Wednesday, August 26, 2015

አዲሱ ለገሰ በድጋሚ ተሰናበቱ

ብአዴን ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አቶ አዲሱ ለገሰ በድርጅቱ የመተካካት መርህ መሰረት የነበራቸውን ሃላፊነት አስረክበው በክብር ስለ መሰናበታቸው ተሰምቷል።
አስገራሚው ነገር የቀድሞው ምክትል ጠ/ሚ/ር ከዚህ በፊት ለመተካካቱ ግምባር ቀደም አርአያ በመሆን በክብር ስለ መሰናበታቸው ተነግሮ ነበር።የሄዱት አዲሱ በሌላ ሀላፊነት ብቅ በማለት የተሰናበቱትን ፖለቲካ ተቀላቀሉት።አሁን ደግሞ በብአዴን ጠቅላላ ጉባኤ ፊት ቀርበው መሰናበታቸው ተነግሯል።


አዲሱ ሄደው አዲሱ የመጡበትን የፖለቲካ ውሃ ቅዳ ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎች የአዲሱ መሄድ መመለስን የተንተራሰ በመሆኑ የመተካካቱ ሂደት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም።ለሳልሳይ ግዜ ላለመመለሳቸውስ ማን እርግጠኛ መሆን ይችላል?

No comments:

Post a Comment