Thursday, May 28, 2015

የጥረቱ ሂደት ዕድገት፤ # ፬ – አንዱዓለም ተፈራ

ቀን፤     ማክሰኞ፤ ግንቦት ፲፰ ቀን፤ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት ( 5/26/2015 ) 11፡00 ጠዋት፤ ፓሲፊክ የሰዓት አቆጣጠር
eskemecheአንድ ነገር ጥሩ እየተካሄደ ያለው፤ የመሰባሰቡ አስፈላጊነት በየቦታው ዋና መነጋገሪያ ጉዳይ መሆኑ ነው። ከዚህ አንጻር፤
  • የኢሕአፓ ዴሞክራሲያዊ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ሁለት አባላት መድቦ፤ በቅድመ ዝግጅቱ ላይ ለውውይት ለመሳተፍ ወስነው አሳውቀውኛል።
  • የሸንጎ አባላት በሙሉ ልባቸው ተካፋይ እንደሚሆኑ አሳውቀውኛል።
  • የሽግግር መንግሥት አመራር አባላት ፈቃደኛነታቸውን ከማበረታቻ ቃላት ጋር ልከውልኛል።

አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ… (ክንፉ አሰፋ)

የ”ምርጫው” ድራማ እየተተወነ ሳለ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ለአቦይ ስብሃት ስልክ ደወሉ። “ሃሎ?” “ሃሎ፣ አቦይ ስብሃት ኖት?” “ነኝ፣ ምን ፈለግክ?” “ዶ/ር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ነን።” “ችግር መስማት አልፈልግም። የታዘዛችሁትን አደረጋችሁ?” “99.8% ህዝብ አልመረጠንም። ግን በታዘዝነው መሰረት ውጤቱን ገልብጠነዋል!” “0.2% ብቻ ነው የመረጠን ማለት ነው?” “አዎን ጌታዬ። ሌላ ምን እንታዘዝ?” “99.8% ህዝብ የስም ዝርዝሩን አንብብልኝ።” አሉ አቦይ ስብሃት እየተባለ ይወራል። አንድ ወዳጄ ስለ አቦይ ስብሃት የነገረኝ ታወሰኝ። ሰውዬው ከግመል እንኳን የማይሻል እንስሳ ብጤ ነው። ግመል ሳትጠጣ ለቀናት ትሰራለች አቦይ ስብሃት ደግሞ ሳይሰራ ቀኑን ሙሉ ይጠጣል። አብዛኞቹ የህወሃት አባላት እድሜያቸው እንደ አስተሳሰባቸው ስላረጀ ጨዋታቸው ከውሃ ጋር ነው።

ምርጫ ቦርድ የአስቂኙን ምርጫ ውጤት ይፋ አደረገ * ኢሕአዴግ 100% አሸነፈ አለ * ምንም አይነት ተቃዋሚ

(ዘ-ሐበሻ) ኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ የዘንድሮውን አሳፋሪ ምርጫ 100% ማሸነፋቸውን ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ገለጸ:: ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ በፓርላማው ውስጥ መቀመጫ እንዳላገኘም ተገልጹዋል:: የገዢው ፓርቲ መሳሪያና ገለልተኛ ያልሆነው ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ኢህአዴግ አዲስ አበባ ላይ ከ23 መቀመጫዎች ኢህአዴግ 23ቱንም መቀመጫዎች አግኝቷል። – ከትግራይ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ31 መቀመጫዎች ውጤት ህውሃት/ኢህአዴግ 31 መቀመጫዎችን – ከአማራ ክልል ከደረሱት የ107 መቀመጫዎች ውጤት ብአዴን/ኢህአዴግ 107 መቀመጫዎች ከኦሮሚያ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ150 መቀመጫዎች ውጤት ኦህዴድ/ኢህአዴግ 150 መቀመጫዎችን

ፍ/ቤቱ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የቀረቡ የሲ.ዲ መረጃዎችን ውድቅ አደረገ

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ዛሬ ግንቦት 19/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ የተቀጠረው አቃቤ ህግ አሉኝ ባላቸው ሲ.ዲዎች እና ቀሪ ምስክሮቹን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ ቀሪ ምስክሮቹን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለማቅረብ ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ የሰጠውን እድል ባለመጠቀሙ እና ምስክሮቹን ላለማቅረቡ የሰጠው ምክንያትም በቂ ባለመሆኑ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ባለመፍቀድ ከዚህ በኋላ ምስክሮቹን እንደማይሰማ አመልክቷል፡፡ አቃቤ ህግ በኤግዚቢትነት ይዟቸው የቆያቸውን የ12ቱን ሲ.ዲዎች ጉዳይ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ሲ.ዲዎቹ በማስረጃ ዝርዝሩ ውስጥ ፕሪንት ተደርገው የተያያዙ ሰነዶችን እንደያዙ ስለተገለጸ ሲ.ዲዎቹ ከማስረጃነትም ሆነ ከኤግዚቢትነት ውድቅ መደረጋቸውን ገልጹዋል፡፡

አሜሪካ ውስጥ ርካሽ እና ውድ የቤት ኪራይ ያለባቸው ከተሞች ተለይተው ታወቁ

(Admas Radio)
ካሊፎርኒያ፣ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ሃዋይ፣ ኒውዮርክ እና ኒውጀርሲ ውድ ቤት ኪራይ ያለባቸው ከተሞች መሆናቸውን ሰሞኑን የወጣ ሪፖርት አሳይቷል።
new-york-city
አንድ በኒውጀርሲ ከተማ ለመኖር የፈለገ ተከራይ ባለሁለት መኝታ ቤት ተከራይቶ ለመኖር አንድ በሰዓት 25 ዶላር የሚከፈልበት የሙሉ ሰአት ሥራ መስራት ይኖርበታል። በኒውጀርሲ በአማካይ የሁለት መኝታ ቤት ዋጋ 1300 ዶላር በወር ነው። አንድ ሰው የቤት ክፍያው ከደሞዙ ከ 30 በመቶ መብለጥ አይኖርበትም – አቅም አለው ለመባል። በዚህ መሰረት 1300 በወር ከፍሎ ለመኖር ቢያንስ በወር አንድ ሰው 4ሺ 500 ዶላር ገቢ ሊኖረው ይገባል።

