ-ሰም’ ይባላል።

ምን እየጠበቅን ነው?

"የትግራይ ሪፑብሊክ ድንበር አል-ወሃ ድረስ ነው"
tigray map

የትግሬ ወያኔ በኃሣብ፣ በዕቅድ እና በተግባር ፀረ-ዐማራ፣ ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሆነ ድርጅት መሆኑን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ያረጋገጠው ሃቅ ነው። ሠሞኑንም ከመገናኛ ብዙሃን የሚደመጠው «የትግራይ ድንበር አል-ውሃ ድረስ ነው» የሚለው ወሬ የዚሁ የሚጠበቀው የትግሬ-ወያኔ ተከታይ እርምጃ እንደሆነ አያጠያይቅም።
ኢትዮጵያን የማፈራረሱ የንድፈ-ኃሣብ መሠረት የተጣለው በተለያዩ የውጭ ኃይሎች እንደሆነ ይታወቃል። ከእነዚህ መካከል ሮማን ፕሮቻዝካ የተባለው የኦስትርያ-ሐንጋሪ መሥፍን (Baron Roman Prochazka) ወጥነት ባለው መንገድ አዘጋጅቶ ያሠራጨው መጽሐፍ ዋና ተጠቃሽ ነው።

Monday, February 16, 2015

በደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ ለሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች መታወቂያ እድሳት ያደረገው የሀርቡ ከተማ 01 ቀበሌ ስራ አስኪያጅ ማህተምና ሌሎች ዶክሜንቶችን እንዲያስረክብ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ – ኮምቦልቻ
በደቡብ ወሎ የቃሉ ወረዳ የክልልና የፌደራል እጩዎች ለምርጫ ቦርድ ማስረጃቸውን ሊያስገቡና ለማሳወቅ ወደ ምርጫ ቦርድ በሄዱበት ወቅት የመታወቂያ እድሳት እንደሚያስፈልጋቸው በተገለፀላቸው መሰረት ወደሚኖሩበት ሀርቡ ከተማ 01 ቀበሌ በመሄድ መታወቂያቸውን አሳድሰው ይመለሳሉ፡፡ ይህ በተደረገ በሁለተኛው ቀን መታወቂያውን ያደሰውን ቴድሮስ የተባለ የቀበሌው ስራ አስኪያጅ በቀበሌው ካድሬዎች ተጠርቶ ‹‹መታወቂያ ለተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች አድሰሀል፤ …..አንተ ባታድስላቸው ኖሮ እጩ ማሳወቂያው ቀን ሊጠናቀቅ የቀረው አንድ ቀን በመሆኑ ላይመዘገቡ ይችሉ ነበር፤ …..ስለዚህ ተቃዋሚዎችን በመርዳትህና በመተባበርህ፤ በቀጣይነትም በሀላፊነት ለመስራት እምነት ስለማይጣልብህ ማህተምና ሌሎች ሰነዶችን ባስቸኳይእንድታስረክብ ›› መባሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው! – ‎ምንሊክ ሳልሳዊ

ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።

‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ!
ምርጫ ቦርድ በየወረዳው ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ‹‹ከቦርድ የሚጠበቅ ውሳኔ ስላለ፣ ሰኞ ተሰብስበን እስክንወስን ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎቹን ወደ ቅጽ 4 እንዳታዘዋውሩ›› የሚል መልዕክት ማስተላለፉን እና ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ከመቀነስ ጀምሮ ፓርቲውን ከምርጫው ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ከምርጫ አስፈጻሚዎች መረጃዎች ደርሰውናል ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

