Wednesday, November 26, 2014

ርዮት አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ሰንድቅ አላማ በላይዋ ላይ ለብሳ በክብር ከቃሊቲ ትወጣለች – ግርማ ካሳ


index
በሃይ ስኩል የእንግሊዘኛ አስተማሪ ነበረች። በሕገ መንግስቱ ላይ የተደነገገዉን መብት በመጠቀም፣ በተለያዩ አገር ውስጥ በሚታተሙ ሜዲያዎች ትጽፋለች። «እነርሱ እንዲጻፍ ከሚፈልጉት ዉጭ እንዲጻፍ የማይፈልጉ ባለስልጣናት፣ የሃሰት ክስ መሰርተዉ፣ ዳኛ ለተብዬዎች መመሪያ ሰጠዉ፣ መሰረተ ልማቶችን ለማፍረስ አሴራለች፣ ሽብርተኛ ናት» ብለዉ ፈረዱባት።
ይች እህት ርዮት አለሙ ትባላለች። ጡቷ አካባቢ ችግር ስላለበት ክትትል እንደሚያሰልጋት እየታወቅም ክትትል እንድታገኝ አልተደረገም። ወደ ሶስት አመት ገደማ ባላጠፋችዉ ጥፋት፣ ኢሕአዴግን ስለተቃወመች ብቻ፣ እየማቀቀች ነዉ። የርዮት ወንጀል አገሯ፣ ሕዝቧን መዉደዷ ነዉ።

ሕዳር ሁለት ለፍትህ እና ለዳኝነት(የህዳር ሁለቷ የፍርድ ቤት ውሏችን) – ኤልያስ ገብሩ

Elias-Gibru-Godana-225x300
አይ ‘ልማት’ ¡
ክፍል – 1
——————
ስለተከሰስኩበት ክስናና ይህንንም ተከትሎ ከእስር ጋር በተገናኘ ሥለነበረው ሁነት አንድ ሁለት በማለት ዛሬ ማውጋት ልጀምር፡፡ ከጽሑፍ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ስቀርብ ለሶስተኛ ጊዜ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ‹‹አውራምባ ታይምስ›› ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ሥራ በጀመርኩ በወራቶች ውስጥ ነበር፡፡ የግንቦት ሰባት አመራሮች በሌሉበትና እነብርጋዲየር ጄነራል ተፈራ ማሞ ታስረው ባሉበት (46 ተከሳሾች) ‹‹ሕገ-መንግሥቱን በሃይል ለመናድ፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ለመግደል በማሴር …ወዘተ›› በሚል የቀረበውን ክስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተገኝቼ የችሎት ሂደቱን የምዘግበው እኔ ነበርኩ፡፡

የነፃነቴ ዋጋ ነብሴ ነው!!! (ግርማ ሰይፉ ማሩ)

023022011171758000000ethiopie
መረጃ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ጠቃሚ ነው ብሎ መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ነው፡፡ የተሟላ መረጃ የሰውን ልጅ ሙሉ ያደርገዋል፡፡ መረጃን አጣሞ ማቅረብ ደግሞ የሰውን ልጅ ውሳኔ ለማጣመም ካልሆነ በስተቀር ግቡ ምን ሊሆን እንደሚችል አይገባኝም፡፡ በሰሞኑ ሰው በላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጥርሱም በጥፍሩም ዘመቻ የጀመረው እኔ ላይ ነው፡፡ ዓላማው ግልፅ ነው፡፡ በነፃነት የማሰብ መብቴን ለድርድር እንዳቀርብ ነው፡፡ ለነፃነቴ ያለኝን ዋጋ የማያውቁ ሰዎችን ይህንን ለማድረግ ቢሞክር ካላቸው የመረጃ እጥረት ወይም ማወቅ ባለመፈለጋቸው ነው፡፡ አንዳንድ ቅን ሰዎች ሰህተት እንደሰራው አድርገው ይቅርታ እንድጠይቅ፤ ይቅርም እንድባል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ በቅን ልቦና ላደረጋችሁት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡

Hiber Radio: የአቶ ግርማ ሰይፉ ንግግር የአንድነት አቋም አይደለም ሲሉ አቶ በላይ ፈቃዱ ተናገሩ * ከለንደን ሶሪያ ሄዶ አሸባሪዎችን የተቀላቀለ አንድ ሀበሻ ተገደለ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ህብር ሬዲዮ ህዳር 14 ቀን 2007 ፕሮግራም !