Saturday, May 23, 2015

የሰማያዊ ፓርቲን የገንዘብ ምንጭ ለማወቅ ምርመራ ተጀመረ

‹‹በፋይናንስ ግኝታችን ጥያቄ ሊነሳ አይገባም›› ሰማያዊ ፓርቲ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ አነጋጋሪ ሆኖ ብቅ ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ለ2007 ዓ.ም. ምርጫ ይፋ ያደረገው የበጀት መጠን ‹‹ከፍተኛ መሆን››፣ የውጭ ፋይናንሰሮች እጅ አለበት የሚል ጥርጣሬ በማስነሳቱ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ለዘንድሮ ምርጫ 92 ሚሊዮን ብር በጀት እንደያዘ ካስታወቀ በኋላ፣ ከሚያነሳቸው ፖለቲካዊ አጀንዳዎች በተጨማሪ የያዘው በጀት መጠን የወቅቱ መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ መንግሥት ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫው በያዘው በጀት መጠን ላይ ጥርጣሬ አለው፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ አዲስ ድህረ ገጽ መልቀቁን ከድርጅቱ ጽ/ቤት ለማወቅ ተችሎል

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ባለፉት ወራቶች ውህደት ከፈጸመ በሆላ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተስፋ የጣሉበት ሲሆን፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ በአካባቢው መፈጠሩና ውጥረት መከሰቱ የሚታወቅ ሲሆን ብዙዎቹ የድል ሽታ መፍጠሩን ይስማሙበታል። ወያኔ በምንም ታምር በሰላማዊ መንገድ ከስልጣን እንደማይወርድ እና በስልጣኑ የመጡበትን ሁሉ መግደል ወይም ማሰር እና ማሰደድ ላይ ያተኮረው የህወሃት ድርጅትን ብቸኛው መንገድ በሁለገብ ትግል ማስወገድ ተገቢ መሆኑን አሁን ያለው ሁኔታ የሚመሰክር መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይስማሙበታል።

በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ዘለፋ አዘል ግምገማ ተካሄደ


ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት  ኢህአዴግ፣  ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው ተገምጋሚ ራሳቸው ሆነዋል። በጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የተደረገው ግምገማ አንድ ሙሉ ቀን የወሰደ ሲሆን፣ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ መጠናቀቁን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም ብዙዎችን የግምገማ ነጥቦች ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸው ለግምገማው መራዘም ምክንያት ሆኗል።

ካድሬዎች የምርጫ ካርድ ላይ ንብን እየለጠፉ ለመራጩ እያደሉ ነው

በጋሞጎፋ ዞን ቁጫና ቦርዳ ወረዳዎች የደኢህዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች የህዝቡን ካርድ እየተቀበሉ የምርጫ ካርዱ ላይ የንብን ምልክት በስቴፕለር በማያያዝ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሚገኙ በጋጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ መኩሪያ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ካድሬዎቹ ህዝቡን 1ለ5 በማደራጀት የንብ ምልክት የተለጠፈበት ካርድ በማደል ‹‹የምትመርጡት ኢህአዴግን ነው›› እያሉ እያስገደዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
የዞኑ፣ የወረዳውና የየ ምርጫ ክልሉ ምርጫ አስፈጻሚዎች ካድሬዎቹ የንብ ምክትን የምርጫ ካርዱ ላይ እያያያዙ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያስገደዱ መሆኑን ቢያውቁም ምንም እርምጃ እየወሰዱ አይደለም ብለዋል፡፡

የወያኔን የይስሙላ ምርጫ አስመልክቶ ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፈ ጥሪ

የተከበራችሁ እናቶቼና አባቶቼ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዲሁም ልጆቼ የምትሆኑ ወጣቶች!!
dr-berhanu-Negaአገራችን የምትገኝበትን አስጨናቂ ሁኔታ ሁላችንም እንረዳለን። የህወሓት/ኢሕአዴግ ፋሽስቶች ቡድን እየገረፈ፣ እያሰረና እየገደለ በካርዳችሁ መርጣችሁ የምርጫ ድግሴን ካላሞቃችሁልኝ እያለ ነው። እንኳንስ ዛሬ ታዛቢ በሌለበት፤ ታዛቢ እያለም እንኳን ወያኔ የሕዝብን ድምጽ በትክክል ቆጥሮ አያውቅም። ወያኔ ለህዝብ ድምጽ ምንም ደንታ የሌለው የኋላቀር ወሮበሎች ቡድን ነው::
ለስንት አስርት ዓመታት ለወያኔ ባርነት እንገብራለን? ለሀያ አስምስት ዓመታት ተገዛን፣ ተገደልን፣ ተቀጠቀጥን፣ ታሰርን፣ ተሰቃየን፣ ልጆቻችን በአገራቸው ተስፋ ቆርጠው ሲሰደዱ በበረሀ ንዳድ አለቁ፤ በባህር ሰጥመው ቀሩ፤ በባዕዳን አረመኔዎች እንደከብት ታረዱ፤ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ተቃጠሉ።

Ethiopian Election: “The political space has been closed” Yilekal Getinet

Addis Ababa (AFP) – Ethiopia, Africa’s second-most populous country, holds general elections Sunday, the first since the death of long-time strongman Meles Zenawi whose successor Hailemariam Desalegn is seen as all but certain to stay in office.
Over 36.8 million Ethiopians have registered for the polls, considered by the international community as a key test of the state’s commitment to bring greater democracy to the Horn of Africa nation.
Rights groups routinely accuse Ethiopia of clamping down on opposition supporters and journalists and using anti-terrorism laws to silence dissent and jail critics.

ኢህአዴግ ሆይ ነቄ ነን ተቀየስ! (ርዕዮት አለሙ – ከቃልቲ እስርቤት)

ርዕዮት አለሙ – ከቃሊቲ እስርቤት
አራት ሆነን ወደምንኖርበት የአሁኑ የማግለያ ክፍል ከመግባቴ በፊት በርካታ እስረኞች በተለምዶ የአራድኛ ቃላት የሚባሉትን በመጠቀም ሲነጋገሩ የመስማት እድል ነበረኝ፡፡ ለርዕሴ የመረጥኳቸው ቃላትንም ያገኘሁት ከነሱው መሆኑን መግለፅ ይኖርብኛል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፤Reeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner.
አንዳንድ እስረኞች የሚፈልጉትን አንዳች ነገር ለማግኘት በጉልበታቸው ወይም ጤፍ በሚቆላ ምላሳቸው ይጠቀማሉ፡፡ ሀይልን በመጠቀም ያስገድዳሉ ወይም ያታልላሉ ማለት ነው፡፡ እንዲህ አይነቶቹ እስረኞች እንደለመዱት ለማድረግ ሲሞክሩ አንዳንዴ ደፋርና የማይታለሉ እስረኞች ላይ ይወድቃሉ፡፡ እናም ለማታለል ወይ ለማስገደድ የሞከረች ባለጌ የሚጠብቃት መልስ “ነቄ ነን እባክሽ! ተቀየሽ! ንኪው!”የሚል ይሆናል፡፡ እኛን ማታለልም ሆነ ማስፈራራት ስለማትችይ ይቅርብሽ፡፡ ዞርበይልን እንደማለት ነው፡፡

