Tuesday, November 11, 2014

የሕወሐት ማ/ኰሚቴ አባል አቶ ኪሮስ ቢተው ከስልጣን እንዲነሱ እየተዶለተ ነው።

የሕወሐት ማ/ኰሚቴ አባል አቶ ኪሮስ ቢተው ከስልጣን እንዲነሱ እየተዶለተ ነው። ኪሮስ የሁለት ዘመናዊ ቪላ ባለቤት ሲሆኑ የመቀሌውን አፓርታይድ መንደር ቪላ መሸጣቸው ይታወቃል።…የአዜብ መስፍን ሁለት ወንድሞችና አንድ እህት በቨርጂኒያ ይኖራሉ። ወንድሞችዋ በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር በማንቀሳቀስ በንግድ ተሰማርተዋል። ያልታደለች አገር የዘረፋ ውጤት መሆኑን ነው።…የአዜብ መስፍን ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ አለበት።…ጄ/ል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እዚህ አሜሪካ ሰንብተዋል። የቀድሞ ሚ/ር ዴኤታ ኤርሚያስ ለገሰና ገብሩ አስራት መፅሐፍ በብዛት ገዝተው መሄዳቸው ታውቋል። የገዢው ባለስልጣናት በሁለቱ መፅሐፍ ተጠምደዋል።…
የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ጀንበር እየጠለቀች ትመስላለች። በአስመራ የተቃውሞ ወረቀቶች እየተበተኑ መሆኑን ከስፍራው የመጣ መረጃ ያስረዳል። ኢሳያስን የሚያወግዙ በራሪ ወረቀቶች አሰራጭታችኋል በተባሉ ወጣቶች ላይ የግድያ እርምጃ ጭምር እየወሰደ ነው። ህዝቡ በኢኮኖሚ ችግር አጣብቂኝ ውስጥ ወድቋል። ለሁለት ዳቦ ከ3ሰዓት በላይ ሰልፍ የሚይዘው ህዝቡ ችግሩን መቋቋም ተስኖታል። የአስመራ ባለስልጣናት በኢሳያስ አመራር ተስፋ ቆርጠዋል።
አርአያ ተስፋማሪያም

No comments:

Post a Comment