Sunday, March 20, 2016

"ኢህአዴግ ነው ቃሉን የሚያጥፍ። ኢህአዴግ ይመስል..." ይሄ ነበር የወሬው መነሻ....

"ኧረ፥ ምን ቃል ይበላል? ቃል አክባሪ ነው።" - ለማደናቆርና ለማናዘዝ።
ኢህአዲግማ ቃል አባይ ነው። ከተፈጠርኩኝ ቃሉን እንዲህ የሚበላ አንድ ሰውም አላየሁም።
ሌላ ሌላውን እንተወው... "20 ዓመት ተፈረደበት" ይባልና ሀብት ያለው በዛ ያለ ብር ሲሰጥ ይቀነስና ይፈታል። ብሩ ከተጠራቀመ 20 ቀንም አይፈጅም፤ ወንጀል ሰራ የተባለው ከቤተሰቡ ጋር ይቀላቀላል። ወንጀል ያልሰራው ምስኪን፣ ነካን ካሉ መቼም አይፈታም። ፃፉ ቢሉም ሲጽፉ ያስራሉ። ስብሰባ ጠርተው የጠሉትን እና ዐይን የጣሉበትን ከስብሰባ ይለቅማሉ።
በኃይለስላሴ ዘመን እንዲህ ያለ ቃል ማጠፍ የለም።
በመንግስቱም ቢሆን እንዲህ የለም። ሰዉ ቁርጡ ይነገረዋል፥ ከዚያ ሲወጣ ይቀጣል። ይሄኛው ግን ወሬው ሌላ፣ ስራው ሌላ።
በእርግጥ ውኃ ሳይሆን ቧንቧው በዝቷል በኢህአዴግ ጊዜ።

በመንግስቱ ጊዜ ሩቅ ሄደንም ቢሆን እንደልብ እንቀዳዋለን። ቦኖም ቢሆን ሱቅ፥ ቀኑን ሙሉ ውኀው ይወርዳል። ወገብ ካልደከመ ውኀው አትቅዱኝ አይልም። አሁን ስሙ ተረፈን። "ቧንቧ አላቸው" ይባላል እንጂ በጥም ስንሞት ማንም አያውቅም። ይህችን ዓመት እንኳን ጥሩ ነው። በ4 ቀን አንዴም ውኀ አላጣንም።
የመብራቱማ
"መለስ በፈረቃ
ኀይሌ በደቂቃ" ነው። ብልጭ ድርግም ይላል። የባሰው መጣ።
መንገዱን እንኳን ለወሬ ነው የሰሩት። እንዲታይላቸው። ሰው መንገድ አይቶ እድገት ያወራል።
.
.
.
ከእናቴ ጋር ውዬ ሳመሽ ይህን ይህን እናወራለን። ይህን ይህን አሰላስላለሁ።
ሀሳቤንም ንግግራችንም ደባልቄ ነው የጻፍኩት።
የእኔ እናት heart emoticon

No comments:

Post a Comment