Thursday, May 21, 2015

ካድሬዎች የምርጫ ካርድ ላይ ንብን እየለጠፉ ለመራጩ እያደሉ ነው

በጋሞጎፋ ዞን ቁጫና ቦርዳ ወረዳዎች የደኢህዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች የህዝቡን ካርድ እየተቀበሉ የምርጫ ካርዱ ላይ የንብን ምልክት በስቴፕለር በማያያዝ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሚገኙ በጋጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ መኩሪያ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ካድሬዎቹ ህዝቡን 1ለ5 በማደራጀት የንብ ምልክት የተለጠፈበት ካርድ በማደል ‹‹የምትመርጡት ኢህአዴግን ነው›› እያሉ እያስገደዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች የ አይ ኤስ ታጣቂዎችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ እያደረጉ ነው


download
ቢቢሲ ባወጣው መረጃ መሰረት አንድ የሊቢያ ባለስልጣን ለቢቢሲ እንደገለፁት በሜዲትራኒያን ባህር በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ አውሮፓ አዘዋዋሪዎች ከስደተኞች ጋር ታጣቂዎቹን በመቀላቀል ወደ አውሮፓ እንዲገቡ እያደረጉ ነው
ታጣቂ ቡድኑ በሰሜን አፍሪካ ጀልባ ባለቤቶች ስራውን እንዲሰሩ በመፍቀድ ከገቢያቸው ደግሞ 50 በመቶ ያህሉን ይቀበላሉ እንደ ቢቢሲ ዘገባ
የአይ ኤስ ታጣቂዎች በባህር በሚደረገው ጉዞ ከሌሎቹ ስደተኞች በምን ይለያሉ? ከዘገባው ያገኙታል .

ሰማያዊ ፓርቲ በ አማራ ክልል እንዳይንቀሳቀስ እየተደረገ ነው


semayawi-party
በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች መጪውን ምርጫ ተከትሎ በርካታ ዜጎች እየታሰሩ መሆናቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አመለከተ፣ በክልሉ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች መጪውን ምርጫ ተከትሎ በርካታ ዜጎች እየታሰሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ ንፁሃን ዜጎችን በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሰው ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ሰንካላ ምክንያት የስርዓቱ ካድሬዎች ባሰማሯቸው በሆዳቸው ባደሩ የደህንነትና የፀጥታ አካላት እየታደኑ መታሰራቸውን አስረድተዋል፣

“ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ)

የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላለፉ! እነሆ መልዕክቱን ያንብቡ፤ ሼር በማድረግም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ይደርስ ዘንድ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት ተጠይቃችኋል!
“ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ)
ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እንዳሸዋ ተበትናችሁ የምትገኙ ወገኖቼ እኔ የተጎዳሁትን ያህል እናንተም የተጎዳችሁ መሆናችሁን በተለያዩ ሀገሮች በተደረጉ ሰልፎች ፤ የዉይይት መድረኮች ላይ በንዴት፤ በቁጭት እና በእልኸኝነት በእንባ ስትራጩ በመሃላችሁ ተገኝቼ ያየኻችሁ ሲሆን ይህም በጣም በኢትዮጵያዊነቴ እንድኮራ አድርጎኛል። አንዳርጋቸውም በወያኔ የጨለማ እስር ቤት እየከፈለ ያለውን መከራና መስዋትነት የትም እንዳልወደቀና እንዳልቀረ በማሰብ እጽናናለው።

የህወሓት አየር ኃይል ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገው ጉዞ መሰረዙ ተሰማ፡፡

በበረራ፣ ጥገና፣ ድጋፍ ሰጪ፣ ዘመቻና አስተዳደር ከ200 በላይ አባላቱን በከፍተኛ ወጪ ለ6 ወራት ሲያሰለጥን የባጀው አየር ኃይል የሰላም ማስከበሩ ተልዕኮ ወደሚከናወንበት ደቡብ ሱዳን ሊጓዙ የተመረጡት መንገደኞች ከየአየር ምድቦቻቸው ተነስተው ደብረ ዘይት ከከተቱ በኋላ ጉዞው ድንገት ተዘርዟል፡፡
ጉዞው የተሰረዘባቸው ምክንያቶች በአባላትና አባላት፣ በአባላትና አመራሮች እንዲሁመም በአመራሮችና አመራሮች መካከል አለመተማመን በመስፈኑ፤ ያለመጠን ስር ሰዶ የተንሰራፋው ጎሰኝነት ተባብሶ በትግርኛ ተናጋሪ የህወሓት ሰዎች መካከልም ውቅሮና አዲግራት ወደሚሉ የመንደር ቡድንተኝነት ቁልቁለቶች በመውረዱ፤ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ አሁንም አብራሪዎች ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን ይዘው ሊኮበልሉ ይችላሉ ከሚል ስጋት በመነጨ፣ ከፍተኛ በሆነ የአቅም ማነስ ችግር፤ ከምርጫው ጋር በተያያዘና ብረት ያነሱ የነፃነት ኃይሎች ጦርነት ይከፍታሉ ተብሎ በመሰጋቱ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በእነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የተመሰረተው ክስ ተሰማ

‹‹በይልቃል ጌትነት እና በዮናታን ተስፋዬ ላይ መስክር እያሉ ያሰቃዩኛል›› ብርሃኑ ተ/ያሬድ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የፌደራል አቃቤ ህግ በቀን ሚያዝያ 22/2007 ዓ.ም በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ላይ የመሰረተው ክስ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ዛሬ ግንቦት 12/2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በንባብ ተሰምቷል፡፡
በብርሃኑ ተ/ያሬድ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ ላይ አራት ሰዎች የተካተቱ ሲሆን፣ እነዚህም 1ኛ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ 2ኛ እየሩሳሌም ተስፋው፣ 3ኛ ፍቅረማርያም አስማማው እና 4ኛ ደሴ ካህሳይ ናቸው፡፡ የሽብር ክስ የቀረበባቸው እነዚህ ተከሳሾች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ (አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና የጸረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 7(1)ን በመተላለፍ ወንጀል እንደተከሰሱ የክስ ቻርጁ ያመለክታል፡፡

እነሀብታሙ፣ የሺዋስ፣ ዳንኤል፣ አብርሃ …ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ 19ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እየታየ፣ እና በእነዘላላም ወርቅአፈራሁ የክስ መዝገብ ተከስሰው የሚገኙት እነሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ባህሩ ታዬ …የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለሰኔ 1፣ 2 እና 3 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ዛሬ በችሎት ጸሀፊ በኩል እንደተሰጣቸው ጠበቃቸው አቶ ተማም አባቡልጉ ገልጸዋል፡፡

አረና ቅስቀሣውን አቋረጠ፤ በአባሎቹ ላይ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ ….VOA

