Monday, December 31, 2012

የተቃዋሚ 33 የፓለቲካ ድርጅቶች ያቆቆሙት ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ሊከሰው መሆኑን አስታወቀ


ታህሳስ 22 2005 ዓ ም
 የምርጫ  ቦርድ ከፍተኛ ሀላፊ የኢህአዴግ አባል ሆነው ለክልልምምክር ቤት አባልነት ምርጫ መወዳደራቸውንም አጋልጦል።
ጊዜዊ ኮሚቴው ለምርጫ ቦርድ ባቀረበው 18 ጥያቄዎች ማስረጃ ያላቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ምርጫ ቦርድን ለፓርላማ አፈጉባኤ እንደሚከስ አስታውቆል።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአስተባባሪ ኮሚቴው የቀረቡት 18 ጥያቄዎች ማስረጃ የላቸውም ብሎ ጥያቄዎቹን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ነው ወሳኝ ያላቸው ማስረጃዎች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ኮሚቴው ይፋ ያደረገው።

ወያኔ የቆለፈውን ቁልፍ መልሶ እራሱን ይውጥዋል።


* በሰለጠነ አለም ውስጥ ብንሆንም በጨቋኝና ተጨቋኝ ስርአት ውስጥ ነን 
* እኛ የምንለው በትክክል እንወዳደር ነው፤ ያንን ደግሞ ወያኔ አልፈቀደውም 

* አገሪቱ ውስጥ ትናንሽ አምባገነኖች እየተፈጠሩ ነው፤ ሲስተም መዘርጋት አለበት                                                   
                                   ከሰብኣዊ 
               ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
                                    

ይድረስ ለወያኔ !!

ወያኔና ፌስቡክ

የወያኔ ካድሬዎች በተለይ ሚዲያው አካባቢ የተሰማሩቱ እንደ 
ፌስቡክ “አቢዩዝ” ያደረጉት የቴክኖሎጂ ውጤት አለ ፡፡ 
ፌስቡክን አያውቁትም ግን ይፈሩታል፣ ይሸሹታል፣ 
ተጠቃሚዎቹንም “አብዮተኞች” በሚል ድፍርስ ስም ይጠራሉ፡፡
 ስለዚህ ወያኔ በፌስቡክ አማካኝነት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም
 መቶ በመቶ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡  ወያኔ የፌስቡክንና የኢትዮጵያን
 ዝምድና አያውቅም። በዚህም የተነሳ የፌስቡክ አብዮት ይነሳብኛል
 ብሎ ሰግቶ ነበር፡፡ (የምዕራብ አፍሪካ ህዝባዊ አብዮት የተቀሰቀሰ
 ሰሞን) በማህበራዊ  ድረ-ገጾች ላይ በጃሚንግ ዘመተ፡፡

የብሔራዊ ደኅንነት ዋስትና ያስፈልጋል !



በእረፍት ጊዜያችን ወይም በሥራ አጋጣሚ በእግር ወይም በተሽከርካሪ ስንንቀሳቀስ በከተማችን ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ኤምባሲዎችን እናስተውላለን፡፡ በተለይ ደግሞ የኃያላኑ አገሮች ኤምባሲዎች ጥበቃና ፀጥታ የሚነግረን አለው፡፡ ወደ ሽሮሜዳ ስትሄዱ እጅግ በሚገርም ሁኔታ የተገነባው የአሜሪካ ኤምባሲ በሩቅ ርቀት የተሠሩለት የኮንክሪት መከላከያዎች ድንገተኛ ጥቃቶችን ታሳቢ ያደረጉ ይመስላሉ፡፡ በሾላ መስመር የአንግሊዝ ኤምባሲም እንዲሁ የኮንክሪት መከላከያዎች የተበጁለት ነው፡፡ በሌሎች ሥፍራዎችም ስትሄዱ የዓለም አቀፍ ተቋማት ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው ትረዳላችሁ፡፡ ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ፖለቲካ ምክንያት ሁሌም ቅድሚያ የሚሰጠው የፀጥታና የደኅንነት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ የተጠናከረ ጥበቃ የሚያስገነዝበን በተለይ ኃያላን አገሮች ለብሔራዊ ደኅንነታቸው ምን ያህል ጥንቁቅ መሆናቸውን ነው፡፡

Saturday, December 29, 2012

መንግሰት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ

ታህሳስ19 ቀን 2005 ዓ/ም
አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡ብ/ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት አንዳንድ አስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው ዋንኛ ስራ አለመሆኑን፤ ነገርግን በመርህ ደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡“ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም የመገንባት ስራ እንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ ከዘር ፣ ከሽብርተኝነት ፣ ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች
ወደ ኢትዮጽያ እንዳይገቡ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እስኪ ይሁና!

ጎበዝ በዚህች መከረኛ አገራችን የመጣ የሄደው በሕዝብ ስም ራሱን ሲያዋድድ አልኖረምና ነው የእኔ የሚገርማችሁ? ወደን ነው እንዴ ኢቲቪን የተቀየምነው? አንድ የልማት ዜና አንድ ወር እየተረከልን ለሌላ ሥራ ከማነሳሳት ይልቅ እያኩራራ ስላሰነፈን ጭምር እኮ ነው። አቤት! ስንቱ በራሱ ዓለም ትልቅ ነኝ ሲል ወደቀ መሰላችሁ? እኔማ ስንቱን እታዘበዋለሁ ይብላኝ እንጂ ማስተዋል ለተሳነው።

Thursday, December 27, 2012

መተካካት አሉታዊ ጎንም አለው ።

የ‘ቦተሊካ’ ነገር ካነሳን አይቀር ይቺን ስሙኝማ…ትንሹ ልጅ አባቱን “አባዬ፣ ፖለቲካ ማለት ምን ማለት ነው?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡ አባትዬውም እንዲህ ሲል ይመልስለታል፡፡
“የእኔ ልጅ፣ ይህንን ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው፡፡ ግን እስቲ ልሞክር፡፡ ለምሳሌ ሠርቼ ገንዘብ የማመጣው እኔ ስለሆንኩ ካፒታሊዝም ነኝ እንበል፣ እናትህ የገንዘቡን ወጪ ስለምትቆጣጣር መንግሥት ነች እንበል፣ የእኛ ሀላፊነት ያንተን ፍላጎት መጠበቅ ስለሆነ አንተን ደግሞ ህዝብ ነህ እንበል፣ ሞግዚቷ የሠራተኛው መደብ ነች እንበል፣ ትንሹ ወንድምህን ደግሞ መጪው ጊዜ እንበለው፡፡ እስቲ ይሄን አስብና ስሜት ይሰጥ እንደሁ ተመልከት…” ይለዋል፡፡ ልጁ አባቱ ስለነገረው ነገር እያሰበ ሄደ፡፡ ያን ዕለት ሌሊት ትንሽ ወንድሙ ሲያለቅስ ሰማና ተነስቶ ወደ ክፍሉ ሄደ፡፡ ትንሹ ልጅ ሽንቱን ሸንቶ ስለነበር ዳይፐሩ በጣም እርሶ ያያል፡፡ ወደ ወላጆቹ ክፍል ሲሄድ እናቱ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷታል፡፡ 

Wednesday, December 26, 2012

አቶ ኃይለማርያም ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል ሲባል ሰምተዋላ።


ምላስ አጥንት ቢኖረው ታድያ ቀጨ..ጨ..ጨ ሲል በሰማነው ነበር ሲዋሹ። አቤት ባለቤታቸው እንዴት ይሳቀቁ ይሆን? እሳቸውም ከአንድ ውሀ ካልተቀዱ እና ቀዳማይቱን መምሰል ካልፈለጉ ተሳቅቀው ማለቃቸው ነው። ውይ …. የሰው ዐይንስ እንዴት አያለሁ ይሉ ነበር። ደግነቱ ቤተመንግሥት ነው ያሉት ማየትም መስማትም ከማይችሉበት ድብቅ ስፍራ ብለን እንለፈውና ነጥቦቹን እንመልከት። አለዚያማ መጻፋችንስ ምን ዋጋ አለው። ክቡርነትዎ ግን ድንገት ተፈቅዶልዎ ይህንን ካነበቡ የፕሮፌሰር አልማርያምን ምክር አይርሱ። አለም እንደትስቅሎት እየሳቁ ይዋሹ እንጂ አለም እንዲስቅቦት እየሟሸሹ አይዋሹ ቂ..ቂ….ቂ……

Tuesday, December 25, 2012

Ethiopia 2012: Human Rights and Government Wrongs


It was a repetition of 2007, 2006, 2005, 2004... Everyday millions of Ethiopians woke up only to find themselves trapped in a time loop where their lives replayed like a broken record. Each "new" day is the same as the one before it: Repression, intimidation, corruption, incarceration, deception, brutalization and human rights violation… They have no idea how to get out of this awful cycle of misery, agony, despair and tribulation.
So, they pray and pray and pray and pray... for deliverance from Evil!

Does bread (teff) cost more today than it did in 2008…, a year ago? Cooking oil, produce, basic staples, beef, poultry, housing, water, electricity, household fuel, gasoline...?
Are there more poor people in Ethiopia today than there were in 2008? More hunger, homelessness, unemployment, less health care, fewer educational opportunities for young people?

የኢትዮጵያ ሰራዊት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ከሚደረጉ ህዝባዊ ትግሎች ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ ቀረበ !


