Monday, February 16, 2015

የደፈረኝና ፤ የደፈረችኝ እሰጥ አገባ – ከመኳንንት ታዬ (ፀሃፊ)

ይህ ትውልድ ሃይል በእጁ ከመያዙም በላይ እውነትን የሚበረብርበት መንሽ በእጁ ስለመኖሩ አያጠያይቅም።በዚህ ሄደት የጉዞ ውጣ ውረድ ውስጥ ስለሚያስፈልገውና ፤ ስለሚፈልገው ነገር እያሰበም እያወራም የመኖሩ ሚስጥር ዛሬ ላይ ስለደረሰበት የስልጣኔ ደረጃም ብቻ ሳይሆን አልፎ አልፎም ምን ከእርሱ እንደሚጠበቅ ከመዘንጋት የመነጨም ነው።ይሁንና ዛሬ ይህችን መጣጥፍ እንድከትባት ያነሳሳኝ አንዳች ነገር በዚሁ በእኔ መኖሪያ አካባቢ የደፈረኝና ፤የደፈረችኝ እሰጥ አገባ በቪኦኤ ከተሰማ በኋላ በየማህበራዊ መድረኩ ብዙ ሲባል መከረሙንም ተከትዬ ብሎም ፓስትር ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት ሲጠየቁ ከሰጧቸው አስተያየት በመነሳትም ጭምር ነው ።
pastor
ይኸውም የዚህ አይነቱ ችግር መኖሾ ምን እንደሆነ ሲገልፁ ከተጠቀሙበት ቋንቋ እንጀምርና “ወሳኝ የሆነ ክፍተት እንዳለ የሚጠቁም ነው” ከሚለው እንነሳ ።እርግጥ ነው በማንኛው ግዜና በማንኛውም ቦታ ያለ ስጋ ለባሽ ሰው ፈተና ያጋጥመዋል ።የፓስተር ተከስተም ከዚህ ያለፈ ሊሆን እንደማይችል መገመት መፅሃፍ ቅዱስን ላነበበ ብዙ አይከብድም።ቅ.ዳዊትን እና ልጁን ማስታወስ በቂ ነውና ።ነገር ግን የክፍተቶቹ ምክንያቶችና አንድ ፓስተር (ሰባኪ) ወደቦታው በሚመጣበት ግዜ አስቀድመው በሱ ዙሪያ መታየት ያለባቸው ምግባሮች ምንድናቸው ?ዶ/ር ቶሎሳ ካነሱአቸው ነጥቦች ውስጥ ተወዳጅነት ፤ታዋቂነት ፤ተጠያቂነት የሚሉት አሉበት ።እንኝህን ነጥቦች በሚያሟለበት ግዜ ታዋቂነትና ተወዳጅነቱ በምን ዙሪያ ላይ ነው?። የሚለውን ስበን ያወጣን እንደሆነ ለራሱ ካለው ትልቅ ግምት የተነሳ የተሻለ መሆኑን ለማስረዳት አንድ ፓስትር ወደ ስብከት በሚመጣበት ግዜ በስፋት ሚያዘውትረው ስብከቱ የድህንነት ጉዳይ ላይ ወይስ በሌላው ሃይመኖት ዙሪያ ላይ ያልተገቡ ዙሪያዎችን መዞር ።

ፓስትር ተከስተ እና እራሳቸው ፓስተር ቶሎሳ(ዶ/ር) የተሻሉ የሰበኩ የሚመስላቸውና እርሳቸው ያነሱአቸውን ታዋቂነትና ተወዳጅነት ለማግኘት ከዚህ በፊት ባሉ ስብከታቸው ላይ ምን እነሱ አስተማሩ?።የሚሰብኩትስ መእመናን በምን ላይ አሜን አሏቸው ነው ።እውነቱን ስናነሳ ቅዱሳን ከመሳደብና በገዳም የሚኖሩ አባቶችን ከባኢታቸው ድረስ በመሄድ በድካማቸውና በችግራቸው ላይ ለመሳለቅ የመሰለን አሳፋሪና አስነዋሪ ነገር ሲናገሩ የሰማንበት ዘመን ይኸው አለንበት ክፍለ ዘመን ነው።ብዙዎቹም ፓስተሮች የመጀመሪያ እውቅናቸውን ሲያገኙ ከዚሁ ባለፈ ትህትና አደለም ።
ብዙዎቹን ለአብነት ከመጥቀስም በላይ አንድ የኔ ቢጤ ከመንገድ ስቦ የወሎ፤ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጌታን ተቀበሉ አስከማለት የተደረሰው አሁንም ይሄም ግዜው እሩቅ አደለም።የስጋ ፍቃድ ከአቅም በላይና በአቅም ልክ ሆኖ የሚጥላቸው የፕሮቱስታን ሰባኪያንን ብቻ አደለም።በአለም ላይ ያሉ ሐይማኖቶችን ሁሉ ይዳስሳል።እዚህ ላይ ልክ ነው የሚል የድጋፍ ሰልፍ እየወጣሁ አደለም። ግን የችግሮች መነሻ የክራቸው ጫፍ ከየት ይመዘዛል የሚለውን ስናይ ነው።የሚቀጥለው ተያያዥነት ያለው ንግግራቸው እና እኔ ያሰመርኩበት “ተጠያቂነት “የሚል ነበር ።እርግጥ ነው አንድ ሰው በሐላፊነት አስካለ ድረስ አንዱና ዋነኛው ነጥብ ተጠያቂነት መሆኑ ግልፅ ነው ።
ነገር ግን ዶ/ር(ፓስተር) ቶሎሳ እንዳሉት ይህ ተጠያቂነት የሚመጣው እና አብሮት መጓዝ ያለበት ስርአተ ቃል የሌላውን ሐይማኖትና ስርአት እንደ እራስ አድርጎ ማየትን የሚጨምር እንደሆነ ሊገነዘቡት ይገባል ባይ ነኝ።ምክንያቱም ከዚሁ መልሳቸው ጋር አያይዘው ወደፊት መሆን ስላለበት ሁኔታ ሲናገሩ”የሞራል ጉዳይ እና ያገልግሎት ብቃት የሚያስመሰክር ስልጠናና ብስለት ያስፈልጋቸዋል” ብለዋል።ማለቱን በይሁንታ እንቀበለውና ሞራል ባመነበት ስርአት አትግደል አታመንዝርና አትስረቅ ቢልና፤ቅዱሳንን እና እግዚአብሔር ያከበራቸውን አትሳደብ የሰው ሃይማኖት እንደ እራስህ ሐይመኖት የሌላውን መእምን እንደራስህ መእምን አክብርን ጨምሮ ስልጠናውን በእርሶና በሌሎች ይህን ልማድ ባደረጉ ፓስተሮች ዙሪያም የመስራት እቅዱን ቢያወጣና ባጀት መድቦ ቢንቀሳቀስ ዶ/ር ያሉትን ተግባራዊ ለማድረግም የቀድሞውን ፓስተር አሁን ከተገዘተ በኋላ አቶ ተከስተን ለማስተማርና ለማሰልጠን ቅርብ ይሆናል።
ቸር እንሰንብት።
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39000#sthash.xBv7S6YI.dpuf

No comments:

Post a Comment