ተቃዋሚው አረና ትግራይ “በአባሎቼ ላይ ተፈፅሟል” ባለው ድብደባና ለምርጫ ቅስቀሣ ሥራ በተከራያት መለስተኛ አውቶቡስ ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት በመላው የትግራይ ክልል የጀመረውን የምረጡኝ ቅስቀሣ ዛሬ ማቋረጡን ይፋ አድርጓል።
ዘጋቢያችን ግርማይ ገብሩ የተሽከርካሪዋ የኋላ መስትዋትና መብራት መሰባበሩን በሥፍራው በአካል ተገኝቶ ተመልክቷል።

የወያኔ መንግስት በመላው አዲስ አበባ በታንክ የተደገፉ ታጣቂዎችን ማሰማራቱ ተነገረ *በለምለም ከበደ*

ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ በባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ  በማስፈራራት ጀምሮአል። በምርጫ ቅስቀሳ የፈራው የወያኔ መንግስት ፓርቲዎችን በክርክሩ መርታት ሲሳነው በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ አይተናል በክርክሩ የህዝብ አመኔታን ያጣው ገዢው ወያኔ የሚጨብጠው ቢያጣ ንቢቱን ተመስሎ በተሰራ ባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ ላይ ይደነፋ ጀምሮአል ድሮም ኮሮጆ በመስረቅ  ነው 25 ዓመት በሃይል የገዛው ።
ገዥው የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ አምስተኛው የኢትዬጲያ ብሄራዊ ምርጫ ግይካሄዳል ፡፡ ሶስተኛውና ተስፋ የፈነጠቀው አገራዊ ምርጫ ተስፋ አስቆራጭ በሆነ የፓለቲካ ምህዳር መዘጋት ከተጠናቀቀ በኋላ የተካሄደውን አራተኛው ምርጫ ኢህአዴግ 99.6  በመቶ የፓርላማ መቀመጫ “በማሸነፍ” ተቆጣጥሮታል፡፡

Sunday, May 17, 2015

በጋምቤላ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዉ ህይወት ጠፋ ESAT NEWS

በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ አካባቢ ሰሞኑን በተቀሰቀሰ ግጭት አምስት ሰዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል ።
በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ማጣታቸውን የሚናገሩት የወረዳው ነዋሪዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ጥያቄዎችን ባነሱ ነዋሪዎች ላይ የሚወስዱት እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል ።

Wednesday, May 13, 2015

ደርግን ያስናፈቀ አገዛዝ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እኔ ለደርግ ሥርዓት ጥሩ ስሜት የለኝም፡፡ በእርግጥ ደርግ ያደረገውን የቀይ ሽብር ፍጅት በወቅቱ ገና መወለዴ ስለነበር በዐይኔ ዐላየሁም፡፡ ይሁንና የሆነውን ሁሉ ግን አባቴም በኢሕአፓነቱ የደርግ ጥቃት ሰለባ ስለነበር እሱ ከነገረኝም ሆነ እኛ ዜጎች የደርግንም ሆነ የሌላውን ማንነት ከመረዳት አንጻር ከታሪክ ብዙ የምንረዳው ነገር አለና ለደርግ ጥሩ ስሜት የለኝም፡፡ ከፈጸማቸው የግድያ እርምጃዎች ጋር በተያያዘ አሁን ሀገራችን ላለችበት ዘንቀ ብዙ ችግሮች ተጠያቂ እንደሆነም አስባለሁ፡፡ በተለይም እነዚያ ብዙ የተማሩ ብዙ የሚያውቁ ብዙ የውጪ ግንኙነት ልምድ የነበራቸው የ62ቱ የቀዳማዊ ዐፄ ኃይሌ ሥላሴ መንግሥት ሚንስትሮችን ጉዳይ ሳስብ ዘወትር ይከነክነኛል፡፡ ኢትዮጵያ ከስር የተነቀለችው ዐይኖቿ የጠፋው ያኔ ነው፡፡

የቀድሞ የመኢአድ የሕዝብ የህዝብ ግኑኙነት ሀላፊን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ኤርትራ ለትጥቅ ትግል መግባታቸውን ገለጹ

“ወያኔን በሰላማዊ ትግል አይወድቅም ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ በትጥቅ ትግል መታገል ነው” ወጣት ተስፋሁን አለምነህ
Tesefahun-Alemeneh_001 (1)
ወጣት ተስፋሁን አለምነህ
የቀድሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ በአገር ቤት የወያኔን አገዛዝ በሰላማዊ ትግል ታግሎ መጣል አይቻልም ብሎ በመወሰን እሱና ሌላው የመኢአድ አባል ደሳለኝ ሲሳይ ከበርካታ ወጣቶች ጋር ኤርትራ የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ሰሞኑን መግባታቸውን ለህብር ሬዲዮ ከስፍራው በሰጠው አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ገለጸ።

አርበኞች ግንቦት 7 አዳዲስ ታጋዮችን አስመረቀ

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ውህደት አድርጎ አንድ ከሆነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ አርበኛ ታጋዮችን ማስመረቁ ተሰማ:: አርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮቹን በኤርትራ ያስመረቀው ያለፈው እሁድ ግንቦት 2 ነው:: ከኤርትራ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ኤርትራ በመግባት አርበኞች ግንቦት 7ን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ:: የምርቃቱን ፎቶዎች ይመልከቱ:: 

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ሴቶች የታሰሩት ኮሚቴዎች ነጻ መሆናቸውን መሰከሩ “ሙስሊሙን ጨካኝ ለማስመሰል የሚደረገው ሴራ አይሰራም”

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴት ሙስሊሞች ባደረጉት ኮንፈረንስ የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ነፃ መሆናቸውን መሰከሩ:: ሙስሊሞችን ጨካኝ ለማስመስል የሚደረገው ሴራም በቅዱስ ቁርአን የማይፈቅደውና የማይገባ ነው ብለዋል:: ሙሉ ቭዲዮውን ይመልከቱ::
ይህን ታላቅ የሴቶች ኮንፈረንስ ያዘጋጀው ሪሳላ ኢንተርናሽናል ነው::

ሳሞራ የኑስ በዋሽንግተን ዲሲ እጅግ ተዋረዱ * ተቃውሞው ቀጥሏል

በዋሽንግተን ዲሲ ማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ድንገት የተገኙት የወያኔው መንግስት መከላከያ ሚኒስተር ጄነራል ሳሞራ የኑስ በኢትዮጵያዊያኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው ውርደትን መከናነባቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ:: በአንድ ለሊት አዳር 12 ሺህ 700 ብር በሚከፈልበት በማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ያረፉት ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከዋሽንግተን ዲሲ ግብረሃይል ወጣቶች ጋር ፍጥጫ ገጥመው ከፍተኛ የሆነ ግብግብ ተፈጥሯል:: አካባቢው በዲሲ ፖሊሶች የታጠረ ሲሆን ሳሞራም ካረፈበት ከዚህ ሆቴል ሊወጣ እንዳልቻለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል::