በህውሀት የብቸኝነት እዝ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ከሚደረጉ ህዝባዊ ትግሎች ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ ቀረበ

ታህሳስ አስራ አምስት ቀን 2005 ዓ ም
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የትግል አቅጣጫውንና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የደህንነት ሀይሎች ለመንግስት ህዝብን የመጨቆኛ መሳሪያ መሆናቸውን አቁመው ከህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፎል::

Monday, December 24, 2012

ኢትዮጵያ ላይ ላዩን ስትታይ፤ የተረጋጋች ሰላማዊ አገር ትመስላለች።

                       ክፍል ሁለት
የአፈና ፕሮፓጋንዳ ለሃይማኖት አክራሪነት ያመቻል
የአገራችን የሃይማኖት ተቋማትና ቡድኖች፣ ከአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር በጥብቅ የተሳሰሩ ናቸው። ለዚህም ነው፤ የፖለቲካ ለውጥና አለመረጋጋት በሚፈጠርበት ወቅት፤ በሃይማኖት ተቋማትና ቡድኖች ውስጥም የተለያዩ ቀውሶችና አዳዲስ እንቅስቃሴቶች የሚቀጣጠሉት። ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ከመነከሩም በተጨማሪ አወዛጋቢ ሹም ሽር እንደተካሄደበት ይታወሳል። በየአካባቢው ግጭት፣ እስርና ግድያ ሲፈጠሩ መቆየታቸውም አይዘነጋም። ከስልጣን የተሻሩት ፓትሪያርክ ከአገር ወጥተው በአሜሪካ ከሌሎች የሃይማኖት ተቋም መሪዎች ጋር ስደተኛ ሲኖዶስ አቋቁመዋል፤ ጳጳሳትን ሾመዋል። ውዝግቡ ለ20 አመታት መፍትሄ ባለማግኘቱ እርቅ አልወረደም። የአገር ቤቱ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ባለፈው ነሃሴ ወር ህይወታቸው ቢያልፍም፣ እስካሁን ሲኖዶሱ አዲስ ፓትሪያርክ ሳይመርጥ ወራት ተቆጥረዋል። 
ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ ጀምሮ ከውዝግብ ያላመለጠው የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትም እንዲሁ፣ በየጊዜው አወዛጋቢ በርካታ ሹም ሽሮችን እንዳካሄደ፣ ከዚሁም ጋር በየጊዜ ግጭት፣ እስር፣ ግድያ እንደተከሰተ ይታወቃል። የካቲት 1987 ዓ.ም በአዲስ አበባ የዘጠኝ ሕይወት ያለፈበትን ግጭት መጥቀስ ይቻላል። የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በዘንድሮው ምርጫም ከውዝግብ አልዳነም። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች ግጭቶች ተከስተዋል። የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያናት ውስጥ የፖለቲካ መልክ ያላቸው እንቅስቃሴዎች አነስተኛ ቢመስሉም፤ ከፖለቲካው አየር ጋር በውዝግብና በክፍፍል እንደሚታመሱ፣ ኢህአዴግ ስልጣን በያዘበት ወቅት ታይቷል። 

“የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል” የሚሉ ምእመናን በሙሉ።

አንቀጽ( 11) 3 መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም !ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም !
<<ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት እርቅና ሰላም ይቅደም>>በሚል መሪ ሀሳብ የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በመጪው እሁድ ከቅዳሴ በሁዋላ የተቃውሞ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ ቀረበ።
ደጀ ሰላም እንደዘገበው ላለፉት 20 ዓመታት በውግዘት የተለያዩ አባቶች አንድ እንዲሆኑ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ አስተዳደርና አንድ ቅ/ሲኖዶስ እንዲኖር ለማድረግ ሲካሄድ የሰነበተው የእርቀ-ሰላም ሂደት በመልካም ውጤት ሊጠናቀቅ ጫፍ ላይ በደረሰበት ጊዜ፤ የታየውን የተስፋ ጭላንጭል በሚያዳፍን መልኩ በጥቂት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ግፊት 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም “አስመራጭ ኮሚቴ” ተቋቁሟል።

Saturday, December 22, 2012

ኢትዮጵያ ላይ ላዩን ስትታይ፤ የተረጋጋች ሰላማዊ አገር ትመስላለች።

                                     ክፍል አንድ
ከመስረታዊው ጥያቄ የምንነሳ ከሆነ ግን፤ ለማሰብ የመፈለግና ያለመፈለግ ጉዳይ ካልሆነ በቀር የፓለቲካ ነገር እጅግ በጣም ቀላል ነው። 
“እያንዳንዱ ሰው፣ በራሱ ሃሳብና ውሳኔ፣ በራሱ ፈቃድና ምርጫ፣ የራሱን ሕይወት የመምራት ነፃነት ሊኖረው ይገባል ወይስ አይገባም?” ...ይሄው ነው ዋናው የፖለቲካ ጥያቄ። ለጥያቄው የምንሰጠው ምላሽ ደግሞ፣ ጠቅላላ የፖለቲካ አቋማችንን ይወስናል። ሌሎቹ የፖለቲካ አጀንዳዎች... መርሆችና ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂና ህጎች በመሉ ከዚህ ጥያቄ ዝርዝርና ምንዝር ናቸው። ጥያቄውን ገልብጠን ልናየው እንችላለን። “የሌሎችን ሕይወት እንዳሻው የማዘዝ ስልጣን የያዘ አካል መኖር አለበት ወይስ የለበትም?”... የፖለቲካ መሰረታዊ ጥያቄ የዚህን ያህል ቀላል ነው። ጥያቄው፣ ጥቅም የሌለው ጊዜ ማሳለፊያ ወይም ጊዜ ማጥፊያ እንደሆነ አድርገን የምንቆጥረው ከሆነ፤ ጥርት አድርገን ለማሰብ አለመፈላጋችንን ያመለክታል። ራሳችንን ለመሸወድ ስንፈልግ ነው፤ ጥያቄውን የምናጣጥለው። አመቺ መስሎ ሲታየንማ፤ “መብቴ ነው፤ ንብረቴ ነው፤ ነፃነቴ ነው፤ በራሴ ሃሳብና ምርጫ የራሴን ሕይወት መምራት መብቴ ነው” ብለን እንከራከራለንኮ። ግን ይህንን ሃሳብ ከምር መሰረታዊ የፖለቲካ መርህ አድርገን ልንቀበለው አንፈልግም። ለምን ቢባል፣ ያልተመቸን ጊዜ፣ “ከግለሰብ መብትና ነፃነት በፊት የአገር ልማት፣ የህዝብ ጥቅም፣ የብሄር ብሄረሰብ ተዋፅኦ ይቀድማል” እንላለን። ለአገር ልማት በሚል ሰበብ ቅድሚያ ብድር ለማግኘት፣ ለህዝብ ጥቅም ተብሎ በሌሎች ሰዎች ላይ የዋጋ ተመን እንዲታወጅ፣ የብሄር ብሄረሰብ ተዋፅኦ በሚል ሰበብ ስልጣን ለመሻማት ስንፈልግ፤ የግለሰብ ነፃነትን እናጣጥላለን። አመቺ ሆኖ ሲታየን፤ “የሃሳብና የሃይማኖት ነፃነት፣ የመደራጀትና የመምረጥ መብት ይከበር” እንላለን። የማይመቸን ሃሳብ ለማፈንና በሰዎች ህይወት ላይ ለማዘዝ ስንፈልግ ደግሞ፤ “ከግለሰብ ነፃነት በፊት፣ አገራዊ መግባባትና የሃይማኖት ትዕዛዝ ይቀድማል” እንላለን። የነፃነት ነገር... እንደሁኔታው የምንጥለውና የምናነሳው፤ እንደአስፈላጊነቱ የምንክበውና የምንረግጠው፤ እንደአመቺነቱ የምንጮህለትና የምንጮህበት እንዲሆን እንፈልጋለን። ለዚህ ነው፤ መሰረታዊውን ጥያቄ የምናጣጥለው፤ ብዙም ልናስብበት የማንፈልገው። ነገር ግን፤ ልናስብበት ስላልፈለግን ብቻ መሰረታዊ ጥያቄነቱ አይሰረዝም። ሰው እስካለ ድረስ መሰረታዊው ጥያቄ ሁሌም ይኖራል። የነበረ፣ ያለና የሚኖር ጥያቄ ነው - በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም አገር - ዛሬ በዘመናችንና እዚ በአገራችን ጭምር።

ቤተ-ክርስቲያን ቤተ-መንግስት ሲሆን ዝም ብለን ማየት የለብንም!