እየከፋ በመጣው የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ የጋራ አቋም መግለጫ

«ለውጥ በማይቆም ተሽከርካሪ የሚጓዝ አይደለም፤ የተከታታይ ትግል ውጤት ነው። ነጻነት የምንፈልግ ሁሉ ጀርባችንን ቀና አድርገን መታገል አለብን። ራሳችን ካልፈቀድንለትና ካልተሸማቀቅን፤ ማንም ሰው እንደ ከብት ሊጋልበን ከቶ አይችልም” ነበር ያሉት ዶር ማርቲን ሉዘር ኪንግ ጁኔር ።
በማንኛውም አገር ቢሆን፣ ነጻ የሆነ የዜና አገልግሎት የማያገኝ፤ ተቆርቋሪ የፖለቲካ ወይንም የማህበረሰብ ወይንም የሲቪክ ድርጅት እና በነጻነት የሚንቀሳቀስ የመገናኛ ብዙሃን አገልግሎች የሌለው ሕዝብ መብት የለውም። መብቱ በመንግሥት የተከለከለ ግለሰብ ሆነ ቡድን፤ ማህበረሰብ ሆነ ሕብረተሰብ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው እድገት አይጎናፀፍም።
ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለሃያ አራት ዓመታት በበላይነት ሲገዛት የቆየችዋ ኢትዮጵያችን ፍትህ፤ ነጻነት፤ ሰብአዊ መብት፤ የሕግ የበላይነት የማይታይባትና አምባገነናዊ ስርዓት የሰፈነባት ሃገር ሆናለች። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ የመድበል ፓርቲ ስርዓት የምትከተል መሆኗ በሕግ መንግስቱ ቢደነገግም፣ በተግባር የታየው ግን ከገዝው ሕወሃት/ኢሕአዴግ ነጻ የሆኑ ድርጅቶችን ሁሉ የማጥፋት ሂደት ነው። የአገሪቷን ሕግ ሆነ የምርጫ ቦርድን አሰራር በጣሰ መልኩ፣ በቅርቡ በአገሪቷ ጠንካራ የሚባለውን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) አመራርን በማገድ ራሱ ያቋቋማቸዉን ተለጣፊ መሪወች መሾሙ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በምርጫ የማያምንና፣ ብቻውን ለሚቀጥሉት ሃያ፤ ሰላሳ አመታት በጉልበት ለመግዛት እንደወሰነ አመላካች ነው። የዜጎችን የመደራጅትና የመሰባሰብ ሰባአዊ መብትም የረገጠ ነው።

አምባገነን ብሔር የለውም !! - አሌክስ አብርሃም

ሰሞኑን የህወሃት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመላው ኢትዮጲያ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በቅድሚያ እንኳን ለአርባኛው አመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ እላለሁ ፡፡ በትጥቅ ትግሉም ወቅት ሆነ ከትጥቅ ትግሉ በኋላ ይህን ቀን ለማየት ሳይታደሉ ያለፉ ብዙዎች ናቸውና ምንም ይሁን ምን ለዚህ ቀን መብቃት ትልቅ ነገር እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡ ይህን ፅሁፍ የምፅፈው በተወለድኩባት ባደኩባትና አሁንም እየኖርኩባት ባለችው ኢትዮጲያ ከተመሰረተ ድፍን 40 ዓመት ያስቆጠረ ጎልማሳ የፖለቲካ ድርጅት ላይ እንደአንድ ዜጋ ያለኝን ቅሬታ ለማሳወቅ ነው ፡፡
ሰሞኑን የድርጅቱን 40ኛ ዓመት በዓል በቴሌቪዥን በሬዲዮ እንዲሁም ከመሃበራዊ ድረ ገፆች ላይ ስመለከት እንዲሁም አገሪቱ ላይ ያለውን ተጨባጭ ችግር ስታዘብ ሳልፈልገው አእምሮየ ታሪክ እየመዘዘ ይሞግተኛል ፡፡ ባጭሩ ይህ በዓል በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ምን ያህል ነው ብየ ሳስብ ከግራና ቀኝ ከህዝቡ የሚሰነዘረውን ትችት አስተያየትና ምሬት ስመለከት በዓሉን ለብቻችሁ እያከበራችሁት ነው የሚል ስጋት ፈጥሮብኛል ፡፡

ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ” ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ” ያወጣው ጽሁፍ

ጋዜጣ (ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው
minilikኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።

