Tuesday, November 27, 2012

ሁሌም ለብሔራዊ ደኅንነታችን መረጋገጥ በንቃት ዘብ እንቁም!



በእረፍት ጊዜያችን ወይም በሥራ አጋጣሚ በእግር ወይም በተሽከርካሪ ስንንቀሳቀስ በከተማችን ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ኤምባሲዎችን እናስተውላለን፡፡ በተለይ ደግሞ የኃያላኑ አገሮች ኤምባሲዎች ጥበቃና ፀጥታ የሚነግረን አለው፡፡ ወደ ሽሮሜዳ ስትሄዱ እጅግ በሚገርም ሁኔታ የተገነባው የአሜሪካ ኤምባሲ በሩቅ ርቀት የተሠሩለት የኮንክሪት መከላከያዎች ድንገተኛ ጥቃቶችን ታሳቢ ያደረጉ ይመስላሉ፡፡ በሾላ መስመር የአንግሊዝ ኤምባሲም እንዲሁ የኮንክሪት መከላከያዎች የተበጁለት ነው፡፡ በሌሎች ሥፍራዎችም ስትሄዱ የዓለም አቀፍ ተቋማት ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው ትረዳላችሁ፡፡ ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ፖለቲካ ምክንያት ሁሌም ቅድሚያ የሚሰጠው የፀጥታና የደኅንነት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ የተጠናከረ ጥበቃ የሚያስገነዝበን በተለይ ኃያላን አገሮች ለብሔራዊ ደኅንነታቸው ምን ያህል ጥንቁቅ መሆናቸውን ነው፡፡

Saturday, November 24, 2012

ታሪክ ለመስራት ታሪክን ማጥፋት ተገቢ አይደለም !!


ይህ የባቡር መሥመር መሰራት የአቡነ ጴጥሮስንና የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት ማፍረስ ምን ይባላል ?
 ኢትዮጵያን እናሳድጋለን ስንል ያሳደጓትን እየዘነጋንና መታሰቢያቸውን እያፈረስን መሆን የለበትም፡፡ <<በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ>>  አረለ የሚለው ተረቱ እውነት ነው፡፡ የምናመጣው አዲስ ነገር ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም፡፡  ወደድንም ጠላንም ይህች ሀገር የታሪክና የቅርስ ሀገር ናት፡፡ ታሪኳን ማፍረስ አንችልም !! ታሪክ ይፈርዳል !!

ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ እንዳትኖር ማን አደረጋት ??


«…ሀገራዊ ታሪካችንንም ሆነ ፖለቲካዊ እውነታዎችን በግልፅ ፍርጥርጥ አድርገን የመናገር ችግር አለብን፡፡ አንድ የፖለቲካ ሁኔታ ወደኋላ መለስ ብለን አንስተን ስንወያይ እውነታውን ለመቀበል ምን ያህል ዝግጁ ነን የሚለው መታየት ያለበት ይመስለናል፡፡ እኔ መሰረታዊ ችግር ነው የምለው ይህንን ነው…» በምድረ ኢትዮጵያ ስለዲሞክራሲ ሲነገር ሲደሶከር ሲዘመርና ሲተነተን ከአራት አስርት አመታት በላይ መቆጠሩ እውነትነው፡፡ ነገር ግን የተነገረውንና የታወቀውን ያህል የዲሞክራሲ ዘር ተዘርቶ ፍሬ ሲያፈራ አልታየም፡፡ ወይም ሊታይ አልቻለም፡፡

Wednesday, November 21, 2012

ልዩነት በድምፅ ብቻ ይፈጠር ዘንድ ለአገሬ ተመኘሁ።

አንድ ወዳጄን ሰለ አሜረካ ምርጫ ጠየቁት ‹‹ለመሆኑ ኦባማ በማሸነፋቸው ምን ተሰማህ?›› አልኩት። ‹‹‘እናቴን ያገባ ሁሉም አባቴ ነው’ ሲባል አልሰማህም? ማንም ቢመረጥ ከብሔሪዊ ጥቅማችን ጋር የሚሄድ ፖሊሲ ካለው ይመቸኛል፤›› አለኝ። በዝምታ ትንሽ በየራሳችን ዓለም ሰጠምን። እንዲህ በፍጥነትና በቅልጥፍና ግልጽ የሆነ ምርጫ ለማድረግ ስንት ዓመት ይፈጅብን ይሆን? እያልን ራሳችንን አስጨነቅነው። ‹‹ለመሆኑ ጓደኛዬ ኦባማ ካሸነፉ በኋላ የተናገሩትን ሰምተሃል?›› አለኝ። ‹‹በምን አባቴ የቋንቋ ችሎታ እሰማለሁ ብለህ ነው? አዳሜ የተሰባበረ እንግሊዝኛ ላያችን ላይ እየለቀቀብን የምንችለው እንኳ ይጠፋብን ጀመር፤›› ስለው ከት ብሎ ሳቀ። ሳቁን ሲያባራ፣ ‹‹ምን አሉ መሰለህ? ‘ዛሬ ዋናው ነገር ኦባማን ወይንም ሚት ሮምኒን መምረጣችሁ ሳይሆን በድምፃችሁ ልዩነት መፍጠራችሁ ነው’ ያሉት ንግግር ውስጤ ቀረ፤›› ካለኝ በኋላ ትንሽ አሰብ አድርጎ፣ ‹‹ሥልጣን የሕዝብነቱ ተረጋግጦ በድምፃችን ልዩነት ለማምጣት የዲሞክራሲ ጉዞ ምንጊዜም ወሳኝ ነው፤›› ሲለኝ ተቀበልኩት። ልዩነት በድምፅ ብቻ ይፈጠር ዘንድ ለአገሬ ተመኘሁ። በመፈክር ሳይሆን በተግባር የሚረጋገጥ ዲሞክራሲ ማን ይጠላል? ከመፈክር ይልቅ ዲሞክራሲ ናፈቀኝ፡፡   

ዲሞክራሲ! ይበልጣል ከመፈክር !!

ሰላም! ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ላላችሁ በሙሉ። አንድ ወዳጄ ይኼንን የአቅጣጫ ሰላምታ እንደማይወደው አጫውቻችሁ አውቃለሁ? ለምንድን ነው ስለው ‹‹የሰው ልጅ እንደ ንፋስ በአቅጣጫ ላይ ተመሥርቶ ሰላምታ ሲለዋወጥ እበሽቃለሁ፤›› አይለኝ መሰላችሁ? የዘንድሮን ሰው የሚያበሽቀውን ነገር ብዛት ቆጥረን መጨረስ አቃተን! ግን ግን ንፋስን ለምንከተል የዘመኑ ሰዎች ይህ ሰላምታ ካልተሰጠ ለማን ይሰጥ? ለራስ ብቻ የሚሮጥበት ዘመን መሆኑን ካየን ዘንዳ ከዚህ ሌላ ምን ይባላል? አንዳችን ያለ ሌላችን መኖር እንደማንችል እያወቅነው ‘እኔ’ን ብቻ ላማከለ ነፍስ መሮጣችን ይገርመኛል። የሚገርማችሁ ደግሞ አባባልን እንኳ መርጠን አለመጠቀማችን ነው። ለምሳሌ ‹‹ዘመኑ የውድድር ነው›› የሚለውን አባባል ለተቀደሰ ይሁን ለረከሰ ተግባር እንደምንጠቀምበት ሳንለይ ለሁለቱም እንዳሻን እንገለገልበታለን። አሁንማ ሙሰኛውም በሰሞነኛ ተቆጣጣሪዎች ሲያላግጥ ‘ዘመኑ የውድድር ነው’ ማለት ጀምሯል አሉ። ‹‹ውድድሩ ጤናማ ዕድገት ለማስመዝገብ ነው? ወይስ እንደተለመደው ጠልፎ ለመጣል ነው?›› 

Monday, November 12, 2012

ለሕዝባችን በመቆም ሕዝብ ይዳኘን !!!