ቤተ-ክርስቲያን ቤተ-መንግስት ሲሆን ዝም ብለን ማየት አጢያትም ወንጀልም ነው፤የወያኔ መንግስት ከቤተ-ክርስቲያን ላይ እጁን ያንሳ!! በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም ያሉ ብጹሃን አባቶቻችን እርቀ ሰላም አውርደው በእምነታችን ደንብ እና ሰርዓት መሰረት ሁሉ ነገር እንዲፈጸም የክርስቲያን ልጆች አጥብቀን መትጋት አለብን፡፡

Thursday, December 20, 2012

“የስልጣን ሽኩቻ” የተባለ ገዳይ ቫይረስ አለ፡፡



 ፍርሃታችንን፣ ስጋታችንን፣ ተስፋችንን፣ ምኞታችንን፣ ጉጉታችንን፣ ፍላጐታችንን፣ ውዴታችንን፣ ግዴታችንን፣ ኃላፊነታችንን…ስሜታችንን ብዙ አውግተናል፡፡እንኳን ለልማት ለጦርነትም (መስዋእትነት) እየቀረ ነው)።
ሆኖም ሰሞኑን ብልጭ ያለችልኝ አንዲት በዓይነቷ ለየት ያለች ፕሮፖዛል አለችኝና በጨረፍታ ላካፍላችሁ፡፡ እኔ የምለው ግን ---- ስለምርጫ ምናምን ሳወጋችሁ ፍርሃት ይሰማችኋል እንዴ? (ቀልቤ ነግሮኝ እኮ ነው!) ለማንኛውም ግን ዘና ብላችሁ ማውራት-- ማማት--- መሳለቅ-- (መሳቀቅ አልወጣኝም!) መብታችሁ ነው፡፡ እውነቴን እኮ ነው--- ነፃ ሰዎች አይደለንም እንዴ! በዚያ ላይ በገዛ አገራችን ላይ ነን፡፡ ስለዚህ የተሰማንን በነፃነት መግለፅ ህገመንግስታዊ መብታችን ነው! (በታጋዮች መስዋዕትነት የተገኘ!) እነሱ እንደሚሉት ማለቴ ነው ።

Wednesday, December 19, 2012

እስክንድር ነጋ እንዲፈታ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ጠየቁ።

የአውሮፓ ፓርላማ 16 አባላት በጋዜጠኛና የኢንተርኔት አምደኛው እስክንድር ነጋ የተራዘመ እሥር የተሰማቸውን ብርቱ ሥጋት በመግለፅ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ደብዳቤ ፅፈዋል፡፡
የደብዳቤውን ይዘት እና የተፃፈበትን ምክንያት አስመልክቶ የቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት ኃላፊ ፒተር ሃይንላይን “ፍሪደም ናው” የሚባለውን ተቀማጭነቱ ዋሽንግተን ዲሲ የሆነ በነፃነትና በፖለቲካ እሥረኞች ጉዳዮች ላይ የሚሠራ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የፕሮግራም ጠበቃ ፓትሪክ ግሪፊትዝን አነጋግሯል፡፡

ጠቅላይ ፍርድቤት የእነ አቶ አንዱዓለምን ይግባኝ አዳመጠ


ታህሳስ ፲(10) ቀን ፳፻፭(2005)  ዓ/ም
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርደ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝግብ በሥር ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ጥፋተኝነት የተፈረደባቸውን የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላትና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ክርክር አድምጧል፡፡
ከቃሊቲ እና ቂሊንጦ እስር ቤቶች የቀረቡት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አንዷለም አራጌ፣ የፓርቲው አመራር አባልና የወጣቶች አደራጅ ኃላፊ ናትናኤል መኮንን፣ የመኢዴፓ ፓርቲ ኃላፊ ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)፣ የቀድሞው የፓርላማ አባል አቶ አንዷለም አያሌው ናቸው፡፡

Tuesday, December 18, 2012

ተጠያቂዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ እንሆናለን፡፡


መንግሥት ሕዝብን የማሳመን፣ የማሳተፍ፣ የማቀፍና የማሰለፍ ግዴታ አለበት፡፡ የግል ዘርፉን የማበረታታት፣ የማጠናከር፣ የማሳተፍና ድርሻውን እንዲጫወት የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ሲቪል ማኅበረሰቡን የማጠናከር፣ በልማት እንዲሳተፍ የማድረግና የማገዝ ግዴታ አለበት፡፡ በመሆኑም እከሌ እምቢ አለኝ፣ እከሌ አደናቀፈኝ ብሎ መንግሥት ምክንያት ማቅረብ አይችልም፡፡ የልማት አካላትን በሙሉ የማያሳትፍ መንግሥት አገርን የማልማትና ከድህነት የማላቀቅ ብቃትና አቅም የሚኖረው መንግሥት ነውና፡፡ ግን በአገራችን የምናየው መንግስት ትልቁን የንግድ ዘርፍ ተቆጣጥሮ ወደ ኪሱ በመጨመር እራሱን በማጠናከር እድሜውን ለማርዘም ፓርቲውን ህውአት እያጠናከረ እንደሚገኝ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ደሃ እንድንሆን የፈረደብን የለም፡፡ ሀብታም እንዳንሆን የተጣለብን ክልከላና እገዳ የለም፡፡ ደሃ ወይም የበለፀገ ሕዝብ ለመሆን ምርጫው የራሳችን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ፡፡ ግልጽና የማያሻማ ምርጫ 
በአሁኑ ጊዜ ከድህነት እንዳንላቀቅ የውጭ ኃይሎች አደናቅፈውናል ብለን መውቀስ አንችልም፡፡ የውጭ እንቅፋትን አስወግደው ከድህነት የሚላቀቁ አገሮችና ሕዝቦችን እያየን ነውና፡፡ ላለመበልፀጋችን ምክንያቱ ሀብት ስለሌለን ነው ብለን ማመካኘትም አንችልም፡፡ ሕዝብ ራሱ ሀብት ነው፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ለብልፅግና የሚረዳ በጣም ሰፊ የእርሻ መሬት፣ ማዕድናት፣ የቱሪዝም መስህቦች፣ የኃይል ማመንጫዎች፣ ወዘተ አሉን፡፡  ዕውቀት ያለው ሰው ስላልተገኘ ነው እንዳንልም በአገር ውስጥም በውጭ አገሮችም በርካታ ባለዕውቀትና ባለሙያ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች›› የሚል መጽሐፍ ቅዱስና ‹‹ኢትዮጵያን አትንኩ›› የሚል ቅዱስ ቁርዓን ይዘን ደግሞ የተረገመች አገር ስለሆነች ነው ብለን ማሳበብ አንችልም፡፡

ስለዚህ ካልለማን፣ ካላደግን፣ ካልበለፀግን፣ በድህነት ከቆረቆዝን፣ በረሃብና በእርዛት ካለቅን፣ ከተሰደድን፣ ከለመንንና ከተዋረድን ጥፋቱ የራሳችንና የራሳችን ብቻ ነው፡፡  በአጠቃላይ ተጠያቂዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ እንሆናለን፡፡ ትክክለኛ ምርጫ አልመረጥንምና፡፡ 

Monday, December 17, 2012

Malawi arrests 42 Ethiopian refugees trying to flee to South Africa


Blantyre, Malawi – Police in the Malawi capital, Lilongwe, Sunday arrested 42 Ethiopians as they tried to flee to South Africa. Immigration Department spokesman Elack Banda said the refugees had fled the UNHCR-Malawi government-run Dzaleka Refugee Camp in the central district of Dowa.
‘We got a tip from the public that a truck was carrying a lot of strange people,’ he said.
Banda said the truck was traced to the city’s populous Kawale suburb and upon inspection the truck was found to contain sacks of unprocessed Malawi tobacco destined for South Africa with the Ethiopians hiding in between the sacks.
‘When we interrogated them, they claimed they were told there was some work for them in South Africa,’ he said.
Banda said the Malawian driver of the truck has also been arrested and that the refugees will temporarily be kept at the Maula Prison ‘for safe-keeping’.
He said the Ethiopians are likely to be sent back to the Dzaleka refugee camp.

Saturday, December 15, 2012

Unity in diversity ለብሄር ብሄረሰቦች እንጂ ለአገራችን ፓርቲዎች አይሰራም፡፡


ያው የግዜው መሪዎችና ባለስልጣኖች እንደሚሉት እንኳን ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ብዬ ነው ወደ ፖለቲካዊ ወጌ የምገባው፡፡ እኔ የምለው ግን… ወደ ባህር ዳር የመሄድ እድል አግኝታችሁ ነበር እንዴ? ለሌላ እኮ አይደለም - የብሄር ብሄረሰቦችን በዓል ለማክበር ነው፡፡ ለምን መሰላችሁ የጠየቅሁት… አንዳንድ መንግሥት መ/ቤት የሚሰሩ ወዳጆቼ ቅሬታ ስላላቸው ነው፡፡ እንደሌላው ጉዳይ ሁሉ በዚህም መጠቃቀም የሚሉት ነገር ሳይኖር አይቀርም መሰለኝ… አንዳቸውም ወዳጆቼ አልሄዱም፡፡ ምነው ስላቸው… ምን እንዳሉኝ ታውቃላችሁ?
“ሜምበሮቹ ናቸው ተመራርጠው የሄዱት!” አሉኝና ቁጭ! (የፓርቲው አባላት ለማለት እኮ ነው!) እኔ ግን ፈፅሞ ላምናቸው አልቻልኩም፡፡ እንዴ… የብሄር ብሄረሰብ መብትና እኩልነት በሚከበርበት እለት አድልዎና መድልዎ ይፈፀማል? ይሄን ለማጥፋት ደግሞ ሌላ የመብት ትግል ሊያስፈለገን እኮ ነው (ኧረ እኛ ትግል ሰልችቶናል! በስንቱ እንታገል !እላያችን ላይ ያለውን የግፍ አረንቋ ሳንጥል ደግሞ ለማለት የፈለኩት ሳይገባቹ አይቀርም መቼም ያው አምባገነኑን ኢህአዴግ ነው ብል ቅር አይላችሁም ! )
እኔ የምለው… በዓሉን አስመልክቶ ኢቴቪ ያቀረበውን ፕሮግራም ተከታትላችኋል፡፡ ከወደ ምስራቁ የአገራችን ክፍል የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አስመልክቶ አስተያየት የሰጡ ሁለት ሰዎች የተናገሩት ነገር አስደምሞኛል፡፡ ሁለቱም ስለቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነበር ያወሱት (ነፍሳቸውን ይማረውና!) አንደኛው ተናጋሪ መለስ የብሄር ብሄረሰቦች ነፃ አውጭና ወዳጅ መሆናቸውን ከገለፀ በኋላ “ሁሉም ብሄረሰብ መለስ የእኔ ብሄረሰብ ናቸው ነው የሚለው…” አለ፡፡በሳቅ !