አባይ ጸሐዬ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የዛቱበት ድምጽ ተለቀቀ – “በአ.አ. ማስተር ፕላን ላይ ዳግም ጥያቄ ካነሱ ልክ እናስገባቸዋለን” አሉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ም እመናንን ለሁለት በመክፈል የኢሕአዴግን የስልጣን ዘመን ያረዘሙት ሕወሓቱ አባይ ጸሃዬ ሰሞኑን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ዛቱ:: ድምጻቸው ተቀርጾም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ በኩል ለሕዝብ ይፋ ሆነ:: አባይ ጸሓዬ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ጉዳይ እንዲራዘም የተደረገው ሕዝቡ ባነሳው ተቃውሞ እንዳልሆነ ገልጸው በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸዋል::
የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዳይሳካ የኦህዴድ ባለስልጣናትም ተባብረዋል ያሉት አባይ ጸሓዬ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ማስፋፊያ ዙሪያ ዳግመኛ ጥያቄ የሚያነሱትን ልክ እናስገባቸዋለን ብለዋል::
ከኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የተገኘው ዜና የሚከተለው ነው::

እኔም ቀንቶኝ ወይዘሪት ነፃነትን የምስመው መቼ ይሆን?

ነፃነት ዘለቀ አንዳንድ  ሰዎች በዕድል ያምናሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በሥራ ብቻ  የሚያምኑ አሉ፡፡ ጥቂቶች በሥራም በዕድልም ያምናሉ፡፡ የኔ ምድብ ከነዚህኞቹ ነው፡፡ አንድ ሰው መቶ ዓመትም ቢለፋና ቢደክም በጥረቱ ላይ መጠነኛ ዕድል ካልታከለበት ሊሣካለት የመቻሉ አጋጣሚ አናሳ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እንደኔ አስተሳሰብና እምነት ዕድል ያልተጨመረበት ጥረት ሥምረቱ የልብ የሚያደርስ አይሆንም፡፡ የአንዱ ወይ የሌላው ባሪያ መሆን እንደማይገባ ግን እረዳለሁ፡፡ ለአንድ ዓላማ ሥኬት መልፋትና መድከም ይገባል፡፡ ዕድል ሲሰምር የልፋት ውጤት ያማረ ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ ግን በተለያዩ አቋራጭ መንገዶችና በሙስና የሚገኝን ሀብት በዕድል ወይም በጥረት እንደተገኘ መቁጠር አይቻልም፡፡

የክፋት ዘመን ምን ያህል ይረዝማል?

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ (ከአዲስ አበባ – ma74085@gmail.com)
… ነቢዩ ዳንኤል በተናገረው መሠረት የሚያረክሰውን አፀያፊ ነገር በተቀደሰ ሥፍራ ቆሞ ታዩታላችሁ፡፡ … በዚያን ጊዜ ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ እመጫቶች ወዮላቸው፡፡ … ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያልሆነ፣ ወደፊትም እርሱን የሚመስል ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይመጣል፡፡ እነዚያ ቀኖች ባያጥሩማ ኖሮ አንድም ሰው መዳን ባልቻለ ነበር፤ ነገር ግን ስለተመረጡት ሰዎች [ሲባል] እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ማቴ. 24
road
ሎሬት ፀጋየ ገ/መድኅን “ረሀብ ስንት ቀን ይፈጃል?” በሚል ርዕስ ስለርሀብ ማለፊያ ግጥም አስነብቦናል – ያኔ በደጉ ዘመን፡፡ የክፋትስ ዘመን ምን ያህል ይሆን? ብለን ደግሞ እኛው ለኛው እንጠይቅ፡፡ 17? 23? 40? 100? 1000 ወይንስ ከዚህም በላይ? የክፋትንና የመልካም ዘመናትን መጥባትና ማክተምስ የሚቆጣጠረው አካል ማን ነው? የፍትህ ሚዛኑስ ምን ያህል ምክንያታዊ ነው? የት ሆኖና በምን አግባብና መለኪያስ ነው ቁጥጥሩን የሚያደርገው? እስኪ ከምንገኝበት ሸውራራ ዳይሜንሽን ወጣ ያለ ጥያቄ እንጠይቅ፡፡ መልስ ሰጭ ባይገኝም መጠየቁ አይከፋም፡፡ የኔቢጤው “ፍጠረኝ ሳልለው ፈጥሮኝ ለመከራ፤ ይሄው እበላለሁ የመከራ እንጀራ” ያለው ወዶ እንዳልሆነ ያጤኗል፡፡ሰው ካልመረረው ሽቅብ አንጋጦ የበላይን(ፈጣሪን) አይወቅስም፤ አያማርርምም፡፡

