Sunday, August 16, 2015

ጆሮ ባለጌ ነው፤ ሳይፈልግ ይሰማል

ጆሮ ባለጌ ነው፤ ሳይፈልግ ይሰማል፡፡ ሳይቆነጠጥ ያደገ ጆሮ ሲሆን ደግሞ ሳይፈልግ የሰማውን ፈልጎም አይረሳም፡፡ ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ንግግሮች እና ከሰጧቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች መካከል ጆሯችን ሳይፈልግ ሰምቶ፣ ፈልገን ልንረሳ ያልቻልናቸው፡- wink emoticon
«የኢትዮጵያ ታሪክ 3000 አመት ነው ሲባል በተደጋጋሚ እሰማለሁ፡፡የኢትዮጵያ ዕድሜ መቶ አመት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የሚናገሩ ሰዎች ራሳቸውን በተረት ተረት እያሞኙ ነው»
«ባድመ ለኤርትራ ተሰጠች ብለው የሚያጉረመርሙ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ይግባኝ የሌለው የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሳኔ ነው፡፡ ስለዚህ ምንም ማድረግ አይቻልም፤ መልመድ ነው፡፡»
«ትግሬዎች አክሱም ሃውልት አላቸው፤ ይህ ለጉራጌ ህዝብ ምኑ ነው? አገዎች ላሊበላ አላቸው፤ ይህ ለኦሮሞ ህዝብ ምኑ ነው? ጎንደሬዎች ቤተመንግስት አላቸው፤ ይህ ለወላይታ ህዝብ ምኑ ነው?»

«ወ/ሮ ገነት ዘውዴ የትምህርት ሚኒስቴር ለመሆን ብቃቱ የላቸውም በሚል ሹመቱን የተቃወሙ ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ የኢህዴግን ፖሊሲ እስካፈፀመ ድረስ 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ ሰው የትምህርት ሚኒስቴር አድርገን ልንሾም እንችላለን፡፡»
«እኔ የመናዊ ነኝ፤ ሁላችንም የመናውያን ነን፡፡ ከነገሥታቱ ቤተሰብ በስተቀር ሁላችንም አረብ ነን»
«እንኳንም ወርቅ ከሆነው ከትግራይ ህዝብ ተወለድኩ» …….. ሃሃሃ መቼም ይሄን የተናገሩት የኦሎምፒክ ሰሞን ይሆናል እንጂ የአንድ ሀገር መሪ እንደ ሜዳሊያ ህዝቦቹን ወርቅ፣ ብር እና ነሐስ እያለ ሲመድብ አይኖርም፡፡

No comments:

Post a Comment