<... በእስር ላይ በሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ሕዝቡ ማወቅ አለበት...በጸረ ሽብር ሕጉ የሚወነጀሉ ላይ የሚቀርበውን ክስ አንቀበለውም :: እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የኦነግ አባላት ቦንብ አፈነዱ ተብሎ ያ ድርጊት ግን በስርዓቱ የደህነት ሰዎች ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን ዊክሊክስ አጋልጧል እነሱ ግፍ እየፈጸሙ የሚያናግሩትን አንቀበልም...አቶ ግርማ ከዚህ ቀደም አንዷለም ግንቦት ሰባት ከሆነ እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ ማለት ነው በሚል ነው እስሩን የተቃወመው ። አሁን የተናገረው ግን የራሱ እንጂ የአንድነት አቋም አይደለም። መጠንቀቅ ያለብን ግን...>

የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በፖስታ የተላከውን የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ደብዳቤ አልቀበልም አለ

(ነገረ ኢትዮጵያ) የአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል 9ኙ ፓርቲዎች ህዳር 21 ለሚያደርጉት የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በፖስታ ቤት የተላከለትን ደብዳቤ አልቀበልም ማለቱን የስብሰባው አስተባባሪ የሆነው የመኢዴፓ ፀሀፊ አቶ ዘመኑ ሞላ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
postal service ethiopia
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 21/2007 ዓ.ም ለሚያደርጉትና መኢዴፓ ለሚያስተባብረው ስብሰባ ረቡዕ ህዳር 10 የመኢዴፓ አመራሮች ደብዳቤውን ለማስገባት ሄደው የነበር ቢሆንም አቶ ማርቆስ ብዙነህ እና እሳቸውን ተክተው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ፈለቀ ታመዋል በሚል የከንቲባ ጉዳይ የካቢኔዎች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ማሳወቂያ ደብዳቤውን አንቀበልም ማለታቸው ይታወቃል፡፡

በለገጣፎ ከተማ ከ32,000 ሺህ በላይ ዜጐች ቤት አልባ ሊሆኑ ነው

(ፍኖተ ነፃነት) የአዲስ አበባ ተዋሳኝ በሆነው ለገጣፎ ከተማ ከ3,000 ሺህ በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ በመወሰኑ ከ32,000 ሺህ በላይ ዜጐች ቤት አልባ ሊሆኑ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ገለፁ፡፡
legetafo Addis ababa
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ለ12 ዓመታት በአካባቢው መኖሪያ ቀልሰው ኖረዋል፡፡ ሆኖም “የከተማ ሰው ወሮናል” የሚል ተቃውሞ በገበሬው እንዲነሳ ያደረጉ የከተማው ባለሥልጣኖች በ2 ቀናት ውስጥ ቤታችን ሊያፈርሱ ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡ የካ ሰዴን ወረዳ የሚገኙት የጉራ፣ሰፈራ፣ድሬ፣ ዳሌ እና ቀርሳ የሚባሉ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኙ ወደ 3000 ሺህ የሚጠጉ ቤቶች እንዲፈርሱ ምልክት ተደርጎባቸዋል፡፡

በአማራ ክልል ቅርሶች በከፍተኛ ሁኔታ እየዘረፉ ከሐገር እየወጡ ነው፡፡

ዳር ፲፮(አስራ ስድስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የደቡብ ወሎና የሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳዎችና አብያተክርስቲያናት ተገቢ ጥበቃ ባለማግኘታቸው የተለያዩ ቅርሶች የተዘረፉና የጠፉ መሆኑን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ በአመት አንድ ጊዜ በሚዘጋጀው የቅርስ ጉባኤ ላይ ገለጸ፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በተለያዩ ወረዳዎች 37 ቅርሶች መሰረቃቸውን ይፋ ያደረጉት የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ አለበል ደሴ ፣በክልሉ ከ2001 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2006 መጨረሻ ባለው ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች 124 መድረሳቸውን ተናግረዋል።
artበክልሉ ብቸኛ የሆነው የደሴ ሙዙየም በስተደቡብ አቅጣጫ ጫካ በመሆኑና ዙሪያውም ምንም ዓይነት አጥር ስለሌለውየጥበቃ ቢሮው ተሰብሮ በውስጡ የነበሩ ሁለቱም የጦር መሣሪያዎች ከነሙሉ ጥይታቸው ከመሰረቃቸውም በላይ እስከአሁንም አለመገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ ቅርሶች በመስታውት ዉስጥ ተቆልፈው ስላልተያዙ ለአቧራና ለአላስፈጊ ንክኪ መጋለጣቸውም ሃላፊው ተናግረዋል።