ኦህዴድና ስሙን የቀየረው ኢህዴን – ሰይፈ ምካኤል

ኦሮሚያን የሚመራው ዛሬ በርካታ ለውጦችን አስመዝግቦአል ይህን ስል ህወሀት ከፈጠራቸው ድርጅቶች ሀቁ “ከዝንጀሮ ቆንጆ. . . “ የሚባለው እንደተጠበቀ መሆኑ ይታወቅልኝ ማለትም ሁሉም ገዳዮች ዘራፊዎችና የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸውን ዘንግቼው አይደለም። _የአማርኛ መጠሪያ የነበራቸውን የቦታ ስሞች ወደ ኦሮምኛ ለውጥቶታል _በከፊል በኦሮሞ ታሪክ ጎልተው በሚታዩ ጉዳዮች ደግሞ የፈጠራ ተረት ላይ ተመርኩዞ የት/ት ስራት ያካሂዳል _የክልሉ ሕዝብ 88% ብቻ ኦሮሞ ሆኖ ሳለ በክልሉ ሕገ-መንግስት ቕንቕን በተመለከተ ኦሮምኛ ግዛትን አስመልክቶ ደግሞ ክልሉ ውስጥ ያሉ ሌሎች ብሔረሰቦች ራሳቸውን በቕንቕቸው እንዳይማሩና የመገንጠል መብት እንዳ ይኖራቸው ድንጋጌ አውጥቶአል _የኦሮሞ ክልል ስፋት ወደፊት በሂደት ከሌሎች ክልሎች ወደ ኦሮሚያ የሚካተቱ መሬቶችን ያካትታል ይላል _በርካታ አስፋልት የተላበሱ መንገዶች ወያኔን አግባብቶ አስገንብቶአል እያስገነባም ይግኛል

ተሂዶበት ከሚፈለገው ቦታ ባላደረሰ መንገድ ተመላልሶ መጓዝ ችግሩ የመንገዱ ሣይሆን የተጓዡ ነው

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ረቡዕ የካቲት ፭ ቀን ፪ሺህ፯  ዓ.ም.                       ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፲   ሰሞኑን የትግሬ-ወያኔ እጀታ የሆነው የምርጫ ቦርድ፣ በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና በአንድነት ለፍትሕና ዲሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ላይ «ከምርጫ ውድድር የማገድ» ውሣኔ ማሣለፉን ሰምተናል። ይህም ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤቶች፣ ፖሊስ፣ አቃቢ ሕግ፣ መከላከያ ሠራዊቱ እና መሰል በ«ሕገ-መንግሥቱ ተቋቋሙ» የተባሉት ተቋሞች በሞላ የወያኔ ሕዝባዊ ድርጅቶች መሆናቸውን በይፋ እና በማያሻማ መንገድ ከታዩባቸው አያሌ ተግባሮች መካከል አንዱ ሆኖ የሚጠቀስ ነው። የምርጫ ቦርዱ ውሣኔ በራሱ ምርጫ ቦርድ የወያኔ ሕዝባዊ ድርጅትና እጀታ ከመሆኑ የመነጨ ብቻ ሣይሆን፣ የተቃዋሚው ጎራ ደጋግሞ በሄደበት እና ምንም ዓይነት ውጤት ባላስመዘገበበት መንገድ መጓዙ ጭምር እንደሆነ ሊስተዋል ይገባል። የትግሬ-ወያኔ በምርጫ ተሸንፎ ሥልጣን እንደማይለቅ ያለፉት አራት የይስሙላ ምርጫዎች ከበቂ በላይ ነቃሾች ናቸው።

