Friday, March 28, 2014

ለአማራ ወያኔዎች የመጀመሪያና የመጨረሻ መልእክት

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
“መልእክት” ያልኩት አቀራረቤን ቀለል በማድረግ የአንባቢያንን ቀልብ ላለመግፈፍ ነው፡፡ እንጂ መነሻየ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነው፡፡ ማስጠንቀቂያም ይባል መልእክት ዋናው ጉዳይ በግሌ የተሰማኝንና የማምንበትን ለወገኖቼ ድኅነት ስልም የምጽፈው ነገር ለባለአድራሻዎቹ መድረሱ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉንም ድረገጾች ትብብር በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ እባካችሁን ለሁሉም ካድሬ መልእክቴን አድርሱልኝ፡፡
ሰው ክርስቶስን መሆን እንዳይችል ጠላት መንገድ እየዘጋበት መቸገሩ የሚታወቅ ነው፡፡ መሆን  ቢፈልግ ግን ይችላል፤ የሚከለክለው አንዳችም ነገር የለም፡፡ ክርስቶስ ራሱም ያለው “እንደኔ ሁኑ፤ እኔን ምሰሉ” ነው፡፡ ችግሩ ክርስቶስን ለመሆን ወይም ቢያንስ ለመምሰል የእምነት ጽናትና እውነተኛ ፍቅርን የተላበሰ ስብዕና ማጣት ነው፡፡ ተራራን ሊያዞር የሚችል እምነት፣ የሚጠላንን ብቻም ሳይሆን የሚገድለንንም ጭምር  የሚያፈቅርና ለጨካኞች የሚራራ ልብ፣ የማይወላውል እምነትንና የማያዳላ ፍቅርን የሚገልጥ በጎ ሥራ ካለ ከፈጣሪና ከአንድያ ልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ውህደት መፍጠርና ጓደኛ መሆን የማይቻልበት ምክንያት የለም፡፡ የሚጠይቀው እውነተኛ የልብ መሰበርን ብቻ ነው፡፡

Thursday, March 27, 2014

“ለውጡ እንደቀረበ ጥርጥር የለኝም” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ከሁለት ወር በፊት ወደ አሜሪካና የአውሮፓ አገራት ለስራ ጉብኝት ሄደው ነበር፡፡ አሁንም ወደ አሜሪካ ጉዞ ሊያደርጉ እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ የአሁኑ ጉዞ አላማ ምንድን ነው?
Eng. Yilkal Getnet Semayawi party chairman with Negere Ethiopia newspaper
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
ኢንጅነር ይልቃል፡- መጀመሪያ ያደረኩት ጉዞ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም፣ የሰራናቸውን እንዲሁም ወደፊት ልንሰራቸው ያሰብናቸውን ስራዎች፤ ሰማያዊ እንደ አዲስ ኃይል ሲመጣ የቆመላቸው ሀሳቦችና እምነቶች ምን እንደሆኑ ለማስተዋወቅ ታስቦ የተደረገ ነበር፡፡ የአሁኑ ግን ከበፊቱ የተለየና ለሰማያዊ ሊቀመንበር በሚል በቀጥታ በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት የተደረገ ግብዣ ነው፡ ፡ የአሁኑ ወጣት የአፍሪካ መሪና ወደፊትም ለአገራቸው መሪ ሊሆኑ የሚችሉ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጥሩ ስራ የሰሩ፣ በውድድር ከተመረጡ በኋላ በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በሚደረግ ምርጫ መመዘኛዎቹን ለሚያሟሉ ሰዎች የሚሰጥ እድል ነው፡፡ በመመዘኛዎቹ መሰረት በማሸነፌ የአሜሪካ መንግስት ሙሉውን ወጭ ሸፍኖ ለሶስት ሳምንት በአሜሪካ የመንግስት አወቃቀርና ዴሞክራሲን ጨምሮ በተግባር የሚሰጡ ስልጠናዎችን የማግኘትና፣ የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣናትም ባሉበት ከተለያዩ ተቋማት ጋርም ለመገናኘት እድል ይኖረኛል፡፡

Ethiopia spies on citizens with foreign technology: HRW

AFP – Ethiopia is using foreign technology to spy on citizens suspected of being critical of the government, Human Rights Watch said in a report released Tuesday.Ethiopia is using foreign technology to spy on citizens
The report accused the government of using Chinese and European technology to survey phone calls and Internet activity in Ethiopia and among the diaspora living overseas, and HRW said firms colluding with the government could be guilty of abuses.
“The Ethiopian government is using control of its telecom system as a tool to silence dissenting voices,” HRW’s business and human rights director Arvind Ganesan, said in a statement.

