Friday, May 31, 2013

Dozens protest Blue Nile dam move outside Ethiopia's Cairo embassy

Limited demonstration erupts outside Ethiopian embassy in Cairo as activists protest perceived infringement on Egypt's traditional share of Nile water
Dozens of Egyptian protesters gathered outside the Ethiopian embassy in Cairo on Friday to protest Addis Ababa's decision earlier this week to temporarily divert the course of the Blue Nile as part of a project to build a series of dams on the river.
Protesters held banners aloft reading, "We reject attempts to take our Nile Water." Others chanted: "We are the source of the Nile Basin."
"After Ethiopia's surprising decision, bilateral relations have now been put to the test," according to a statement by the 'Copts without Borders' group, one of the protests' main organisers.
The statement added: "Any agreement between President Mohamed Morsi's government and its Ethiopian counterpart will not be recognised, since Morsi has lost all legitimacy before the Egyptian people."

ሃምሳም ሰውም ይውጣ ሃምሳ ሺህ ግን አንድ ፀባይ እሱም “ፍፁም ሰላማዊ!”abetokichaw

935293_421802944584325_731290226_nአቤት የርዕሴ ርዝመት… ደግሞ በዛ ላይ ቀጥሎ የምናገረውን ማሳበቁ! “ቢወዳት ነው ቢጠላት ባሏ በሻሽ አንቆ ገደላት” አይነት ሆነኮ፡፡
ለማንኛውም ቀጥሎ ስለ ሰላማዊ ሰልፉ ጥቂት ልናወጋ ነው፡፡ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ እና በጥቅሉ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ስለ ሰላማዊ ትግል ስናወራ ስለ ሙስሊም ኢትዮጵያውን በማውራት ብንጀምር የወጋችንን ደረጃ ከፍ ደርገዋል ሞገስም ይሰጠዋል እና  እንቀጥል…
መንግስታችን በዛን ሰሞን በገዛ ቴሌቪዥኑ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ተቃውሞ በሌላው ህብረተሰብ ላይ የተቃጣ ትንኮሳ አስመስሎ ኮሳሳ የሆነ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሲሰራ አይተን ታዝበን ታዝበን ታዝበን አልወጣልንም፡፡
በተደጋጋሚ እንዳየነው ሙስሊም ኢትዮጵያውን ከአመት በላይ በመስጂዳቸው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ያሳዩን ጨዋነት ገዢዎቻችንን ያሳፈረ ነበር የሚለው ቃል አይገልፀውምና “አፈር ያስበላቸው ነበር” ማለት ይሻላል፡፡ (አረ እንደውም አፈር ደቼ እንበል እንጂ… ሃሃ… “ደቼ” የምትለውን ቃል ትርጓሜ ከሳቴ ብርሃን መዝገበ ቃላትን ላይ ባገላብጥም፤ ደቸር፣ ደቻሪ ደቻራ፣ ደችሮ ብሎ ይዘላታል እንጂ ትርጉሟን አላስኮርጅ አለኝ…) የምር ግን የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጨዋነት የተላበሰ ተቃውሞ ገዢውን እና አሳሪውን መንግስታችንን አፈር ደቼ ያበላ ነበር ከሚለው ውጪ ገላጭ ቃል ከየት ይገኝለታል?

መኢአድ አንድነት ከሰማያዊ ጎን ቆሙ – ከግርማ ካሳ

Muziky68@yahoo.com
ግንቦት 22 ቀን 2005. .
ዜጎች ሃሳባቸዉን በነጻነት የመግለጽ፣ የመሰባሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙሉ መብት አላቸው። ይሄንን መብት በመጠቀም አገር ቤት የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ፣ በአፍሪካ ሕብረት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ይጠራል። ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት፣ ለባለስልጣናት ሰልፍ እንደተጠራ ማሳወቅ ብቻ ስለሚያስፈልግ፣ የፓርቲዉ አመራር አባላት ማስታወቂያ ለማስገባት ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር ይሄዳሉ። የአስተዳደሩ ሃላፊዎች ግን ሊያናግሯቸውም ሆነ ማስታወቂያዉን ሊቀበሏቸው ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀረ። ተደጋግሞ ሙከራ ቢደረግም፣ በሕጉ መሰረት የሰማያዊ ፓርቲን ማስታወቂያ ተቀብለው፣ አስፈላጊዉን ትብብር ማድረግ የነበረባቸው የኩማ ደመቅሳ ሰራተኞች ግን ዜጎችን ማንገላታት መረጡ።ዜጎች ሰልፍ በሚጠሩበት ጊዜ ለባለስልጣናት የሚያሳዉቁት፣ ፍቃድ ለመጠየቅ ሳይሆን፣ የትራፊክ መጨናነቅ፣ የኮንስትራክሽን ግንባታዎች የመሳሰሉ ችግሮች ካሉ፣ አስፈላጋዊዉን ዝግጅት ማድረግ፣ ያም ካልተቻለም ደግሞ ሰልፉ የሚደረገበትን ሌላ አማራጭ ቦታ ወይንም ጊዜ በመግለጽ፣ እንዲተላለፍ መጠይቅ ይችሉ ዘንድ ነዉ።

