Wednesday, August 26, 2015

አሁንም ኢትዮጵያዊያን መሰደዳቸውን አላቋረጡም፡፡

በኢትዮጵያዋ የድንበር ከተማዋ መተማ አሁንም ኢትዮጵያዊያን መሰደዳቸውን አላቋረጡም ሲል ዘጋርዲያን ዘገብዋል።
መንግስት ጥበቃውን አጠናክሮ በአካባቢው ብዙ ሰራዊት ቢያሰማራም በቀን ከ100 እስከ150 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞ ድንበር አቋርጠው ይሰደዳሉ። መተማ ከተማ ወደ መቶ ሽህ የሚገመት ነዋሪዎች ያላት ስትሆን የኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሌ ስደተኞች መተላለፊያ ናት።

የትግራይ ነጻ ዓውጭ ድርጅት ወያኔ የተባለ ወሮበላ ቡድን፥ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመው በደል ያስመረረው የሰሜን ጎንደር ሕዝብ የሚያሰማው በምስል የተደገፈ የድረሱልን ጥሪ፥

ጎንደርን ከትግራይ በሰሜን በኩል የሚለየው የተፈጥሮ ወሰን፣ የተከዜ ወንዝ፣
በምዕራብ ከሱዳን የሚለየው የተፈጥሮ ወሰን የ ጓንግ ወንዝ መሆኑ ይታወቃልና፥ ከዚህ እውነታ ንቅንቅ ማለት በምንም መንገድ የማይሞከር ነው፥
እርስታችንን የማስከበርና ድንበራችን የመከላከል ሃላፊነት ዓለብን እያለ ነው ገበሬው፥ ስለዚህ ይህ እኩይ የወያኔ ዓላማ ዓገራችንን ወደከፋ የእርስበርስ እልቂት እንዳይወስዳት ሁላችንም በዓንድነት የወያኔን ሥርዓት በቃ ልንለው ይገባል፥
ዓማራን ዓጥፍቶ ኢትዮጵያን ለመበታተንና ታላቋን ትግራይ ለመመስረት የሚያደርገው ከንቱ ምኞት በቸልተኛነት የማይታይ ዓይን ያወጣ ወረራ ነው፥
በተለይም በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎጃምና በጎንደር ዓማራ ሕዝብ ላይ የተያዘው የማፈናቀልና የዘር ማጥፋት ዘመቻ፥ ደረጃውን ከፍ ዓድርጎ በሰሜን ጎንደር ክፉኛ እየሰሩበት ይገኛል፥

አንተ የምትተኛ ንቃ!

አንባገነኖችን የበለጠ አንባገነን፡ ጨካኞችን የበለጠ ጨካኝ ያደረገውን አስተሳሰባቸውን ዛሬ በተቃውሞ መልክ ወደ ህዝብ እያወረዱ ይገኛሉ። ሆነ ብለው በታቀደና በተጠና መልኩ የተጠበቡበትን ከግብር እና ከእንጀራ አባቶቻቸው ከፋሽስቶች የተማሩትን የከፋፍለህ ግዛ እስትራቴጂ በመጠቀም በቅድሚያ የኢትዮጵያዊነት ተቀዳሚ አቅንቃኝ የነበሩትን አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን የመቆጣጠርና የማዳከም ስራ ጨረሱ፡፡ የኦሮሞን ህዝብ በአማራው ላይ በጠላትነት እንዲነሳና በሁለቱ ታላላቅ ህዝቦች መካከል የጠላትነት መንፈስን ለመፍጠር ሰሩ፡ በዚህም የፈለጉትን ያህል ፍሬ አፈሩ። ቀጥሎም ሙስሊሙን ከክርስትያኑ ለማጋጨት በሙስሊሞች ስም ብዙ ቤተ መቅደሶችን አቃጠሉ። ብዙ ክርስቲያኖችን ገደሉ።

ሰምተሃል ኮካ

ድመት አይጥ እንዲይዝ ተብሎ ችቦ አይበራለትም! 
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ጠበቃ ይሞትና ወደ ሰማይ ቤት ይሄዳል፡፡ በገነት በራፍ ላይ ቅዱስ ጴጥሮስ ያገኘዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የሁሉም ሰው ኃጢያት መዝገብ በእጁ ነውና የጠበቃውን ስም ፈልጎ ያገኘዋል፡፡ ከዚያ የሰራውን ኃጢያት ዝርዝር ያያል፡-
1ኛ. አንድን ከአየር መበከል ጋር ተያይዞ የተከሰሰን ሰው በመከላከል ጥብቅና ቆሟል
2ኛ. ደህና ገንዘብ ይከፈልሃል ስለተባለ ብቻ በግልፅ በነብስ ግድያ የተከሰሰን ነብሰ ገዳይ በመከላከል ጥብቅና ቆሟል፡፡ 
3ኛ. አብዛኛዎቹን የጥብቅና ደምበኞቹን ከልኩ - በላይ አስከፍሏል፡፡
4ኛ. አንዲትን የዋህ ሴት ለሌሎች ወንጀለኞች ጥፋት ማምለጫ ሰበብ እንድትሆን በመፈለግ፤ እንዲፈረድባት አድርጓል፡፡ 

አንዱ በአንድ ወቅት

አንዱ በአንድ ወቅት ቢራ አትጠጡ የቴዲን ሙዚቃ አትስሙ በማለት ከፖለቲከኛነት ወደፓስተርነት ተቀይሮ ህዝቡንም ከህወሀት ባርነት ሳይሆን ከሐጢያት ባርነት ለማውጣት ሲታትር ከሸፈ።
አሁን ደግሞ "የፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያምን መፅሐፍ በማቃጠል የኦሮሚያን ህዝብ ነፃ እናወጣለን" በሚል የተዘጋጀ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በኦነግ አዘጋጅነት ተካሄደ የሚል ዜና ከOMN እየጠበኩኝ ነው።
እመኑኝ ኦነግ የሚባል ድርጅት በህይወት የለም። በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የኦነግ አባል ነን እያሉ የሚደሰኩሩት ኦሮመኛ ተናጋሪ የህወሀት ሰዎች ናቸው።

በሓወልቲ ሰማእታት ለምትገኘው ኣቶ Daniel Berhane

፩) ኣብዛኞቹ የቀበሌና ወረዳ ተወካዮች፣ የሴቶችና የገበሬዎች ማህበራት ተወካዮች፣ ማንበብና መፃፍም እንደማይችሉ ማረጋገጥ ከፈለግክ የተሰጣቸው ማስተወሻ በእጃቸው መኖሩና ኣለመኖሩ ለማየት ሞክር
፪) ኣቶ ኣባይ ወልዱ የኮሚቴው ኣባል መሆን ኣይጠበቅባቸውም። በሳቸው ስር ወይም ኔትወርክ ያሉ ሌሎች ኣባላት የኮሚቴው ኣባል ሁነው ኣስፈፅመዋል።
ይህም የሃገራዊ ምርጫ ልምድ መቅሰም ትችላለህ። እንደ የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ቅስቀሳና ፍላጎት ቢሆንማ ማንም ኣባይ ወልዱ በስልጣን እንዲቆይ ኣይፈልግም ነበር።

‹‹ወራዳ! አሁንም እደግመዋለሁ ወራዳ!›› ያለው ማን ነበር?

አቶ መለስ ናቸው! እውነታቸውን ነው፡፡ መንግስት ተብየው፣ ህወሓት/ኢህአዴግ ወራዳ ነው!
ዛሬ የእሳቸውን አባባል ልጠቀም ነው፡፡ ‹‹መንግስት›› የሚባለው ወራዳ ነው፡፡ እደግመዋለሁ ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት ደህንነትና አባላቱን የሀሰት ምስክርነት አስጠንቶና አደራጅቶ ፍርድ ቤት የሚልከው ኢህአዴግ ወራዳ ነው! ወራዳ!

