አንድ ወዳጄን ሰለ አሜረካ ምርጫ ጠየቁት ‹‹ለመሆኑ ኦባማ በማሸነፋቸው ምን ተሰማህ?›› አልኩት። ‹‹‘እናቴን ያገባ ሁሉም አባቴ ነው’ ሲባል አልሰማህም? ማንም ቢመረጥ ከብሔሪዊ ጥቅማችን ጋር የሚሄድ ፖሊሲ ካለው ይመቸኛል፤›› አለኝ። በዝምታ ትንሽ በየራሳችን ዓለም ሰጠምን። እንዲህ በፍጥነትና በቅልጥፍና ግልጽ የሆነ ምርጫ ለማድረግ ስንት ዓመት ይፈጅብን ይሆን? እያልን ራሳችንን አስጨነቅነው። ‹‹ለመሆኑ ጓደኛዬ ኦባማ ካሸነፉ በኋላ የተናገሩትን ሰምተሃል?›› አለኝ። ‹‹በምን አባቴ የቋንቋ ችሎታ እሰማለሁ ብለህ ነው? አዳሜ የተሰባበረ እንግሊዝኛ ላያችን ላይ እየለቀቀብን የምንችለው እንኳ ይጠፋብን ጀመር፤›› ስለው ከት ብሎ ሳቀ። ሳቁን ሲያባራ፣ ‹‹ምን አሉ መሰለህ? ‘ዛሬ ዋናው ነገር ኦባማን ወይንም ሚት ሮምኒን መምረጣችሁ ሳይሆን በድምፃችሁ ልዩነት መፍጠራችሁ ነው’ ያሉት ንግግር ውስጤ ቀረ፤›› ካለኝ በኋላ ትንሽ አሰብ አድርጎ፣ ‹‹ሥልጣን የሕዝብነቱ ተረጋግጦ በድምፃችን ልዩነት ለማምጣት የዲሞክራሲ ጉዞ ምንጊዜም ወሳኝ ነው፤›› ሲለኝ ተቀበልኩት። ልዩነት በድምፅ ብቻ ይፈጠር ዘንድ ለአገሬ ተመኘሁ። በመፈክር ሳይሆን በተግባር የሚረጋገጥ ዲሞክራሲ ማን ይጠላል? ከመፈክር ይልቅ ዲሞክራሲ ናፈቀኝ፡፡
No comments:
Post a Comment