Friday, December 14, 2012

“የሽብር ሕግ” የሚለውን የብዥታ አጠራር ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎችን በደፈናው ለመፈረጅ ጉዳይ አውሎታል፡፡


 ኢትዮጵያ ኤርትራ በ2012 ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ ተባለ

በዚህ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የአውሮፓዊያን ዓመት በታሪክ ቁጥራቸው ከመቼም ጊዜ የበለጠ ጋዜጠኞች የታሰሩበት ነው ሲል አንድ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን ዛሬ አስታወቀ።

በኒውዮርክ መሰረቱን ያደረገው CPJ ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረት ባለፉት 11 ወራት 232 ጸሃፊዎች፣ የፎቶ ጋዜጠኞች እና የህትመት አዘጋጆች ታስረዋል። ይሄም በ1996 ከተመዘገበው 185 ታሳሪዎች ቁጥር በእጅጉ የላቀ ሆኗል።

በዚህ መረጃ መሰረት የሲፒጄ የአፍሪካ ክፍል አስተባባሪ ሞሀመድ ኪታ ጋዜጠኞችን በማሰር በማያስመሰግን ደረጃ ስለሚገኙ አገሮች አብራርተዋል፡፡ በሞሀመድ አባባል በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢራንን ተከትላ ቱርክ አንደኛ አሣሪ ሃገር ነች፡፡ ከዚያም ቻይና ትከተላለች፡፡ ከዚያም ኤርትራና ሦሪያ ይከተላሉ፡፡ እነዚህ አምስቱ ግንባር ቀደም ሃገሮች ናቸው፡፡ በርግጥ፣ ኢትዮጵያን፣ ኡዝቤክስታንን፣ ሳዑዲ አረቢያን፣ የመንን ጨምሮ ሌሎችም ሃገሮች እንዳሉ አብራርተዋል፡፡

ዝርፊያ በኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ተጧጥፏል !!


በኢትዮጵያ በ2003 ዓም ብቻ 100 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ተዘርፎ ወደ ውጭ ባንኮች መግባቱ ታወቀ።

ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ጥናቱን ይፋ ያደረገው አለማቀፍ እውቅና ያለው ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ( Global Financial Integrity ) የተባለው ተቋም ሲሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2010 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2003 ዓም ብቻ ከኢትዮጵያ በተለያዩ መንገዶች ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ 5 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን 400 ሺ ዶላር ወይም በጊዜው በነበረው ምንዛሬ ወደ  100 ቢሊዮን  ብር ነው።

አቶ ሃይለማርያም የሕዝብ ራእይ ለምን በአምባገነን ስም ይጠራል?



 የአንድ አገር ጠቅላይ ሚኒስትር  በውጭ ፖሊሲ ዙሪያ የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጥ አካል መሆኑ በህገመንግስቱ ተቀምጧል።
አቶ ሃይለማርያም “የታላቁን መሪ ራእይ” እንደሚተገብሩ ቃል ገብተዋል፤ ለውጥ እንደሚያደርጉ ግን አልገለፁም፡፡ ኢህአዴግ በአቶ መለስ ፍላጎት ብቻ ይመራ፣ የኢትዮጵያ ህዝብም በሰውየው ፍላጎት ይገዛ ነበር፡፡ ከዛ ፍላጎት ማፈንገጥ ለግምገማ ያጋልጥና በጠላትነት ያስፈርጅ ነበር፡፡ ያገዛዙ ጠባይ በድርጅቱ አባላትም አለመተማመንን አስርፆና አስፍኖ፣ አባላቱ በግልፅ ሃሳባቸውን እንዳይገልፁ አፍኖ ስለቆየ ኢህአዴግ ከአቶ መለስ ሞት በሁዋላም እስካሁን የሚመራው በሟቹ መንፈስ ነው፡፡አባላቱ ከአፋኙ ባህል ገና አልተላቀቁም፡፡ ስለዚህ የአቶ ሃይለማርያም ንግግር የተጀመረውን መቀጠል ከሚለው ሃሳብ አለመውጣቱ ለጊዜው አያስገርምም፡፡
አቶ ሃይለማርያም የኢህአዴግ ባለስልጣን ሆነው፣ በተለይም በመለስ ዜናዊ ተመርተው ለዚሁ ስልጣን የበቁ እንደመሆናቸው፣ ባጫር ጊዜ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋትና አንዳንድ የፖለቲካ ለውጦችን በማድረግ አገሪቱን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገር ይችላሉ ብሎ መጠበቅ አይቻልም፡፡ በተለይም ቁልፍ የሆኑ ተቋሞች እንደ ዴህንነትና የጦር ሓይሉ በወንጀል የሚጠየቁና በሙስና የተጨማለቁ የህወሓት ሰዎች ቁጥጥር ውስጥ እስከሆኑ ድረስ ለውጥ ይመጣል ብሎ መጠበቅ አይቻልም፡፡

Thursday, December 13, 2012

ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማርያም መሪ ወይስ ተመሪ ?


ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማርያም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለምታደርገው የእግር ኳስ ጨዋታ ቦታ እንዲለወጥ መጠየቁን አላውቅም ብለው አልጀዚራ ቴሌቪዥን ተናገሩ። 


አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይህን የተናገሩት ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።  ረዩተር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መላኩ አየለን በመጠቀስ  ” ለተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እግር ኳስ ፌደሬሽኑ የጨዋታው ቦታ እንዲቀየር መጠየቁን ” ዘግቦ ነበር። ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንም ለጉዳዩ  የዜና ሽፋን መስጠታቸው ይታወቃል።
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

Can Ethiopia and Eritrea finally find peace?

የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ ሊፈነዳ ደርሷል !!



በአንድ አገር ዕድገትና ልማት የሚመጣው በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በሕዝብ ተሳትፎ ጭምር ነው፡፡ ሕዝብ ለራሱ ምን እንደሚፈልግ ወይም ምን እንደሚጠቅመው የሚወስነው ራሱ ነው እንጂ መንግሥት አይደለም፡፡ ስለዚህ የመንግሥት ሚና (ድርሻ) ዲሞክራሲን በተከተለ ሥርዓት የሕዝብ ፍላጐት ማስፈጸም ብቻ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለፉት21 አመታት የገዥ መደቦች መራራ ጭቆናና የአስተዳደር በደል ያሳለፈ ሕዝብ ነው፡፡


ኢሕአዴግ ለዲሞክራሲ፣ ለመልካም አስተዳደር፣ ለሕግ የበላይነትና ለሰብዓዊ መብቶች እንደማይቆረቆር ቢታወቅም፣  የዜጐች ሰብዓዊ መብቶችን ሲጣሱና ሲረገጡ ያያል፤ ይሰማልም፡፡

ኢሕአዴግ የዜጐችን ክብር፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲን ለማምጣት ለ17 ዓመታት ታግያለው ቢልም፤ መስዋዕትነትም ከፍያለው ቢልም፡፡ ሆኖም የዜጐችን ሰብዓዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት በጽናት አላከበረም፡፡ የአስተዳደርና ፍትሕ አካላትም በከፍተኛ ሙስና ተዘፍቀዋል፡፡ የሚነዱት መኪናና የሚኖሩበት ቤት ማሳያ ነው፡፡ በዚሁ ምክንያት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ዜጐች ላይ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እየተፈጸሙ ይታያሉ፤ ተፈጽመዋልም፡፡

Wednesday, December 12, 2012

የሰው አገር የሰው ነው !

የሰው አገር የሰው ነው ማንም ሰው ከአገሩ ተሰዶ ቢኖር እንደራስ አገር መቼም አይሆንም ! ሰው በአገሩ፣ ሰው በወንዙ ተብሎ የለ? ሰው በአገሩ ላይ ቢጣላና ያለመግባባት ቢፈጠር፣ በዚያው በመንደሩ፣ በአካባቢውና በአገሩ ይዳኛል፡፡ እርቅም ይወርዳል ከዚያም የተለመደው ማኅበራዊ ግንኙነታቸው እንደነበር ይቀጥላል፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘው በጋራ ማደግና መበልፀግ ዕጣ ፈንታቸው ይሆናል፡፡

Tuesday, December 11, 2012

አበሻ እንኳን አሜሪካ ማርስ ላይ ቢወጣም መከፋፈሉ አይቀርም!



