Wednesday, August 26, 2015

ቴዲ አፍሮን ከፋሽስት ርዝራዦች ጥርስ እናስለቅቅ!

አስደንጋጭ መረጃ ስለ ቴዲ አፍሮ!
ከዛሬ ወር በፊት አንድ የህወሃት ሰላይ እንዲህ አለኝ፡፡ የቴዲ አፍሮን አዲሱን ዜማ እየሰማሁ ሳለ አምልጦት ነው መሰል እንዲህ አለኝ ከዚህ በኋላ በምንም ተዓምር የቀድሞ ዝናውን አያገኝም፡፡ ለምን ስለው ለሱ የታሰቡ ነገሮች አሉ አለኝ፡፡ ምንድንነው ስለው ሀገር ቤት ለሚገኙ ማንኛውም ድርጅት ለቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ስፖንሰር እንዳይሆኑ ያለበለዚያ የንግድ ፈቃዳቸው እንደሚቀማ የተነገራቸውም አሉ፡፡ ከዛስ አልኩት እንደውም እየሰራ የሚገኘውን አዲሱን አልበም በዱርዬዎች ለማሰረቅ ሀሳብ ቀርቦ ነበር፡፡ በዚህም እሱን በኢኮኖሚ ማዳከም ስለሚያስፈልግ ብሎ ጨመረልኝ፡፡ እስካሁን ከቁም ነገር አልቆጠርኩትም፡፡

ሌላም ቀጠለ እንደውም ሀገር ቤት የሚገኙ ታዋቂ የሙዚቃ አቀናባሪዎችም የቴዲን ሙዚቃ ቢያናቀብሩ በጸረ ሽብር ህጉ ሊከሰሱ እንደሚችሉ የተነገራቸው አሉ ግን አልሰሙም አለኝ፡፡ ሌላስ አልኩትና ዘረገፈልኝ ከዚህ በፊት ጥቁር ሰው ብሎ ዘፍኖ ምንሊክን በማድነቅ የዘፈነውን የፖለቲካ ይዘት በመጽሃፍ ታትሞ ካድሬዎች ሰልጥነው፡፡ የተሰበሰበው መረጃ የሚያመለክተው በማንኛውም የመንግስት የልማትና ፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ሲሳተፍ አይታይም እሱ ማን ስለሆነ ነው ብሎ አንድ የትግራይ ሰው በቁጣ ሲናገር ተደምቷል አለ፡፡ በርካታዎቹ ቢቃወሙትም፡፡ ሰውዬው ሲያብራራም እሱ ሃብታም ስለሆነ ነው መንግስትን የማይቀርበው እንደሌሎቹ አርቲስቶች የኛ ጥገኛ ለማድረግ እሱን በኢኮኖሚ ማድቀቅ ዋነኛ ስራ መሰራት አለበት አለ፡፡ የሚሸጠውን ሙዚቃ ማስተጓጎል፣ከተቻለም መዝረፍ እንደ ስልት ቢያዝ ብሎ የተናገረ ሰው ነበር አለኝ፡፡ ከዚያም አንተስ ስለ እሱ ያለህ አመለካከት ስለው እኔ ተወልጄ ያደግኩት እዚህ አዲስ አበባ ስለሆነ በነርሱ ደረጃ ሃሳባቸው አይዋጥልኝም አለኝ፡፡ በወቅቱ ጉዳዩን ከምንም ስላልቆጠርኩት ረስቼው ነበር፡፡
አሁን ደግሞ የኢሳቱ መሳይ መኮንን ቴዲ አፍሮ እየተገፋ ነው ሲል ትዝ አለኝ፡፡ በርግጥም ቴዲ ላይ ከባድ ጫና እየበረታበት ይገኛል፡፡ እግዚአብሄር የመቻል አቅም ሰጥቶት እንጂ ብዙ በደል ደርሶበታል፡፡ ግን እስካሁን ትንፍሽ አላለም፡፡ እሱ ባይናገርም እኛ ለርሱ በመቆም የምንወደውን ቴዲ ከህወሃት መንጋጋ ፈልቅቀን በማውጣት ነጻ ሰው ልናረገው ይገባል፡፡ ኮርኩማ አፍሪካ እንዳለው እሱንም ኮርኩመን እናስወጣዋለን እያሉ የሚገኙትን የህወሃት የፋሽስት ርዝራዦችን ማሳፈር ይኖርብናል፡፡ ቴዲ እንወድሃለን፡፡

No comments:

Post a Comment