ሀብታችን ነጻነት እንጂ ባቡር አይደለም

አሁን አሁን እጅግ እየከፋ የመጣው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ፀረ ዴሞክራሲ እና ፀረ ሰላም መሆኑ በይበልጥ ግልጥ እየሆነ ከቀን ወደ ቀን እየተሰፈረ ያለው የግፍ ፅዋ ሞልቶ የመፍሰሱ ጉዳይ አለም ሁሉ የሚያውቀው የወቅቱ ዘገባ ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየጋመ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ መከራና ግፍ እየተቀበለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ወያኔ ባቡር አሳይቶ ህዝብን ለማሳቅ መሞከሩ ትውልድን እንደህጻን ቆጥሮ በብልጭልጭ ነገር እያባበሉ ማስተኛትን ይመስላል። መጽሀፍ ስለ ሰይጣን ሲናገር እንደ ብርሀን መልዐክ ለመግደልና ለማሳሳት ራሱን ይለውጣል ይላል። ታዲያ ቢያብለጨልጭ ለመግደል ብቻ መሆኑ ደግሞ ሊታሰብበት ይገባል።

የደፈረኝና ፤ የደፈረችኝ እሰጥ አገባ – ከመኳንንት ታዬ (ፀሃፊ)

ይህ ትውልድ ሃይል በእጁ ከመያዙም በላይ እውነትን የሚበረብርበት መንሽ በእጁ ስለመኖሩ አያጠያይቅም።በዚህ ሄደት የጉዞ ውጣ ውረድ ውስጥ ስለሚያስፈልገውና ፤ ስለሚፈልገው ነገር እያሰበም እያወራም የመኖሩ ሚስጥር ዛሬ ላይ ስለደረሰበት የስልጣኔ ደረጃም ብቻ ሳይሆን አልፎ አልፎም ምን ከእርሱ እንደሚጠበቅ ከመዘንጋት የመነጨም ነው።ይሁንና ዛሬ ይህችን መጣጥፍ እንድከትባት ያነሳሳኝ አንዳች ነገር በዚሁ በእኔ መኖሪያ አካባቢ የደፈረኝና ፤የደፈረችኝ እሰጥ አገባ በቪኦኤ ከተሰማ በኋላ በየማህበራዊ መድረኩ ብዙ ሲባል መከረሙንም ተከትዬ ብሎም ፓስትር ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት ሲጠየቁ ከሰጧቸው አስተያየት በመነሳትም ጭምር ነው ።
pastor
ይኸውም የዚህ አይነቱ ችግር መኖሾ ምን እንደሆነ ሲገልፁ ከተጠቀሙበት ቋንቋ እንጀምርና “ወሳኝ የሆነ ክፍተት እንዳለ የሚጠቁም ነው” ከሚለው እንነሳ ።እርግጥ ነው በማንኛው ግዜና በማንኛውም ቦታ ያለ ስጋ ለባሽ ሰው ፈተና ያጋጥመዋል ።የፓስተር ተከስተም ከዚህ ያለፈ ሊሆን እንደማይችል መገመት መፅሃፍ ቅዱስን ላነበበ ብዙ አይከብድም።ቅ.ዳዊትን እና ልጁን ማስታወስ በቂ ነውና ።ነገር ግን የክፍተቶቹ ምክንያቶችና አንድ ፓስተር (ሰባኪ) ወደቦታው በሚመጣበት ግዜ አስቀድመው በሱ ዙሪያ መታየት ያለባቸው ምግባሮች ምንድናቸው ?ዶ/ር ቶሎሳ ካነሱአቸው ነጥቦች ውስጥ ተወዳጅነት ፤ታዋቂነት ፤ተጠያቂነት የሚሉት አሉበት ።እንኝህን ነጥቦች በሚያሟለበት ግዜ ታዋቂነትና ተወዳጅነቱ በምን ዙሪያ ላይ ነው?። የሚለውን ስበን ያወጣን እንደሆነ ለራሱ ካለው ትልቅ ግምት የተነሳ የተሻለ መሆኑን ለማስረዳት አንድ ፓስትር ወደ ስብከት በሚመጣበት ግዜ በስፋት ሚያዘውትረው ስብከቱ የድህንነት ጉዳይ ላይ ወይስ በሌላው ሃይመኖት ዙሪያ ላይ ያልተገቡ ዙሪያዎችን መዞር ።

