Saturday, December 22, 2012

ቤተ-ክርስቲያን ቤተ-መንግስት ሲሆን ዝም ብለን ማየት የለብንም!

ቤተ-ክርስቲያን ቤተ-መንግስት ሲሆን ዝም ብለን ማየት አጢያትም ወንጀልም ነው፤የወያኔ መንግስት ከቤተ-ክርስቲያን ላይ እጁን ያንሳ!! በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም ያሉ ብጹሃን አባቶቻችን እርቀ ሰላም አውርደው በእምነታችን ደንብ እና ሰርዓት መሰረት ሁሉ ነገር እንዲፈጸም የክርስቲያን ልጆች አጥብቀን መትጋት አለብን፡፡

መልእክት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች እንዲሁም መንግስት በሀይማኖቶች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ለምትቃወሙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ።
የኢህአዴግ መንግስት ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ፈተና ሲደርስባት ኖሯል ።ያለፈውን ሁሉ ለእግዚሐብሄር ሰጥተን ቤተ ክርስቲያናችንን አንድ እንዲያደርግልን አምላካችንን በፀሎት በምንጠይቅበት በዚህ ሰዓት ሌላ ፈተና ከፊታችን ተጋርጧል።በመንግስት ግፊት በእኛም የሀጢያት ብዛት ከሁለት የተከፈለው ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ ሆኖ በአባቶቻችን መሀከል የተከሰተውም ችግር በእርቅ ይፈታል ብለን በምንጠብቅበት ጊዜ መንግስት እንደ ዛሬ 20 ዓመቱ ሁሉ የአምላካችንን ትእዛዝ ተቀብሎ የምእመናን እረኛ የሚሆነንን አባት ሳይሆን የኢህአዴግን ፖሊሲ በቤተክርስቲያናችን የሚያሰፍን "አባት" ሊሾምልን ዝግጅቱን ጨርሷል።እኛም እንደ አለፉት አመታት የመንግስትን ጣልቃ ገብነት በዝምታ አንመለከትም ያልን የቤተክርስቲያን ልጆች ይህንን የቤ/ክርስቲያናችንን ቅፅር የተዳፈረ ህገ ወጥ ተግባር የቤ/ክርስቲያናችንን ስርዓት በጠበቀ መልኩ እንዴት መቃዎም እንዳለብን የምንወያይበት"የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል I do Care about EOTC" የሚል ሁሉ ከቤተክርስቲያን ጎን ይቁም !!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
            ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment