Tuesday, August 4, 2015

ጉዳዩ

ጉዳዩ የኦሮሞዎች ነው ብለው በኦነግ ስም ብዙ ንፁሀን የግፍ ገፈት ሲጋቱ ዝም ብለው አለፉ፤
ጉዳዩ የጋዜጠኞች ስለሆነ ምን አገባኝ እያሉ ስለእነርሱ ይጮሁ የነበሩትን እያሳደደ ሲያስር እና ከሀገር ሲያሳድድ ትንፍሽ አላሉም፤
የማህበራዊ ድህረ ገፅ ፀሀፊዎችን የሚመለከት ነው ብለው ሕገ መንግስቱ ይከበር ያሉ ትንታግ ወጣቶች ከአመት በላይ የሌለውን ፍትሕ ፍለጋ ሲንከራተቱ ይሕ የእኛም ጉዳይ ነው ሳይሉ ባልሰማ ባላየ አለፉ፤

ጉዳዩ ከእኔ ሀይማኖት ጋር አይደለም ብለው መንግስት በሀይማኖት መሀል አይግባ ያሉ በሕዝብ የተወከሉ መሪዎች እስከ 22 አመት ሲፈረድባቸው ለምን ብሎ የመጠየቅ ፍላጎት እንኳ አላሳዩም፤

ነገስ?
ነገማ ጉዳዩ የናትናኤል ነው ጉዳዩ የእገሌ ነው እያሉ በዝምታቸው መከራን ለብዙሀን ይደርስ ዘንድ 'ይተጋሉ'!!!

No comments:

Post a Comment