ዲሞክራሲአዊቷ አገር ጥምር ሪከርድ ሰበረች። -ከ-ከተማ ዋቅጅራ

መቼስ ሪከርድ ተሰበረ ስል ቀነኒሳ በቀለ ወይም መሰረት ደፋር ወይም ጥሩነሽ ዲባባ አልያም ገንዘቤ ዲባባ ሌላም ሌላም ብላችሁ ግምታችሁን ለአትሌቶቻችን እንደምትሰጡ ተስፋ አደርጋለው። የምነግራችሁ ግን በአትሌቶቻችን የተሰበረ ሪከርድ አይደለም። ዲሞክራት ከሆኑ አገሮች መኃል በዲሞክራቷ የተሰበረ ሪከርድ ነው። ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ነገሰባት እየተባለች የሚነገርባት ለዚች አገር ዲሞክራሲ አመጣን የሚሉትም የሚዘፍኑላት ከበሮ  ድድም ድድም ደርብ ደርብ ተብሎ የሚጨፈርላት አገር.. የዲሞክራሲ ውጤቶችን በከፊል እንይ።

ዘንድሮ ምርጫ ያለ አይመስልም፣ አዲስ አበባም እንቅልፍ ላይ ናት -በላይ ማናዬ

አዲስ አበባ ከዛሬ ነገ ትነቃለች ተብላ ብትጠበቅም እንቅልፍ ውስጥ ናት፡፡ ጭልጥ ብላ ተኝታለች፡፡ 10 ዓመት ሙሉ እንቅልፍ ያልሰለቻት ከተማ ብትኖር አዲስ አበባ ናት፡፡ የዛሬ 10 ዓመት በዚህ ወቅት ከተማዋ የምር ንቁ ሆና ነበር፡፡ እድሜ ለቅንጅትና ለህብረት እንጂ ያኔ በዚህ ወቅት ላይ አዲስ አበባ በየዕለቱ አዲስ ክስተትን ታስተናግድ ነበር፡፡ ያኔ ሸገር እንቅልፍ አልነበራትም፤ የፖለቲካ ግለት ውስጥ ነበረች፡፡ አሁን ላይ ያቺ ግለታም ከተማ እንቅልፍ ላይ ነች፡፡ ምርጫ እንደሁ የአንድ ቀን ክንውን ነው፡፡ ዳሩ ግን የምርጫ ጣዕሙ ሂደቱ ነው፡፡ ሂደት ያለው ምርጫ ከተማን ቀርቶ ገጠርን አያስተኛም፤ ግለታም ነው፡፡ ሂደት ያለው ምርጫ ልክ እንደ 1997 ዓ.ም ምርጫ ወቅት ሀገርን ያነቃቃል፤ ድብርትን ይገፍፋል፡፡ በተለይማ እንደ አዲስ አበባ ያሉ ከተሞች ሂደት ባለው ምርጫ እንቅልፍ አይኖራቸውም፡፡ ዘንድሮ ግን ምርጫ ያለ አይመስልም፡፡ ምርጫ አለ ከተባለም ሂደት የሌለው ምርጫ ነው ማለት ነው፡፡

እናንተ ለአገልግሎት ነበር። እነሱ ዘበኛ ነው የሚፈልጉት። – ዳዊት ዳባ

እርጉዝ ነኝ እያለችህ ሴትን ልጅ ሆዷን ረግጠህ ፅንስ አስወረድክ። አሮጊትና ሽማግሌ በጫማ ጥፊ ሳይቀር የሚደበድቡ  አሉ።  አንድን ሚስኪን ወገን አስርና አስራ አምስት ሆነው ለጉድ ሲቀጠቅጡም በተደጋጋሚ አየን። መፍክር ብቻ በጁ ይዞ የጋራ ለሆነ መብትና በደል  ሊያሰማ አደባባይ የወጣ ዜጋ  አቅማቸውን ለማሳየት በብዙ ቁጥር ደግሞ ስልጠናችውን የጠቀማሉ። የማጥቂያ እቅድ ይሰጣቸዋል። ቆረጣው፤ ከብባአድርገው፤ አደፍጠው ብቻ ያለ ወታደራዊ እውቀት ሁሉ ተፈፃሚ ማድረጉ እንዳቅሚቲ  አይቀራቸውም ። ይህ ሁሉ መሀል ከተማ  አዲስ አበባ ውስጥም ነው እየተፈፀመ ያለው። በዚህ ሰሞን እንደገና አገረሸ እንጂ ይህን አይነቱ ታሪክ ሀያ አራት አመት አለው። ብዙ ንፅሁን ዜጎች መገደላቸውን፤ አካለ ጎዶሎ መሆናቸውንና ስብእናቸው መደፈሩ ተመዝግቧል። ሁላችንም ሳንሰማው ያልቀረነው።

