Saturday, August 1, 2015

ከ40 በላይ የወያኔ አየር ሀይል ሰራተኞችና ባለሙያዎች መጥፋታቸው ተነገረ

በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከአየር ሀይል ከ40 በላይ ሰራተኞችና ባለሙያዎች በስልጣን ላይ ያለውን የወያኔ አገዛዝ በመክዳት ወደተለያዩ ቦታዎች መጥፋታቸው ታወቀ:: የአየር ሀይል የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ከደብረዘይት ጠቅላይ መምሪያና ከተለያዩ የአየር ሀይል ምድቦች የጠፉት ባለሙያዎች 14 ቴክኒሺያኖችን የሚጨምር ሲሆን አብራሪዎችም እንደሚገኙበት ታውቋል::
ለአንድ ወር በስራ ገበታቸው ያልተገኙትን እነዚህን ሰራተኞችና ባለሙያዎች ለመያዝ የህወሀት መከላከያ ሚኒስቴር አሰሳ እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል:: ቴክኒሺያኖቹና አብራሪዎቹ ተቃዋሚዎችን ሳይቀላቀሉ እንደማይቀር የኢሳት ምንጮች ይገልጻሉ:: በአንድ ወር ብቻ ይሄን ያህል ባለሙያ መክዳቱ ለአየር ሀይል ከፍተኛ ኪሳራ እንደሆነም ይነገራል::

No comments:

Post a Comment