Tuesday, August 4, 2015

ከእባብ ዕንቁላል እርግብ አይጠበቅም።

የውጭ ገዳይ ሚንስቴራችን( የውጭ ገዳይ ያለው አቤ ቶክቻው ነው ) ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና ጥበቃ ሚንስቴር በነበሩ ጊዜ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ የገቡ ሲሆን አንዳንዶች በየዋህነት ሰውዬውንና ስርዓቱን ነጣጥሎ እስከማየት ደረጃ ደርሶ ነበር። ሰውዬው በተፈጥሮ ከአንደበቱ ክፉ የማይወጣውና የፖለቲካ አቋሙ ከሩቅ ሆኖ ለሚመለከት ሰው ለዘብተኛ አይነት ስለሆነ ከጤና ጥበቃ አንስቶ ወደ ውጭ ገዳይ ሚንስቴር ሲወስዱት እኔን ጨምሮ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በየዋህነት "ምናለ ይሄን ሰውዬ ከፖለቲካ ጋር ባያነካኩት" እስከማለት ደረጃ የደረሰ የህዝብ ፍቅር የነበረው ሰው ቢሆንም ባለፈው ሳምንት ከቪኦኤ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ምክንያት ከኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ ውልቅ ብሎ ወጥቷል።
ሰሞኑን በየቦታው የሚወራው ሁሉ ሰውዬው ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ሲሆን አብዛኛው ሰው እስከዛሬ ሰውዬውን ከስርዓቱ ነጥሎ ሲመለከተው ስለነበረ በሰውዬው ቃለ ምልልስ ተከፍቷል።
ቀድሞውኑ ከእባብ ዕንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ መጠበቅ ቅጥ ያጣ የዋህነት ነው።

No comments:

Post a Comment