በጋምቤላ ክልል ያለው የኤች አይቪ ስርጭት በሀገር አቀፍ ደረጃ ካለው ስርጭት በላይ መሆኑ ተገለፀ

በ2 ሰዓታት 2ሺ ሰዎችን ለመመርመር ታቅዷል
በሀገራችን ለ26ኛ ጊዜ የፊታችን ህዳር 22ቀን 2007 ዓ.ም የሚከበረውን የአለም የኤድስ ቀን አስመልክቶ ትናንት በካፒታል ሆቴል እና ስፓ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለፀው በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለው የኤች አይ ቪ ስርጭት 1ነጥብ 5 በመቶ ሲሆን፤ በጋምቤላ ክልል ያለው ስርጭት ግን 5 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ ተገኝቷል። በክልሉ ያለው የኤች አይ ቪ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ በተለይ በሴት ወጣቶች ላይ ያለው ስርጭት አሳሳቢ ነው ተብሏል። በክልሉ በከፍተኛ ሁኔታ ለኤች አይቪ ተጋላጭ ናቸው በተባሉት ሴቶች ዘንድ ያለው ስርጭት 8 በመቶ ሲሆን፣ በወንዶች ላይ ደግሞ 5 በመቶ መሆኑ ተገልጿል። በክልሉ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ 380 አዲስ የኤች አይቪ ተጠቂዎች መመዝገባቸውንም ይፋ ሆኗል።
news
በክልሉ ያለው የኤች አይቪ ስርጭት ከፍተኛ እንዲሆን ያደረገው በህብረተሰቡ ዘንድ ስለኤች አይ ቪ በሽታ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑ ነው ያሉት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲዱሞ አደር፣ ከዚሁ በተጨማሪም ክልሉ ከተለያዩ አምስት ብሔረሰቦች የተዋቀረ እንደመሆኑ የየብሔረሰቡ ባህል በዚህ ስርጭት ከፍተኛ መሆን የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል። በክልሉ በተለይ የውርስ ጋብቻ የተለመደ መሆኑን የገለፁት አቶ ዲዱሞ፤ በዚህም አንድ ወንድ ሲሞት የሞተበትን ምክንያት ሳያጣራ ልጅ ወይም ወንድም የዚያን ወንድ ሚስት ስለሚወርስ ይህም የበሽታውን ስርጭት ከፍ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ ሆኗል። ከሌሎች አካባቢዎች ለየት ባለመልኩ ወንዶች እና ሴቶች በነፃነት የሚገናኙበት “ፍሪ ዴይ” የሚባለው ባህልም ሌላኛው የዚህ ምክንያት እንደሆነ ኃላፊው ገልጸዋል።

ስለደፈራ፤ ደፈር ብለን ስናወራ (በእውቀቱ ስዩም)

ኣስገደዶ መድፈር በእንስሳት በኣሶች እንዲሁም በነፍሳት ኣለም ውስጥም ይስተዋላል፡፡ይልቁንም ለሰው እሩብ ጉዳይ በሆኑ ዝንጀሮዎች ዘንድ የተለመደ ነው፡፡ተፈጥሮ በደፋሪነት ያጨቻቸው ባብዛኛው ወንዶችን ቢሆንም ሞገደኛ እንስቶችም ኣልጠፉም፡፡ለምሳሌ ወንዱ ንብ ከሴቷ ጋር ሲሳረር ሴቲቱ በዚያ ነገር ቆልፋ ትይዝበታለች፡፡በጦዘ ስሜት ውስጥ ሆና ኣልመዝምዛ ትቆርጥበታለች፡፡ወይም በጅንኖች ኣባቶቻችን ኣነጋገር ትሰልበዋለች፡፡ኮርማው ንብ በጀንደረባነት የመቀጠል እድል የለውም፡፡ በደረሰበት ጥቃት ያልጋ ቁራኛ ማለቴ የቀፎ ቁራኛ ሆኖ ይሞታል፡፡ሰራተኛ ንቦች ኣስከሬኑን ከቀፎው ጠርገው ወደ ውጭ ይጥሉታል፡፡
ኣብሬሽ ኣድሬ ሲነጋ ልሙት
ላፈር ኣይደለም ወይ የተፈጠርኩት
የሚለው የሙሉቀን መለሰ ዘፈን የኮርማ ንቦችን ህይወት በደንብ ይገልጣል፡፡

Monday, November 24, 2014

በፒያሳው ቦንብ ፍንዳታ ዋና አቀናባሪው ተስፋዬ ገ/አብ መሆኑን ያውቃሉ? (ሊያነቡት የሚገባ) (በአለማየሁ መሰለ )

Image

ለዛሬ የማቀርበው መረጃ ተስፋዬ ገብረአብ እንደ ሸፋን ከሚጠቀምበት የደራሲነት እና
የጋዜጠኘነት ስራ ባሻገር ለማመን በሚያዳግት ይሰራ የነበረውን የወንጀል ድርጊት ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
ከዚህ በታች አባሪ ተደርጎ የተያያዘው በእጅ የተጻፈ መረጃ፣በእጄ ላይ ካሉ መረጃዎች መሃከል
ትኩረቴን የሳበው ነው።እንደምትመለከቱት በራሱ በተስፋዬ ገብረአብ እጅ የተጻፈ ነው።ከሌሎች
መረጃዎች ለየት የሚያደርገው ደግሞ፣እንደሌሎች መረጃዎች በፎቶኮፒ እጄ ላይ የቀረ ሳይሆን፣
ዋናው (ኦርጅናል)መሆኑ ነው። ምክንያቱም በቀጥታ ወንጀል የተጻፈበት ሆኖ ስለታየኝ ነው።ከእጅ
ጽሁፉ ላይ እንደምትመለከቱት፣መኩሪያ መካሻ ከተባለ ግለሰብ ጋር ድብቅ(ህቡእ) ስራ ለመስራት
ጀምረው ነበር።እንደኔ ግምት የኤርትራ መንግስትን ጥቅም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስፈጽማል
ብለው ያሰቡትን ተልእኮ ለመፈጸም አሲረው ነበር፡፡እንደ መረጃው ከሆነ መኩሪያ መካሻ የተባለው
ግለሰብ ከፒያሳው ቦንብ ፍንዳታ በኋላ ፈርቶ ይሁን ሌላ ባይታወቅም፣ከተስፋዬ ጋር ያለውን
ግንኙነት አቋርጧል።የፒያሳው የቦንብ ፋንዳታ ብሎ የተገለጸው ደግሞ ሌላ ሳይሆን በ2002 እኤአ
በትግራይ ሆቴል ላይ የደረሰው ፍንዳታ ነው።