Wednesday, March 26, 2014

የመስዋዕትነት ወንጌል (ከጸጋዬ ገ/መድኅን አርአያ)

ከጸጋዬ ገ/መድኅን አርአያ
በአጤ ኀይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት (በ1960 አካባቢ) ኤድመንድ መሪ የተባለ አሜሪካዊ የዕለታዊው ኢትዮጵያ ሔራልድ ጋዜጣ አማካሪ ሆኖ ይሰራ ነበር። እኛም እንጠረጥረው እንደነበረ ሁሉ የአሜሪካ ስለላ ድርጅት ሠራተኛ (ኮንታክት ማን) ነው። (እግዜሩ ይይላቸውና ለካ በእኛም መሐል ሰዋቸውን ይተክሉ ነበር) ኤድ መሪ የሥነ ጽሑፍ ሰው ስለሆነ በማስታወቂያ ሚኒስቴር “ተረፈ ዜና” የምንለውን – የማይታተመውንና የማይታወጀውን (በራዲዮና በቴሌቪዥን) በንጥረ ነገሩ መውሰጃ ሥፍራ የተነፈስነውን ሁሉ ሰብስቦ ካገጣጠመው በኋላ ወደ አሜሪካ ሲመለስ Kulubi የሚል መጽሐፍ አወጣ። እንግዲህ ተረፈ ዜና የገባችሁ ይመስልኛል። ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ብዙ ሳንርቅ- ጠባያችንን ወደማያውቁ ሰፈሮች በወረራ መልክ ሳንዘምት እዚያችው ከባዕታችን እንደልማዳችን እንቀማምስና (ከቢራ አያልፍም) ቶሎ ወደ ማተሚያ ቤት እንመለሳለን። እንግዲህ ደግሞ ወደ ማተሚያ ቤት እንመለሳለን። “ምሳችንን እንጠጣ” ይላሉ አንዳንዶቻችን። ቀስ ብሎ ሁላችንም እንዲህ እንደምንል ተደርጐ ተወርቶብናል።

Thursday, March 20, 2014

የኢትዮጵያ ተተኪ ሴቶች ትውልድ መነሳሳት! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!”

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ !
Semayawi party female youth activists released
እ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡ ከዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባፈነገጠ መልኩ በኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው ስልጣንን የሙጥኝ በማለት ከህግ አግባብ ውጭ በህዝብ ላይ ደባ በመፈጸም ላይ የሚገኙትን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ዕኩይ ምግባር የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው በማሰብ ወጣት ሴቶቹ እውነታውን ያለምንም መሸፋፈን በማጋለጥ እምቢ አሻፈረኝ በማለት ተቃውሟቸውን ለዓለም በይፋ አሰምተዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ተቃውሟቸውን አጠናክረዋል፣

አባ መላ ሳይበላ ተበላ !

ሆዳም! ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም!

አዜብ ጌታቸው
አባ መላ ነኝ የሚለው የፓልቶኩ ብርሃኑ ዳምጤ ሰሞኑን የሰራው ስራ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው።  ከአንድ ድርጅት ውልቅ ብለው በዚያው ጀንበር ሌላው ድርጅት ጥልቅ የሚሉ፤ ያም ሳይጥማቸው ወይም ሳይመቻቸው ይቀርና ወዲያው ደሞ ወደ ሌላ 3ኛ 4ኛ….. ድርጅት ጥልቅ ውልቅ የሚሉ ጥቂት የማይባሉ ቅብዝብዞችን አውቃለሁ።እነኚህ አይነቶቹ የቻሉትን ያህል እንደ ፌንጣ ዘለው ዘለው በመጨረሻ እዩኝ እዩኝ ያለ ……እንዲሉ፦ ራስን ብቻ አባል በሚያደርገው ዲፕሬሽን ወደ ተሰኘው ድርጅት ይገቡና ፍጻሜያቸውም እዛው ይሆናል።
ሰሞኑን በአባ መላ የታየው ዝላይ ግን በፌንጣ ተምሳሌት ከተገለጹት ቅብዝብዞች የተለየ ነው፡፡ አባ መላ ውልቅ ካለበት የወያኔ ጓዳ ያሞሌ ተመኑን ቀንሶ ዳግም ጥልቅ ብሏል። ስለዚህ ለአባ መላ ተግባር በተምሳሌነት የምትጠቀሰው ፌንጣ ሳትሆን የተፋውን መልሶ የሚውጠው ጉማሬ ይመስለኛል ።