                           ብዙ ጊዜ ለአፍሪካ ወይም ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ አሜሪካ ምሳሌ መሆን የለባትም የሚሉ ክርክሮች ይሰማሉ፡፡ አሜሪካ የተለያዩ ሕዝቦች፣ ባህሎች፣ ዕምነቶችና አመለካከቶች ያሉባት ትልቅ አገር ስትሆን በበርካታ ምክንያቶች ከአፍሪካ ወይም ደግሞ ከኢትዮጵያ ትለያለች የሚል መከራከሪያ አለ፡፡ አፍሪካ አኅጉራችንን ለጊዜው እንተዋትና ኢትዮጵያ ላይ በማተኮር ይኼንን መከራከሪያ እንሞግት፡፡ ኢትዮጵያ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ቋንቋዎች፣ ዕምነቶች፣ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች ያሉባት አገር ብትሆንም ለዓለም ምሳሌ መሆን የሚችል መቻቻል ያለባት አገር መሆኗን ማስታወስ የግድ ይለናል፡፡ እንደ አሜሪካ ከተለያዩ አገሮችና አኅጉራት የፈለሱ ሕዝቦች ባይኖሯትም፣ የራሳቸው ማንነት ያላቸው ነገር ግን ለዘመናት በኢትዮጵያዊነታቸው ታውቀው የሚኖሩ የተለያዩ ሕዝቦች አሏት፡፡ እንደ አሜሪካ የተለያዩ አመለካከት፣ ፍላጎት፣ ዕምነትና የመሳሰሉት መለያዎች ያሉዋቸው ብሔር ብሔረሰቦቻችን በሰላምና በመቻቻል መኖርን ለረጅም ዓመታት ካዳበሩ እንደምን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ማራመድ ያቅታቸዋል?

Thursday, November 8, 2012

ኢትዮጵያውያን ለለውጥ አንድ ስንሆን ማንም አያቆመንም፡፡

  


     የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት፣ የሰው ዘር መገኛ፣ በውጭ ወራሪዎች ሳትደፈር ነፃነቷን አስጠብቃ በሉዓላዊነቷ ፀንታ ች፣ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን በልዩነት ውስጥ የፀና አንድነት ፈጥራ ች፤ ኢትዮጵያ። አገራችን ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ የምትታወቅባቸው በርካታ አዎንታዊ ገፅታን የተላበሰች ብትሆንም ውን ዘመ በነበረችበት ሁኔታ በአሉታዊ ገፅታ ስትነሳ እየለች ተገኛለች

Wednesday, November 7, 2012

ህዝብን በህትመት ነፃነት ማፈን አይቻልም !!!

                  በፍራቻ የሚነጥፍ ብዕርም ሆነ በአፈና የሚንበረከክ የትግል ማንነት የለንም!ኢህአዴግ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስቴር አስቀምጧል፡፡ እንደ  አለመታደል ሆኖ ግን አዲሱም ሰው የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር ዱካ የሚከተሉ፣ መለስ የጀመሩትን አፈና የሚያስቀጥሉ፣በመለስ የሙት መንፈስ የሚመሩ በመሆናቸው አሁንም በኢትዮጵያችን አንጻራዊ የሚባል እንኳ ለውጥ ለማየት አልቻልንም፡፡በተለይም “አዲሱ” መንግስት ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጦችን ከአደባባይ በማጥፋት የሀገሪቱን የፕሬስ ነፃነት ጉዞ ክፉኛ ወደኋላ መመለሱ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚያስከትል መሆኑን ከግምት ያስገባ አይደለም፡፡

Thursday, November 1, 2012

ኧረ የፍትህ ያለህ !! ያለ ነፃነት መኖር በቃኝ! በቃን መኖር ሰለቸን ! ለውጥ ያስፈልጋል!





             
   በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር እና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ዜጎች በእኩልነት ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያስቡ፣ የሚናገሩ፣የሚፅፉና የሚቆረቆሩ በጠቅላላው ለእነዚህ ፅንስ ሐሳቦች ዘብ የሚቆሙ በሙሉ የስርዓቱ ጠላቶች ተደርገው በመቆጠር ላይ ናቸው::
   ለአገሪቱ አንድነትና ሉአላዊነት ብልፅግና በጣም ከሚቆጠሩ መሪዎቿና የፓርቲአቸው ጠባብ ጎሰኛ ፖሊሲ የተለየ የሚያስቡ ዜጎችና ቡድኖች ሁሉ ጠላትና ሽብርተኞች ወይንም አሽባሪዎች ወይም በዘመኑ አባባል ጽንፈኛ ተደርገው ይቆጠራሉ።