የዛሬውን ፖለቲካዊ ወግ በጥያቄ እንድጀምር ፍቀዱልኝ፡፡ ጥያቄው ደግሞ ለናንተ ነው፡፡
“በዘንድሮ የከፍተኛ ተቋማት ተመራቂዎች ላይ ምን ለየት ያለ ነገር አስተዋላችሁ?” በተለይ በኢቴቪ መስኮት ከምረቃ በኋላ ምን እንደሚሰሩ ሲነግሩን የሰነበቱትን ተመራቂዎች ማለቴ ነው፡፡ ተመራቂዎቹ ለኢቴቪ ጋዜጠኞች የሰጡትን ምላሽ የታዘቡ አንዳንድ ተመልካቾች፤ ሁሉም አንድ ዓይነት ጥያቄ ከነመልሱ የተሰጣቸው ይመስላሉ የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ ነገርዬውን ስታዩት ግን እውነት ይመስላል (መረጃ ማቅረብ ባይቻልም!)
“ከመንግስት ሥራ ጠባቂ ሳይሆን ሥራ ፈጣሪ መሆን ነው የምፈልገው” ከሁሉም “የኢቴቪ ተመራቂ” አንደበት የሚሰማ ምላሽ ነበር፡፡
ባለፈው ሳምንት እዚሁ ጋዜጣ ላይ ባለድግሪ ኮብልስቶን ጠራቢዎችን አስመልክቶ ሁለት የአገሪቱ አንጋፋ ምሁራን በሰጡት አስተያየት፤ ማንም የፈለገውን ተምሮ የፈለገው ሥራ ላይ የመሰማራት መብት እንዳለው ገልፀዋል (በደንብ እስማማለሁ!)
ተመራቂዎቹም እየነገሩን ያሉት የልባቸውን ከሆነ “እሰየው” ብለናቸዋል (ንግግራቸው የተጠና ተውኔት ቢመስልም) አንድ ግልፅ ያልሆነልኝ ነገር ግን አለ - ተመራቂዎቹ “ሥራ ፈጠራ” የሚሉት ያንኑ ኮብልስቶን ይሆን እንዴ?

Monday, December 10, 2012

አገራችንን የማን እንደሆነች አላወቅናትም !

በመካከላችን አንድነት የሚኖረው መቼ ነው? መተሳሰብ የሚሰፍነው መቼ ነው? ለየራሳችን ፍላጎት መተሳሰቡን (‹‹የመረዳዳት ባህላችንን››) እናቆየውና የራሳችን የሁላችን ስለምንላት ሀገራችን የጋራ አስተሳሰብ አለን? አይመስለኝም፡፡ ብዙዎቻችን ከራሳችን ውጭ ማንም ያለ አይመስለንም፡፡ ሀገሪቱም ከእኛ ውጭ አሳቢ እንደሌላት እንድመድማለን፡፡ አለዚያም ሀገሪቱን ረግጠን እና በሀገሪቱ አላግጠን ለማለፍ መለኮታዊ ቅባት እንደተቸረን ይሰማናል፡፡ ይህማ ባይሆን እኩልነታቸውን አስከብረናል በምንልበት ሀገር ዘለፋን አፈናጥረን በተውን ! 

Saturday, December 8, 2012

“ሹመት፤ ማዕረግ ሳይሆን የአገልግሎት ቃል ኪዳን ነው”

መሥራት ካልቻላችሁ ለምን ሾምኳችሁ ከሚል አለቃ ይሠውረን፡፡ መሥራት ሳይችሉ ሹመትን ለሹመት ብቻ ብለው ከሚቀበሉም ባለሟሎች ያድነን፡፡ የህዝብን ብሶት የሚፈቱ እንጂ ህዝብን እናስወግድ የሚሉ እንዳይገጥሙን እንፀልይ፡፡ ለህዝቡ ነው ለእኔ የቆምከው? የሚል ሹም ላያችን ላይ እንዳይንሰራፋ ነቅተን እንይ፡፡ የሚያስረዳ፣ ዐይን - የሚገልጥና ለመልካም አስተዳደር የቆመ ባለሥልጣን እንጂ እኔ ያዘዝኩህን ብቻ ፈጽሞ የሚል አይዘዝብን! ገደል እንዳንገባ ገደሉን የሚያጥርና ከመውደቅ የሚያድነን እንጂ “ወዶ ገደል ገባ!” ከሚል ኃላፊ ያድነን፡፡ ከሚያየው የማያየው የሚሻልባት አገር ሳትሆን፤ ልቦና የሰጠው ህዝብ የሚኖርባት አገር ትሆን ዘንድ የልባችን ይሙላልን፡፡ 

Friday, December 7, 2012

የተለመደው የምርጫ ውዝግብ የተጀመረ ይመስላል ?





የተለመደው የምርጫ ውዝግብ የተጀመረ ይመስላል - እዚህች አዲስ አበባ ሸገር እምብርት ላይ፡፡ በእርግጥ የማስጀመርያው ተኩስ ገና አልተተኮሰም ፓርቲዎች ግን እስኪተኮስ እንኳን አልጠበቁም፡፡ እናም በግንቦት ለሚካሄድ ምርጫ በጥቅምት ውዝግብ ተጀምሯል እያልኳችሁ ነው (በምርጫ ውዝግብ ሪከርድ ሳንሰብር አንቀርም!) ይሄ እንግዲህ ለአካባቢና ለአዲስ አበባ ምርጫ ነው፡፡ በ2007 ዋናው አገራዊ ምርጫ ላይ ምን እንደሚፈጠር የሚያውቀው አንድዬ ብቻ ነው፡፡ 

ማወቅ ያለብን ከዚህ በሁዋላ ለወያኔ/ኢሕአዴግ ተጨማሪ ዕድሜ ከተሰጠው፣ ከወያኔ/ኢሕአዴግ በላይ ወንጀለኛ የሚሆነው ተቃዋሚው ነው።






የወያኔ  ጥንካሬ፣ዓላማው፣አደረጃጀቱ፣ያሰባሰበው  የሰው  ኃይል  ወይም  የነደፈው  ፖሊሲ
አይደለም።  የጥንካሬው  መሠረቱና  ምንጩ  ወያኔ  ጠንካራ  ተቃዋሚ  የሌለው  ዕድለኛ  ቡድን
መኆኑ  ነው፡፡  የሕወሓት  ጥንካሬ  ሌላ  ምንም  ሳይሆን፣የተቃዋሚው  ሁለንተናዊ  ድክመት
ነው።  የተቃዋሚው  ድክመት  መሠረትና  ምንጩ  ደግሞ፣  የተበታተነና  እንኩዋን  አብሮ
ለመሥራትና  ለመኖር  የጋራ  ጠላቱ  በሆነው  ወያኔ  ላይ  አንድ  ዓይነት  አመለካከት  መቅረጽ
ያልቻለ  መኆኑ  ነው።  ይህም  በመሆኑ፣የተቃዋሚው  ሁለንተናዊ  ድክመት፣ለወያኔ  ዙሪያገብ
ጥንካሬ ሰጥቶት ይገኛል።

አይ ባይ ያጣው የኢህአዴግ ህገ መንግስት !


106 አንቀጽ የተዋቀረዉን የኢህአዴግን ህገ መንግስት በጨረፍታ።
ያዉ ሁላችንም እንደምናዉቀዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ህገ መንግስት የተረቀቀዉ 18 አመት በፊት ህዳር 29/1987 . ነበር። ከነሐሴ 15/1987 . ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ዉሏል።
አንቀጽ 9/1 ህገ-መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ህግ ነዉ
አንቀጽ 10/2 የዜጎች እና የህዝቦች ሰብዐዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ
አንቀጽ 12/1 የመንግስት አሰራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት
አንቀጽ 21/1 በጥበቃ ስር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸዉን በሚጠበቅ ሁኔታዎች ሜአዝ መብት አላቸዉ
አንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸዉ

Monday, December 3, 2012

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጉባዔ ተግባሩና ተግዳሮቱ


1. ህግ የማያከብር መንግስት
የኢህአዴግ መንግስት የፍትህ የዳኝነትና የፖሊስ አካላት እንዲቋቋሙ አድርጓል፡፡ እነዚህ የፍትህ አካላት አንዳንድ የሚወስዱትን ህገ-ወጥ እርምጃ ሳይ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን የኢህአዴግን መንግስት ለሚቃወሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በአጠቃላይ የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጫን የተመሰረቱ ይመስሉኛል፡፡ በማንኛውም ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ፖሊስ መጀመርያ ግለሰቡን ..ከኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች.. አንዱ መሆኑን እና አለመሆኑን ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ይሁንታ ካላገኘ የማሰር አቅም አይኖረውም፡፡ የፍትህ አካላትም ክስ የሚመሰረቱበትን የግለሰቡን ማንነት አስቀድመው ከኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላቸዋል፡፡ ዳኞችም እንግዲህ በአንፃሩ ከኢህአዴግ መንግስት በአመለካከት ያልተለዩ ከሆኑ ወንጀል ቢፈፅምም ተጠርጣሪ ጠያቂ አለበት ማለት ይከብዳል፡፡ የፖለቲካ ታማኝነቱ ሳይታወቅ የተከሰሰ ..አባል.. እንኳ በችሎት ላይ እያለም ክሱ እንዲሰረዝለት የሚደረግበት አጋጣሚ አለ፡፡

Tuesday, November 27, 2012

ሁሌም ለብሔራዊ ደኅንነታችን መረጋገጥ በንቃት ዘብ እንቁም!



በእረፍት ጊዜያችን ወይም በሥራ አጋጣሚ በእግር ወይም በተሽከርካሪ ስንንቀሳቀስ በከተማችን ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ኤምባሲዎችን እናስተውላለን፡፡ በተለይ ደግሞ የኃያላኑ አገሮች ኤምባሲዎች ጥበቃና ፀጥታ የሚነግረን አለው፡፡ ወደ ሽሮሜዳ ስትሄዱ እጅግ በሚገርም ሁኔታ የተገነባው የአሜሪካ ኤምባሲ በሩቅ ርቀት የተሠሩለት የኮንክሪት መከላከያዎች ድንገተኛ ጥቃቶችን ታሳቢ ያደረጉ ይመስላሉ፡፡ በሾላ መስመር የአንግሊዝ ኤምባሲም እንዲሁ የኮንክሪት መከላከያዎች የተበጁለት ነው፡፡ በሌሎች ሥፍራዎችም ስትሄዱ የዓለም አቀፍ ተቋማት ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው ትረዳላችሁ፡፡ ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ፖለቲካ ምክንያት ሁሌም ቅድሚያ የሚሰጠው የፀጥታና የደኅንነት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ የተጠናከረ ጥበቃ የሚያስገነዝበን በተለይ ኃያላን አገሮች ለብሔራዊ ደኅንነታቸው ምን ያህል ጥንቁቅ መሆናቸውን ነው፡፡

Saturday, November 24, 2012

ታሪክ ለመስራት ታሪክን ማጥፋት ተገቢ አይደለም !!