Monday, March 17, 2014

Mining Corruption in Ethiopia: A Reply to Clare Short

Open letter or open pandering to corruption?

“As I look around the EITI implementing countries, I do not accept that the situation for civil society in Ethiopia is worse than a great many of them.” That was the didactic pronouncement of Ms. Claire Short, Chair of the  Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) in her “Open Letter” to Ali Idrissa, Faith Nwadishi and Jean-Claude Katende who are civil society representatives on the EITI Board and the Outreach and Candidature Committee. Short penned her bizzare  Open Letter to announce her resolute conviction that EITI should give Ethiopia the green light because she “passionately believe[s] that the entry bar to candidates should be clearly and simply whether there is enough space for civil society to work with EITI,  and that compliance and validation should be a test whether civil society participation is free, fair and independent.”

Friday, March 14, 2014

ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ለችግሮቻችን የመፍትሄው ቁልፍ (ገለታው ዘለቀ)

የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ላለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በዛሬዋ ኣጭር ጽህፌ በነዚህ መራራ ጥያቄዎች ዙሪያ ቁንጥል ኣሳብ ለማቀበል ኣስቢያለሁ።
በርግጥም ሁላችን  ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን ሳለ፣ እየተጉላላን ያለነው እኛው ሆነን ሳለ፣  እንደገና መልሰን  የሃገራችን ችግር የት ጋር ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናወጋቸው ሰዎች ምናልባትም ግራ ሊጋቡ ቢችሉ ኣይደንቅም። ነገር ግን መጠየቃችን ትክክል ነው።

የፀረ ግብረ ሰዶማዊነት ሕጋችን ቢከለስስ?

(የሙሴቬኒ ዓይነት የፖለቲካ ቁርጠኝነት አስፈላጊ ነው)
defend family
የዛሬው ጽሑፌ መነሻውና መድረሻው በዚህ ሳምንት አነጋጋሪ ስለነበረው የኡጋንዳ የፀረ ግብረ ሰዶም ሕግና አገራችን በንፅፅር የምትወስደውን ልምድ መቃኘት ነው፡፡
ኡጋንዳ ይህንን ሕግ በማውጣቷ ዓለም ተደንቋል፡፡ አፍሪካን ግን የሚደንቅ አይደለም፡፡ አገራችንንማ ሕጓን እንድታጠነክር ካልሆነ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚታገስ ባህልም ሕግም ኖሯት አያውቅም፡፡ ዜናው እጅጉን የሳበው ምዕራባውያንን ነው፡፡ ኡጋንዳ እንደ ሌሎቹ የአፍሪካ አገሮች በአንድ ወቅት ቅኝ ገዥ ስለነበራት የድሮው አስተሳሰብ የተፀናወታቸው ወገኖች ተቃውሞውን አድምቀውት ሰንብተዋል፡፡ አገራችን በማንም ቅኝ ተገዝታ ባለማወቋ፣ ባህሏ የራሷ በመሆኑ ተቃዋሚዎች የመተቸቱን ሞራል የኡጋንዳን ያህል አያገኙትም፡፡ ከዓለም ጋር አንድ በሚያደርገን በተባበሩት መንግሥታትም ቢሆን አንድ የሆነ አቋም ባለመኖሩ፤ ቢኖርም በተዓቅቦ (Reservation) ስለምናልፈው አስቸጋሪነቱ ቅርብ አይደለም፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ጉባዔ በተደጋጋሚ የሰዎቹን መብት በሕግ ዕውቅና እንድትሰጥ አገራችንን ቢጠይቋትም የማይሸረሸር የተቃውሞ አቋሟን አንፀባርቃለች፡፡