ትናኤል ያለምዘውድ ለብይን ተቀጠረ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ህዝቡን ከጠራው ሰልፍ ጋር በተያያዘ በትናንትናው ዕለት ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ናትናኤል ያለምዘውድ ዛሬ ግንቦት 5/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ የተሰማበት ሲሆን ለግንቦት 11/2007 ዓ.ም ለብይን ተቀጥሯል፡፡
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበው ናትናኤል ቀደም ብለው ክስ እንደተመሰረተባቸው የፓርቲው አባላት በተመሳሳይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 490(3) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲረበሽ አድርጓል የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡

የሀገር ሀብት ዘረፋ፤ስደት፤እሥራትና ግድያው እንዲቆም ህወሃትን ከሥልጣኑ አውርደን መጣል ግዴታችን ነው።

ገብርየ በለው።  
ካልገደሉ አያቆሙንም ነው ያለው ሐብታሙ አያሌው?( ወጣቱ የፖለቲካ መሪ)ሟች ማን ገዳይ ማን?ታጋይ ይሞታል እንጅ ትግል አይሞትም።
    EPRDFፋሽስቱና አረመኔው የህወሃት ቡድን ፀረ-ሕዝብነቱን ፀረ-ኢትዮጵያዊነቱን አጠናክሮ ለ24 ዓመታት ያህል ሲዘልቅ ከባድና ከፍተኛ የሆኑ ጠባሳ የታሪክ አሸራዎችን እያስመዘገበ ማለፉ በግልጽ የሚታወቅ የሚጨበጥና የሚዳሰስ ታሪካዊ ክህደት ነው።በተለይ ከ1997 ምርጫ በኋላ በቀቢጠ ተስፋ የሚሠራውን አሳጥቶት ይገኛል ከ2007 ምርጫ በፊት በምርጫ መስናዶ ያሳያቸው የአውሬነት ባህርያትም በውል ሊስተዋሉ የሚገባቸው ናቸው።
     በአንፃሩ ደግሞ ይህን የህወሃት ታሪካዊ ክህደትና የቅጥረኝነት አስነዋሪ ተግባር ለመመከት በኢትዮጵያዊነታችን የምናምን ዜጎች የሄድንበት ርቀት ወንዝ የሚያሻግር ሆኖ አላገኘሁትም። ጉዳዩ ህወሃት የሰጠን የቤት ሥራ ብቻውን አቅም እንድናጣ አድርጎናል ብየም አልገምትም። የራሳችን ችግርም አስተዋፅኦ አድርጓል።

ኃይለማርያም ደሳለኝ እምባ እስኪተናነቃቸው ድረስ በአርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ ተተቹ

ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችንና የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በሙሉ ሲያስገመግሙ ከከረሙ በሁዋላ በመጨረሻ ራሳቸው 15 ሰአታት በፈጀ ግምገማ ተገምግመዋል። አብዛኞቹ በአቶ ሃይለማርያም የስራ ችሎታና አመራር ላይ ዘለፋ ቀረሽ ሂስ አቅርበውባቸዋል። አቶ ሃይለማሪያም የቀረበባቸውን ሂስ ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸው ግምገማው ረጅም ጊዜ እንዲወስድ አድርጓል። ግምገማው ከምርጫው በሁዋላ የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ ባለስልጣናትን ለመለየት እና ግድፈታቸውን አርመው ሰርተው እንዲጠብቁ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

Monday, May 11, 2015

የሰሜን ጎንደር ህዝብ እኛን ምረጡንና የማዳበሪያ እዳችሁን ቀስ ብላችሁ ትከፍላላቸሁ እየተባሉ ነው።

SC
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙት የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች ህዝብ አይመርጠንም የሚል ስጋት ስላደረባቸው ለህብረተሰቡ የማደናገርያ ቃል እየገቡለት መሆናቸውን ተገለፀ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው- የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘውን ህዝብ በማዳበሪያ እዳ ተማርሮ እንደሚገኝ አስቀድመው ስለተረዱ ሱሪያችሁን በጭንቅላታችሁ አውጡ አይነት አስገዳች መመሪያ በመስጠት እያስጨነቁት እንዳልቆዩ አሁን ላይ ደርሰው ከህብረተሰቡ በርካታ ተቃውሞ ስላጋጠማቸው የወሰዳችሁትን የማዳበርያ እዳ ቀስ ብላችሁ በሚቀጥለው አመት ትከፍሉታላችሁ በማለት በመጪው ግንቦት ወር ላይ ተመርጠው የስልጣን እድሜአቸውን ለማስረዘም ህዝቡን እያታለሉት መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አስረድቷል፣

ገዥው ፓርቲ ኦሮሚያ ውስጥ ምርጫውን ጀምሮታል ተባለ

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገዥው ፓርቲ ምርጫውን ከአሁኑ እንደጀመረው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ካድሬዎች መራጮችን በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ እያደራጁ ‹‹ኦህዴድ/ኢህአዴግን መርጫለሁ›› በሚል እያስፈረሙና ፎርም እያስሞሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ ተደራጅተው ‹‹ኦህዴድን መርጠናል›› ብለው እንዲፈርሙ የተደረጉ ዜጎች ፎርሙን ከሞሉበት ቀን ጀምሮ የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ መሪዎቻቸው እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ መሪዎችም ኢህአዴግን ከአሁኑ መርጠዋል ተብለው የተደራጁ ዜጎችን ስምና የምርጫ ካርድም ለኦህዴድ/ኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች እንደሚሰጡ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

“በሰማያዊ እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂው የከተማ አስተዳደሩ ነው” ሰማያዊ ፓርቲ

ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ሚያዝያ 29/2007 ዓ.ም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ ምርጫ ቦርድ በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዲወጣ ጠይቋል፡፡ የተሻሻለውን የምርጫ ህግ 532/1999 ዓ.ም አንቀፅ 58 ቁጥር 1 ላይ ‹‹አንድ ዕጩ ተወዳዳሪ መታወቂያ ካገኘበት ቀን አንስቶ ምርጫው ሁለት ቀን እስኪቀረው ድረስ ከአስተዳደሩ ሆነ ከማዘጋጃ ቤት ፈቃድ ሳይጠይቅ በፅሁፍ በማሳወቅ ብቻ የድጋፍ ስብሰባዎች አሊያም ሰላማዊ ሰልፎችን የመጥራት መብት አለው›› የሚለውን የጠቀሰው ሰማያዊ ፓርቲ ሆኖም ይህንን መብት መነፈጉን ገልጾአል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በደብዳቤው ይህን ህግ ተከትሎ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተደጋጋሚ ጊዜ የህዝባዊ ስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ቢያቀርብም አስተዳደሩ ስለማይቀበል ፓርቲው በደተጋጋሚ ጊዜ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር አለመግባባት እንዲፈጥርና ሌሎች ችግሮችም እንዲደርሱበት አድርጓል ብሏል፡፡ ፓርቲው ግንቦት 9/2007 ዓ.ም ከመራጩ ጋር ለመገናኘት መስቀል አደባባይ ላይ ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚጠራ ለአስተዳደሩ ቢያሳውቅም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊጠቀሙበት የሚገባው መስቀል አደባባይ ላይ ህዝባዊ ስብሰባ ማድረግ እንደማይችል በከተማ አስተዳደሩ መከልከሉን ገልጾአል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ህገወጥ ባለቻቸው የውጪ ዜጎች ላይ ዘመቻ ከፈተች

south africa
ሀገሪቱ በቅርብ ጊዜያት በተነሳ የውጪ ዜጎችን ኢላማ ባደረገ ተቃውሞና ጥቃት ስትታመስ ቆይታለች “አፍሮ ፎቢያ” ተብሎ እስኪሰደብ ድረስ በዛ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ስደተኞች በዚሁ ዜኖ ፎብያ በተባለ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውም የሚዘነጋ አይደለም
አሁን ደግሞ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በህገ ወጥ መንገድ ወደሀገሪቱ ገብተዋል ያሏቸውን የውጪ ዜጎች ማደንና ማሰር እንደጀመሩ ነው የተነገረው ደቡብ አፍሪካ መሰንበቻዋን የመከላከያና ፖሊስ ሀይሏን በጆሀንስበርግ አሰማርታ ህገ ወጥ ስደተኞችን ማሰሯ ተሰምቷል

የሰማያዊ ዘጠና ሁለት ሚሊዮን ወያኔን አስጨንቆታል

ሪፖርተር እንዳስነበበን የሰማያዊዎቹ በጀት ኢህአዴግን ጭንቀት ላይ ጥሎታል። ዋ….አይ ከየታባታቸው አመጡት፤ ብለው ግራ ግብት ያላቸው አቶ ሬድዋን ”ኮንሰርት አላዘጋጁ፣ ቱጃሮች አይደሉ፣ ልማታዊ ባለሃብቶች አልደገፏቸው” ሲሉ ጭንቀታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል። አቶ ሬድዋን ተጨንቀውም አላባሩ ይሄንን ጉዳይ የሚመለከተው አካል እንዲመርምር አዘናል አይነትም ብለዋል። (እኛ ግን እነርሱ ሃያ ሶስት ሚሊዮን ሲያወጡ የአባይን መዋጮ ለቅስቀሳ አዞሩት እንዴ ብለን አልመረመርንም!) የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እንደተናገሩት ፓርቲያችን ሁለት መቶ እጮዎች በገዢው ፓርቲ ጉልበተኝነት ተሰርዘውበት እንጂ ኢህአዴግን ልናሳርፈው ጠንክረን እየሰራን ነው ብለዋል። (በሾርኔ ኢህአዴግን ለማሳረፍ ዘጠና ሁለት ሚሊዮን ምን አላት አይነት ነው!)

ግለሰቡ የ 7 ወር ነብሰ ጡር የሆነችውን ወጣት ሚስጥሬን አወጣሽ በሚል አስገድዶ ከደፈረ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏታል፡፡ ሙሉ ዘገባ ይከታተሉ



ግለሰቡ የ 7 ወር ነብሰ ጡር የሆነችውን ወጣት ሚስጥሬን አወጣሽ በሚል አስገድዶ ከደፈረ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏታል፡፡ ሙሉ የፖሊስን ዘገባ ይከታተሉ

ፖሊስ በሰማያዊ አባላት ላይ አለኝ የሚለውን መረጃ እንዲያቀርብ የ‹‹መጨረሻ›› አንድ ቀን ተሰጠው

ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ሊቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን የሽብር ድርጊት ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳትና በመሳተፍ›› ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሚያዝያ 30/2007 ዓ.ም ጠዋት በቄራ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው የ6000 ብር የሰው ዋስትና ተፈቅዶላቸው የነበር ቢሆንም ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ በእስር ላይ እንዳቆያቸው ይታወቃል፡፡

የሻማ መዘዝ (አርአያ ተስፋማሪያም)

ሻለቃ ፅጌ ትባላለች፤ (አሁን ኰሎኔል) ..የጄ/ል ሰዓረ መኮንን ባለቤት ናት። ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 1997ዓ.ም ምሽት ኢህአዴግ ምርጫውን አስመልክቶ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ጠርቶ ነበር። ሻለቃ ፅጌ ከጠባቂዋ ደህንነት ጋር በስፍራው ተገኝታ ሻማዋን እያበራች በጦር ሃይሎች ሆ/ል በር በኩል ታልፋለች። በሆስፒታሉ በር ከቆመው ጠባቂ ዘብ ጋር አብራ የምታወራ የሆ/ ሉ ሜንስ ቤት ሰራተኛ እያፌዘች «ስሚ አንቺ የያዝሽው ሻማ የኢህአዴግ ንብ እሁድ ይቃጠልበታል..በቅንጅት» ትላታለች። ሻለቃ ፅጌ ተንደርድራ በመሄድ በጥፊ ስትማታ ልጅቷም አንገቷን በማነቅ ሻለቃዋን መሬት ላይ ጥላ ስትረግጣት የሻለቃዋ ደህንነት ሽጉጡን መዞ ሲጠጋ የበሩ ዘብ ክላሹን ወድሮ ይተናነቃሉ። ሻለቃዋን አላውቋትም ነበር።

Wednesday, May 6, 2015

የፖለቲካ ጥግ

ምርጫ 
በአፍሪካና በአውሮፓ
*አል ባሺር ተቃዋሚዎች በሌሉበት በዝረራ አሸነፉ
*የ71 ዓመት ባለጸጋ፤የ26 አመት ሥልጣን

    እምብዛም የማይገርማችሁን አንድ ወሬ ልንገራችሁ፡፡ ለ26 ዓመታት ሱዳንን የገዙት የ71 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ ኡመር ሃሰን አልበሽር፤ሰሞኑን በሱዳን በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 94 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፈዋል ተባለ፡፡ ምርጫ የተባለው ወጉ እንዳይቀር ነው እንጂ አልበሽር ለብቻቸው ነው የተወዳደሩት፡፡ ዋና ዋና የአገሪቱ ተቃዋሚዎች ቀደም ብለው ነው ራሳቸውን ከምርጫው ያገለሉት፡፡  ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ አልነበረም የሚሉት ተቃዋሚዎቹ፤ ሲቪል ማህበራትና ሚዲያው በመንግስት ታፍነው እንደነበር ይናገራሉ፡፡ በነገራችን ላይ አልበሽር በ1989 ዓ.ም በመፈንቅለ መንግስት ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ይኸው ለ26 ዓመታት ሱዳንን ሲገዙ ቆይተዋል፡፡ አልበሽር በዓለም አቀፉ የጦር ፍ/ቤት የዘር ማጥፋት እንዲፈጸም በማዘዝ ተከሰው በተገኙበት እንዲያዙ ውሳኔ ተላልፎባቸው ነበር፡፡

መንግስት፤ “ዜጐቼ ለምን ይሰደዳሉ?” ብሎ ይጠይቅ!