የደኢህዴን አመራር የህዝብ ቁጣ ላይ እሳት እየጨመረ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳደሩ ተናገሩ

የደኢህዴን አመራር የህዝብ ቁጣ ላይ እሳት እየጨመረ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳደሩ ተናገሩ
‹‹በአመራሩ መካከል ትርምስና ጥርጣሬ ተፈጥሯል››
‹‹ሰማያዊና መድረክ ማሸነፍ ይችሉ ነበር›› አቶ ደሴ ዳልኬ
በቅርቡ ታደለ ቱፋ የተባለ ግለሰብ በጋሞ ብሄር ላይ የጻፈውን መፅሃፍ አስመልክቶ በደኢህአዴን አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በተደረገ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደሴ ዳልኬ የደኢህዴን አመራር የህዝብ ቁጣ ላይ እሳት እየጨመረ ነው ሲሉ መግለፃቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ የደረሰው የድምፅ ማስረጃ አረጋገጠ፡፡
የጋሞ ጎፋ ዞን በተለይም የአርባ ምንጭ የደኢህዴን አመራር በፌደራል ደረጃ በጥርጣሬ እንደሚታይ የገለፁት አቶ ደሴ ዳልኬ የጋሞ ጎፋ ዞን የደኢህዴን አመራሮች ከመጽሐፉ ፀሐፊ ጀርባ አሉ በሚል አመራሩ እርስ በእርስ ጥርጣሬ ውስጥ እንደሚገኝም ነገረ ኢትዮጵያ እጅ የገባው ድምፅ አረጋግጧል፡፡ በዚህም ምክንያት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደርና በሌሎች አመራሮች መካከል ግልፅነት እንደሌለ ገልጸው ‹‹እናንተ ለእኔ ግልፅ ሁኑ!›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ተከስቶ ያለው ድርቅ

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ተከስቶ ያለው ድርቅ የምግብ ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ እንዲሄድ ማድረጉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ተረጂዎች ቁጥር መጨመርን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት የተጨማሪ የ230 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ጥሪ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል ።
ለምግብ እጥረት አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱ 14 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መካከል 4.5 ሚሊዮን የሚሆኑት በተያዘው አመት አስቸኳይ የምግብ እርዳታን እንደሚፈልጉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል። በሀገሪቱ የተከሰተው የዝናብ እጥረት አደጋ ከተተነበየው የከፋ ነው ያሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ሀላፊዎች በምግብ እጥረቱ የሚጎዱ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን ይፋ አድርጓል ።

ጥቂት ትዝታ ዶ/ር ነጋሶ ቤት ከነበረኝ ቆይታ

ዳንኤል ተፈራ
ትናንት አንድ ቀጠሮ ይዘን ነበር….. አዎ!... ይሄው በቀጠሯችን መሰረት ከች፤ የመብራቱ መኖርና ‹‹የኢንተርኔት ኮኔክሽን›› መከሰት ታክሎበት በትናንትናው ዕለት ከዶ/ር ነጋሶ ጋር ስለነበረኝ ቆይታና ትዝታ ጥቂት ለማለት በቃሁ፡፡
ዶ/ር ነጋሶ የሚኖሩት ብስራተ ገብርኤል አካባቢ በመንግስት ቤት ነው፡፡ ያውም ፖለቲካው ላይ ሲያከሩ ቂመኛው ህወሃት/ኢህአዴግ ‹‹ልቀቁ!›› እያለ እያንገራገራቸው ነዋ! ለአዛውንቱ ፕሬዘዳንት ግርማ በየወሩ 400 ሺ ብር ሆጭ እያደረገ የሚያቀማጥለው ገዥ ፓርቲ ለዶ/ር ነጋሶ ዞሮ መግቢያ ጎጆ ሊከለክላቸው ይፈልጋል፡፡ የመለስ/ኃይለማሪያም አገዛዝ በስልጣን ዘመናቸው የነበራቸውን መኪና ነጥቆ በእግራቸው ከህዝብ ጋር እየተጋፉ ሲሄዱ እየተመለከተ መሳቅ ያምረዋል - ጥርስ የለውም እንጅ፡፡ ነገርግን ዶ/ር ነጋሶ ከህዝብ ጋር በመሆናቸው ከበሩ እንጅ እንደጠበቁት አልተዋረዱም፡፡

ሰበር መረጃ ውጥረቱ እያገረሸ መሆኑ ተሰማ

መከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት ወይም ወረራ ለማድረግ ከፍተኛ ሰራዊት እያከማቸባቸዉ በሚገኙት በሰሜኑ አካባቢዎች አለመረጋጋት ነግሰዋል።
በትናንትናዉ እለት አንድ ጓድ መሪ 9 የሰራዊት አባላትን ከመመሪያ ዉጭ ይዞ በመንቀሳቀሱ እርሱን ለመከተል ፍለጋ ላይ የነበረ አነስተኛ የጦር ክፍል የኤርትራን ቀጠና አልፎ በመሄዱ ተደምስሷል።

አዲሱ ለገሰ በድጋሚ ተሰናበቱ

ብአዴን ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አቶ አዲሱ ለገሰ በድርጅቱ የመተካካት መርህ መሰረት የነበራቸውን ሃላፊነት አስረክበው በክብር ስለ መሰናበታቸው ተሰምቷል።
አስገራሚው ነገር የቀድሞው ምክትል ጠ/ሚ/ር ከዚህ በፊት ለመተካካቱ ግምባር ቀደም አርአያ በመሆን በክብር ስለ መሰናበታቸው ተነግሮ ነበር።የሄዱት አዲሱ በሌላ ሀላፊነት ብቅ በማለት የተሰናበቱትን ፖለቲካ ተቀላቀሉት።አሁን ደግሞ በብአዴን ጠቅላላ ጉባኤ ፊት ቀርበው መሰናበታቸው ተነግሯል።

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ባለ ሃብቶች ሀብታቸውን እያሸሹ ነው


በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ባለ ሃብቶች በትግራይ ክልል ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተደረገላቸው ቅስቀሳ በክልሉ ውስጥ ያለው ስር የሰደደ ብልሹ የአስተዳደር ሁኔታመጀመሪያ ይስተካከል ማለታቸውን ተገለፀ።
በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ያላቸውን ሃብት በትግራይ ክልል እንዲያሰማሩ ይርዳው በተባለ ከፍተኛ የህወሃት ካድሬ ነሓሴ 3/2007 ዓ/ም በተካሄደው ቅስቀሳ የተሞላበት ስብሰባ በብልሹ አሰራራችሁ የተጨማለቀውን አሰራራችሁ ካልተስተካከለ ገንዘባችንና ግዚያችንን አናባክንም ብለው እንደተቃወሙ ታወቀ።

የህውሃት አሽከር የሆነው ብአዴን

የህውሃት አሽከር የሆነው ብአዴን አሽከር ደመቀ መኮነን አማራው ተገፍቷል ተፈናቅሏል ይህን ህገ ወጥ ተግባር ደግሞ ብአዴን ብቻ ሳይሆን ሁሉም የመንግስት ድርጅቶች ሃላፊነቱን መውሰድ አለባቸው ብሎ መናዘዝ መጀመር ከምን የመነጨ ይሆን? ይህ ነገር ውጫዊ ተፅእኖው ምን ያህል እንደበረታባቸው ማሳያና የተገፋውን የተገደለውን የተባረረውን አማራ አለንልህ ችግርህን የምንፈታልህ እኛው እና እኛው ብቻ ነን ሌሎች የሚሉህን አትስማ ብሎ የከሰረ ፖለቲካ የመስራት የታሰበች ቧልት መሆኗን 100%( ቅርጫ ቦርድ ይህ የእኛ ነው ለምን ተጠቀምህ እንደማትሉኝ ተስፋ አለኝ) አውቀናል ነቅተናል። 

ቴዲ አፍሮን ከፋሽስት ርዝራዦች ጥርስ እናስለቅቅ!

አስደንጋጭ መረጃ ስለ ቴዲ አፍሮ!
ከዛሬ ወር በፊት አንድ የህወሃት ሰላይ እንዲህ አለኝ፡፡ የቴዲ አፍሮን አዲሱን ዜማ እየሰማሁ ሳለ አምልጦት ነው መሰል እንዲህ አለኝ ከዚህ በኋላ በምንም ተዓምር የቀድሞ ዝናውን አያገኝም፡፡ ለምን ስለው ለሱ የታሰቡ ነገሮች አሉ አለኝ፡፡ ምንድንነው ስለው ሀገር ቤት ለሚገኙ ማንኛውም ድርጅት ለቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ስፖንሰር እንዳይሆኑ ያለበለዚያ የንግድ ፈቃዳቸው እንደሚቀማ የተነገራቸውም አሉ፡፡ ከዛስ አልኩት እንደውም እየሰራ የሚገኘውን አዲሱን አልበም በዱርዬዎች ለማሰረቅ ሀሳብ ቀርቦ ነበር፡፡ በዚህም እሱን በኢኮኖሚ ማዳከም ስለሚያስፈልግ ብሎ ጨመረልኝ፡፡ እስካሁን ከቁም ነገር አልቆጠርኩትም፡፡

ከ4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ ያስፈልጋል ተባለ

1796634_222183061305326_875283870_n
በኢትዮጵያ 4 ነብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጋር የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በተያዘው አመት 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታስቦ የነበረ ቢሆንም፤ የተረጅዎች ከግምት ውጪ ላሻቀበው የተረጅዎች አሀዝ ብቻ 230 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ 4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ በጋራ መግለጫው ላይ የተመለከተ ሲሆን፤ከዚህ መካከል መንግስት 33 ሚሊዮን ዶላር ያህሉን መመደቡና ቀሪው 200 ሚሊዮን ዶላር በአስቸክይ ከውጭ ለጋሾች የሚጠበቅ መሆኑ ተገልጿል።