የጎሣ ፖለቲካ፣ የጎሣ ግጭቶች እና መዘዛቸው በኢትዮጵያ – በዘመነ ወያኔ

(ክፍል አንድ)
article 39
ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ላለፉት አስርት አመታት ጎሣና ኃይማኖትን መሰረት አድርገው በተደጋጋሚ ጊዜያት በተከሰቱት ግጭቶች ዙሪያ እና ግጭቶቹ ባስከተሉት ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ላይ የሚያተኩር ነው። በተለይም ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ ጎሣን መሰረት ያደረገውን የኢሕአዴግ ፌዴራላዊ የመንግስት አወቃቀር ተከትሎ በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ የተከሰቱ ዋና ዋና ግጭቶችን ይዳስሣል። ለግጭቶቹ መንስዔ ተደርገው የሚጠቀሱትን ጉዳዮች፣ በግጭቶቹ ሳቢያ በሰው ሕይወትና በሕዝብ ንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን፣ ግጭቶቹ እንዳይከሰቱ ለመከላከልም ሆነ ከተከሰቱ በኋላም ለማብረድ እና  ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመፍታት በመንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች፣ የመንግስት የግጭቶች አፈታት ስልት፣ እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን ይህ ጽሑፍ በመጠኑ ይዳስሳል።

ትዝብት – ደርሶ መልስ ዲያስፖራ (አንደኛ)

አትክልት አሰፋ (ቫንኩቨር)
ነገሩ የሆነው አዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነው። ቆነጃጅት ወጣት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ባሉ የከተማው ደለላዎች ጋር በመተባበር እጅግ ዘግናኝ ስራ ይሰራሉ። ደላሎቹ የቆነጃጅቶቹን ተማሪዎች ፎቶ የያዘ ትልቅ ካታሎግ ይዘው ከአዲስ አበባም ሆነ ከአቅራቢያው ከተሞች አለዚያም ከዚያው ከአዋሳ ከተማ ብቅ የሚሉ ሃብታም ደንበኞቻቸውን የተማሪ ኮረዶችን ፎቶ በመስጠት ያስመርጣሉ።
ሰውየው ውብ ወጣት ተማሪ ኮረዳ እንደሚፈልግ በሰው በሰው የተገናኘውን ደላላ ይጠይቃል። እናም ከተሰጠው የፎቶ ድርድር ላይ ማመን ያቃተውን የአንዷን ውብ ፎቶ እያሳየ ‘ይህችን ታውቃታለህ?’ ሲል ይጠይቃል። የደላላ መልስ አንድ ነው… ሁሉንም ስለሚያውቃቸው አልተቸገረም ‘አዎ እሷን ይፈልጋሉ?’ ሲል ይጠይቃል።

ችግር ነው አስቀድሞ ማሰብ (ፐ/ር መስፋን ወ/ማርያም )

ወያኔ/ኢሕአዴግ ጥሩምባ ነፍቶ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች ነጻነት ብሎ ከአወጀና ሁሉንም ለሃያ ሁለት ዓመታት በተስፋ ከአስፈነደቀ በኋላ ችግር ተፈጠረበት፤ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚባለው ነው፤ ችግሩ አፍ ከሚችለው በላይ ለመጉረስ ከራስ ጋር መተናነቅ ሆነ፤ ችግሩ የማሰብ ድርቀት ነው፤ ችግሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጀምሮ እስከቀበሌ መዋቅር ያሉትን ሁሉ በአንድ ዘዴ እያባበሉና እያታለሉ ማደናበር ነው፤ ችግሩ በሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘዴው ሻግቶ ዓላማው ደብዛው መጥፋቱ ነው፤ ቸግሩ የዘዴው መሻገትና የዓላማው መክሸፍ መጋለጡ ነው፤ ችግሩ ወያኔ የተቀመጠበት የሥልጣን ወንበር መቆርቆር መጀመሩ ነው።

