Wednesday, August 26, 2015

አንድ አሜሪካዊ ወደ ትልቅ

አንድ አሜሪካዊ ወደ ትልቅ እና ቆንጆ ሬስቶራንት ከምታምር
ሚስቱ ጋር ይገባል ፡፡ ሬስቶራንቱ በሰው ተሞልቷል ...... ወደ
ሬስቶራንት እንደገባ ጥግ ላይ ብቻውን የተቀመጠ ጥቁር
አፍሪካዊ ያያል ፡፡ ይህ አሜሪካዊ ጥቁር በጣም ይጠላ ነበርና
"አስተናጋጅ "ብሎ ጮክ ብሎ ተጣራ.... አስተናጋጁም በፍጥነት
መጣ ፡፡ የኪስ ቦርሳውን አወጣና እዚህ ሬስቶራንት ላሉት
በሙሉ ከዛ ጥቁር ሰው ውጭ ( ወደ አፍሪካዊው እየጠቆመ )
የሚበላ ምግብ ታዘዛቸው አለው ፡፡ ይህን ይከታተል የነበረው
አፍሪካዊ በፈገግታ አሜሪካዊውን አየው ፡፡

አሜሪካዊው በዚህ
ሰውየ ተበሳጨ.... እንደገና አስተናጋጁን ጠራና ከዚህ ጥቁር
ሰው ውጭ ለሌሎች የሚጠጣ ወይን በኔ ሂሳብ አቅርብላቸው
አለ ፡፡ ይህ ጥቁር ሰው ግን አሁንም የተጋባዦቹን ያክል ደስተኛ
ነበር ፡፡ ነጩ ሰውየ በጣም ገረመው አስተናጋጁን ጠራውና ይህ
ጥቁር ሰው ሳልጋብዘው እንደተጋበዘ ሰው ደስተኛ ያደረገው
ምንድነው ?? ብሎ ጠየቀው ... ጌታየ አያውቁትም እንዴ የዚህ
ግዙፍ ሆቴል ባለቤት እኮ እሱ ነው .... ነጩ ሰው በድንጋጤ
ክው አለ ፡፡ እንደ የሎጥ ሚስት ደርቆ ቀረ !!
----
እና ምን ለማለት ፈልገህ ነው አምራን ?? ካላችሁኝ ...
ጠላታችን እኛን የጎዳ መስሎት የሚያደርገው ተግባር
ለኛ ግን ጥሩ አጋጣሚ ሆኖ የሚያልፍበት ጊዜ አለ !!!

No comments:

Post a Comment