Sunday, August 16, 2015

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት (ክፍል ሦስት) – የሌ/ጀነራል ፃድቃን እና የሌ/ጀነራል አበበ ድብቅ ገመና

ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ተንሳይ ፃድቃን ገ/ተንሳይ ኤርትራዊ ከሆኑት ወላጆቹ ስራየ አውራጃ ሰገነይቱ ተወልዶ አድጎ ልክ እንደ ሳሞራ የኑስ ወደ ትግራይ የመጣው በስደት ነው፡፡ ከወላጆቹ ጋር ከኤርትራ ተሰዶ ማይጨው የመጣው በ1955 ዓ.ም ነበር፡፡ ወደ ደደቢት በረሀ አምርቶ ህወሓትን የተቀላቀለው የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን በማቋረጥ ከመቀሌ ኮብልሎ ነው፡፡ ፃድቃን ገ/ተንሳይ ከእነ ሳሞራና ሌሎች የህወሓት ድኩማን ጀነራሎች በወታደራዊ ዕውቀቱ የተሻለ እንደሆነ ይወራለት እንጂ ማንነቱ በትክክል ሲፈተሽ በደደቢት በረሀ ከወሰዱት እዚህ ግቢ የማትባል የአንድ ወር ወታደራዊ ትምህርት በስተቀር ምንም አይነት እውቀት የሌለው፣ በውጊያም እንደ መለስ ዜናዊና ሳሞራ የኑስ እልምያለ ፈሪ እና በየትኛውም ጦርነት ላይ ተዋግቶም ሆነ አዋግቶ የማያውቅ እንደሆነ እሱን በቅርበት የሚያውቁት ሀቁን ይመሰክራሉ፡፡
አነሩ መለስ ዜናዊ ድመቶችን በዙሪያው ሰብስቦ ነብር መስሎ ለመታየት ለ21 ዓመታት ሲፍጨረጨር እንደታየው ሁሉ ወጠጤው ፃድቃን ገ/ተንሳይም በግልገሎች መካከል ቆሞ ሰንጋ መስሎ ለመታየት ሞክሯል፡፡ በ1971 ዓ.ም ዓብይ ወዲ እና ዓዲ ኮኾብ እንዲሁም በተጨማሪ በ1973 ዓ.ም ሀውዜን ላይ በተደረጉት ውጊያ መሰል መጠነኛ መቆራቆሶች ፃድቃንን ከድንጋይ ስር ተደብቆ በፍርሀት ሲርበተበት በአይኖቹ በብረቱ እደተመለከተው የቀድሞው የህወሓት ነባር ታጋይ ገ/መድህን አርአያ ይናገራል፡፡ በመሆኑም ሦስት ጊዜ በተደጋጋሚ ፈርቶ ከጦር ሜዳ የሸሸው ፃድቃን ገ/ተንሳይ ለአምስት ወራት መታሰሩን ከህወሓት ዶሴ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የኋላ ታሪኩ ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ከመለስ ዜናዊና ከስብሀት ነጋ ጋር ባለው የጠበቀ ወዳጅነትና ቅርርብ የእስር ጊዜውን ካጠናቀቀ በኋላ በለስ ቀንቷቸው መላ አገሪቱን እስከ ተቆጣጠሩበት 1983 ዓ.