በ106 አንቀጽ የተዋቀረዉን የኢህአዴግን ህገ መንግስት በጨረፍታ።
ያዉ ሁላችንም እንደምናዉቀዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ህገ መንግስት የተረቀቀዉ ከ18 አመት በፊት ህዳር 29/1987 ዓ.ም ነበር። ከነሐሴ 15/1987 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ዉሏል።
አንቀጽ 9/1 ህገ-መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ህግ ነዉ
አንቀጽ 10/2 የዜጎች እና የህዝቦች ሰብዐዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ
አንቀጽ 12/1 የመንግስት አሰራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት
ያዉ ሁላችንም እንደምናዉቀዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ህገ መንግስት የተረቀቀዉ ከ18 አመት በፊት ህዳር 29/1987 ዓ.ም ነበር። ከነሐሴ 15/1987 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ዉሏል።
አንቀጽ 9/1 ህገ-መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ህግ ነዉ
አንቀጽ 10/2 የዜጎች እና የህዝቦች ሰብዐዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ
አንቀጽ 12/1 የመንግስት አሰራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት
አንቀጽ 21/1 በጥበቃ ስር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸዉን በሚጠበቅ ሁኔታዎች ሜአዝ መብት አላቸዉ
አንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸዉ
አንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸዉ
አንቀጽ 27 ማንኛዉም ሰዉ የማሰብ የሕሊና እና የሃይማኖት ነፃነት አለዉ
አንቀጽ 29 ማንኛዉም ሰዉ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለዉን አመለካከት ለመያዝ ይችላል
አንቀጽ 30 የመሰብሰብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለዉ
አንቀጽ 32/2 ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገሩ የመመለስ መብት አለዉ
አንቀጽ 37 ፍትህ የማግኘት መብት
አንቀጽ 41/3 ማንኛዉም ዜጋ በመንግስት ገንዘብ በሚካሄዱ ማህበራዊ አገልግሎቶች በእኩልነት የመጠቀም መብት አለዉ
አንቀጽ 79/3 ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸዉን በሙሉ ነፃነት ያከናዉናሉ
አንቀጽ 87/5 የመከላከያ ሰራዊት ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያካሂዳል
አንቀጽ 91/2 የሀገር የተፈጥሮ ሀብቶችንና የታሪክ ቅርሶችን መጠበቅ የመንግስትና የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነዉ
አንቀጽ 92/2 ማንኛዉም የኢኮኖሚ ልማት እርምጃ የአካባቢዉን ደህንነት የማያናጋ መሆን አለበት
አንቀጽ 102/1 የምርጫ ቦርድ ነፃና ትክክለኛ ምርጫ በገለልተኝነት እንዲያካሂድ ከማንኛዉም ተፅዕኖ ነፅ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል እያለ ብዙ ህጎች ተጽፈዋል።የትኛው ህግ ተተግብሮ ያውቋል ውላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው !
የፕሬዝዳናቱን ስልጣን ገደብ አድርጎ የስራ ዘመን ስድስት ዓመት ሲሆን። ከሁለት ጊዜ በላይ ለፕሬዝዳንትነት ለመመረጥ አይችልም ይላል።
የጠቅላይ ሚኒስተሩን ስልጣንና ተግባር አንቀጽ 74 በደንብ ተቀምጧ ብዙ ስራዎችንም ያከናዉናል። አንቀጽ 75 ደግሞ ስለ ምክትል ጠ/ሚኒስተር ይናገራል።
እኔ ደግሞ ይሄን ህገ መንግስት የኢህአዴግ ሳይሆን የቀድሞዉ ጠ/ር መለስ ዜናዊ ህገ መንግስት ነዉ የምለዉ የሱን ስልጣን ገደብ ሳያደርግ የሌሎቹን ባለስልጣናት ስልጣን ገደብ ያደረገ ስለሆነ።
የቀድሞ አትበሉ ለካ ተብለናል ምክንያቱም በሱ ራዕይ እየተመራን ስለሆነ ብዬ ነበር። አለም ላይ ካሉ ሀገሮች በሞተ ሰዉ መንፈስ የምትመራ ብቸያዋ ሀገር ሳትሆን አትቀርም። ETV የሞተ ሰዉን ማስነሳት ቢችል እንደ አላዛር ሟች መለስ ዜናዊን ያስነሳዉ ነበር።ሙት ለሙት ያለቅሳል አይደል የሚለዉ ብሂሉ !!
እሽ ኋይለ ማርያም ደሰለኝን ማን እንበለዉ የአሁኑ ወይስ የድሮዉ እሱ ግን ማንም ቢባል ምንም ምንም አይመስለዉም። እነዚህን አንቀጽ የጠቃቀስኩት ከብዙ በጥቂቱ በኢህአዴግ መንግስት የማይተገበሩ የህገ መንግስት ክፍሎች ስለሆኑ ነዉ።ለአገራችን የህዝብ ጭሆት የሚሰማ መንግስት ይስጠን !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
No comments:
Post a Comment