Friday, November 21, 2014

ጀግናችን ምን አስባ ይሆን?

የተወለደችው በአዲስ አበባ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በእቴጌ መነን (ያሁኑ የካቲት 12) 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ለጥቃም የከፍተኛ ተቋም ትምህርቷን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ሙያን በመማር የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያዘች። ከዚያም በተመረቀችበት ሙያ በዳኝነት ያገለገለች ሲሆን በ1997ቱ ምርጫ ወቅት ቀስተዳመና ፓርቲን በመቀላቀል ወደ ቅንጅት ከተዋሃደ በኋላ ምርጫውን ማሸነፍ በመቻላቸው ምርጫው እንዳለቀ የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆና ተሾማለች።
                                                 birtukan 1
ነገር ግን በወቅቱ በነበረው የምርጫ ድምፅ መጭበርበርና ከወያኔ ጋር በተፈጠረው ውዝግብ አምባገነኑ ወያኔ ጀግናዋ እህታችንን ጨምሮ ሁሉንም አመራሮች አስሮ ነበር። ከ18 ወራት እስራትና ስቃይ በኋላ የወያኔ ምስ በሆነው ይቅርታ በሉኝ ፈሊጥ ይቅርታ ጠይቀዋል በማለት ሊለቀቁ ቻሉ።

Tuesday, November 18, 2014

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

በቢሮክራሲያዊ ሴራ የዜጎችን ህገመንግሥታዊ መብት ማፈን ሠላማዊ ትግሉን አያቆመውም!!
ዘጠኝ /9/ ህጋዊ ሰውነት ያለን ፓርቲዎች በትብብር ለመሥራት በተስማማነው መሠረት የአጭር ጊዜ የጋራ ዓላማችንን ማስፈጸሚያ ተግባራት የመጀመሪያ ዙር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የአንድ ወር ዕቅድ አውጥተን ወደ ሥራ መግባታችን ይታወሳል፡፡ የዚሁ የአንድ ወር ዕቅድ አካል ከሆኑት ተግባራት ቅዳሜ በ6/03/07ዓ.ም ‹‹ዲሞክራሲያዊ ምርጫና የአፈጻጸም መርሆዎች›› በሚል ርዕስ የአዳራሽ ውይይት በተሳካ ሁኔታ አከናውነን በትናንትናው ዕለት በ07/03/07ዓ.ም ደግሞ ከአዲስ አበባ ሰሜን ምስራቅ /ከአራት ኪሎና አካባቢው / ህዝብ ጋር በአደባባይ በቤልኤር ሜዳ ተገናኝተን በምርጫ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የትብብራችን አባል የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባውን እንዲያስተባብር በሰጠነው ኃላፊነት- የፖለቲካ ስብሰባ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 3/1983 የምጠይቀውን ሁኔታ አሟልቶ ለከንቲባ ጽ/ቤቱ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በ02/03/07 ደብዳቤ ማስገባቱ፣ የጽ/ቤቱ ክፍልም ለደብዳቤው በ04/03/07 ዓ.ም መልስ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

አዲሱ የአምልኮ፣ አለባበስ እና አመጋገብ ስርዓት በአ. አ. ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 30 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ መመሪያ ተላለፈ

አቡ ዳውድ ኡስማን

ትምህርትህ ሚኒስተር የዜጎችን ህገ መግስታዊ መብት በመጣስ አዲስ ባወጣው የአምልኮ፣ አለባበስ እና አመጋገብ ስርአት ደንብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 30 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ትዕዛዝ ማስተላለፉን ምንጮች ዘግበዋል፡፡
በአዲሱ የትምህርት ሚኒስተር ደንብ መሰረት ማንም ሙስሊም ሃይማኖቱ የሚደነግግበትን ግዴታዎች መፈፀም የሚከለክል ሲሆን በተለይም ሙስሊም ሴት እህቶቻችን ሂጃባቸውን እንዲያወልቁ አልያ ደግሞ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ የሚያስገድድ ነው፡፡

London man Andy Tsege faces death penalty in Ethiopia (BBC)

ondon man Andy Tsege faces death penalty in Ethiopia
(BLBC)
The family of a north London man who is facing the death penalty in Ethiopia has said the government should be doing more to help get him home.
Andy Tsege, from Islington, who opposes the Ethiopian authorities, was seized in June and has been in solitary confinement ever since, his family says.
The Foreign Office says he is not being held "illegally".
BBC London's Charlotte Franks spoke to Mr Tsege's partner Yemi Hailemariam, Maya Foa from human rights organisation Reprieve, and Andy's sister Bezu Tsege.