Thursday, May 30, 2013

የግንቦት 7 ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ህዝቡ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረበ

የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ከግንቦት 11 – 19/2005 አ/ም በበርካታ ወቅታዊ፣ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እና የድርጅቱን አዲስ ም/ቤት በመምረጥ ወያኔን በማስወገድ ረገድ ሊከተል የሚገባውን ጠቋሚ አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን ከተሳታፊው በመውሰድ ወሳኝ የሆነ ውይይት አድርጓል።
ንቅናቄው ከተለያዩ አለማት በአባላት የተወከሉ ጉባኤተኞች እና በተለያዩ የስራ ክፍል የሚገኙትን የድርጅቱን አባላት ያሳተፈ፤ ከዚህ በፊት ከተደረጉትም ጉባኤዎች እጅግ የላቀ አባላት የተገኙበት ነበር።
ጉባኤው የነበረውን የም/ቤት ሪፖርት፣ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኦዲትና ማናጅመንት ኮሚሽን፣ የግልግልና ዳኝነት ኮሚቴን እና የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማዳመጥ ጥልቅ የሆነ ወይይቶች አደርጓል።
የግንቦት 7 ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች፤ ደርጅቱ የጀመረውን ወያኔን የማስወገድ ትግል በየትኛውም አቅጣጫ አስፈላጊ ሆኖ የታመነበትን ማናቸውም መንገድ ሁሉ በመጠቀም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የዘረኝነትን ስርአት ድባቅ መምታት፤ አልፎም ዘላቂ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አስቸኳይና ማንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ግዴታው አድርጎ መውሰድ ያለበት አጣዳፊ ስራ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰላም አየርና የዲሞክራሲ ጮራ ሁሌም የሚፈነጥቅባት፣ ህዝብ ካለፍርሃትና ሰቀቀን ወጥቶ የሚገባባት፣ ህዝብ በነጻነት የፈለገውን ፓርቲ የሚመርጥበት፣ የሚያወርድበት፣ ስልጣን የህዝብ መሆኑን የሚረጋገጥበት፣ የመንግስት አካላት ለህዝብ ተጠያቂ የሚሆኑበት፣ ነጻ ሚዲያ ለመልካም አስተዳደር ግንባታ የሚያገለግልበት፣ ፍትህ ለሁሉም በእኩል የሚሰጥበት፣ ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎች የመኖር፣ ሀብት የማፍራት፣ ቤተሰብ የመመስረት፤ ከቦታ ወደ ቦታ ያለምንም ገደብ የሚንቀሳቀሱበት መብት እንዲኖራቸው፣ እና የሃይማኖት ነጻነት ይኖረን ዘንድ የድርጅቱ ጉባኤተኞች ሙሉ መሰዋእት ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ሲሉ በድጋሚ ቃል በመግባት መራራ የሆነውን ትግል እጅ ለእጅ ተያይዞ ተራራውን ለመውጣት እና ለማቋረጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

Wednesday, May 29, 2013

ሙስናም የኢኮኖሚ ዕድገቱ ውጤት ነው እንዳንባል ሰግቻለሁ!

ከኤሊያስ
ያልተዘመረላቸው ጃንሆይ እየተዘመረላቸዉ ነው! (ዕድሜ ለአፍሪካ 50ኛ ዓመት!)
የፓርላማ አባላት የመንግስት ባለሥልጣናትን እያፋጠጡልን ነው (እሰይ!)
ወደፊት ለምትመሰረተው “አንድ አፍሪካ” የሂሩት በቀለን ዘፈን መረጥኩላት!
  ሰሞኑን በኢቴቪ እየቀረበ ያለውን የሙስና “ድራማ-መሳይ” ማስታወቂያ አይታችሁልኛል? መቼም ይሄንን የፀረ-ሙስና ዘመቻው አካል ነው ማለት በጣም ያስቸግራል፡፡ (ሙስናን ለማባባስ ያሰበ ወገን አለ እንዴ?) የአንድ መ/ቤት ሃላፊ (ካድሬ ይመስላል) ሠራተኞቹን ሰብስቦ ሙስናን በጋራ መታገል እንደሚገባቸው ሲደሰኩር ነው ሞባይሉ የሚጮኸው፡፡ ይቅርታ ጠይቆ ስብሰባውን አቋርጦ ይወጣና ቢሮው ውስጥ ከባለሃብት ጋር ይወያያል (የሙስና ውይይት እኮ ነው!) በመጨረሻም ከባለሃብቱ በፖስታ የታሸገ መጠኑ የማይታወቅ ገንዘብ (ሙስና) ተቀብሎ ወደ ሙስና ስብሰባው ይመለሳል፡፡ ከዚያም ምንም እንዳልተፈፀመ “ሙስናን በቁርጠኝነት መታገል አለብን” የሚል የካድሬ ሰበካውን ይቀጥላል፡፡ በዚሁ ነው የሙስና ማስታወቂያው የሚቋጨው፡፡
(ሳይጀመር እኮ ነው ያለቀው!) ቆይ ዓላማው ግን ምንድነው? መቼም አስመሳይ ሞሳኞችን ማስተዋወቅ አይመስለኝም (ምን ሊሰራልን?) ወይስ ለማዝናናት ዓላማ የተሰራ ነው? (እንደኔ ግራ ከመጋባት ይሰውራችሁ!) እኔ ከማስታወቂያው የተረዳሁትን ልንገራችሁ? “ሙስናም ሰርቶ በሰላም ስብሰባን መቀጠል ይቻላል!” የሚል ነው፡፡ እውነቴን እኮ ነው---ከሙስና በኋላ ኑሮ ያለችግር ይቀጥላል የሚል መልዕክት ነው ያለው። (ሞሳኝ እንዳይቀጣ የሚደነግግ ህግ ወጣ እንዴ?) አያችሁ … የሙስናን ነገር አላምነውም፡፡ ወረርሽኝ ነገር እኮ ነው! እናም ሞሳኙ ሳይቀጣ የሚጠናቀቅበት የሰሞኑ ማስታወቂያ ሙስናን እንደሚፀየፍ አንድ ዜጋ አልተመቸኝም ለማለት ያህል ነው፡፡