በአሜሪካ የሚኖረው የሕወሐት ወንጀለኛ

ከኢየሩሳሌም አርአያ
The Ethiopian author, former TPLF torture czar and spymaster “Professor” Bisrat Amare
Bisrat Amare former head of TPLF Intelligence
የሕወሐት አባል የሆነውና በአሜሪካ የሚኖረው ብስራት አማረ በርካታ ወንጀሎችን እንደፈፀመ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ሕወሐት በረሃ እያለ የባዶ 6 እስር ቤት ዋና ሃላፊ የነበረው ብስራት አማረ የኢ.ህ.አ.ፓ አባላት የነበሩት እነ ፀጋዬ ገ/መድህን (ደብተራው) ጨምሮ በሕወሐት የተያዙትን በሙሉ ወረኢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በነበረ እስር ቤት በጅምላ አሰቃይቶ እንደገደላቸው ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎች « ኢዲዩና ፊውዳል..» በሚል ባዶ 6 ተብሎ ይጠራ በነበረው እስር ቤት ተሰቃይተው እንዲገደሉ የተደረጉት በብስራት አማረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ ከዚህ በተጨማሪ የድርጅቱን በርካታ አባላት እንዳስገደለ አያይዘው ገልፀዋል።

Wednesday, March 12, 2014

አሸባሪዎቹ የጣይቱና የሚኒሊክ ሴት ልጆች

ቹቸቤ
የሰማያዊ ፓርቲ ቢጫ ለባሽ ወጣት ሴቶች መታገታቸውን ሰምተን ነበር። አንጋፋው ክስ ደግሞ እናትና አባታቸውን ጮክ ብለው መጥራታቸው መሆኑ ሲነገረን የጥፋታቸው ልክ ታሰበን። የትግራይ ናፃ አውጪዎችና ለነርሱ ለመታዘዝ ፈቃዳቸውን ያሳዩ ገባሪዎች በሙሉ ለተልዕኮ ትምህርት የማይመቹትን እነ ባዮሎጂንና ኬሚስትሪን ዞር አላሉባትም። በርካቶቹ የራሳቸውን ስም ከረሱ የቆዩ ስለሆኑ ዘር በጅምላው እንጂ ቤተሰብ በነጠላው አይገባቸውም። እናም እነዚህ ወጣቶች የሚኒሊክና የጣይቱ ልጆች ነን ማለታቸው አሸበራቸው።Arrested Semayawi party members and supporters
ትንሽ እወቀት ያለን እኛ ግን በመጀመርያ ሴቶች ወላጅም አዋላጅም መሆናቸውን እናውቃለንና የሚኒሊክና የጣይቱ ልጆች ነን ቢሉ አይደንቀንም። እንዲያውም “ጎሸ ሰው ጫካ በቀል አጉራ ዘለል ሲሆን ነው እንጂ የመጣበትን ሲያውቅ ጥሩ ነው።” ብለን ያደነቅን እናቅፋለን የወደድን ለጋብቻ እንጠይቃለን። ወጉ እንደዚህ ነዋ! በጋብቻ ተደራጅቶ የሚኒሊክና የጣይቱን ስም ማቆየት ስለምን ያስፈራል? ዘር መተካት ደግ ነው እንላለን። እንዴ ፌዴራሎች ጠለፋ ይሆን እንዴ የፈፀሙት?

