Saturday, December 29, 2012

እስኪ ይሁና!

ጎበዝ በዚህች መከረኛ አገራችን የመጣ የሄደው በሕዝብ ስም ራሱን ሲያዋድድ አልኖረምና ነው የእኔ የሚገርማችሁ? ወደን ነው እንዴ ኢቲቪን የተቀየምነው? አንድ የልማት ዜና አንድ ወር እየተረከልን ለሌላ ሥራ ከማነሳሳት ይልቅ እያኩራራ ስላሰነፈን ጭምር እኮ ነው። አቤት! ስንቱ በራሱ ዓለም ትልቅ ነኝ ሲል ወደቀ መሰላችሁ? እኔማ ስንቱን እታዘበዋለሁ ይብላኝ እንጂ ማስተዋል ለተሳነው።
‹‹እኔምለው ማስተዋልና ማመዛዘን የሚባሉትን የጠቢብ ሰው መለያዎች ከፈረንጅ አገር ማስመጣት ይቻል ይሆን እንዴ?›› በማለት ጓደኛሄን ተየቁ? ‹‹አንተ ደግሞ ሰው ያው ሰው አይደል እንዴ? ፈረንጅ እንደ ቁሳቁስ ያልካቸውን ነገሮች ማምረት ቢችል ኖሮ ስንቱን አስቀያሚ ታሪክ ባልተጻፈ ነበር፤›› አለኝ። እኔማ ፈረንጅ የማይፈበርከው የለም ከሚል የሞኝ አስተሳሰብ መላ ያገኘሁ መስሎኝ ነበር። ‹‹የቸገረው እርጉዝ ያገባል›› ነዋ ተረቱ። ኧረ ዘንድሮ ነገር ያረገዘው በዝቷል!     
                                    ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!


No comments:

Post a Comment