Monday, May 11, 2015

የሰማያዊ ዘጠና ሁለት ሚሊዮን ወያኔን አስጨንቆታል

ሪፖርተር እንዳስነበበን የሰማያዊዎቹ በጀት ኢህአዴግን ጭንቀት ላይ ጥሎታል። ዋ….አይ ከየታባታቸው አመጡት፤ ብለው ግራ ግብት ያላቸው አቶ ሬድዋን ”ኮንሰርት አላዘጋጁ፣ ቱጃሮች አይደሉ፣ ልማታዊ ባለሃብቶች አልደገፏቸው” ሲሉ ጭንቀታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል። አቶ ሬድዋን ተጨንቀውም አላባሩ ይሄንን ጉዳይ የሚመለከተው አካል እንዲመርምር አዘናል አይነትም ብለዋል። (እኛ ግን እነርሱ ሃያ ሶስት ሚሊዮን ሲያወጡ የአባይን መዋጮ ለቅስቀሳ አዞሩት እንዴ ብለን አልመረመርንም!) የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እንደተናገሩት ፓርቲያችን ሁለት መቶ እጮዎች በገዢው ፓርቲ ጉልበተኝነት ተሰርዘውበት እንጂ ኢህአዴግን ልናሳርፈው ጠንክረን እየሰራን ነው ብለዋል። (በሾርኔ ኢህአዴግን ለማሳረፍ ዘጠና ሁለት ሚሊዮን ምን አላት አይነት ነው!)

ይህ በእንዲህ እንዳለ መድረክ በተለይ ኦሮሚያ ላይ አምርሮ ይዟል። ዶክተር መረራ ዘንድሮ ኦህዴድን ሳጠራ ወንበር ላይ አስቀምጠው የፓርላማውን መቀመጫ ሳይወስዱበት አይቀርም። ትግራይ ላይም አረና/ መድረክ ህውሃትን የአመት ፈቃት ሊያሰጣት እየጣረ ነው! የሪፖርተር መስፈንጠሪያ ይሄውላችሁ!http://www.ethiopianreporter.com/…/9686-%E1%8B%A8%E1%88%B0%…

No comments:

Post a Comment