ታሪካችን የደብተራ ነው አላችሁኝ?

ከዋልን ካደርን ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን። የኢትዮጵያን ታሪክ ማጠልሸት ሰሞኑን እንደ ወረርሽኝ ሆኗል። የኢትጵያን ታሪክ የደብተራ ተረት ነው ብሎ ማጣጣል፣ ደብተራን ከአማራ ጋር ብቻ ማያያዝ ያለማወቅ በሽታ ካልሆነ ምን ይባላል? አለማወቅን ማወቅ ጤና፣ አለማወቅን አለማወቅ ደግሞ በሽታ ነው።
ደብተራ ያየውን የሰማውን በከተበ ለምን ይንቋሸሻል? የደብተራ ጥፋቱ አስቀድሞ መሰለጠኑ ነው፤ ፊደል የስልጣኔ በር ነው፤ ደብተራ ደግሞ ፊደል የቆጠረ የመጀመሪያ ሰው ነው፤ የኢትዮጵያ ደብተሮች በጊዜያቸው ከነበሩት ሰዎች አስቀድመው የሰለጠኑ ናቸው፤ ስልጣኔውን ያገኙትም በፊደል በኩል ነው። አስቀድመው በመሰልጠናቸውም፣ ለሁላችንም የሚሆን ነገር ጽፈው አለፉ። ባይሰለጥኑ ኖሮ ታሪክን ለመጪው ትውልድ ስለማስተላለፍ አይጨነቁም ነበር። ከደብተራ ውጭ ታሪክን ለመጪው ትውልድ ጽፎ ስለማስቀረት ያሰበ ማን ነው? ተራው ገበሬ ዝናብ መጣ ሄደ፣ ተራው ነጋዴ አሞሌ ተወደደ ረከሰ፣ ተራው ወታደር ድንበር ሰፋ ጠበበ፣ ንጉስ ግብር ጨመረ ቀነሰ ከማለት ውጭ ታሪክ ጽፎ ስለማስተላለፍ ተጨንቆ ያውቃል? ስለጥበብ ስለውበት ተጨንቆ የጻፈውም ደብተራው ነው።

Wednesday, November 12, 2014

ቁምነገርና ፌዝ አለመለየት “አደጋ አለው!”

 ኢህአዴግ ብዙ ይዘገያል እንጂ አንዳንድ ነገሮችን እኮ ይቀበላል፡፡ (ምንጩን አጣርቶ ነው ታዲያ!) ምን ሰምተህ ነው አትሉኝም! ሰሞኑን በEBC እንደሰማሁት፣ የመንግስት ተቋማት የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች (የህዝብ ግንኙነት ለማለት ነው) በፌስ ቡክ አጠቃቀም ላይ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን ዓላማውም በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ የሚሰራጩ “በሬ ወለደ” ዓይነት ውሸቶችን ለመመከትና እውነታውን ለማሳወቅ ነው ተብሏል፡፡ ደስ አይልም - ውሸትን በእውነት መመከት!! (እውነት አንፃራዊ ናት እንዳትሉኝ!) ለማንኛውም ግን ፌስ ቡክን እዘጋዋለሁ ከሚል ‹ቴረር› ወይም ‹ሆረር› ሺ ጊዜ ይሻላል (ይሻላል ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ ውሳኔ ነው!) በነገራችሁ ላይ በግል ፕሬሶችም ላይ ተመሳሳይ ውሳኔ ይሻል ነበር፡፡ በአንድ ጊዜ እኒያን ሁሉ የፕሬስ ውጤቶች ዝም ጭጭ ከማሰኘት ማለቴ ነው፡፡ (ያኔ አልተገለጠለት ይሆናላ!)
ወደ ሌላ አጀንዳ ከማለፋችን በፊት አንድ ሁለት ቀልዶችን ብነግራችሁስ፡፡

አምባገነንነት እንደ ፖሊዮ ከምድረገፅ መጥፋት አለበት!

ባለፈው ሳምንት ቡርኪናፋሶን ለ27 ዓመታት እንደ ግል ንብረታቸው ሲያዙባት የከረሙት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓዎሬ፤ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ሲሉ ህገመንግስቱን ለማሻሻል ያደረጉት (ንቀትና ድፍረት የተቀላቀለበት ነው) ሙከራ ያስከተለው ውጤት ያልጠበቁት ነበር፡፡ (አመዳቸውን ቡን ሳይል አልቀረም!) ምንም ቢሆን የህዝብ አመፅ አይጠብቁማ፡፡ መቼም የሥልጣን እህል ውሃቸው ቢያልቅ ነው እንጂ አምባገነኖች እንዲህ በቀላሉ ከቤተመንግስት እኮ አይወጡም፡፡ (ያውም በአንዲት ቀን አብዮት?!) አመጽና ተቃውሞን በሃይል ለመመከትና ለማፈን ሁሌም ታማኝና አስተማማኝ ወታደራዊ ኃይል ከጎናቸው አይጠፋም፡፡ የስልጣን ገመዳቸው ተበጠስ ያለው ጊዜ ግን ወታደሩም ፊቱን ያዞርባቸዋል፡፡ በአምባገነኖቹ የአፍሪካ መሪዎች በእነ ጋዳፊ፣ ሁስኒ ሙባረክ…አይተነዋል፡፡ 