“አሁንም እንሄዳለን፤ምንም ተስፋ የሚሰጥ ነገር የለም”
ኢህአዴግ ከስንት አንዴ ፕሮፓጋንዳው ቢቀርበትስ?

  መንግስት አይኤስ የተባለውን ጨካኝና አሸባሪ ቡድን ለማውገዝ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ እንደ አጀማመሩ አልተጠናቀቀም፡፡ (ለተቃውሞ ወጥቶ ተቃውሞ ገጥሞታል!) በሰላም የተጀመረው ተቃውሞ በረብሻና በብጥብጥ ተቋጨ፡፡ (መንግስትን መቃወም እኮ መብት ነው!) ትንሽ ቅር ያለኝ ግን ምን መሰላችሁ? ሁለት ተቃውሞዎች በአንድ ቀን፣ በአንድ ቦታ፣ መደረጋቸው ነው፡፡ እንደኔ ቢሆን ሁለቱ ተቃውሞዎች ባይደባለቁ እመርጥ ነበር (የሚያስመርጥ ሲኖር አይደል!) አንዳንዴ ተቃውሞ ፋታ አይሰጥም መሰለኝ፡፡ ተቃውሞ የነበራቸው ወገኖች የዚያኑ ዕለት መቃወሙን ግን ለምን ፈለጉት? ምናልባት ሌላ ቀን የሰልፍ ፈቃድ የሚሰጠን የለም ብለው ይሆናል (በስጋት ማለት ነው!) ወይም ደግሞ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ትላልቅ ባለስልጣናትን መስቀል አደባባይ ሲያዩ፣ መንግስትን ለመቃወም ከዚህ የተሻለ ቀን ሊኖር አይችልም ብለውም ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ዕድሉን ተጠቀሙበት ማለት ነው፡፡

ብሩንዲ ተናወጠች! ….. በቀጣይነትስ!?!

11041764_459898677512558_6207929217884897390_n11150872_459898670845892_8559125555464246976_n
ከወደ ብሩንዲ ሕዝብ ነቅሎ ተነስቷል። በአገሪቱ ሊካሄድ ጥቂት ጊዜያት በቀሩት አገራዊ ምራጫ ላይ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ራሱን በእጩነት ያቀረቡት አንባገነኑ ፔሬ ኑኩሩንዚዛን ሕዝብ በቃህ በማለት ተናንቋቸዋል። ጭንቅ ውስጥ የገባው የፔሬ አገዛዝ ከሕዝባዊ ማዕበሉ ለመትረፍ እየተወራጩና አንዳንድ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ቢሆንም ሕዝቡ እርምጃዎችን ሳይገቱት ፊት ለፊት በመጋፈጥ ጉዞውን ወደ ቤተ መንግስቱ አድርጓል።

በሁመራ አከባቢ ህወሀት እስከአሁን ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን ገድሏል

የቀድሞዋ የጎንደሬዎች ከተማ ሁመራ አሁን ደግሞ የጎንደሬዎች መቀበሪያዋ የጅምላ መጨፍጨፊያዋ ሁመራ በየቀኑ የወገን የድረሱልን የሰቆቃ ድምፅ ይሰማል ሁኖም ግን ሰሚ ጀሮን አላገኘም ።
ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በሰሜን ጎንደር ምዕራባዊ ክፍል ከአማረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ የፀዳ ክልል ለመፍጠር ከ40 ዓመታት በላይ የሰራበት ቢሆን እንዳሁኑ ለይቶለት አያውቅም ቀደም ሲል በወልቃይት በጠገዴ በትግል በበረሃ እያሉ ጀምረው ነዋሪዎችን ሌሊት ሌሊት ከቤታቸው እያፈኑ የደረሱበት ሳይታወቅ የቀሩ አያሌ ወገኖች ነበሩ ።

ምርጫ ቦርድ ኢሕአዴግ ለፌዴራል ምርጫዉን እንዳሸነፈ አረጋገጠ – የሚሊዮኖች ድምጽ

ከሁለት ሳምንታት በኋላ ምርጫ ይደረጋል። ሆኖም ከምርጫው በፊት ኢሕአዴግ እንዳሸንፈ ምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ ላይ ባስቀመጠው ሰነድ አሳወቀ።
አርባ ሰባት የሚሆኑ ድርጅቶች እንደሚካፈሉ ምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገ ሲሆን አርባ አምስት የሚሆኑት ለፌዴራል ፓርላማ ተወዳዳሪዎች አሰልፈዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

11160072_915886671787265_6445929843768954805_o10993110_915886668453932_4236053262013168927_o
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ትናንት ሚያዝያ 27/2007 ዓ.ም ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብትና ሰራተኞች ምክትል ዋና ፀኃፊ የሆኑት ሚስተር ስቲቭ ፌልድስቴይን ጨምሮ ሌሎችንም ኃላፊዎች አግኝተው ስለ ኢትዮጵያና ስለ ቀጠናው ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡

Tuesday, May 5, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ የአፍሪካ ህብረት ምርጫውን እንዳይታዘብ እንደሚፈልግ ገለጸ •የህብረቱ ታዛቢ ቡድን ፓርቲዎችን አነጋግሯል

ሰማያዊ ፓርቲ የአፍሪካ ህብረት 5ኛውን ሀገራዊ ምርጫ እንዳይታዘብ እንደሚፈልግ ለህብረቱ ታዛቢ ቡድን ገለጸ፡፡ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም በምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎችን በተናጠል በምርጫው ዙሪያ ያነጋገረ ሲሆን፣ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ቡድኑን ያነጋገሩት አቶ ወረታው ዋሴ እና አቶ እምዕላሉ ፍስሃ ህብረቱ ምርጫውን እንዳይታዘብ እንደሚፈልጉ አስረድተዋል፡፡

ህወሃት የአንድ ቤተሰብ የፖለቲካ ስብስብ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ

ህወሃት የአንድ ቤተሰብ የፖለቲካ ስብስብ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ እዩልኝ … .. ሁለቱም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሲሆኑ ሌሎችን ለአብነት ያክል የቀድሞ የትግራይ ክልል ር / መስተዳደር የነበረው ያሁኑ የደህነት ሹም አቶ ፀጋይ በረሄ እና የትግራይ ክልል አፈ ጉባዔ የሆነችው የስብሃት ነጋ ታናሽ እህት ቅዱሳን ነጋ አርከበ ዕቁባይ የዚሁ ቤተ ሰብ ቤተ ዘመድ እና የመሳሰሉት በጥቂቱ ይገኙበታል !!

