Wednesday, May 13, 2015

ሳሞራ የኑስ በዋሽንግተን ዲሲ እጅግ ተዋረዱ * ተቃውሞው ቀጥሏል

በዋሽንግተን ዲሲ ማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ድንገት የተገኙት የወያኔው መንግስት መከላከያ ሚኒስተር ጄነራል ሳሞራ የኑስ በኢትዮጵያዊያኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው ውርደትን መከናነባቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ:: በአንድ ለሊት አዳር 12 ሺህ 700 ብር በሚከፈልበት በማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ያረፉት ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከዋሽንግተን ዲሲ ግብረሃይል ወጣቶች ጋር ፍጥጫ ገጥመው ከፍተኛ የሆነ ግብግብ ተፈጥሯል:: አካባቢው በዲሲ ፖሊሶች የታጠረ ሲሆን ሳሞራም ካረፈበት ከዚህ ሆቴል ሊወጣ እንዳልቻለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል::
ኢትዮጵያውያኑ “ኢትዮጵያውያንን የሚያሰቃይ ወንጀለኛ ለፍርድ ይቅረብ” በሚል ሳሞራ ላይ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው:: በሽንግተን ዲሲ መጥተው በኢትዮጵያውያኑ ውርደትን ከተናነቡ የወያኔ ተላላኪ ባለስልጣናት ውስጥ ስብሃት ነጋ; ሬድዋን ሁሴን; ሶፊያን አህመድና ሌሎችም ይገኙበታል:: ግብግቡ አሁንም የቀጠለ ሲሆን የደረስንበትን መረጃ እናሳውቃችኋለን:: 

No comments:

Post a Comment