በኦጋዴን ነጻ አዉጭ በአርበኞች ግንቦት 7 እና በጥምር ሐይሎች በሁለት አቅጣጫዎች ከፍተኛ ጦርነት ተቀሰቀሰ


በኦጋዴን ነጻ አዉጭ በርበኞች ግንቦት 7 እና በጥምር ሐይሎች በሁለት አቅጣጫዎች ከፍተኛ ጦርነት ተቆስቁሶ ነገር ግን የመጨረሻ የማጥቃት እርምጃ ለመዉሰድ ታግደናል እየተደበደብን ነዉ፤፤
ይላል የወያኔ መንግስት የሰሜኑ እና የምስራቁ እዝ።
ዛሬ ለሊት ከ23፡00 ሰአት ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ልዩ ኮዱ 13.274645/ 37. 878478 በሰሜን ኦጋዴን ጋላዲ ጠረፍ አካባቢ ከባድ ዉጊያ ገጥሞናል በተለይ ሰራዊታችን በአየር ሐይሉ ላይ ምንም እምነት የለዉም፤፤
ዞሮ ሁሉ ሊደበድበን ይችላል ቃኘዉ አየር ሐይል በረራዎችም እያመጡ ያለዉ መረጃ ምንም የትም የማያደርስ ነዉ።

የደኢህዴን አመራር የህዝብ ቁጣ ላይ እሳት እየጨመረ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳደሩ ተናገሩ

‹‹በአመራሩ መካከል ትርምስና ጥርጣሬ ተፈጥሯል››
‹‹ሰማያዊና መድረክ ማሸነፍ ይችሉ ነበር›› አቶ ደሴ ዳልኬ
በቅርቡ ታደለ ቱፋ የተባለ ግለሰብ በጋሞ ብሄር ላይ የጻፈውን መፅሃፍ አስመልክቶ በደኢህአዴን አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በተደረገ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደሴ ዳልኬ የደኢህዴን አመራር የህዝብ ቁጣ ላይ እሳት እየጨመረ ነው ሲሉ መግለፃቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ የደረሰው የድምፅ ማስረጃ አረጋገጠ፡፡

በሽብር ክስት ታስረው የነበሩት እነ ኣብራሃ ደስታ ዛሬ ጥዋት ከእስር ተፈቱ።

11035502_771235849624393_3401706099381023667_n
ጀግኖቹ እነ ኣብራሃ ደስታ ዛሬ ጥዋት ሓሙስ 14 / 12 / 2007 ዓ/ም ከእስር በነፃ ተፈቱ።
ከዓመት በፊት በሽብር ክስት ታስረው የነበሩት ጀግኖቹ የሰለማዊ ትግል ጀግኖች ከተከሰሱበት የፈጠራ ክስ ነፃ ተብለው ተፈትተዋል።
፩) ኣብራሃ ደስታ ከዓረና
፪) ሃብታሙ ኣያሌው ከኣንድነት
፫) የሺዋስ ኣሰፋ ከሰማያዊ
፬) ዳኑኤል ሺበሺ ከኣንድነት
ከተከሰሱበት የሽብር ክስ በነፃ ተሰናበቱ።

የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል።

የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል። ኣብዛኛው የትግራይ የፌስቡክ ኣክትቪስቶች፣ ወጣቶችና ሙሁራን የህወሓት ኣባላት፣ ሌሎች ለውጥ ፈላጊ ኣክትቪስቶችና ሌሎች ፖለቲከኞች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ። የኣርከበ በድምፅ በጉባኤው መሳተፍ ለብዙዎች የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወደ ኣሸናፊነት የተጠጋ ቢመስላቸውም ጉዳዩ ሌላ ነው። ኣርከበ ተመልሶ የማይወዳደር መሆኑ ስላረጋገጡ የትግራዩ ኣንጃም እንዲሳተፍ በኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ታስረው የመጡት የወረዳ ተሳታፊዎች(ማንበብና መፃፍ የማይችሉ የሚገኙባቸው ሴቶችና ገበሬዎች የሚገኙባቸው የኣባይ ወልዱ ታማኞች ) እንዲፈቅዱለት ኣድርገዋል።

ብአዴን በተለያዩ ክልሎች እና በውጭ አገር የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ለማደራጀት ያደረገው ሙከራ መክሸፉን አስታወቀ።

ድርጅቱ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ እንደገለጸው፣ ለረጅም ጊዜ በአመራርነት ቆይቶ ስልጣኑን በመተካካት ሂደት ባስረከበውና ቁልፍ ስልጣኑን በተረከበው መካካል የመግባባት ችግር መኖሩን ገልጿል። ነባሩ አመራር ሁሉንም ሃላፊነት አስረክቦ ድርጅቱን የመልቀቅና ራሱን ገለል አድርጎ ለመኖር ይፈልጋል ያለው ብአዴን፣ በዚህም ላይ ነባሩ አመራር በአዲሱ አመራር እንደማይረካና ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያቀርብም ገልጿል። ቁልፍ ስልጣን የተረከበው አዲሱ አመራርም የራሱን አቅም የማያውቅ፣ ስልጣኑን ካስረከበው ነባር አመራር ለመማር ፍላጎት የሌለው ነው ብሎአል። በአዲሱ እና በነባሩ አመራር በኩል ለታየው አለመግባባት ምንጩ ዲሞክራሲያዊ ትግል አለመጎልበት፣ አድባርይነት ፣ ፊት ለፊት ለመታገል አለመፈለግ፣ ድክመቶችን ለመቀበል ፍላጎት አለመኖር፣ ሂስና ግለሂስን አለመቀበልና የድርጅቱን አሰራሮችን በተግባር ለማዋል ፍለጎት አለማሳየት ናቸው ብሎአል።

ትኩረት ፍለጋ.... ለኔ፣ እኔ፣ የኔ

ትኩረት ፍለጋ Attention seeking በሽታ ነው።
ሆኖም ይህ ክፉ ባህሪ አደገኛ የአዕምሮ በሽታ መሆኑን ስለማናውቅ በደፈናው "ትኩረት ሽቶ/ሽታ ነው" እንላለን። ብዙ ጊዜ ሕፃናት ላይ የሚታየው ትኩረት ፍለጋ እድሜ ሲጨምር እየለቀቀ የሚመጣ ቢሆንም አንዳንድ ሰዎች ላይ ከበጎው ትኩረት መሻት መስመር ያልፍና የእኔነት ደዌ ይጣባል።
ባህሪው በአዋቂዎች ላይ ሲሆን የሕይወትን ዋጋ እስከመክፈል እንደሚያደርስ በሥነልቡና ዘርፍ የተሰማሩ የጤና ባለሞያዎች ይገልጻሉ። የሌሎችን ትኩረት ለመሳብ ሲሉ የትኛውንም፣ ማንኛውንም ዋጋ ይከፍላሉ። ሊዋሹ ይችላሉ፣ ወይም ለትኩረት ሲሉ ብቻ ገንቢ የሆኑ ሥራዎችን በመስራት ለስኬታማነት ይደክማሉ።

አንድ አሜሪካዊ ወደ ትልቅ

አንድ አሜሪካዊ ወደ ትልቅ እና ቆንጆ ሬስቶራንት ከምታምር
ሚስቱ ጋር ይገባል ፡፡ ሬስቶራንቱ በሰው ተሞልቷል ...... ወደ
ሬስቶራንት እንደገባ ጥግ ላይ ብቻውን የተቀመጠ ጥቁር
አፍሪካዊ ያያል ፡፡ ይህ አሜሪካዊ ጥቁር በጣም ይጠላ ነበርና
"አስተናጋጅ "ብሎ ጮክ ብሎ ተጣራ.... አስተናጋጁም በፍጥነት
መጣ ፡፡ የኪስ ቦርሳውን አወጣና እዚህ ሬስቶራንት ላሉት
በሙሉ ከዛ ጥቁር ሰው ውጭ ( ወደ አፍሪካዊው እየጠቆመ )
የሚበላ ምግብ ታዘዛቸው አለው ፡፡ ይህን ይከታተል የነበረው
አፍሪካዊ በፈገግታ አሜሪካዊውን አየው ፡፡

ነባር ታጋይ

ፈትለወርቅ ይባላሉ። ነባር ታጋይ ናቸው። የህወሀት ማህክላዊ ኮሚቴ አባል ናቸው። የአባይ ፀሀዬ ሚስት ነበሩ። የባለሀብቱ ዳዊት ገብረእግዚያብሄር እህት ናቸው። ምን ማለት ፈልጌ ነው
፩) የህወሀት ማህከላዊ አባላት ሚስት ውሽማ አክስት ወንድም አጎት የሚሰበሰብበት የቤተ ዘመድ ስብሰባ መሆኑ ና
፪) ባላሀብቱን ጠርጥር ጠርጥር እያለኝ መሆኑን ነው።

'አስተርጓሚ'