ም ድረስ በኮሚሰርነት ተመድቦ ቆይቷል፡፡ ቢሆንም ዳር ቆሞ ሲመለከት ኖረ እንጂ አንድም ጊዜ ተሳስቶ ጦርነት አልመራም፡፡ ፃድቃን ገ/ተንሳይ ከበረሀ ጀምሮ ፈፅሞ በማይግባባውና እጅግ በጣም ይጠላው በነበረው ሀየሎም አርአያ ግድያ ከመለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ እና አርከበ ዑቁባይ በተጨማሪ እጁ እዳለበት መቶ በመቶ የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡ ፃድቃን ገ/ተንሳይ ከኤርትራ ጋር በተደረገው ውጊያ እሱ ባወጣው መቶ በመቶ የተሳሳተ የጦር ስልት ምክኒያት በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ የደሀው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች ፆረና ላይ ያለአግባብ በከንቱ ረግፈው ቀርተዋል፡፡ ሬሳቸው እንኳን የሚለቅመው ጠፍቶ በፆረና ተራሮች ላይ ተዘርተው አፅማቸው ተልከስክሶ አሁንም ይገኛል፡፡ መሀይሙ ጀነራል ፃድቃን የቀየሰው የጦር ንድፍ መቶ በመቶ ሲበለሻሽና ከፍተኛ እልቂት ሲደርስ ከሱ በታች ያሉ ሌሎች ጀነራሎችን አስከትሎ ከአከባቢው ሸሽቷል፡፡ ፃድቃን ገ/ተንሳይ በጡረታ ስም ከሰራዊቱ ይገለል እንጂ በስልጣን ዘመኑ በዘረፋ ያካበተው ከፍተኛ ሀብት ሳያንሰው ኤታማጆር ሹም በነበረበት ጊዜ ያገኘው የነበረው ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ ተከብሮለት በእጅጉ በተንደላቀቀ ህይወት ውስጥ ይገኛል፡፡ ሌተናል ጀነራል አበበ ተ/ኃይማኖት ወይንም ጆቤ መቀሌ የተወለደው አበበ ተ/ኃይማኖት ህወሓትን የተቀላቀለው በ1968 ዓ.ም ሲሆን ልክ እንደማናቸውም የህወሓት ጀነራሎች የአንድ ወር ወታደራዊ ስልጠና ከወሰደ በኃላ የሐለዋ ወያኔ ባዶ ስድስት ወይንም የትግራይ ጓንታናሞ ኃላፊ ሆኖ በቀጥታ ቡምበት ላይ ተመደበ፡፡ የታጋዮች ቀራኒዮ የነበረውና ዕልፍ ዓዕላፍ ንፁሀንን ህይወት ቅርጥፍ አድርጎ የበላው ያ አደገኛ ወህኒ ከቡምበት ተነስቶ ወደ አጽርጋት ሱር ከተዛወረበት 1969 ዓ.ም እስከ 1974 ዓ.ም ኃላፊው አበበ ተ/ኃይማኖት ነበር፡፡ ብስራት አማረ፣ ታደሰ መሰረት፣ ተስፋዬ መረሳ፣ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል፣ ተስፋዬ አፅብሃ፣ ዘአማኑኤል ለገሰ፣ አበበ ዘሚካኤል፣ ዘርዓይ ይህደጎ፣ ሐሰን ሽፋ እና ክንፈ ገ/መድህን በዋነኝነት ከአበበ ተ/ኃይማኖት በተጨማሪ ሐለዋ ወያኔ ወይንም ባዶ ስድስት በተባለው አደገኛ ወህኒ ውስጥ በየጊዜው በሚታሰሩ ታጋዮች ላይ ሰቆቃና አሰቃቂ ግድያ ሲፈፅሙ የኖሩ ናቸው፡፡ አበበ ተ/ኃይማኖትና ሌሎችም ሰቆቃና አሰቃቂ ግድያ ፈፃሚ የህወሓት ታጋዮች ተጠሪነታቸው ለመለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ እና አባይ ፀሐዬ ነበር፡፡ አበበ ተ/ኃይማኖት ወይንም ጆቤ የሐለዋ ወያኔ-ባዶ ስድስት ወህኒ ቤት ኃላፊ ሆኖ በሰራባቸው ዓመታት ውስጥ በግፍ በታሰሩ ንፁሀን ታጋዮች ላይ እንዲፈፀሙ ካደረጋቸው በርካታ የማሰቃያ ወይም የ”ቶርቸር” ድርጊቶች መካከል ሴቶችንም