የአባ መላ (ብርሃኑ ዳምጤ) መገለባበጥና ኢሳት

እንደልቡ/ዳግም (ከቫንኮቨር፣ ካናዳ)
አባ መላ ማን ነው?
በቅጽል ስሙ “አባ መላ” በእውነተኛ ስሙ ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ ተብሎ ይጠራል፣ በ60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ አዛውንት ነው (ምንም እንኳ ስራው እንደ እድሜው ባይሆንም)። ፓልቶክ የሚባለውን የማህበራዊ መገናኛ መድረክ በመጠቀም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዲስኩር በማሰማት ይታወቃል። በወጣትነቱ ኢህአፓ ውስጥ ነበር የሚባለው ብርሃኑ ዳምጤ ወዲያውም የኢህአፓን መዳከም አይቶ ወደ ደርግ ቡድን መቀላቀሉን የሚያውቁት ይናገራሉ። በወቅቱ አብረውት በኢህአፓ ውስጥ ይሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን ለደርግ በእጅ መንሻ መልክ አሳልፎ ሳይሰጥ እንዳልቀረ በደርግ ካድሬነት ቆይታው የሚያውቁት ይጠረጥራሉ አንዳንዶች ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይናገሩታል።Aba Mela low rank Ethiopian government cadre
ብርሃኑ ዳምጤ ከደርግ መውደቅ በኋላ በስደቱ ዓለም (ዳያስፖራ) ፖለቲካ መድረክ ብቅ ያለው በምርጫ 97 ወቅት የዝነኛውን ቅንጅት ማልያ ለብሶ ነበር። ይሁንና በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት/ወያኔ መንግስት ምርጫውን አጭበርብሮ፣ የምርጫውን መጭበርበር የተቃወሙትን በገፍ በአደባባይ በጥይት ደብድቦ፣ ህዝቡ የመረጣቸውን የቅንጅት አመራሮች፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨመሮ ከ50 ሺህ በላይ ባብዛኛው ወጣቶችን አስሮና በየጦር ካምፖቹ አጉሮ በአምባገነንነቱ ለመቀጠል ሲወስን ብርሃኑ ዳምጤም ባፋጣኝ የቅንጅትን ማልያ አውልቆ የህወሃት/ኢህአዴግን ማልያ ለብሶ ቁጭ አለ።

ጃዋር መሐመድ In My Mind!

ከአብርሃ ደስታ

ጎበዝ ሰው አያስፈራኝም (ጉረኝነቴ) ምክንያቱም ጎበዝ ሰው ብቃት አለው። ብቃት ያለው ሰው በሐሳብ (በምክንያታዊነት) ያምናል። በምክንያት የሚያምን ሰው ደግሞ አያስፈራም። ምክንያቱም በሐሳብ (በምክንያት) ከሚያምን ሰው ጋር ስትገናኝ ምክንያታዊነት እንደ መስፈርት በመጠቀም በሐሳብ ትከራከራለህ እንጂ ወደ ሌላ የሐይል መንገድ አትሯራጥም። በሐሳብ መከራከር ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም። ምክንያቱም በምክንያት ስትከራከር አንድም ሰውየው ያሳምነሃል አልያም ደግሞ አንተ ታሳምነዋለህ። አንዳቹ ካሳመናቹ ሁለታችሁ ትስማማላቹ። ካልተስማማችሁ ደግሞ በሐሳብ ትለያያላቹ። በሐሳብ መለያየት በራሱ ችግር የለውም።

ጃዋር መሐመድ በፖለቲካ ብቃታቸው ከማደንቃቸው ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች አንዱ ነው። እስከ ቅርብ ግዜ ጃዋር በሚሰጣቸው ትንታኔዎች እደነቅ ነበር። አንድ ግዜ ዕድል አግኝቼም አድናቆቴን ገልጨለታለሁ።

Friday, March 7, 2014

በግድቡ ሕይወታቸው የተገደበ ኢትዮጵያውያንን ለማትረፍ የሚደረገው እርብርብ (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ከሁለት ዓመታት በፊት በዚህ በያዝነው ወር “ግድቡ እና አደጋው፡ ግልገል ጊቤ ሦስት በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ በደቡብ ኢትዮጵያ በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ከሚካሄደው ልማት ጋር በተያያዘ መልኩ ግድቡ ሊያስከትል በሚችለው እንደምታ ላይ ትኩረት በማድረግ ትንታኔ አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትንታኔዬ በዚህ የልማት ሰበብ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ በአካባቢው ስነምህዳር ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽእኖ እና ግድቡ በአካባቢው ለዘመናት ሰፍረው በሚኖሩት ህዝቦች ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የአካባቢ ጥበቃ ድርጅቶች መንግስት ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ ድምጻቸውን ሲያሰሙ እኔም የሀሳቡ ተጋሪ በመሆን የነበረኝን ጥልቅ ስጋት በተደጋጋሚ አሰምቸ ነበር፡፡People of Omo River Basin sold down the river
ከዚህም በተጨማሪ “በኦሞ ወንዝ ሸለቆ ያለውን ምቹ ያልሆነ ሁኔታ እና ተጋርጦ የሚታየውን የወደፊት አደጋ አስቀድመው ግንዛቤ በመውሰድ ታላላቆቹ ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቃቸውን በማስመልከት የነበረኝን ልዩ አድናቆት እና ምስጋና አቅርቤ ነበር፡፡

ሰጪው ሕዝብ ሆይ፣ ተቀበል!!