የትናንትናው የገንዘቤ ዲባባ ቃለ መጠይቅ ላይ የነበረው ጉደኛ 'አስተርጓሚ' ተብዬ ላይ ትዝብታችንን መግለፃችንን ተከትሎ፥ የተለያዩ ወዳጆች፣ በውስጥ መልእክትም በአደባባይም፥ “ቋንቋ አለመቻል ምንም ማለት አይደለም።” “የውጭ አገር ቋንቋ ባይችል አያስወቅስም።” እና መሰል የመከላከያ ነገሮችን ተናግረዋል።
እርግጥ ነው ቋንቋ አለመቻል ምንም ማለት አይደለም። እንኳን የውጭ ቋንቋ ይቅርና፣ የቤተሰቦቹን ቋንቋ ባይችልም ምንም ማለት አይደለም። ሲጀመር ቋንቋ ክህሎት እንጂ እውቀት አይደለምና ባይችሉ አያሳፍርም። መቻሉም ቢያስደንቅ እንጂ፥ የሚያስኮፍስ ነገር አይደለም። ሰው እንደዋለበትና እንደፈለገው ልክ የትኛውንም ቋንቋ ማወቅና በአግባቡ የመጠቀም ክህሎቱን ማሻሻል ይችላል።

Tuesday, August 25, 2015

አንደንቁዋሪው ዲስኩር … “ቁዋሚ ጥቅም እንጂ ቁዋሚ ወዳጅ የለም “! ቦጋለ ካሳዬ፣ አምስተርዳም

ብርሃኑ ነጋ በርሃ ገባ! ‘አሜሪካ ተቀምጠህ የጦርነት ፉከራኽን ተወን’! እያልን ስናብጠለጥለው እነሆ በተግባር አፋችንን ዘጋው አይደለም እንዴ? ተቀብለናል አቤ ቶኪቻው…. ስላቅህ እውነትነት አለው። ሰውየው መጀመሪያ የኢህአፓ አባል ሆኖ ነበር በ17 አመቱ የሽፈተው ። ዛሬ ደግሞ ከ40 አመታት በሁዋላ የአርበኝነት ትግል ለማካሄድ አስመራ ገብቱዋል። ምንም እንኩዋን ግንቦት ፯ ኤርትራ ከመሸገ ቢሰነባብትም ብርሃኑ ጨክኖ በዚህ እድሜው በርሃ ይገባል ብዬ በግሌ አስቤ አላውቅም ነበር።
ድጋፍ
ኢሳት ሬዴዮ ይሁን ቴሌቪዢን የብርሃኑን በርሃ መግባት ተከትሎ ለአርበኞች-ግንቦት-7 ድጋፍ እንዲገኝ እየተጋ ነው። አንድ ነጻ ካልሆነ የመገናኛ ብዙሃን የሚጠብቅ ስራ ነው ። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዲሆንለት ይመስለኛል ኢሳት የሚሰበሰበውንም ገንዘብ በብር እያሰላ እየዘገበ ነው። ሚሊዮን በሚሊዮን እየተሆነ ነው።

ኢትዮጵያ፣ እምነታችን፣ አገራችን ባንድነታችን

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እራሱን ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው አምባገነን ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለረጅም ጊዜ በኃይማኖት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት በመሰንዘር በኢትዮጵያ ለብዙ ጊዜ ሊቆይ የሚችል የኃይማኖት ቅራኔ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡Ethiopian Muslims protest Jan 23, 2014
እ.ኤ.አ በ1991 የወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፖለቲካ ስልጣን እርካብን በሕዝብ ፈቃድ ሳይሆን በጠብመንጃ ኃይል ከተቆጣጠረ በኋላ የአስመሳይነት ባህሪውን በመጠቀም በተግባር ሳይሆን በባዶ ፕሮፓጋንዳ ሌት ከቀን የሚለፈልፍለትን የይስሙላ የእኩልነት እና የመቻቻል መርሆ ሰፍኗል በማለት በኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታይ ማህበረሰብ ዘንድ እርካሽ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ሲፍጨረጨር ቆይቷል፡፡
ወያኔው የሙስሊሙን ማህበረሰብ የእምነት ግንዛቤ አሳንሶ በመመልከት እና እኔ አውቅልሀለሁ በማለት ከእምነቱ ተከታይ ህዝብ ልቆ በመታየት የትሮጃን ፈረስ በመሆን በመጋለብ ሲዳክር ይታያል፡፡

አሸባሪነት ሲሉ – ያኔ እሰከ ዛሬ (ታሪኩ አባዳማ)

ታሪኩ አባዳማ ነሐሴ 2007
ላለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት በላይ በወያኔ አገዛዝ ስር የጭካኔ በትር ሰለባ የሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ቁጥር በቀላሉ የሚሰላ ባይሆንም እንበለ-ሕግ ሰብአዊ መብት ማዋረዱ መርገጡ ግን እነሆ እስከ ዛሬ አላባራም። በአዲስ አበባ የሚፈፀመውን ግፍ እና በደል ሳይውል ሳያድር በትኩሱ ለማወቅ ዕድል ቢኖርም በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች በምስጢር እስር ቤቶች እየታጎሩ ፣ በየጉድባዎች እየተረሸኑ የሚገኙ ሰለማዊ ዜጎች እሪታቸው የገደል ማሚቶ መሆኑ ቀጥሏል። ዛሬም እሪሪሪሪ ተገፋሁ… የሚለው ኢትዮጵያዊ ድምፅ ከመቸውም ግዜ የበለጠ ጎልቶ እያስተጋባ ነው። ወያኔ ሆነ ብሎ በሚቀሰቅሰው የሀይማኖት እና የጎሳ አምባጓሮ ውድ ህይወታቸውን ያጡ ፣ ቤት ንብረታቸው የወደመ ፣ የተፈናቀሉ ምስኪን ዜጎች ቁጥር እያሻቀበ ነው።
አሸብር ዜናዊ አስታቅፎን በሄደው ‘የሽብር ህግ’ መሰረት ፍፁም ሰላማዊ የሆኑ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች እስከ ሀያ ሁለት ዓመት በሚደርስ እስራት ፍርደኛ ተብለው የወህኒ ኑሯቸው መራዘሙ ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው። ባለ ‘ራዕዩ መሪ’ ለገሰ ዜናዊ ያወረሰን የተወልን ሌገሲ።

ሆዳም ቢሰበሰብ መግላሊት ኣይከፍትም

ከብርሃኑ ተስፋዬ
የሰይጣኑን ሙት ኣመት ለማክበር በሚዘጋጁበት ወቅት ወያኔዎች ሆዳም ዲያስፖራዎችን ወደ ኣዲስ ኣበባ ጋብዘው ቡራ ከረዩ የሚሉበት ሁኔታ ስለገረመኝ ነው ይህን ጽሁፍ ለንባብ የማቀርብላችሁ። በመሆኑን መልካም ንባብ።Ethiopian Diaspora
መነሻ
በመጀመሪያ የሰው ልጅ ከትውልድ ቀየው ወደ ተለያዩ ቦታ ወይም የኣለም ክፍሎች የሚሰደደው ኣንድም በሃገሩ ባለው የፖሊቲካ፣ የሶሽያልና የኢኮኖሚ ሁኔታ ኣለመመቻቸት ነው ቢባል ማጋነን ኣይሆንም። እውነቱና ሀቁም ይህ ሆኖ ሳለ የተሰደደበት ችግር በሚቀረፍበት ጊዜ ኣንድም በኣካል ኣሊያም በሃሳብ፣ ማቴሪያል፣ ወይም በገንዘብ ለሃገሩ ኣስተዋጾ ያደርጋል። ይህንን ኣይነት ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለው ግን በተሰደደበት ወቅት የነበረው የመንግስት ስርኣት ሲቀየር የሚከተላቸው ፖሊሲዎች ዲያይስፖራውን እንደ ኣንድ ኣገር ገንቢ ኣካል ቆጥሮ በእኩልነት ማሳተፍ የቻለ እንደሆነ ነው።

የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ! (ከኤርሚያስ ለገሠ)

ከኤርሚያስ ለገሠ (ክፍል አንድ )
1 – ደስታ እና ሀዘን
ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ ሊያነሳት በመቻሉ ደስ ይለኛል። እንኳን ለዚህ አበቃህም ማለት እፈልጋለሁ።Ermias Legesse former Woyane govt. employee
በሌላ በኩል ገዥው ቡድን በምክንያት እያሰረ በምክንያት የሚፈታበት ሁኔታ ለራሱ ስልጣን መቆያ ትክክል ቢሆንም ለኢትዬጲያ የፍትህ ስርአት ምን ያህል ንቀት እንዳለው የሚያሳይ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው። ሰዎች በህውሀት ላይ አደጋ ሲጋርጡ በፓለቲካ ውሳኔ ይታሰራሉ…ህውሀታዊ ምክንያት !። ገዥው ቡድን ላይ የተጋረጠው አደጋ በሌላ ጐን ሲያጋድል ደግሞ በእጁ ይዞ የሚያሰቃያቸውን ይፈታል…ህውሀታዊ የመፍታት ምክንያት!!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ወያኔ እና የሚዘረፈው ሰራዊት (መሳይ መኮንን)

መሳይ መኮንን (የኢሳት ጋዜጠኛ)
ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ የተሳተፍኩበትን የሰላም አስከባሪ ዘመቻ አጋጣሚ በአስረጂነት ማሳየት እችላለሁ::Ethiopian peacekeeping troops
እኤአ በ2003-2004 በመንግስታቱ ድርጅት የበላይነት: በአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚነት ከተላከው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት ጋር ወደ ቡሩንዲ ሄጄ ነበር:: ወደ 18 የምንሆን አስተርጓሚዎች ከ8 ወር እስከ 1 ዓመትቆይተናል:: ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ:: ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈጸመውን የህወሀቶችን ለከት ያጣ ስግብግብነትን ላጫውታችሁ::

ነጻነታችን በእጃችን፣ ህወሃት ካልተገረሰሰ እስሩም ግድያውም ይቀጥላል!