ይህ የባቡር መሥመር መሰራት የአቡነ ጴጥሮስንና የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት ማፍረስ ምን ይባላል ?
 ኢትዮጵያን እናሳድጋለን ስንል ያሳደጓትን እየዘነጋንና መታሰቢያቸውን እያፈረስን መሆን የለበትም፡፡ <<በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ>>  አረለ የሚለው ተረቱ እውነት ነው፡፡ የምናመጣው አዲስ ነገር ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም፡፡  ወደድንም ጠላንም ይህች ሀገር የታሪክና የቅርስ ሀገር ናት፡፡ ታሪኳን ማፍረስ አንችልም !! ታሪክ ይፈርዳል !!

ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ እንዳትኖር ማን አደረጋት ??


«…ሀገራዊ ታሪካችንንም ሆነ ፖለቲካዊ እውነታዎችን በግልፅ ፍርጥርጥ አድርገን የመናገር ችግር አለብን፡፡ አንድ የፖለቲካ ሁኔታ ወደኋላ መለስ ብለን አንስተን ስንወያይ እውነታውን ለመቀበል ምን ያህል ዝግጁ ነን የሚለው መታየት ያለበት ይመስለናል፡፡ እኔ መሰረታዊ ችግር ነው የምለው ይህንን ነው…» በምድረ ኢትዮጵያ ስለዲሞክራሲ ሲነገር ሲደሶከር ሲዘመርና ሲተነተን ከአራት አስርት አመታት በላይ መቆጠሩ እውነትነው፡፡ ነገር ግን የተነገረውንና የታወቀውን ያህል የዲሞክራሲ ዘር ተዘርቶ ፍሬ ሲያፈራ አልታየም፡፡ ወይም ሊታይ አልቻለም፡፡

Wednesday, November 21, 2012

ልዩነት በድምፅ ብቻ ይፈጠር ዘንድ ለአገሬ ተመኘሁ።

አንድ ወዳጄን ሰለ አሜረካ ምርጫ ጠየቁት ‹‹ለመሆኑ ኦባማ በማሸነፋቸው ምን ተሰማህ?›› አልኩት። ‹‹‘እናቴን ያገባ ሁሉም አባቴ ነው’ ሲባል አልሰማህም? ማንም ቢመረጥ ከብሔሪዊ ጥቅማችን ጋር የሚሄድ ፖሊሲ ካለው ይመቸኛል፤›› አለኝ። በዝምታ ትንሽ በየራሳችን ዓለም ሰጠምን። እንዲህ በፍጥነትና በቅልጥፍና ግልጽ የሆነ ምርጫ ለማድረግ ስንት ዓመት ይፈጅብን ይሆን? እያልን ራሳችንን አስጨነቅነው። ‹‹ለመሆኑ ጓደኛዬ ኦባማ ካሸነፉ በኋላ የተናገሩትን ሰምተሃል?›› አለኝ። ‹‹በምን አባቴ የቋንቋ ችሎታ እሰማለሁ ብለህ ነው? አዳሜ የተሰባበረ እንግሊዝኛ ላያችን ላይ እየለቀቀብን የምንችለው እንኳ ይጠፋብን ጀመር፤›› ስለው ከት ብሎ ሳቀ። ሳቁን ሲያባራ፣ ‹‹ምን አሉ መሰለህ? ‘ዛሬ ዋናው ነገር ኦባማን ወይንም ሚት ሮምኒን መምረጣችሁ ሳይሆን በድምፃችሁ ልዩነት መፍጠራችሁ ነው’ ያሉት ንግግር ውስጤ ቀረ፤›› ካለኝ በኋላ ትንሽ አሰብ አድርጎ፣ ‹‹ሥልጣን የሕዝብነቱ ተረጋግጦ በድምፃችን ልዩነት ለማምጣት የዲሞክራሲ ጉዞ ምንጊዜም ወሳኝ ነው፤›› ሲለኝ ተቀበልኩት። ልዩነት በድምፅ ብቻ ይፈጠር ዘንድ ለአገሬ ተመኘሁ። በመፈክር ሳይሆን በተግባር የሚረጋገጥ ዲሞክራሲ ማን ይጠላል? ከመፈክር ይልቅ ዲሞክራሲ ናፈቀኝ፡፡   

ዲሞክራሲ! ይበልጣል ከመፈክር !!

ሰላም! ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ላላችሁ በሙሉ። አንድ ወዳጄ ይኼንን የአቅጣጫ ሰላምታ እንደማይወደው አጫውቻችሁ አውቃለሁ? ለምንድን ነው ስለው ‹‹የሰው ልጅ እንደ ንፋስ በአቅጣጫ ላይ ተመሥርቶ ሰላምታ ሲለዋወጥ እበሽቃለሁ፤›› አይለኝ መሰላችሁ? የዘንድሮን ሰው የሚያበሽቀውን ነገር ብዛት ቆጥረን መጨረስ አቃተን! ግን ግን ንፋስን ለምንከተል የዘመኑ ሰዎች ይህ ሰላምታ ካልተሰጠ ለማን ይሰጥ? ለራስ ብቻ የሚሮጥበት ዘመን መሆኑን ካየን ዘንዳ ከዚህ ሌላ ምን ይባላል? አንዳችን ያለ ሌላችን መኖር እንደማንችል እያወቅነው ‘እኔ’ን ብቻ ላማከለ ነፍስ መሮጣችን ይገርመኛል። የሚገርማችሁ ደግሞ አባባልን እንኳ መርጠን አለመጠቀማችን ነው። ለምሳሌ ‹‹ዘመኑ የውድድር ነው›› የሚለውን አባባል ለተቀደሰ ይሁን ለረከሰ ተግባር እንደምንጠቀምበት ሳንለይ ለሁለቱም እንዳሻን እንገለገልበታለን። አሁንማ ሙሰኛውም በሰሞነኛ ተቆጣጣሪዎች ሲያላግጥ ‘ዘመኑ የውድድር ነው’ ማለት ጀምሯል አሉ። ‹‹ውድድሩ ጤናማ ዕድገት ለማስመዝገብ ነው? ወይስ እንደተለመደው ጠልፎ ለመጣል ነው?›› 

Monday, November 12, 2012

ለሕዝባችን በመቆም ሕዝብ ይዳኘን !!!

                           ብዙ ጊዜ ለአፍሪካ ወይም ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ አሜሪካ ምሳሌ መሆን የለባትም የሚሉ ክርክሮች ይሰማሉ፡፡ አሜሪካ የተለያዩ ሕዝቦች፣ ባህሎች፣ ዕምነቶችና አመለካከቶች ያሉባት ትልቅ አገር ስትሆን በበርካታ ምክንያቶች ከአፍሪካ ወይም ደግሞ ከኢትዮጵያ ትለያለች የሚል መከራከሪያ አለ፡፡ አፍሪካ አኅጉራችንን ለጊዜው እንተዋትና ኢትዮጵያ ላይ በማተኮር ይኼንን መከራከሪያ እንሞግት፡፡ ኢትዮጵያ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ቋንቋዎች፣ ዕምነቶች፣ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች ያሉባት አገር ብትሆንም ለዓለም ምሳሌ መሆን የሚችል መቻቻል ያለባት አገር መሆኗን ማስታወስ የግድ ይለናል፡፡ እንደ አሜሪካ ከተለያዩ አገሮችና አኅጉራት የፈለሱ ሕዝቦች ባይኖሯትም፣ የራሳቸው ማንነት ያላቸው ነገር ግን ለዘመናት በኢትዮጵያዊነታቸው ታውቀው የሚኖሩ የተለያዩ ሕዝቦች አሏት፡፡ እንደ አሜሪካ የተለያዩ አመለካከት፣ ፍላጎት፣ ዕምነትና የመሳሰሉት መለያዎች ያሉዋቸው ብሔር ብሔረሰቦቻችን በሰላምና በመቻቻል መኖርን ለረጅም ዓመታት ካዳበሩ እንደምን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ማራመድ ያቅታቸዋል?

Thursday, November 8, 2012

ኢትዮጵያውያን ለለውጥ አንድ ስንሆን ማንም አያቆመንም፡፡

  


     የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት፣ የሰው ዘር መገኛ፣ በውጭ ወራሪዎች ሳትደፈር ነፃነቷን አስጠብቃ በሉዓላዊነቷ ፀንታ ች፣ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን በልዩነት ውስጥ የፀና አንድነት ፈጥራ ች፤ ኢትዮጵያ። አገራችን ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ የምትታወቅባቸው በርካታ አዎንታዊ ገፅታን የተላበሰች ብትሆንም ውን ዘመ በነበረችበት ሁኔታ በአሉታዊ ገፅታ ስትነሳ እየለች ተገኛለች

Wednesday, November 7, 2012

ህዝብን በህትመት ነፃነት ማፈን አይቻልም !!!