የኢሳያስ ቃለመጠየቅና የብሔርተኞች ጫጫታ

ቶኮላ
isayas afewerkiኢሳት ወደ ኤርትራ ተጉዞ የኤርትራውን ፕሬዝዳንት ማናገሩ ከተሰማ ወዲህና በተለይም የቃለመጠይቁ ቅንጣቢ ከቀረበ ቦኋላ እየበገኑ ያሉት ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ በወያኔ የብሄር ፖለቲካ እናተርፋለን ብለው ሲዳክሩ አመታት ያስቆጠሩ ብሄርተኞች ጭምር መሆናቸውን ጭፍሮቻቸው በሶሻል ሚዲያ ላይ ለማስተጋባት ከሚሞክሩ አስተያየቶች ለማየት እየቻልን ነው:: “በሚንልኪ ዘመን የደነቆረ በሚንልክ እየማለ ይኖራል” እንደተባለው እነዚ ሰዎች ከመንደርተኝነት ተላቀው አለማችን ከቀዝቃዛው ጦርነት ፍጻሜ ወዲህ የደረሰቺበትን እድገት ምነው መረዳት ተሳናቸው? የሚል ጥያቄ ያስጨንቀኝ ጀምሮአል:: በኤኮኖሚ የበለጸጉት የአውሮጳ አገሮች ብንዋሃድ ነው በአለም ውስጥ ተገቢ ስፍራችንን ይዘን መቀጠል የምንችለው በማለት አንድ ለመሆን ሲጣደፉ የኛዎቹ በቋንቋ ተካለን የየራሳችንን የፖለቲካ ጎጆ ብንቀልስ ነው የሚበጀን ማለታቸው የጤና ነው?

በሬ ሆይ ሳሩን አገኘሁ ብለህ ገደሉን ሳታይ… የግል አጭር አስተያየት

ከአበባዉ ላቀው (labebaw@gmail.com)
ሰሞኑን የኤርትራዉ “ፕሬዘዳንት” ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢሳት ቴሊቪን ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል። በዚህም እርሱ የተናገረዉን  ትርጉም ስሰማና አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች ልባቸዉ ሲማልል ስሰማ በጣሙን አዘንሁ። ምክንያቱም እያንዳዱ ኢትዮጵያዊ  ይህን እብድ ጠንቅቆ ያውቀዋል የሚል ግምት ነበረኝ። ሆኖም ግን ግምቴ ትክክል አለመሆኑን የሰሞኑንን ግርግር በደንብ አሰረዳኝ።
ይህን ኢሳያስ የሚባል isayaበደ ዉሻ ኢትዮያን ነክሶ ዜጎቿን ለእብደት የዳረገ የሰይጣን ፍጡር አምነን ልባችን በተደጋጋሚ አይነሸዋረር! ብርሀኑ ነጋያራሱ ተልኮ ያለዉ ጸረ-ኢትዮጵያ ነዉ። 97ቱን የምርጫ ድል ከሕዝብ እጂ ተነጥቆ ለወያኔ ጀባ እንዲባል በጓሮ በር ከበረከት ጋር ስምምንነትያደረገ እኮ እርሱ ነዎከምርጫ ሳምንት ቢኋላ ማክሰኞ ሊደረግ የነበረውን የሙት ከተማ አድማ ከበረከት ጋር ተስማምቶ እንዳይደረግ ያደረገእኮ እርሱ ነውያልሞተቸዉ ብርቱካን ሚዴቅሳ ትመሰክራለች። የብርሀኑን ከሀዲነት 16 የልደት ዘመኑ ጀምሮ በበረሃ ያደረገዉን የክህደትወንጀሎች ለማወቅ አሲምባ የነበሩሰዎችን ጠይቃችሁ ተረዱ።

