Wednesday, August 26, 2015

‹‹ወራዳ! አሁንም እደግመዋለሁ ወራዳ!›› ያለው ማን ነበር?

አቶ መለስ ናቸው! እውነታቸውን ነው፡፡ መንግስት ተብየው፣ ህወሓት/ኢህአዴግ ወራዳ ነው!
ዛሬ የእሳቸውን አባባል ልጠቀም ነው፡፡ ‹‹መንግስት›› የሚባለው ወራዳ ነው፡፡ እደግመዋለሁ ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት ደህንነትና አባላቱን የሀሰት ምስክርነት አስጠንቶና አደራጅቶ ፍርድ ቤት የሚልከው ኢህአዴግ ወራዳ ነው! ወራዳ!

ይህን የምለው ዝም ብዬ አይደለም፡፡ ብልግናም ተሳዳቢነትም አይደለም፡፡ ያንሰዋል፡፡ ይህን የምለው ማሙሸት አማረ ላይ የቀረቡትን ምስክሮች አይቼ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዳኛውም ቢሆን በልቡ የአቶ መለስን ቃል ቢጠቀም ደስ የሚለው ይመስለኛል፡፡ ካየሁት፡፡ አቃቤ ህጉ ደግሞ አቶ መለስ የሰደቡት አይነት ሰው ነው! እጅግ እጅግ ያሳዝናል!

No comments:

Post a Comment