በፋይናንስ ችግርና በአንድነት ጉዳይ የሚፈተነው መድረክ

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ሒደት ውስጥ ብልጭ በማለት ለብዙዎች የተስፋ ስንቅ አስይዞ የነበረው ምርጫ 97 በአወዛጋቢ ሁኔታ ከተጠናቀቀ በኋላ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች የአገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወደኋላ እየተንሸራተተ ነው በማለት ይተቻሉ፡፡ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ደግሞ አገሪቱ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታና አጠቃላይ ለአገሪቱ ዕድገት ወሳኝ የሚባሉ ውሳኔዎችንና አሠራሮችን መዘርጋቱን ይሞግታል፡፡

አቃቢ ህግ በጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ላይ የመሰረተውን ክስ እንዲያሻሽል ታዘዘ •ክሱ ተሻሽሎ መቅረቡን ለማየት ለህዳር 24 ቀጠሮ ተሰጥቷል

163243-thumb
የፌደራል አቃቢ ህግ በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በጦማርያኑና በጋዜጠኞቹ ላይ የመሰረተውን የሽብር ክስ እንዲያሻሽል የልደታ ከፍተኛ ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ፍርድ ቤቱ ዛሬ ህዳር 3/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቀደም ብሎ የተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ መርምሮ ብይን በመስጠት በንባብ አሰምቷል፡፡ በዚህ መሰረትም ፍርድ ቤቱ በክስ መቃወሚያው ላይ የቀረቡትን ዝርዝር ነጥቦች መርምሮ በተወሰኑ ነጥቦች ላይ አቃቢ ህግ ክሱን እንዲያሻሽል ትዕዛዝ ሲሰጥ፣ በሁለተኛነት ቀርቦ የነበረው የክስ ይዘት በአንደኛው የክስ ይዘት ላይ መጠቃለል ስለሚችል ሁለተኛውን የክስ ይዘት ፍርድ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ አድርጎታል፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ ከፍተኛ ኦፊሰር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ቃሊቲ ጉምሩክ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ ኦፊሰር፣ አቶ ዘመን ይሰማው 40,000 ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
cuffsየፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በተጠርጣሪው ላይ የመሠረተው ክስ እንደሚያስረዳው፣ የፈረንሣይ ኤምባሲ ሠራተኛ በነበሩት በሚስተር ሚሼል ሪቻርድ ስም የገባ ተሽከርካሪን፣ አቶ ተዋበ ዘለቀ የተባሉ ግለሰብ በ450,000 ብር ይገዛሉ፡፡

Tuesday, November 11, 2014

በአዲስአበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በተለይ በዚህ ሳምንት ተባብሶ መቀጠሉ የአዲስአበባ ነዋሪዎችን እያበሳጨ ነው፡፡

ነዋሪዎች እንደሚሉት በተለይ ባሳለፍነው አንድ ሳምንት ጊዜያት ውስጥ መቆራረጡ በወሳኝ ሰዓታት ጭምር
ማለትም በምሽት እና በጠዋቱ ጊዜያት ተጠናክሮ መቀጠሉንና በዚህ ምክንያት ለከፍተኛ ኪሳራና ወጪ እየተዳረጉ
መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣናት «የኃይል እጥረት የለም፣ እንዲያውም ተርፎን ለጎረቤት ሀገራት ኤክስፖርት እያደረግን ነው» በሚሉበት
በዚህ ወቅት በተለይ የአፍሪካ ርዕሰ መዲና መሆንዋ በሚነገርላት አዲስአበባ ከተማ በቀን በአማካይ እስከ ሶስት
ጊዜ ያህል በተደጋጋሚ ኤሌክትሪክ የሚቆራረጥበት ምክንያት ጨርሶ ሊገባቸው እንዳልቻለ አስረድተዋል፡፡

አምሳሉ ገኪዳንና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ታሰሩ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የብር 20,000(የሃያ ሺህ ብር) ዋስ ተጠይቆበት ወደ ማረፍያ ክፍል መግባቱ ታወቀ፡፡
ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የጅማ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበበት ክስ የፕሬስ ህጉን በሚፃረር መልኩ ለአራት ቀናት በማዕከላዊ ታስሮ የተለቀቀው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ክሱ እንደ አዲስ እንዲቀሰቀስበት ከተደረገ በኋላ ዛሬ በተለምዶ ገዳም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ሁለተኛ የወንጀል ችሎት ከእንቁ መፅሔት አምደኛ አምሳሉ ገ/ኪዳን ጋር እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