ተስፋዬ ነጋ (ዋሽንግተን፣ ዲሲ)
ዛሬ እነሆ እነ ሀምታሙ አያሌው፣ ዳኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና፣ አብርሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ የወያኔ ፍርድ ቤት ወስኗል የሚል ዜና ሰማሁ። እንኳንም በውሸት ክስ የታሰሩት ወደየቤተሰቦቻቸው በሰላም ተቀላቀሉ። ከሚወዱት ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ እጅግ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥራል። የቤተሰቦቻቸውን ናፍቆታቸውን በአግባቡ እንዲያጣጥሙ ምኞቴ ነው። እውነት መጨረሻ ላይ እውነት ሆና መውጣቷ አይቀርም፣ ይኸው እውነት ነጻ አወጣቻቸው።abraha desta in jail
የሆኖው ሆኖ እነዚህ ወጣቶች ከመጀመሪያውም መታሰር አልነበረባቸውም። በወንጀል ደም ተጨማልቀው የሚዋዥቁ አረመኔዎች አልነበሩም። ለአገራቸውና ለህዝባቸው ከፍተኛ ራዕይ የሰነቁ ንጹህ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፣ አሁንም ንጹሃን ናቸው። ወያኔዎች ሰላማዊ ዜጎችን በማሰር የፖለቲካ ትርፍ እናገኛለን ብለው ቢያስቡም፣ የእነአብርሃ ደስታ መታሰር የህወሃትን ድንቁርና ከማጋለጥ ውጭ በተቃዋሚው ወገን ላይ ያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ የለም። እንዲያውም ተቃዋሚዎች የትግሉን ዳራ በጥልቅ እንዲመረምሩና የወደፊቱን የትግል አቅጣጫ በጥንቃቄ እንዲቀይሱ አደረጋቸው እንጂ! የታሳሪዎችን ንጹህነት ደግሞ ህወሃቶችም (እዉነትና ውሸት የማያገናዝቡ ሆዳም ካድሬዎችም ጭምር) በሚገባ የሚመሰክሩ ይመስለኛል፣ ያው የሞት ሽረት ነገር ሆኖባቸው ቢያስሯቸውም! የህወሃት ሰዎች ለስልጣናቸው የሚያሰጋቸውን ሁሉ በሃሰት ክስ ከመወንጀል ተቆጥበው አያውቁም፣ እነዚሁ ፖለቲከኛ ወጣቶች በምሳሌነት ሊቀርቡ ይችላሉ፣ የእስሩ ገፈት ቀማሾች ዞን 9ኞችም ሌሎች ሰለባዎች ናቸው።

ማሪንጌ ቻቻ ፤ የወያኔ (የሃይልዬ) ጨዋታ – ሰሎሞን ታምሩ ዓየለ (ከካሊፎርኒያ)

የሃይልዬ የድርቅ ፖለቲካ !!!
ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባም !!!
ሰሎሞን ታምሩ ዓየለ (ከካሊፎርኒያ)
ለጽሁፌ መነሻ የሆነኝ በቅርቡ የኢትዮጵያው ጠ / ሚኒስቴር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ” የዳያስጶራ “ ሳምንት በሚል በአዲስ አበባና አካባቢዋ ስለተከበረውና ከተሳታፊዎቹ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ በአገራችን እየተንሰራፋ ስላለው ድርቅ ገጽታውን እንዲያብራሩ ተጠይቀው እንደነበር ይታወሳል። የሰጡትን ምላሽ በኢሳት ሬዲዮ ካዳመጥኩኝ በኋላ ሰውዬው ምን ነካቸው ? ምንስ ቢተማመኑ ነው የኢትዮጵያውን ድርቅ ከካሊፎርኒያና ከአገረ አውስትራሊያ ጋር ለማዛመድ ያነሳሳቸው የሚል ሃሳብ በጭንቅላቴ እየተመላለሰ ስላስቸገረኝ ፤ እስቲ እኔም የድርሻዬን የማውቀውንና የተረዳሁበትን መንገድ አንድ ልበል በሚል ምላሽ ለመስጠት ነው። ከሁሉ ደግሞ የደነቀኝ “ ዳያስጶራው “ ንግግራቸውን በጭብጨባ ማጀቡ፤ ኢትዮጵያ ሌላ ተፈጥሮን መቆጣጠር የሚችል መሪ አገኘች ወይ የሚል ጥያቄ በህሊናዬ ማጫሩ አልቀረምና የድርቁን ችግር በራሷ ጥረት ብቻ ልትቀረፍ የተዘጋጀች አገርም መሰለኝ።

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
Semayawi Party elected Yilkal Getnet
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በጠቅላላ ጉባኤው የተነሱትን ጠንካራ ጎኖች በማጠናከርና ድክመቶችን በመቅረፍ ለሚቀጥለው ሶስት አመት ፓርቲያቸውን ለመምራት ቃል ኪዳን ሲገቡ!
አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በድጋሜ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡
ትናንት ነሀሴ 16/2007 ዓ.ም ጉባኤውን የጀመረው ፓርቲው በዛሬው ሁለተኛና የማጠቃለያ ውሎው የፓርቲውን ሊቀመንበር፣ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላት ምርጫን አድርጓል፡፡

እጅግ በጣም ደማቅ የአርበኞች ግንቦት 7 ድጋፍ ዝግጅት በቬጋስ

ጋሻው ገብሬ
እጅግ በጣም ደማቅ የአርበኞች ግንቦት 7 ድጋፍ ዝግጅት በቬጋስ ተከናውኖ በማየቴ እድለኛ ነኝ። ቬጋሶችን “እንኳን ደስ ያላችሁ” ማለት በጣም ይገባል። የድጋፍ ማሰባሰቡ ከ70 ሺ ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።
Patriotic Ginbot 7 Las Vegas fundraise
እኔ በስደት ወደ አሜሪካ የመጣሁት እአአ 1981 ዓም ነበር።አሜሪካ የመማርና የመስራት እድል የሰጠኝ የተመሰገነ ሰው መርዳት የሚወዱ ሰዎች ያሉበት አገር ነው።ልክ እንደኔ በስደትም በሌላ ምክንያትም የመጣችሁ ይህን የኔን አባባል ትደግፋላችሁ ብዬ አምናለሁ።ላስ ቬጋስም በተለያዩ ምክንያት የመጡ ኢትዮጵያውያንን አገኘሁ። ወደ ቬጋስ ሄጄ ስለ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንድናገር እድል በማግኘቴ ነው አየሩም የወገን ፍቅሩም ሞቅ ያለውን ከተማ አይቼው መጣሁት።

ቴዲ አፍሮ

ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:: ለቴዲ የህወሀት ኢትዮጵያ አላስቀምጥ ብላዋለች:: ምናልባትም ቴዲ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል:: በግሌ በተለይ ሰሞኑን የሚደርሱኝ መረጃዎች የህወሀትን የዕብሪት ለከት ማጣት የሚያሳዩ ቴዲንም ከሚወደው ህዝብና ከሚሳሳላት ሀገሩ እንዲለያይ የሚገፋፉ ናቸው:: ቴዲ መሰደድ እንደማይፈልግ የትኛውንም በደል ተቋቁሞ በሀገሩ መኖር ለምርጫም የማይቀርብ ጉዳይ እንደሆነ ባውቅም ትዕግስትም ልክና ድንበር አለውና የሰሞኑ ግፊትና ግፍትሪያ ከመራር ውሳኔ ሊያደርሰው እንደሚችል አምኜአለሁ::

Sunday, August 16, 2015

ሲነግሯችሁ የማትወዱት ( ሄኖክ የሺጥላ )