ጭምር ርቃን ገላቸውን ከግንድ ጋር በማሰር ለረጅም ጊዜ ፀሀይና ብርድ እንዲፈራረቅባቸው ማድረግ፣ ገልብጦ የእግር መዳፍን መግረፍ፣ ከ16 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን አሽዋ ከወንዶች ብልታቸው ላይ ከሴቶች ደግሞ ጡታቸው ላይ ማሰር፣ በፈላ ውሀ መቀቀል፣ በጋለ ብረት መቀመጫን ማቃጠል፣ ጭንቅላትን ወደታች ዘቅዝቆ ማንጠልጠል፣ ባዶ እግርን በሾህ ላይ እንዲራመዱ ማድረግና ከፍተኛ ክብደት ያለው ብረት ወይንም ድንጋይ አሸክሞ ለረጅም ጊዜ ማቆም ዋና ዋና ዎቹ ናቸው፡፡ እነኚህ የማሰቃያ ወይንም “ቶርቸር” አይነቶች ዛሬም በየእስር ቤቱ በስራ ላይ እተተገበሩ ይገኛሉ፡፡ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ የህወሓት ደህንነቶች ሴቶችን በወር አበባቸው ሳይቀር ልብሶቻቸውን አስወልቀው ዕርቃናቸውን አቁመው በሀፍረተ ስጋቸው እየተሳለቁ የሚመረምሯቸው መሆኑ በቅርቡ የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡ አበበ ተ/ኃይማኖት በሱር የሐለዋ ወያኔ ወይም ባዶ ስድስት ኃላፊ በነበረበት ወቅት የወልቃይት ህዝብ በገፍ እየታፈሰ እንዲረሸንና በጅምላ እዲቀበር በማድረግ ዘር ማጥፋት ፈፅሟል፡፡ አበበ ተ/ኃይማኖት ከአደገኛው እስር ቤት ኃላፊነቱ በ10 ሺህዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ሰቆቃና ጭፍጨፋ ከመፈፀምና የገበሬውን ሰራዊት ማርኪሲዝምና ሌኒንዝም ርዕዮተ ዓለም ከማስተማር በዘለለ ለአንድ ጊዜ እንኳን ውጊያ ላይ አልተሳተፈም ፡፡ ልክ እንደ ሳሞራ እና ፃድቃን እሱም ለጀነራልነት የበቃው ለእነ መለስ ዜናዊና ስብሀት ነጋ ባለው ታማኝነትና አጎብዳጅነት ብቻ ነው፡፡ አገራችንን ረግጠው በኃይል ለመግዛት ከቻሉ በኋላም እንኳን ሊኮፈስባት በገንዘብ የገዛት የህግ ባችለር ዲግሪው ከሙያው ጋር የማትገናኝ በመሆኗ እሱንም እንደሌሎቹ የበረሃ ጓዶቹ የህወሓት ጀነራሎች የጦር ማሃይምነት ድቅድቅ ጨለማ ውጦት ቀርቷል፡፡ አበበ ተ/ኃይማኖት ወይም ጆቤ ልክ እንደ ሳሞራ የኑስ የወጣለት ሴሰኛ በመሆኑ የበረሃ ጓዶቹን ሚስቶች ሳይቀር በማባለግ ይታወቃል፡፡ የአየር ኃይል አዛዥ በነበረበት ወቅት አየር ኃይል ጠ/መምሪያ ቢሮ የምትሰራውን የሜ/ጀነራል መሃሪ ዘውዴን ባለቤት በማባለጉ “ባለቤቴን ማባለጉ አልበቃ ብሎ ባልሽን ወደ አንዱ ጦርነት ስለምልከው እና ስለሚሞት ልጅ ውለጅልኝ እያለ ባለቤቴን ቁምስቅሏን እያሳያት ነው፤” ሲል መሀሪ ዘውዴ ክንፈ ገ/መድህን በተገደለበት የህወሓት ከፍተኛ መኮንኖች ስብሰባ ላይ ከሶታል፡፡ ከእሱ በኋላ የአየር ኃይል አዛዥ የሆነውን ሜጀር ጀነራል ሞላ ኃ/ማሪያምን ሚስቱን ቢሰጠው የጀነራልነት