የሕወሐት ማ/ኰሚቴ አባል አቶ ኪሮስ ቢተው ከስልጣን እንዲነሱ እየተዶለተ ነው።

የሕወሐት ማ/ኰሚቴ አባል አቶ ኪሮስ ቢተው ከስልጣን እንዲነሱ እየተዶለተ ነው። ኪሮስ የሁለት ዘመናዊ ቪላ ባለቤት ሲሆኑ የመቀሌውን አፓርታይድ መንደር ቪላ መሸጣቸው ይታወቃል።…የአዜብ መስፍን ሁለት ወንድሞችና አንድ እህት በቨርጂኒያ ይኖራሉ። ወንድሞችዋ በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር በማንቀሳቀስ በንግድ ተሰማርተዋል። ያልታደለች አገር የዘረፋ ውጤት መሆኑን ነው።…የአዜብ መስፍን ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ አለበት።…ጄ/ል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እዚህ አሜሪካ ሰንብተዋል። የቀድሞ ሚ/ር ዴኤታ ኤርሚያስ ለገሰና ገብሩ አስራት መፅሐፍ በብዛት ገዝተው መሄዳቸው ታውቋል። የገዢው ባለስልጣናት በሁለቱ መፅሐፍ ተጠምደዋል።…

Monday, November 10, 2014

ግልጽ ደብዳቤ ”ለጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለማርያም ደሳለኝ : ከታሳሪ ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች

163243-thumb
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስታችንን ያክብሩ!
ሠላም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!? እንዴት ነዎት? ያስታውሱ ከሆነ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢከፊሉ የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች ‘ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ’
“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እባክዎትን የተለያዩ የመንግስት አካላት የሕገ መንግስታችንን ድንጋጌዎች እየጣሱ ነውና እርስዎም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 74/13/ መሠረት ሕገ መንስቱን የማስከበርና የማክበር ግዴታ ስላለብዎት ሕገ መንግስቱን ያክብሩ”በማለት አንዲት አጭር ደብዳቤ ፅፈንልዎት ነበር፡፡

የወያኔ ግፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ

የወያኔ ግፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ

ዘረኛዉ ወያኔና ባለሟሎቹ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላና በሸኮ መዠንገር አካባቢ የሚያካሄዱትን የማንአለብኝነት የመሬት ዝርፍያና ዜጎችን እርስ በርስ በማጋጨት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያደርጉት አራዊታዊ ሩጫ የተነሳ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ህዝብ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የማይችል እልቂት እየተፈጸመበት ነዉ። የመዠንገር ህዝብ የሞትና የህይወትን ያክል የማይወጣዉ ምርጫ ስለቀረበለት ተወልዶ ያደገበትን የአባቶቹንና የአያቶቹን አካባቢ ለቅቆ በመዉጣት እራሱን ለመከላከል ባደረገዉ እንቅስቃሴ የብዙ ንጹሃን ዜጎችና ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ምስኪን ወታደሮችም ህይወት ማለፉ በይፋ እየተሰማ ነዉ።

ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በደህንነቶች ተመለሱ

162114-thumb
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ጄ/ል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ለመውጣት ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ በደህንነቶች እንዳይወጡ መደረጋቸውን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል።
ከመከላከያ የጦር አዛዥነታቸው በጄ/ል ሳሞራ የኑስ እንዲነሱ የተደረጉት ጄ/ል አበባው ከአገር እንዳይወጡ የተደረገበት ምክንያት ግልፅ እንዳልሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የተለያዩ ጥያቄዎች እንዳሉ በመግለፅ ለኢታማጆር ሹሙ ጄ/ል ሳሞራ ከረር ያለ ሪፖርት ያቀረቡት ጄ/ል ሰዓረ፣ ጄ/ል ሞላና ጄ/ል አበባው መሆናቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ በሳሞራ የተሰጠው መልስ ” የትምህክተኞች ጥያቄ ነው፤ ችግር የለም..» የሚሉና ጥያቄዎቹን የሚያጣጥሉ እንደነበሩ አስታውሰዋል።

አቶ በረከት ስምዖን ያስገቡትን የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ሕወሓቶች እንዳልተቀበሉት ተነገረ; “እለቃለሁ የሚል ከሆነ ሃብቱ መመርመር አለበት” ተብሏል

index
ምንሊክ ሳልሳዊ
-በውሳኔው የማይስማማ ከሆነ በሱና በቤተሰቡ በወዳጆቹ ስም የተመዘገበው ሃብት እንዲጣራ ተብሏል::
-ሳያገግሙ ስብሰባ እንዲመራ እና ሚዲያ ላይ እንዲቀርብ ታዟል::
የብአዲን/ኢሕአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡት የስልጣን መልቀቂያ ለጊዜው በሚል ውድቅ መደረጉን ሆኖም በቅርቡ መልስ ይሰጥበታል ሲሉ የሕወሓት ባለስልጣናት መመለሳቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::

The day Ethiopian protestors shut a busy street in Brussels

Tribute to heroic Ethiopian protestors in Brussels
Ethiopian protesters shut down busy street in BrusselsI had the privilege to watch, with tears choking my eyes, the stunning demonstration, in front of the EU Headquarters, by heroic Ethiopians that shut a busy street in Brussels. Ethiopians converging in a display of colorful unity from all over Europe and probably beyond made history by their unique act of patriotism.