ህውሃት እና እሱን የሚደግፈው አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ፣ ሆድ አደሩ አማራና ፣ አማራን በመጥላቱ የህወሓት ክንድ የሆነው ሌላው ዘርም በአንድነት አንድ የሚያደርጋቸው ነገር አማራን ቀና የሚያረግ ሃሳብ ፣ አማራን የሚያነሳሳ መልእክት ፣ አማራን የሚያነቃቃ መንፈስ እጅግ መጥላት እና መፍራታቸው ነው ። እንግዲህ ሕልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም እንዲሉ ፣ እኛም የምትጠሉት ፣ እጅግ የማትወዱትን እውነት እንጽፈዋለን ፣ የረገጣችሁት ሕዝብ ይነሳ ዘንድ በደሉን ደግመን ደጋግመን እንነግረዋለን ፣ የገደላችሁት ሕዝብ ጉልበት ያገኝ ዘንድ ፣ ይነደው ዘንድ ፣ ይቆጨው ዘንድ ፣ ወደ ልቦናው ይመለስ ዘንድ ፣ ይህንን አረመናዊ ተግባራችሁን ይመክት ዘንድ ፣ እንወተውታለን ። የውሃ ጠብታ እያደር ድንጋይ እንደሚበሳ እናውቃለን ። ስለዚህ በናንተ ሴራ እና ተንኮል የበደነውን ማንኛውም ግፍ የተዋለበትን ሕዝብ ፣ ከግፉ ፣ ከመከራው ፣ ከገባበት የባርነት ሰንሰለት ራሱን ያነጻ ዘንድ ፣ እናንተን ቢከረፋችሁም ፣ እናንተ ባትወዱትም፣ እኛ ግን ሃሳቡን ወደፊት እናመጣዋለን ፣ ምክንያቱም እናንተን የሚጥለው ይህ ሃሳብ ብቻ እንደሆነ ስለምናውቅ ። እንዴት እንደተነሳችሁ ስለምናውቅ ፣ እንዴት እንደምትወድቁም ስለሚገባን ።

በቴክሳስ ዳላስ ከተማ ዛሬ ለአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከ52,000 የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡን ዘገቢያችን ከስፍራው ገለጸ።

ሰበር ዜና ፡- በቴክሳስ ዳላስ ከተማ ዛሬ ለአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከ52,000 የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡን ዘገቢያችን ከስፍራው ገለጸ።
ዛሬ ቅዳሜ በቴክሳስ በተካሄደው ሀገርን የማዳን ህዝባዊ የአርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ላይ በርካታ በቴክሳስ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች መገኘታቸው ታውቆል። አክቲቪስትና ጋዜጠኛ አበበ ገላው አሁን የተጀመረው የነጻነት ትግል ተጠናክሮ ማህበረሰቡ የሚገባውን ማድረግ ይገባዋል ብለዋል። የቀድሞው ኮሚኒኬሽን ሚንስተር ኤርምያስ ለገሰ በማያያዝ ዛሬ የህወሃት ሰራዊት ይህን ሃይል የሚቆቆምበት ሞራል ያለ አይመስለኝም ምክንያቱም በሰራዊቱ የተፈጠረው አለመግባባትና የማንነት ጥያቄ የጭዋታውን ሜዳ እንደሚቀይረው ተናግረዋል።
በዚሁ ስብሰባ ላይ አንድ ጫራታ $32, ሺ ብር በላይ ተሽጦል። 

ኢትዮጵያ፡ የህወሀት አምባገነንነት የተንሰራፋባት ምስኪን ሀገር (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ኢትዮጵያ፡ የህወሀት አምባገነንነት የተንሰራፋባት ምስኪን ሀገር፣
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ ለበርካታ ዓመታት ያዘጋጀኋቸውን ትችቶች እና ጸሁፎች በአንድ ላይ በማሰባሰብ ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ በማሰብ almariam.com በሚለው ድረ ገጼ እያሰባሰብኩ ባለሁበት ጊዜ የኢትዮጵያ ሪቪው መጽሔት/Ethiopian Review Magazine (ERM) ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2000 ጽሁፎችን በድረ ገጽ ማውጣት ከመጀመሩ በፊት መጽሄቱ በጽሁፍ ህትመት ግንኙነት ያወጣቸውን የእኔን ትችቶች እና ጽሁፎች አገኘሁ፡፡
Prof-Alemayehu-G-Mariam-200x200
እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ የኢአርኤም/ERM ከፍተኛ አርታኢ ሆኘ ስሰራ በነበረበት ጊዜ በኢትዮጵያ እና በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ፖለቲካ ላይ የጻፍኳቸውን የበርካታ ጽሁፎችን ስብስብ እንደገና አገኘሁ፡፡ ሆኖም ግን የውስጣዊ ይዘታቸውን ምንነት ስብስብ አላገኘሁም፡፡  ኢአርኤም/ERM እ.ኤ.አ ከጥር 1991 እስከ 2000 ድረስ ጽሁፎችን ያወጣ የነበረው በህትመት የመገኛኛ ዘዴዎች በመጠቀም ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ኢአርኤም/ERM ለዘጠኝ ዓመታት ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆኑ እያተመ ያወጣቸውን ሁሉንም የህትመት ጽሁፎች ማግኘት እና ማሰባሰብ አልቻልኩም፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ ጠንቃቃ በሆኑ የስራ ባልደረቦቼ እገዛ በቅርቡ የጥቂቶችን ጽሁፎች አድራሻ ለማግኘት ችለናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቀሪዎቹን የበርካታዎቹን ጽሁፎች አድራሻ ፈልገን እናገኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ከወያኔ ጓዳ ሾልኮ የወጣ ጸረ-አማራ ሴራ፣ ያልሰማህ ስማ፥የሰማህ አሰማ (አባ ኮስትር በላይ)


ከወያኔ ጓዳ ሾልኮ የወጣ ጸረ-አማራ ሴራ፣ ያልሰማህ ስማ፥የሰማህ አሰማ!
አባ ኮስትር በላይ

የናዚ ወያኔ ቀዳሚ ሰለባ የሆንከዉ ወገኔ ሆይ «ጅብ ከሚበላህ፣ በልተኸው ተቀደስ»!!
«ትናንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ዐማራው ስለሆነ፣» እያንዳንዱ ትግሬ ዐማራን በማጥፋት እንቅስቃሴ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን፣ የወያኔ የአገር-ውስጥ እና የውጭ የስለላ ቡድኖች ከፍተኛ አመራሮች በጥናቶቻቸው እንዳሣዩ የታመኑ የሞረሽ-ወገኔምንጮቻችን አረጋገጡ።
TPLF Nazi
ሰነዱ በአገሪቱ ውስጥ ካሉት ነገዶች ትግሬን የሚያሰጋው ሌላ ማንም ሳይሆን፣ ዐማራው መሆኑን፣ እና ይህ ነገድ በምንም ተዓምር የመደራጀት ዕድል እንዳያገኝ ወያኔ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት ያስገነዝባል። ለዚህም ግብ ተግባራዊነት የተነደፉ ስልቶች፦
ሀ) ዐማራዎች ከሁለት በላይ ሆነው እንዳይንቀሳቀሱ የተጠናከረ የስለላ እና የክትትል መረብ እንዲዘረጋ ማድረግ፤
ለ) ወደውጪ አገር ለመሰደድ የሚፈልገውን ዐማራ በተለያዩ ስልቶች እንዲሰደድ ሁኔታዎችን በስውር በማመቻቸት ማሰደድ፤
ሐ) በአገር ቤት ያለውን እና ለመሰደድ ፈቃደኛ ያልሆነውን ደግሞ አንገቱን ሳያቀና በልዩ ልዩ መንገዶች ማስወገድ፤

ሰቆቃ በማዕከላዊ -ማዕከላዊ ውስጥ የተነቀለው የአበበ ካሴ ጥፍር (አበበ ካሴ)


ሰቆቃ በማዕከላዊ -ማዕከላዊ ውስጥ የተነቀለው የአበበ ካሴ ጥፍር
አበበ ካሴ

‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡››
Torture in TPLF prison 2
እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ ቆይቻለሁ፡፡ ማዕከላዊ በነበርኩበት ወቅት የሁሉም እግርና እጆቼ ጥፍሮች ተነቅለዋል፡፡ አንዳንድ ቀን እጄ ላይ የሆነ ነገር ስለሚወጉኝ ጥፍሮቼ ሲነቀሉ አላውቅም፡፡ ስነቃ ነው መነቀላቸውን የማውቀው፡፡ ከዛም ቁስሉን እየነካኩ ያሰቃዩኛል፡፡ ማደንዛዣ ለምን እንደሚወጉኝ አላውቅም፡፡ ጥፍሮቼን ሲነቅሉኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜም ራሴን እንድስት ያደርጉኛል፡፡ እጅና እግሬን አስረው እንደ ፍሪጅ ያለ እቃ ውስጥ ያለ በረዶ ውስጥ ያስቆሙኛል፡፡ ለብዙ ሰዓት በጣም ቀዝቃዛ የሆነ ቦታ ላይ እስክደነዝዝ ቆሜ እውላለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ርዕዮት ተናገረች ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ


የኢትዮጵያ ርዕዮት ተናገረች
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

አይበገሬዋ ጀግናዋ ርዕዮት! 
በንጹሀን ዜጎች ላይ ስቃይን በመፈጸም ከሚታወቀውና ከአዲስ አበባ ከተማ እምብርት በስተደቡብ ምስራቅ ተንጣሎ ከሚገኘው እና በተለምዶ ቃሊቲ እየተባለ ከሚጠራው የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት (የኢትዮጵያ “ሮቤን ደሴት” ማለትም ነልሶን ማንደላ የታሰሩበት) ባልተጠበቀ ጊዜ የተለቀቀችው ጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ ከማጎሪያው እስር ቤት በወጣች በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ቃለ መጠይቅ ሰጠች፡፡
Reeyot-pix-3
ዴሞክራሲ እና ፍትህ የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን እስከምትሆን ድረስ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ የሆነች ኢትዮጵያን እስከማይ ድረስ ትግሌን በተጠናከረ መልኩ እቀጥላለሁ በማለት የዓላማ ጽናቷን በድጋሜ አረጋግጣለች፡፡
ርዕዮት በአምባገነኑ ገዥ አካል የ14 ዓመታት እስር ተበይኖባት ይህ እስር እንደገና ወደ 5 ዓመታት ከተቀየረ በኋላ 4 ዓመታት ከ17 ቀናት (1480 ቀናትን) በእስር ቤት አሳልፋለች፡፡
አሁን በህይወት በሌለው በመለስ ዜናዊ እና በእርሱ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) የጸረ ሽብር ሕግ እየተባለ በሚጠራው ሰላማዊ ዜጎችን የማጥቂያ መሳሪያ የፈጠራ እና የሸፍጥ ክስ ተመስርቶባት ነበር ወደ ዘብጥያ የተወረወረችው፡፡
ታላቁ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ለዘረኛው የጥቂት ነጮች ፈለጭ ቆራጭ አምባገነን ስርዓት ጭቆና አራማጆች እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር፣ “በማዘግየት በኩል ውጤታማ ልትሆኑ ትችላላችሁ፣ ሆኖም ግን ደቡብ አፍሪካ ወደ ዴሞክራሲ የምታደርገውን ሽግግር በምንም ዓይነት መልኩ በፍጹም ልታስቀሩት  አትችሉም፡፡“

ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው! አርበኞች ግንቦት 7


ህወሓት በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያ ላይ ያሰፈነው ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲመሠረት እና የሀገራችን አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማኖር አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ተገዶ የገባበት የመረረ የአመጽ ትግል መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በጀግነትና በጽናት እየታገሉ ነው።

Dr. Berhanu in Eritrea 4
ይህ ትግል በባርነትና በነፃነት መካከል የሚደረግ ወሳኝ ትግል ነው። የዚህ ትግል ውጤት የእኛ የዚህ ዘመን ትውልድ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የወደፊት ታሪክ፤ የልጅ ልጆቻችንን ሕይወት ይወስናል። በዚህም ምክንያት ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነፃነት ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን ሊቆም ይገባል።

ህወሓት በፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥ ተኩኖ ህወሓትን ማዳከም አርበኝነት ነው!


July 21, 2015
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ አባላት የሚከተለው መልዕክት ማስተላለፍ ይሻል።
ህወሓት ጥቂት አባላትና ደጋፊዎች ይዞ ታላቂትዋን ኢትዮጵያ ለማንበርከክ እና ሀብቷን ለመመዝበር እናንተን መጠቀሚያ ያደረጋችሁ መሆኑን የምታውቁት ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ የተባሉ ድርጅቶች የራሳቸው ድርጅታዊ ነፃነት የሌላቸው የህወሓት አገልጋዮች መሆናቸው እነሱ ራሳቸው የሚነግሯችሁ ከመሆኑም በላይ እናንተም በዕለት ተዕለት ተግባራችሁ የምትታዘቡት ሀቅ ነው። እነዚህ ድርጅቶች ህወሓትን ለማስደሰት ሲሉ የራሳቸውን ሕዝብ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚዘርፉ፣ ከቀየው የሚያፈናቅሉ፣ መኖሪያ ቤቱን የሚያስፈርሱ መሆናቸው እናንተም እየተሳተፋችሁበት ያለ ሥራ ነውና የምታውቁት ነው።

አንድ አፍታ በሸዋሮቢት እስር ቤት በላይ ማናዬ

በላይ ማናዬ አዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ በሚገኘው ሰሜን በር መናሃሪያ ከጓደኛዬ ጋር የጉዞ ትኬታችንን በእጃችን አስገብተን ‹‹ሸዋሮቢት! ሸዋሮቢት›› በሚል መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ (በተለምዶ ቅጥቅጥ የሚባል መኪና) ውስጥ ገብተን ቦታችንን ይዘናል፡፡ ለጉዟችን ሻንጣ አልያም ከበድ ያለ ሸክም አልያዝንም፡፡ ሸዋሮቢት ለመሄድ ካለምኩ ረዘም ያለ ጊዜ ቢያልፈኝም ለመተግበር ዛሬን (ነሃሴ 7/2007 ዓ.ም) መጠበቅ ነበረብኝ፡፡ ወደ ሸዋሮቢት የምሄደው እዚያ ርቀው የተወሰዱ የህሊና እስረኛ ወንድሞቼን ለመጠየቅ ነው፡፡ ጓደኛየም ሆነ እኔ ሸዋሮቢት የሚገኘውን የፌደራል ማረሚያ ቤት አናውቀውም፡፡ ስለሆነም የሚያውቁ ሰዎችን መማተራችን አልቀረም፡፡
Showa Robit
የጉዞ መኪናችን ገና መናሃሪያውን ሳይለቅ ከተቀመጥንበት ወንበር ኋላ ያለ ወንበር ላይ የተቀመጡ አንዲት እናት ደጋግመው የድካም ትንፋሽ ሲተነፍሱ በመስማቴ ዞር አልኩ፡፡ አፍንጫየን ትኩስ የቤት ዳቦ ሽታ ስቦ አስቀረው፡፡ እኒህ እናት እንደኛው ሸዋሮቢት የታሰረ ሰው ሊጠይቁ እየሄዱ መሆናቸውን ተገነዘብኩ፡፡ የድካም ትንፋሻቸውን እንደገና ሲተነፍሱ ሰማሁ፤ የመማረርና የመሰላቸት ትንፋሽ! እኒህ እናት እኔና ጓደኛየ ለመጀመሪያ ጊዜ የምንሄድበትን የሸዋሮቢት እስር ቤት ስንቴ ተመላልሰውበት ይሆን ስል ራሴን ጠየቅሁኝ፡፡

አንዳርጋቸውና ጓዶቹ – ከአንተነህ መርዕድ

andargachew Tisgeአምና ሰኔ 2006 ዓ ም አንዳርጋቸው ጽጌ በትራንዚት ላይ እያለ ከየመን በወያኔ መታፈኑ ሲነገር ሃዘንና ንዴት ያልተሰማው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። ወያኔ ኤርትራ ውስጥ እንዳለ ሊገድለው ያደረገውን ሙከራ ኢሳት በተከታታይ ስላቀረበው ምን ያህል አዳጋ ውስጥ እንዳለ ለሁሉም ግልፅ ነበር። የአንዳርጋቸው መያዝ ከታለመው ግብ  በተፃራሪ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ከዳር ዳር በቁጣ በማንቀሳቀሱ አፋኞቹ አምባገነኖች ከጠበቁት ውጭ ራሳቸውን ችግር ውስጥ ነው ያገኙት። መታፈኑ ለአስርት ዓመታት አፍዝዞ የያዘን ፍርሃትንና ክፍፍልን ሰባብሮ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጋራ እንዲቆም ከማድረጉም በላይ አንዳርጋቸው የደላ ኑሮውን ትቶ በረሃ ለበረሃ የተንከራተተለት፣ በርሃብና በበሽታ የተንገላታለት፣ ከጓዶቹ ጋር ለኢትዮጵያውያን ነፃነት ይበጃል ብሎ የደከመለት ግንቦት ሰባት በብዙ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ እንዲገባና የማይነጥፍ ድጋፍ ባልተጠበቀ ፍጥነት እንዲያገኝ ሲያደርግ የወያኔንና የመሰሎችን ጎራ ናዳ ልኮባቸዋል።

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት (ክፍል ሦስት) – የሌ/ጀነራል ፃድቃን እና የሌ/ጀነራል አበበ ድብቅ ገመና

ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ተንሳይ ፃድቃን ገ/ተንሳይ ኤርትራዊ ከሆኑት ወላጆቹ ስራየ አውራጃ ሰገነይቱ ተወልዶ አድጎ ልክ እንደ ሳሞራ የኑስ ወደ ትግራይ የመጣው በስደት ነው፡፡ ከወላጆቹ ጋር ከኤርትራ ተሰዶ ማይጨው የመጣው በ1955 ዓ.ም ነበር፡፡ ወደ ደደቢት በረሀ አምርቶ ህወሓትን የተቀላቀለው የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን በማቋረጥ ከመቀሌ ኮብልሎ ነው፡፡ ፃድቃን ገ/ተንሳይ ከእነ ሳሞራና ሌሎች የህወሓት ድኩማን ጀነራሎች በወታደራዊ ዕውቀቱ የተሻለ እንደሆነ ይወራለት እንጂ ማንነቱ በትክክል ሲፈተሽ በደደቢት በረሀ ከወሰዱት እዚህ ግቢ የማትባል የአንድ ወር ወታደራዊ ትምህርት በስተቀር ምንም አይነት እውቀት የሌለው፣ በውጊያም እንደ መለስ ዜናዊና ሳሞራ የኑስ እልምያለ ፈሪ እና በየትኛውም ጦርነት ላይ ተዋግቶም ሆነ አዋግቶ የማያውቅ እንደሆነ እሱን በቅርበት የሚያውቁት ሀቁን ይመሰክራሉ፡፡