‹‹ሰላማዊ ትግሉ ሲጠናከር ስርዓቱ ወደ አውሬነት ይቀየራል››

ነገረ ኢትዮጵያ
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
• ‹‹ቃል ኪዳናችንን ማጥበቅ አለብን!››
(በዛሬው ዕለት ለቀድሞው የአንድነት አመራሮችና አባላት የተዘጋጀው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ላይ ከተናገሩት)
10994318_665307356928259_3852354460061459043_n
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ፓርቲ ጣኦት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ቅንጅትንም አፍርሶታል፡፡ አንድነትንም አልፈረሰም ብለው እንዳይከሱኝ እንጅ አፍርሰውታል ማለት እችላለሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰማያዊ ላይም አንድ ነገር ማምጣታቸው የማይቀር ነው፡፡ ያ ማለት ግን ሰላማዊ ትግሉ ምን ያህል እንዳስፈራቸው ነው የሚያሳየው፡፡ አገዛዙ በፓርቲዎች ላይ የሚወስደው እርምጃ የሚያሳየው ሰላማዊ ትግሉ መጠናከሩን እንጅ ወደኋላ መመለሱን አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲህ አይነት ችግር ሲከሰት ሰላማዊ ትግሉ አበቃለት ይላሉ፡፡ ሆኖም አገዛዙ ሰላማዊ ትግል አስፈርቶት አውሬ ሲሆን የሚያረጋግጥልን ሰላማዊ ትግሉ መጠናከሩን ነው፡፡

ቀና በል ይሉኛል– ወዴት ልበል ቀና

10989028_861493467244057_5753878234862957005_nቀና በል ይሉኛል– ወዴት ልበል ቀና
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ በየት በኩል ልሙት::

የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ

በፌብርዋሪ 14, 2015
አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ 
unnamed (3)
ፌብርዋሪ 14, 2015 በኖርዌይ የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሰረት የአባላት ጠቅላላ 3ኛ  እና 4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ የሥራ ክንውን ሪፖርት የቀረበበት የተሳካ አጠቃላይ ስብሰባ አድርገዋል። በስብሰባው ላይ በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎና በተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የሚኖሩ የድርጅቱ አባላቶች የተገኙ ሲሆን የአባላት ስብሰባው አስቀድሞ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት በኖርዌጂያን የሠዓት አቆጣጠር ከቀኑ 13፡30 ተጀምሮዋል።

Hiber Radio: የህወሓት አስተዳደር የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እየተጻረረ መሆኑ.. ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም ማቀዷ… የኢ/ር ይልቃልና የዶ/ር መረራ ወቅታዊ ቃለምልልስ… አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የሚጠይቅ ከ70 ሺህ በላይ ፊርማ ተሰባስቦ ለእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር መሰጠቱ… የቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ያስከተለው ክፍፍልና ሌሎችም -

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ የካቲት 8 ቀን 2007 ፕሮግራም

እንኳን ለ78ኛው የየካቲት 12 የሰማእታት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ
<...ምርጫ ቦርድ ሆን ብሎ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ህገ ወጥ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ያለው ይመስላል … ትግላችንን ግን የበለጠ አጠናክረን እንቀጥላለን...> ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)
በቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫና ተከትሎት የመጣው ክፍፍል ስለ ጉዱዩ ከሰበካው ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ከዶክተር አለባቸው ደሳለኝ የቤተክርስቲያኒቱ አስመራጭ ኮሚቴ ዋና ፀሀፊ አቶ መላኩ አምባቸው እና የሰበካው ጉባኤ ምርጫ ህጋዊ አይደለም ተቀባይነት የለውም ከሚሉ ወገኖች አቶ ዩሀንስ ዳኘው ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ
የየካቲት 12 መታሰቢያ (ልዩ ጥንቅር)