                  በፍራቻ የሚነጥፍ ብዕርም ሆነ በአፈና የሚንበረከክ የትግል ማንነት የለንም!ኢህአዴግ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስቴር አስቀምጧል፡፡ እንደ  አለመታደል ሆኖ ግን አዲሱም ሰው የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር ዱካ የሚከተሉ፣ መለስ የጀመሩትን አፈና የሚያስቀጥሉ፣በመለስ የሙት መንፈስ የሚመሩ በመሆናቸው አሁንም በኢትዮጵያችን አንጻራዊ የሚባል እንኳ ለውጥ ለማየት አልቻልንም፡፡በተለይም “አዲሱ” መንግስት ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጦችን ከአደባባይ በማጥፋት የሀገሪቱን የፕሬስ ነፃነት ጉዞ ክፉኛ ወደኋላ መመለሱ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚያስከትል መሆኑን ከግምት ያስገባ አይደለም፡፡

Thursday, November 1, 2012

ኧረ የፍትህ ያለህ !! ያለ ነፃነት መኖር በቃኝ! በቃን መኖር ሰለቸን ! ለውጥ ያስፈልጋል!





             
   በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር እና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ዜጎች በእኩልነት ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያስቡ፣ የሚናገሩ፣የሚፅፉና የሚቆረቆሩ በጠቅላላው ለእነዚህ ፅንስ ሐሳቦች ዘብ የሚቆሙ በሙሉ የስርዓቱ ጠላቶች ተደርገው በመቆጠር ላይ ናቸው::
   ለአገሪቱ አንድነትና ሉአላዊነት ብልፅግና በጣም ከሚቆጠሩ መሪዎቿና የፓርቲአቸው ጠባብ ጎሰኛ ፖሊሲ የተለየ የሚያስቡ ዜጎችና ቡድኖች ሁሉ ጠላትና ሽብርተኞች ወይንም አሽባሪዎች ወይም በዘመኑ አባባል ጽንፈኛ ተደርገው ይቆጠራሉ።

Wednesday, October 31, 2012

አገርን መከፋፈል አይቻልም አይሳካም !!!



የተከበሩት ኔልሰን መንዴላ እንዲህ ይሉናል ”….. ፍቅር አብሮን የተወለደ በተፈጥሮ ያገኘነው ነው። ጥላቻ ግን በትምህርት ያገኘነው ነው። ስለዚህ ጥላቻን በትምህርት ልናስወግደው እንችላለን።….”። ግን በ’ኛ ሀገር ለወያኔ ገዥዎቻችን ጥላቻና ክህደት አብሮ’ቸው የተፈጠረ ይመስላል። ያለፈው አልበቃቸው ብሎ አሁንም የጥላቻንና የዘረኝነትን መርዝ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ ይረጫሉ። ”ለምን?..” ያለውን ደግሞ ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይገላሉ፣ ያስገድላሉ። እንደ’ነሱ ጠበንና አንሰን፣ ሀገራዊነትን አውግዘን፣ ስብእናችን ሁሉ ”ጎጠኝነት” አንዲሆን ሌት ተቀን ይደክማሉ። ለመሆኑ ከዘመናት በፊት ”ዘሬ የሰው ልጅ ነው፤ ሀገሬም ዓለም ነው።” ያለው ደራሲ (ስሙን ማስታወስ ስላልቻልኩ ይቅርታ።) በዚህ ዘመን ወያኔወችን እጅ ቢጥለው ምን ይል ይሆን? እነሱስ ምን ያደርጉት ይሆን?

Thursday, October 25, 2012

ታጋይን በማሰርና በመግደል ትግሉን ማሰር አይቻልም !!!

 የሚመቸውን ህግ በማውጣት ሰውን በፀረ ሽብርተኛ በመክሰስ በማሰርና በመግደል ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ ለሱ የሚመቹትን እና ለሱ የሚሰግዱትን በማገልገል ሌላውን ሕዝብ ከሌላ አገር የመጣ ይመስል እያሰቃየው በሚገኝበት ወቅት ላይ መሆኑን መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም ! ‹‹ ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትም›› የሚል ፅኑ መፈክር በማሰማት በበርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ወደስልጣን የወጣው የኢህአዴግ መንግስት መፈክሩን በመዘንጋት“ታሪክ ራሱን ይደግማል” እንደሚባለው ያለፉትን ገዥዎች ታሪክ እየደገመ ይገኛል፡፡ደርግ ራሳቸውን ‹‹ገንጣይ፣ አስገንጣይ፣ ወንበዴ፣ ሽፍታ…››የመሳሰሉ ስሞችን እየሸለመ ለማጥላላት እንደሞከረው ሁሉ ኢህአዴግም ከጣለው አምባገነን መንግስት ምንም ሳይማር ‹‹ህገ-መንግስቱን በኃይል ለመናድ›› እና አሁን ደግሞ ‹‹ሽብርተኛ››በማለት ዘላለማዊ ሆኖ በመቆየት በመሻት የሰላማዊ ትግሉን ፈርለ ማስለቀቅ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር የሆኑትንና ጋዜጠኞችን  በማሰርና የፈለገውን ፍርድ በመስጠት እፎይታ ለማግኘት ሲሞክር እያስተዋልን ነው ፡፡የኢህአዴግን አገዛዝ ከደርግ የሚለየው ደርግ በአደባባይ ገድሎ ሲፎክር ኢህአዴግ ደግሞ ህግ አውጥቶና ህግ ጠቅሶ ሞት ይበይናል።

Sunday, October 14, 2012

ምን ይበጃል ? ምንስ ይሻላል ?


            የቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ካከተመ በኋላ እና አለም ወደ አንድ የርዕዮት ዓለም ካምፕ እየገባች ባለችበት አጋጣሚ የስልጣን አክሊል የደፉት ገዢዎቻችን የነፃውን ፕሬስ ዓለም በዚች ሀገር እውን እንዲሆን ሁኔታዎችን ብናመቻች የሰለጠነው አለም ያከብረናል በማለታቸው በርካታ ጋዜጦችና መጽሄቶች ለህትመት በቅተው እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ሆኖም ግን የነፃው ፕሬስ አርበኞች አደገኛውን የጎሳ ፖለቲካ መርዝ ለማርከስ እና የስርዓቱን ብልሹ አሰራር እንደ እሳት በሚፋጅ ብእራቸው ስለተቹ ጥሩ ነገርም ከተሰራ በማመስገናቸው የተነሳ የአገዛዙ አማካሪዎችም ሆኑ ፊት አውራሪዎች በበጎ አይን አልተመለከቷቸውም፡፡ የተለያዩ ስልቶችንም እየተጠቀሙ የነፃውንፕሬስ አባላት የመበተን እርምጃ ወስደዋል፡፡

Thursday, October 11, 2012

ኢህአዴግ ነፃውን ፕሬስ ለማጥፋት የጀመረውን ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም!!!




የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የነፃ ፕሬስ አስፈላጊነት

ትልቅ ቦታ እንዳለው ከልብ እናምናለን፡፡ ያለነፃ ፕሬስ ዴሞክራሲ
አለ ብሎ መናገር ማወናበድ እንጅ እውነት ሊሆንም አይችልም፡፡
የነፃ ፕሬስ መኖር በራሱ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መኖር መገለጫ
ነውና፡፡ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖርም ነፃ ፕሬስ ይኖራል፡
፡ ወደ እኛ ሃገር ስንመለስ ግን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነው
እናገኛቸዋለን፡፡ ኢህአዴግ መንግስት ሆኖ ለባለፉት 21 ዓመታት
ሃገሪቱን ሲያስተዳድር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በወረቀትና በቃል
እንጂ ከዚያ በዘለለ በተግባር ሲፈፅም አላሳየንም፡፡ ለመተግበር
የሞከራቸውንም እንደ ቀንዳውጣ ቀንድ መልሶ ሸሽጎታል፡፡ ስለዚህ
በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማያምን ገዢ ፓርቲ ስለሆነ ለነፃው ፕሬስ
ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ በመስጠት ፈንታ አጥፊና ደምጣጭ
ሆኖ እየሰራ ነው፡፡

Tuesday, October 9, 2012

እውነተኛው ምርጫ መቼ ይሆን ??


ከ2ዐዐ2 ምርጫ ዋዜማ ጀምሮ አሁንም ድረስ ያልበረደ የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንበ (ለነገሩ ህግ ነው) ለምን አትፈርሙም ከኢህአዴግ የሚቀርብ ያልተቋረጠ ጥያቄ ነው፡፡ ይህንን እንከን የለሽ የምርጫ ሥነ- ምግባር ደንብ ካልፈረማችሁ ንግግር ብሎ ነገር የለም በማለት በፓርላማ ቀርበው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም ተናግረዋል፡፡ አሁንም ሌሎች እየነገሩን ያሉት ቃል በቃል ይህንኑ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ላለመደራደር፣ ላለመወያየት ይህ ምክንያት እስካለ ድረስ ሌላ መፈለግ አይጠበቅባቸውም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ለሕዝብ ዝርዝሩን ማሳወቅ ተገቢ ስለሆነ ዛሬ በዚህ ጽሑፍ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

Saturday, October 6, 2012

ሲሞቱ ዲሞክራት የሆኑ መሪ


                                                                                                                          

              ገድል እንደሰራ ሰው እንዲሰበክላቸው መደረጉ መነጋገሪያ ከሆነ ወራቶች አለፉ ,,, እውነት ለመናገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህይወት እያሉ አምባገነን መሆናቸውና ጥፋቶችን በዜጎች ላይ መፈፀማቸው ከማንም የሚሸሸግ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ባያስደስትም የተወሰኑ የራሳቸውን ሰዎች አስደስተው አርፈዋል ። መጥፎ ተግባራትም ነበሯቸው፡፡ ሆኖም ከፈፀሟው ጥፋቶች አንፃር በየመንደሩ፣ በየትራንስፖርት አገልግሎቱ፣ በየመስሪያ ቤቱ፣ በየቤተክርስቲያኑና በየመስጊዱ ስለሳቸው ጥሩ ነገር አይወራም ነበር፡፡

Thursday, October 4, 2012

መቻቻል ወይስ መቻል !!!