Agegnehu Asegid
ሕዝብ ሆይ! እስከዛሬ “ሕዝብ አይወቀስም” የሚል የጋራ ስምምነት ውስጥ ተጎሽበህ ከወቀሳዎች ክልል ውጪ ሆነህ አሳልፈሃል። ወቀሳን የአንደበትህ ጌጥ አድርገህ በህዝብ አይከሰስም መርህ ብዙ ተከሳሾች ፈልፍልሃል። እኔ ግን የስምምነቱን አጥር ጥሼ ልወቅስህ መጣሁ።
ሕዝብ ሆይ ተቀበል!!

እኔ የምልህ ሕዝብ አንቀላፍተሃል እንዴ? ብዙ ነቄዎች “ሕዝብን ለማንቃት…” በሚል ሰበብ ተደራጅተው ዓላማቸውን ሲያሳኩ አያለሁ። አልነቃህም ማለት ነው? መች ነው የተኛኸው? ኸረ ለመሆኑ ምንስ ላይ ተኛህ? እንደምታውቀው “አልጋው” ተይዟል። አልጋውን ለመጠበቅ በዓይናቸው እንቅልፍ የማይዞር ሰዎች ተኝተውበታል። እስቲ አሁን በፈጠረህ እንቅልፍ ላይተኙ አልጋን መቆጣጠር ምን ይሉታል? ብዙዎች ይህን አይተው አልጋውን፣ “እንቅልፍ አልባው አልጋ” ሲሉ ይጠሩታል፤ ባለ አልጋውንም “እንቅልፍ የሌለው እንቅልፍ አምጪ” ይሉታል። ….እሺ እነሱንስ ተዋቸው፤ አንተ ግን አልጋው ተይዞብህ ምን ላይ ተኛህ? መደብ ላይ አስተኙህ እንዴ? ነው ዝም ብለህ መሬት ላይ ነው የተኛኸው? ወይስ በቁምህ ነውየተኛኸው? …እንዴት ደክሞሃል ጃል! ግን ምን ሰርተህ ደከመህ? መቼም ሌሎችን ስትወቅስ መሆን አለበት።

ብሄር ብሄረሰብ፤ የዘር ፓለቲካ…

ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር)
destawats@yahoo.com
እውቀት ይስፋ፣ ድንቁርና ይጥፋ
ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ።
ተስፋ ገብረሥላሴ
ፊደል የቆጠርሁት በአገራችን የህትመት ፋናወጊ (እና አርበኛ) የሆኑት ተስፋ ገብረሥላሴ ያሳትሟት በነበረው የባለ ፲ ሣንቲም ፊደል ነበር። ከፊደሏ ሽፋን ላይ ታዲያ ‘ተስፋገብረሥላሴ
ዘብሄረ ቡልጋ’ ይላል። መጠየቅ እወድ ነበርና መርጌታን ‘የንታ ብሄረ ቡልጋ ምን ማለት ነው?’ ብየ ጠየኳቸው። የንታም ልጄ ብሄር ማለት በግእዝ አገር ማለት ነው። ቡልጋ ደሞ ሽዋ ክፍላገር ውስጥ የሚገኝ አውራጃ ነው። የተስፋ ገብረሥላሴ አገር እዚያ ነው፤ አሉኝ።
ከዚያ አስኮላ ትምርት ገብቸ ፬ኛ ክፍል ህብረተሰብ መጽሀፍ ውስጥ የኢትዮጵያ ‘ብሄረሰቦችን’ የሚያሳይ ስዕል ተደርድሮ አየሁ። በተለይ ሲዳማን የዎከሉት ቆንጃጅት ሙገጫ ሲዎግጡ የሚያሳየው ስእል አይረሳኝም። ይሁን እንጅ ብሄረሰብ የሚለው ቃል አልገባኝም ነበርና አስተማሪየን ጠየኳት። እሷ ግን ጎሳ፣ ነገድ ቅብጥርሴ ብላ የባሰ ግራ አጋባችኝ። ደግነቱ ማታ ማታ የንታ ዘንድ ወንጌል እማር ነበርና ወንበር ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብዬ ሄጄ የንታን ‘ብሄረሰብ ምን ማለት ነው?’ ብዬ ጠየኳችው።