Saturday, November 1, 2014

Aid in the wrong hands – The Telegraph

Is Ethiopia’s government, whose security forces are guilty of rape and torture, a worthy recipient of £329 million of British taxpayers’ money?
30 years ago, Band Aid mobilised a generation of British teenagers behind the campaign to help Ethiopia recover from famine. Today, Ethiopia is the second-biggest beneficiary of British aid, receiving no less than £329 million last year. And yet the same government that is favoured by this largesse has also carried out appalling atrocities.

አብርሃ ደስታ; ሀብታሙ አያሌው; የሽዋስ አሰፋ ; ዳንኤል ሺበሺ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው

• አብርሃ ደስታ የሁለት ድርጅቶች አባል ነው የሚል ክስ ተመስርቶበታል
• ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ታዟል
ነገረ ኢትዮጵያ 
በልደታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በተሰየመው ችሎት 10 ተከሳሾች በፌደራል አቃቢ ህግ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ100 ገጽ በላይ የክስ ቻርጅ የተነበበላቸው ሲሆን ከክስ ቻርጁ ጋር ከ300 ገጽ በላይ የምርመራ ሰነድ ቀርቦባቸዋል፡፡
የክሱ መዝገብ የተከፈተው ዘላለም ወርቃገኘሁ በተባለውና ‹‹የግንቦት 7 አመራር ነው፡፡›› ተብሎ ክስ በተመሰረተበት ግለሰብ ሲሆን በዚህ የክስ መዝገብ የተካተቱትም፡-
1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ
2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው
3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ
4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ
5ኛ ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ
6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ
7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን
8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ
9ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ደጉ
10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ሕዝብ እንደማይመርጠው አውቋል – ግርማ ካሳ

ኦሮሞ ነን የሚሉ ኦነግ እየተባሉ በአሥር ሺሆች ታሰሩ። አማርኛ ተናጋሪውን፣ ጉራጌዉን፣ ጋሞዉን ፣ ወላያታውን ….ግንቦት ሰባት ናችሁ እያሉ ማጎር ቀጠሉ። የቀራቸው ትግሬው ነበር። በትግራይ የተነሳዉን ጠንካራ የዲሞክራሲና የለዉጥ ጥያቄ እየጨመረባቸው ሲመጣ፣ “ደሚት ናችሁ” በማለት፣ ይኸው የግፍ ዱላቸውን የትግራይ ተወላጆች ላይ ማሳረፍ ጀመረዋል።
ዛሬ አራት ወጣት ፖለቲከኞች፣ ሃብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ ፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ ሽብርተኞች ተብለው በኦፊሴል ክስ ተመስርቶባቸዋል። አምስት በመቶ ሊፈቱ ይችላሉ የሚል ግምት ነበረኝ። እንኳን ሊፈቱ ጭራሽ ሌሎች ስድስት ኢትዮጵያዉያን ተጨምረዋል። የአ/አ ዩኒቨርስቲ ማስትሬት ተማሪ የሆነው ወጣት ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ ዮናታን ወልዴ ፣ አብርሃም ሰለሞን ፣ ሰለሞን ግርማ ፣ ባህሩ ደጉና ተስፋዬ ተፈሪ ይባላሉ።

ማዕከላዊ የሚታሰሩት የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ቁጥር አሻቅቧል * በርካታ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል

የህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት በኢንቨስትመንት ስም የጋምቤላን ክልል ነዋሪዎች እያፈናቀሉ በያዙት መሬት ምክንያት እንደተቀሰቀሰ የሚነገርለትና ለወራት በዘለቀው ግጭት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ በርካታ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ዛሬ ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት መቅረባቸው ታወቀ፡፡
ነዋሪዎቹ ከጋምቤላ ክልል ወደ ማዕከላዊ ከመጡ በኋላ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡ ዜጎች ወደ ችሎቱ በሁለት የፖሊስ አውቶቡሶች የመጡ ሲሆን በቁጥር ቢያንስ 50 እንደሚደርሱ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ችሎቱ በዝግ እንደተካሄደም ለማወቅ ተችሏል፡፡

United States call for the Ethiopian government to release journalists

U.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist

Press Statement
Jen Psaki
Department Spokesperson
Washington, DC
October 30, 2014
The United States is deeply concerned by the October 27 sentencing of Ethiopian journalist Temesgen Desalegn to three years in prison forU.S. Deeply Concerned by Sentence of Ethiopian Journalist “provocation and dissemination of inaccurate information.” Freedom of expression and freedom of the press are fundamental elements of a democratic society, and the promotion and protection of these rights and freedoms are basic responsibilities of democratic governments.