ጆሮ ባለጌ ነው፤ ሳይፈልግ ይሰማል

ጆሮ ባለጌ ነው፤ ሳይፈልግ ይሰማል፡፡ ሳይቆነጠጥ ያደገ ጆሮ ሲሆን ደግሞ ሳይፈልግ የሰማውን ፈልጎም አይረሳም፡፡ ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ንግግሮች እና ከሰጧቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች መካከል ጆሯችን ሳይፈልግ ሰምቶ፣ ፈልገን ልንረሳ ያልቻልናቸው፡- wink emoticon
«የኢትዮጵያ ታሪክ 3000 አመት ነው ሲባል በተደጋጋሚ እሰማለሁ፡፡የኢትዮጵያ ዕድሜ መቶ አመት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የሚናገሩ ሰዎች ራሳቸውን በተረት ተረት እያሞኙ ነው»
«ባድመ ለኤርትራ ተሰጠች ብለው የሚያጉረመርሙ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ይግባኝ የሌለው የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሳኔ ነው፡፡ ስለዚህ ምንም ማድረግ አይቻልም፤ መልመድ ነው፡፡»
«ትግሬዎች አክሱም ሃውልት አላቸው፤ ይህ ለጉራጌ ህዝብ ምኑ ነው? አገዎች ላሊበላ አላቸው፤ ይህ ለኦሮሞ ህዝብ ምኑ ነው? ጎንደሬዎች ቤተመንግስት አላቸው፤ ይህ ለወላይታ ህዝብ ምኑ ነው?»

አይነጋ መስሏት...

በየትኛውም የአለም ሃገራት ድርቅ ሊከሰት ይቻላል፡፡ ድርቅ ማለት በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ በሆነ ምክንያት የሚፈጠር የአየር ፀባይ መዛባትን ተከትሎ የሚከሰት የውሃ እጥረት ነው፡፡ 
ይህ የውሃ እጥረት በእፅዋት እና እንስሳት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እንደ ህዝቡ ነቃተ ህሊና እና እንደ መንግሥቱ አርቆ አሳቢነት ይወሰናል፡፡ ለዚህም ነው <ድርቅ ረሃብ አይደለም> የሚባለው፡፡ 
እንደ ዶሮ ከህዝብ አፍ ስር የሚለቅም መንግሥት ባለበት ሀገር ድርቅና ረሃብ አንድ ናቸው፡፡ 

ሰላሳ ሶስት መኮንኖች ከየታሰሩበት እዝ ተግዘው አለም በቃኝ ተወረወሩ… (ስም ዝርዝር ተያይዟል)

የወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ 7 መቶ አለቆች 5 ሻምበሎች 8 ሻለቆች 13 ኮሎኔሎች በድምሩ 33 የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከሰሜን እዝ እና ከደቡብ ምስራቅ እዝ ታስረው የነበሩበት መኮንኖች ተግዘው አዲስ አበባ ቃሊቲ አለም በቃኝ ካለፍርድ መወርወራቸው በወታደራዊ ደህንነት መምሪያ ከፍተኛ መኮንን የሆኑና እስረኞቹ ተግዘው ወደ አለም በቃኝ ሲወርዱ የተመለከቱ የአይን እማኝ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል። የአይን እማኙ እንዳሉት በምድር ጦር የደህንነት ክፍል እና በወህኒ ቤቱ መካከል ከማንም እስረኛ ጋር እንዳይገኛኙ ተደርጎ እንዲታሰሩ በጥብቅ ምስጢር የተረካከቡት እስረኛ ወታደሮች በየእዙ ውስጥ በመንግስት ላይ ታሴራላችሁ ወታደሩን ታነሳሳላቹ በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን እንዲነግስ አድርጋችኋል ሕገ መንግስታዊ መብቶች የሚሉ ጥያቄዎችን ደጋግማችሁ ታነሳላችሁ ከጠላቶቻችን ጋር አብራችኋል በሚል ተሰብስበው የታሰሩ እና በእዞቹ አካባቢ ያለውን የአካባቢ ሰላም መደፍረስ እና የወታደሮች ጉርምርምታ በመፍራት ይዘዋቸው ወደ አዲስ አበባ ካለፍርድ አለም በቃኝ እንዳስገቧቸው ታውቋል።

Tuesday, August 11, 2015

ውድ ቴዲ አድሃኖም – ውሸትም ክብር አለው (ከስንሻው ተገኘ)

በምገኝበት አገር አብሮኝ የሚሰራ አፍሪካን-አሜሪካን ወዳጅ አፍርቻለሁ። ስለ ኢትዮጵያ አንዳንድ የታሪክ ግንዛቤዎች እንዲኖሩት ጉጉት ስላለው ደስ እያለኝ ከማውቃት አካፍለዋለሁ። አንዳንድ ጊዜ ግን የምደነግጠው እኔ ከማውቀው በላይ እየሄደ ስለ ኢትዮጵያ አዳዲስ ነገር፣ “ይቅርታ ምጥ ለእናቷ አስተማረች እንዳይሆንብኝ…” ይልና አዳዲስ ክስተቶችን ይነግረኛል። የትናንቱ ጥያቄው ደግሞ ልዩ ነበር። ይኸው ማይክል የምለው ጓደኛዬ “የኢትዮጵያ Gestapo ምን ስም አለው?” ብሎ አፋጠጠኝ። (በነገራችን ላይ ጌስታፖ ትልቁ የሂትለር የአፈናና የግድያ ተቋም ነበር። ይህ ከ 32,000 ሰራተኞች በላይ የነበሩት የስለላ ተቋምና ለአርያን ዝርያ ጠላት ናቸው የተባሉትን አይሁዶች፣ ኮሙኒስቶችና፣ የናዚ ፍልስፍና የሚቃወሙትን ሁሉ በስልት የሚያስወግድ ድርጅት በራሱ ጠንካራ ውስጣዊ መንግስት ነበር።)

የእስረኛው ማስታወሻ በኢትዮጵያ እውነትና ፍትህ ከትቢያ የተሻለ ቦታ ቢኖራቸው ኖሮ (አንዷለም አራጌ)

 የእስረኛው ማስታወሻ በኢትዮጵያ እውነትና ፍትህ ከትቢያ የተሻለ ቦታ ቢኖራቸው ኖሮአንዷለም አራጌ
ውድ ኢትዮጵያውን፡-
ሕዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት በሆነበት ሃገር ፍትህ ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ትቀመጣለች፡፡ እውነትም ምሰሶና ወጋግራ ሆና ፍትህን ዘወትር የመደገፍ እድሏን ትጎናጸፋለች፡፡ በኢትዮጵያ የፍትህና የእውነትን የክብር ቦታና ሚና አፈ-ሙዝ ወስዶታል፡፡ ፍትህና እውነት ደግሞ ትቢያ ላይ ተጥለዋል – ምንም እንኳ እንደወደቁ ባይኖሩም፡፡
Andualem's Family
በኢትዮጵያ ፍትህና እውነት ትቢያ ላይ ባይጣሉ ኖሮ ለዓመታት ይቅርና ለሰዓታት እንኳን በእስር ቤት ግርጌ መጣል ባላስፈለገንም ነበር፡፡ ፍትህና እውነት በኢትዮጵያ አድራሻ ቢኖራቸው ኖሮ ለዚህ ዓለም እንግዳ የሆኑት ልጆቼ ለዓመታት ሳይሆን ለሰዓታት እንኳን የአባታቸውን ፍቅር በግፍ ባልተነጠቁ ነበር፡፡ ፍትህና እውነት የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን ብትሆን ኖሮ ለዓመታት ሳይሆን ለሰዓታት እንኳን ባለቤቴ ከእኔ ጋር የመኖር ሰብዓዊ መብቷን ተገፋ በወጣትነት እድሜዋ የመበለትነት ህይወት የመግፋት እዳ ባልወደቀባት ነበር፡፡ ፍትህና እውነት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እንኳን መንሳፈፍ ቢችሉ ኖሮ በሃሰት ዶሴ ከታሰርኩ በኋላም ለዓመታት በእስር ቤት ውስጥ ተጨማሪ የግፍ ፅዋ እንድንጎነጭ ግድ ባልሆነብኝም ነበር፡፡ በኢትዮጵያ እውነትና ፍትህ ከትቢያ የተሻለ ቦታ ቢኖራቸው ኖሮ ረጅም ርቀት አቆራርጠው ሊተይቁኝ የሚመጡ ጠያቂዎቼ የመጠየቅ መብታቸውን ለዓመታት ሳይሆን ለሰዓታት እንኳን ባልተነፈጉም ነበር፡፡