Saturday, March 1, 2014

የአፍሪካ ቀንድ፤ ዙሪያው እሳት መሀሉ ብሶት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

የአፍሪካን ቀንድ ሰሞኑን ትኩሳት ይዞታል፤ ሁኔታውን ለማብራራትና ለመተንተን ሰፊ ቦታን ስለሚፈልግ አንባቢው ራሱ እንዲያስብበት በመተው ሁነቶችን ብቻ ማቅረቡ የተሻለ ነው፤ የኢትዮጵያን የውስጥ ሁኔታ ትተን በአፍሪካ ቀንድ የሚከተሉትን የተለያዩ ግጭቶችን እንመለከታለን፤Prof. Mesfin Woldemariam
1. በጦርነት ሁኔታ ሁኔታ ላይ ያሉ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች፤–
ኤርትራና አትዮጵያ
ሰ.ሱዳንና ደቡብ ሱዳን
1.በውስጥ ብጥብጥ ላይ ያሉ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች
ሰ.ሱዳን በውስጥ
ደ.ሱዳን በውስጥ
ሶማልያ
በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ለጊዜው ግጭት የማይታይባቸው አገሮች ኬንያና ጂቡቲ ብቻ ናቸው፤ ኬንያ ከብሪታንያ ጋር ባለው የቆየ ትስስርና በኬንያ በሚኖሩ የብሪታንያ ሰዎች ምክንያት ጋሻ አለው፤ ጂቡቲም የቆየ የፈረንሳይ ጋሻ ቢኖረውም በአሁኑ ጊዜ አሜሪካም ተጨማሪ ጋሻ ስለሆነ የውጭ ኃይል አይደፍርም፤ ጂቡቲና ኬንያ በእውነትም እንደጌታዋን የተማመነች በግ ናቸው!

ለአማራ ትግሬዎች የመጀመሪያና የመጨረሻ መልእክት

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
“መልእክት” ያልኩት አቀራረቤን ቀለል በማድረግ የአንባቢያንን ቀልብ ላለመግፈፍ ነው፡፡ እንጂ መነሻየ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነው፡፡ ማስጠንቀቂያም ይባል መልእክት ዋናው ጉዳይ በግሌ የተሰማኝንና የማምንበትን ለወገኖቼ ድኅነት ስልም የምጽፈው ነገር ለባለአድራሻዎቹ መድረሱ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉንም ድረገጾች ትብብር በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ እባካችሁን ለሁሉም ካድሬ መልእክቴን አድርሱልኝ፡፡
ሰው ክርስቶስን መሆን እንዳይችል ጠላት መንገድ እየዘጋበት መቸገሩ የሚታወቅ ነው፡፡ መሆን  ቢፈልግ ግን ይችላል፤ የሚከለክለው አንዳችም ነገር የለም፡፡ ክርስቶስ ራሱም ያለው “እንደኔ ሁኑ፤ እኔን ምሰሉ” ነው፡፡ ችግሩ ክርስቶስን ለመሆን ወይም ቢያንስ ለመምሰል የእምነት ጽናትና እውነተኛ ፍቅርን የተላበሰ ስብዕና ማጣት ነው፡፡ ተራራን ሊያዞር የሚችል እምነት፣ የሚጠላንን ብቻም ሳይሆን የሚገድለንንም ጭምር  የሚያፈቅርና ለጨካኞች የሚራራ ልብ፣ የማይወላውል እምነትንና የማያዳላ ፍቅርን የሚገልጥ በጎ ሥራ ካለ ከፈጣሪና ከአንድያ ልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ውህደት መፍጠርና ጓደኛ መሆን የማይቻልበት ምክንያት የለም፡፡ የሚጠይቀው እውነተኛ የልብ መሰበርን ብቻ ነው፡፡