Monday, December 31, 2012

የተቃዋሚ 33 የፓለቲካ ድርጅቶች ያቆቆሙት ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ሊከሰው መሆኑን አስታወቀ


ታህሳስ 22 2005 ዓ ም
 የምርጫ  ቦርድ ከፍተኛ ሀላፊ የኢህአዴግ አባል ሆነው ለክልልምምክር ቤት አባልነት ምርጫ መወዳደራቸውንም አጋልጦል።
ጊዜዊ ኮሚቴው ለምርጫ ቦርድ ባቀረበው 18 ጥያቄዎች ማስረጃ ያላቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ምርጫ ቦርድን ለፓርላማ አፈጉባኤ እንደሚከስ አስታውቆል።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአስተባባሪ ኮሚቴው የቀረቡት 18 ጥያቄዎች ማስረጃ የላቸውም ብሎ ጥያቄዎቹን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ነው ወሳኝ ያላቸው ማስረጃዎች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ኮሚቴው ይፋ ያደረገው።

ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚዎች የቀረቡትን ቅሬታዎች ለወር ያህል ከገመገምኩ በሆላ ሰጠሁ ያለው ምላሽ አሳፋሪና ነገ በህዝብ ዘንድ የሚያስወቅስ መሆኑን ያመለከተው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድማስረጃ እንድናቀርብ ሳይጠይቀንና ሳያነጋግረን ውሳኔውን በመንንግስት ሚዲያ ማወጁ አሳዝኖናል ብለዋል።
የጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴው አባልና የቦርድ አመራር አቶ ገብሩ ገብረማሪያም ከጋዜጠኞች ምን ማስረጃ አላችሁ ተብለው ለቀረበ ጥያቄ ለሁሉም በቂ ማስረጃ አለን በማለት የምርጫ ቦርድ  የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሬት ዳይሪክተር ወ/ሮ የሺ ፍቃደ የኢህአዴግ አባል ሆነው ለምርጫ የተወዳደሩበት ማስረጃ አቅርበዋል።:
የክልል ም/ቤት አባላት ምርጫ ጣቢያ የድምጽ ቆጠራ ውጤት መተማመኜ በሚለውና የምርጫ የምርጫ ቦርድ አርማ ባለበት በዚህ ሰነድ የእጩ ተወዳዳሪዋ የወ/ሮ የሺ ፍቃደ ስም የሚገኝበት፡ በብአዴን ፓርቲ በንብ ምልክት ፡ እየታዩ ያመጡት የድምጽ ብዛትና ደረጃቸው የሰፈረበት ፡ ለአማራ ክልል ምክር ቤት የደብረ ብርሀን እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን ያሳያል።
የጊዜያዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ አንድም ማስረጃ የሌለው ጥያቄ አላቀረብንም ፡ ካሉ በሆላ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጸሚ በመሆኑና ሊያነጋግረንም ፡ ማስረጃ እንድናቀርብ ሳይጠይቀንም ጥያቄያችሁን ውድቅ አድርጌያለሁ ማለቱ እንዳሳዘናቸው ገልጠዋል።:
                                                                         ከሰብኣዊ

    1 comment:

    1. ሚስተር ቤንጃሚን የኢሜል ዝርዝሮችን እነሆ ፣ Lfdsloans@outlook.com ፡፡ / ወይም ደግሞ ንግዴን ለመጀመር በ 90,000.00 ዩሮ ብድር የረዳኝ WhatsApp + 1-989-394-3740 እና እኔ በጣም አመስጋኝ ነኝ ፣ እዚህ አንድ ነጠላ እናት ነገሮች እንዳላደረጉ መንገድ ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው ፡፡ ከእኔ ጋር ቀላል ይሁኑ ግን ንግዴ እየጠነከረ ሲመጣ እና እያሰፋ ሲሄድ እያየሁ በሚስተር ሚስተር እርዳታ ፊቴ ላይ ፈገግታ አሳየኝ ፡፡ የገንዘብ ድጋፍን መፈለግ ወይም በዚያ ንግድ ውስጥ መከራን ማለፍ ወይም የመነሻ የንግድ ሥራ ፕሮጀክት መጀመር መፈለግ ይህንን ማየት እና ከችግራቸው ለመውጣት ተስፋ ሊኖረው ይችላል ... እናመሰግናለን ፡፡

      ReplyDelete