ማዕረግ ትከሻው ላይ እንደሚያስርለት ነግሮት ሞላም በጉዳዩ ተስማምቶ የሁለት ልጆቹን እናት ለአበበ ተክለ ኃይማኖት በማከራየት ከኮሎኔልነት ጀነራል በመሆን ህልሙን አሳክቷል፡፡ በመጨረሻም የሞላ ኃ/ማሪያም ትዳር በአበበ ተ/ኃይማኖት ምክንያት ሊፈርስ ችሏል፡፡ አበበ ተ/ኃይማኖት የአየር ኃይል አዛዥ በነበረበት ወቅት አየር ኃይል የቁልቁለት ጉዞ በሸርተቴ የተጓዘ ሲሆን የራሽያን ጀነራሎች በአማካሪነት ስም አምጥቶ ቀዳዳውን ለመሸፈን ተፍጨርጭሯል፡፡ ብ/ጀነራል ተጫኔ መስፍንንም ከእስር ቤት አውጥቶ አማካሪው አድርጎታል፡፡ ከሴሰኝነት በተጨማሪ የህወሓት ዋነኛ መለያዎች የሆኑት ዘረኝነትና ሌብነት አበበ ተ/ኃይማኖት ላይም በጉልህ ይታዩ ነበር፡፡ በመሆኑም አየር ኃይሉን አንድ አይነት ቋንቋ በሚናገሩ የአንድ አካባቢ ሰዎች ሞልቶታል፤ እስኪበቃውም መዝብሮታል፤ አስመዝብሮታል፡፡ አበበ ተ/ኃይማኖት በአንድ ወቅት በአሉዌት ሄሊኮፕተር ተሳፍሮ ወደ ጋምቤላ ሲሄድ ካላበረርኩ ብሎ አብራሪውን በማስቸገሩ አብራሪው ቦታውን ለቆለት ተቀብሎ አሉዌት ሄሊኮፕተሯን ልክ እንደ እምቧይ ከምድር አፍርጧታል፡፡ በተጨማሪም አበበ ተ/ኃይማኖት ሲጋራ፣ ዊስኪ እና ሴት ለማስመጣት በየከተማው ሄሊኮፕተር ይልክ ነበር፡፡ አበበ ተ/ኃይማኖት ምንም እንኳን ዛሬ በስጋ ከህወሓት የተነጠለ ቢመስልም በመንፈስ ግን ጨርሶ አልተለየም፡፡ በ1993 ዓ.ም የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከሁለት ሲሰነጠቁ በአንጃነት ተፈርጀው የተባረሩት የቀድሞ ታጋዮች እንዲመለሱ ተወስኖ ጥሪ ሲደረግላቸው አበበ ተ/ኃይማኖትንም አካተውት ወደ ባንዳዎች ስብስብ ለመመለስ እና በባንዳነቱ ለመቀጠል ስምምነቱን ገልጿል፡፡ የምድር ኃይሉ እና የአየር ኃይሉ ቁንጮ የነበሩት ሁለቱ የህወሓት ጀነራሎች አበበ ተ/ኃይማኖት እና ፃድቃን ገ/ተንሳይ ከመከላከያ ሰራዊቱ ሲወገዱ በህወሓት መንደር አንዳች ለውጥ አለመታየቱ የሰዎቹን ሚናየለሽ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ የጀነራልነትን ማዕረግ ለበሱት እንጂ ከጀነራልነቱ ማዕረግ ጋር የሚመጣጠን ወታደራዊ ዕውቀት የሌላቸው ቦታ ብቻ የያዙ ባዶ ዕቃዎች መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡ ግንቦት 8 ቀን 1981 ዓ.ም ተሞክሮ በከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ተሳታፊ የነበሩት ጀነራሎች መረሸን ግን ከአንድ ዓመት በኋላ ደርግን ለውድቀት ዳርጎታል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45863#sthash.mnKw0G26.dpuf

No comments:

Post a Comment