ኢትዮጵያዉያን በየመን ከፍተኛ ስቃይ ውስጥነን ድረሱልን እያሉ ነው

10421433_648203905313009_8566024657772797199_n11150458_502642179888444_2469264559864257823_n11150413_459916237507061_7974566446017824762_n
በስደተኛ አቅሟ ያጠራቀመችዉን ጥሪት ለቦምብ ሚሳዬል አረር ገብራ ከአደን ዳግም ለተሰደደችዉ ኢትዮጵያዊት ጦርነቱ ከፋ፤ «የሚጠጣ ዉሐ ጠፋ፤ ወይም ተመረዘ»-ከሚለዉ ወሬ ያለፈ የጦርነቱ ሰበብ ምክንያት፤ የመርዙ ደረጃ፤ የመርዙ ምንነት፤ የመራዡ ማንነትም ግልፅ አይደለም።
ኢትዮጵያዉን ስደተኞች ደቡብ አፍሪቃ ላይ እሳት ተለቀቀባቸዉ።ነደዱሞቱ።ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ ሰምጠዉ አለቁ።ሊቢያ ላይ ታረዱ።እስራኤል ዉስጥ ዜጋም ሆነዉ ይዋረዱይገለሉአሁን ደግሞ ይደበደባሉ።የመን ዉስጥ በባዘነጥይትሚሳዬል ተገደሉ።
የተረፉት በምግብ፤ ዉሐ፤ መጠለያ እጦት እየተሰቃዩ እንበለ ተስፋ ቀንያሳላሉ።

ምርጫ ቦርድ ኢሕአዴግ ለፌዴራል ምርጫዉን እንዳሸነፈ አረጋገጠ – የሚሊዮኖች ድምጽ

ከሁለት ሳምንታት በኋላ ምርጫ ይደረጋል። ሆኖም ከምርጫው በፊት ኢሕአዴግ እንዳሸንፈ ምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ ላይ ባስቀመጠው ሰነድ አሳወቀ።
አርባ ሰባት የሚሆኑ ድርጅቶች እንደሚካፈሉ ምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገ ሲሆን አርባ አምስት የሚሆኑት ለፌዴራል ፓርላማ ተወዳዳሪዎች አሰልፈዋል።
መንግስት ለመቆጣጠር አንድ ድርጅት 274 የፓርላማ መቀመጫዎችን ማሸነፍ ይጠበቅበታል። ምርጫ ቦርድ ባሰፈረው ሪፖርት መሰረት፣ ኢሕአዴግ ለ501 የፓርላማ መቀመጫዎች ተወዳዳሪዎች ያሰለፈ ሲሆን (በደቡብ ክልል፣ በአማራዉ ክልል፣ በትግራይ እና በአዲስ አበባ በሙሉ) ፣ በሌሎች ክልሎችም የራሱ አጋር ደርጅቶች በስፋት እንዲወዳደሩ አድርጓል። (በነገራችን ላይ መድረክ በአማራው ክልል ዜሮ ተወዳዳሪዎችን ነው ያሰለፈው)

በመተማ ከተማ ሕዝቡና የወያኔ ፖሊስ ተጋጩ

ዛሬ ጥዋት Pow and medic 3_xlarge
በመተማ ከተማ የአካባቢው ባለስልጣናት የከተማይቱን ኑዋሪዎች ህገወጥ ቤት ሰርታቹሃል በማለት ያለምንም ማስጠንቀቂያ በተኙበት አፍራሽግብረ
ሀይሉ ቤታቸውን ዘለው
 በዶዘር ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ በእንቅልፍ ላይ የነበሩ ነዋርዎች በፍርስራሽ ውስጥ ተቀብረው ሞተውል ይህም ያከተለው የከተማይቱ ኑዋሪዎች ቁጣ ወደተቃውሞ ተለውጦ  በወያኔ ፖሊስ  እና በከተማይቱ ኑዋሪዎች መካከል ለ1:30 ያክል የፈጀውጊያ ተካይዳል። በአውደ ውጊውም ከአምስት በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ60 በላይ የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸውን የአን እማኞች የገለፁ ሲሆን እስካሁንም ግጭቱም እንዳልበረደ ተነግራል።

Sunday, May 3, 2015

በአይሲስ ላይ ኢትዮጵያ የሃይል እርምጃ መውሰድ አለባት ያሉ የሠራዊቱ አዛዦች ታሰሩ

ethiopians isis
ሊቢያ ውስጥ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግፍ የተሞላበት ግድያ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት በማለት የጠየቁ የሰራዊት አዛዦች እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ::

ሶፊያን አህመድ በዋሽንግተን ዲሲ ተዋረደ * የወያኔ ተላላኪዎች በዲያስፖራው ውሻ መሆናቸውን ቀጥለዋል (Video)

ሶፊያን አህመድ በዋሽንግተን ዲሲ ተዋረደ * የወያኔ ተላላኪዎች በዲያስፖራው ውሻ መሆናቸውን ቀጥለዋል
በውጭ ያለው ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የወያኔ ተላላኪ ባለስልጣናትን እና የወያኔ ባለስልጣናትን እንደውሻ አሳፍሮ ወደ መጡበት መመለሱን ቀጥሎበታል:: መለስ ዜናዊ.. አቦይ ስብሃት.. ሬድዋን ሁሴን… ህላዊ ዮሴፍ.. ቴዎድሮስ አድሃኖም…

Friday, May 1, 2015

አሜሪካ አይሲስን ለምን ፈጠረችው? – ክንፉ አሰፋ

ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሄራዊ የሃዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ። እንደ ግብጽ አጀማመር ቢሆን የሊብያው አይሲስ ክንፍ ድሮ-ድሮ ከምድረ-ገጽ ይጠፋ ነበር። ግና አልሆነም። አሜሪካ ጣልቃ ገባች። ግብጽ የአሜሪካን “ጸረ-ሽብር” ዘመቻ በማገዝዋ ምስጋና ማግኘት ሲገባት በተቃራኒው ተወገዘች።   ከጥቂት ድብደባ በኋላ ፔንታጎን ግብጽን አስጠነቀቀ[0]።