     በአገራችን ያለው የፖለቲካ አለመግባባት እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብ እንሰማለን፡፡ በተለይ ተቃዋሚዎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በየመድረኩ ጮኸዋል፡፡ የአገራችን ጉዳይ ያገባናል ያሉ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ ሁኔታ የእርቅ ጥሪውን ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በኢህአዴግ በኩል ግን ማን ከማን ተጣላና ነው እርቅ የሚያስፈልገው? ሲባል ሰምተናል፡፡ ስለ ዛሬው ከመነጋገር ይልቅ ወደ ኋላ እየተመለሱ ያለፉትን ሥርአቶች ማውገዝ እንደ ባህል ተደርጎ ቆይቷል፡፡ ይህ ደግሞ ለማንም አይጠቅምም፡፡ የአገሪቱ ጉዳይ የዜጎቿ ጉዳይ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ማንም ስለማንም አውቅልሃለሁ የሚልበት ጊዜ ማክተም ያለበት አሁን ይመስለኛል።

እውነት ይነገር! ውሸት ይቁም!




የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ዜና
ረፍትን ተከትሎ የታክስ ከፋዩ ሕዝብ ንብረት በሆነው
የመንግሥት ብዙሃን መገናኛ የሚነገሩትን የፕሮፓጋንዳ
ውርጅብኝ እየተከታተልን ነው፡፡ ኢትዮጵያን የምድር ገነት
የማስመሰሉ ጥረት የተሳካላቸው የሚመስላቸው ካሉ
ተሳስተዋል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን አገራችንን እየኖርንባት
ነው፡፡ የምናውቃት ነች፡፡ ከውጭ አገር አልመጣንም፡፡

በዘር እንዳንዘረዘር !!


                  የጓደኛችን ቋንቋው፣ ዘሩ፣ ሃይማኖቱና ፖለቲካዊ አመለካከቱ ምን ያደርግልሃል? ደጋ ውስጥ ቢፈጠር ቆላ፣ ወይናደጋ ቢወለድ  ተራራ ጫፍ ላይ፤ አንዴ ተፈጥረናልና ሰው ስለመሆናችን ብቻ ማሰቡ ይበልጣል።

  ከመጀመርያው ዓለም ጦርነት ማገባደጃ ቦኋላ በጀርመን ማደግ ጀምሮ የነበርው ´´የናሺናል ሶሻሊስት ፓርቲ´´ የናዚ የፖለቲካ ዘይቤን በማስፋፋት ፣ የፋሺስቶች የቀኝ ክንፍ እንቅስቃሴ በዛን ወቅት በዋናነት ይታገል ፣ ይዋጋ ነበረው አንዱ ኮሚኒስቶችን ነበር ፡፡ እነዚህን ክፍሎች ዒላማ ካደረገበት ምክንያት አንዱ ፣ በወቅቱ በዓለማችን ዙርያ እየተጠናከረ የነበረውን ፣ የኮሚኒስቶች እንቅስቃሴ ለመቋቋምና ፣ በስራቸው እየተደራጀ የነበረውን የሰራተኛውን ክፍል (working class ) ከኮሚኒስቶች ነጥሎ በናዚስቶች ስር ለማሰለፍና ነበር ፡፡

Monday, October 1, 2012

ኃይለማሪያም ደሳለኝን ተስፋ አታድርጉ




ኃይለማሪያም ወይም ኃይለ ወያኔ ክፍት ወንበር ላይ ቂጢጥ ማለቱ አይገርመንም:: ድሮም
አውታንቲ ሾፌር ይሆናል  :: ግን መኪናውም መንገዱም ያው ነው :: ምኑ ላይ ነው
ዓሥራትነቱ ወይም ተስፋነቱ ?  እስቲ  እንግዲህ እንዴት እንደሚያፋድስ  እናየዋለን::
ዘንድሮ ጉድ እኮ ነው ! የአገር ቤቱ አዘንተኛ ሲገርመን ለካስ በተቃዋሚው ሰፈርም ነጠላ
ያዘቀዘቁ ነበሩ :: አገር የማዳኑ ጉዳይ  ቀረና እንታረቅ፤  እንቻቻል ሆነ ለቅሶው ።

Friday, September 21, 2012

ቁም ነገር ተናጋሪ የሌለበት አገር…………..



      የሚናገረው የማያጣ መንግስት፣ የሕዝቡ አመል የማይታወቅበት ፣ የሚያዳምጠው መሪ ያጣ ህዝብ ።ይህ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ። እኛ ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ የሚነገረን እንጂ የሚያዳምጠን መሪ ለማግኘት አለመታደላችን ። ያለመታደል ብቻ ሳይሆን ብናገኝ እንኳን አሜን ብለን ለመቀበል ያልታደልን ፍጥሮች ሆነናል ። ልክ እንደሌሎቹ የአፍሪካ ወንድሞቻችን ስልጣን የባለስልጣኖች እንጂ የሕዝብ ሆኖ አያውቅም ። በዚህ ሁናቴ ነበር ኢትዮጵያ ውስጥ አዳማጭ ያገኘ ሕዝብ መስለን ስንታይ የነበርነው ። ትንሽ ሰዎች ወይንም የስርሀቱ ደጋፊዎች እንሆናለን አድማጭ አግኝተን መላው ሕዝብ እንዳገኘ አድርገን ስንሰብክ የነበረው በውሸት ለማስመሰል አድማጭ መሪ እንዳለን ስናወራ ከነበረ ግን ውሸት የትም አያደርስምና ዋጋ መክፈላችን አይቀሬ መሆኑንም መረዳት መቻል ይኖርብናል ።  << የህዝብ ይሁንታ >> የሚለውን ቃል መቀለጃ ከሆነባቸው ሀገሮች መካከል አንዷ የኛዋ ኢትዮጵያ እንደሆነች መናገር ደፋር አያስብለኝም ። ደግሞ እናውራው ፣ እንፃፈው ከተባለ ምሳሌውስ ቢሆን ሞልቶ ተርፎን የለ።

Sunday, September 9, 2012

ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ.....

እያወቅን በትርጉም !
      የእድገትና ልማት አብሳሪው ብቻ የሆነውን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሁልጊዜ አንድም ፕሮግራም ሳያስቀር በንቃት እና በትግስት ከሚከታተሉት ውስጥ ነኝ ምክንያቱም ምንም አማራጭ ከሌለው ሰው ስለነበርኩ ። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ፕሮግራሙን ሲጀምር << እንደምን አመሻቹ ዲሽ የሌላችሁ >>  ብሎ የሚጀምር ሳተላይት ቴሌቪዥን ይመስለኛል። ውሸት የመሰራቤቱ ባህሪው ስለሆነ ማለቴ ነው ። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ስመለከት ምን ውሸት ተገኘ ብዬ ሰለምመለከት በትግስቴ ሁሉም ጓደኞቼ የቤተሰብ አባላት እንዲሁም የስራ ባልደረቦቼ እንደተደነቁብኝ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ።

Saturday, September 8, 2012

ኢትዮጵያን አትንኩ አትከፋፍሉ!!



        የኢትዮጵያ የገዥዉ መንግስት፣የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ተቋማት፣ድርጅቶችና በአጠቃላይ ግለስቦች ኢትዮጵያ የሚያገለግሉ እንጂ ከኢትዮጵያ በላይ አይደሉም :: በኢትዮጵያ ሊጠቀሙና ሊጠናከሩ የሚችሉትም ለኢትዮጵያ ሲሰሩና ለኢትዮጵያ ሲቆሙ ብቻ ነዉ።
     ኢትዮጵያን እያፈረሱ እንድትነካ  እንድትጎዳ እየሰሩና እየተንቀሳቀሱ ለኢትዮጵያ ቆሜያለሁ ማለት አይቻልም።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነት፣ የመስመር ልዩነት፣ የአመለካከት ፣የአስተሳሰብና የአፈጻጸም  ልዩነት ሊኖር ይችላል ቢኖርም አያስደንቅም :: የአመለካከት  ልዩነት ያለባትንና ዲሞክራሲ የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ለመገንባት ነዉ የምንመኘዉ የምንሰራዉም ነገር ግን የአመለካከትና ሌላም ሌላም ልዩነት ቢኖርም  ኢትዮጵያን በመጠበቅ ፣በማክበርና  በማስከበር  ልዩነት ሊኖረን አይገባም:: እዉነተኛ ኢትዮጵያዉያን ከሆንን ማለት ነዉ።

Thursday, August 30, 2012

Welcome to your Blog!!!!

እንኳን በደሕና መጣችሁ!!!!
ሰብኣዊ የናንተው መወያያ ድሕረገጽ ናት::
ሓሳባችሁን በጽሁፍ ኣካፍሉን::