ማንዴላ በመጨረሻዋ የፍርድ ቀን ለዘረኞች ያለው

ሉሉ ከበደ
ኢትዮጵያን በቁጥጥሩ ስር ያዋላት የትግራይ ዱር አራዊት ቡድን ዛሬ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየጫነ ያለውን የአፓርታይድ አይነት ስራት እነ ኒልሰን ማንዴላ ከደቡብ አፍሪካ ምድር ከስሩ መንግለው ለመጣል እጅግ ብዙ መስዋእትነትና ምእተ አመት የሚጠጋ ጊዜ ነበር የወሰደባቸው።Former South African president Nelson Mandela
ምእራቡም ሆነ ምስራቁ አለም ለአፍሪካውያኑ የነጻነት ትግል ፈጥኖ እውቅናና ድጋፍ አለመስጠቱና በተለይ ምእራቡ ከነጮቹ ጋር ተመሳጥሮ በተዘዋዋሪ እነሱን መደገፉ ትግሉ ረጅም ጊዜ እንዲወስድና የነጻነቱም ቀን እንዲርቅ ቢያደርገውም፤ በትግሉ መሪዎች ፍጹም ቆራጥነትና ለሞት መዘጋጀት እንዲሁም በህዝቡ አንድነትና ጽናት አፓርታይድ ተወግዶ የደቡብ አፍሪካ ህዝብ መሪ መሾምና መሻር ችሏል በነጻነት።
እርግጥ  በኢትዮጵያ የበላይነቱን የተቆጣጠሩት የህውሀት ዘረኛ ሰዎች ከደቡብ አፍሪካ ነጮች ጋር ሊያነጻጽራቸው የሚያስችል ስልጣኔና ለነጩ አለም ቀረቤታ አላቸው ባንልም፤ ለሀያላኑ መንግስታት በሎሌነት እስከቀረቡና የሚታዘዙትን እስከፈጸሙ ድረስ ድጋፋቸውን እንደማይነፍጓቸው ባይናችን እያየነው በመኖር ላይ ነን። ይሁንና ከሁሉም በላይ ለወያኔ መቅበጥና ከልከ ማለፍ፤ ለነሱ የልብልብ ማግኘትና በላያችን ላይ መግነን ተጠያቂው እራሳችን ነን። አንድ ሆነን በቶሎ እነሲህን የኢጣሊያ ጣእረመንፈስ ነጋሲያን ፋሺሽቶች ማስወገድ ተስኖን የህዝቡን ደም እየጠቡ፤ የሀገሪቱን ሀብት እየዘረፉ መወፈራቸውን ቀጥለዋል።

ኢህአዴግ የሚያሸንፈው መቼ ነው?

ጌታቸው ሽፈራው
መቼም ይህን ጥያቄ ስጠይቅ የግንቦት 20ን ‹‹ድል››፣ የ2002ና የባለፈውን ሚያዚያ 2005 ዓ/ም የቀበሌ፣ የወረዳ……ምርጫም ጨምሮ በመከራከሪያነት በማንሳት ምን ነካው ኢህአዴግ እኮ እያሸነፈ ነው የሚሉ አይጠፋም፡፡ ለእኔ ማሸነፍ ማለት የህዝብን ልብና አዕምሮ (hearts and minds) መያዝ ሲቻል ነው፡፡ በሀይልማ ከሆነ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ በአጠቃላይ ቀኝ ገዥዎቹ አፍሪካውያንን በወታደራዊ ሀይልና በሌሎች አቅሞቻቸው በመብለጣቸው እስከ መቶ አመት ድረስ ገዝተዋል፡፡ በኤሲያን ደቡብ አሜሪካ ደግሞ ከ200 እስከ 800 አመትም የተገዙ ህዝቦች ነበሩ፡፡ ለጊዜው አሸናፊ የመሰሉት ቅኝ ገዥዎች የእነዚህን ህዝቦች ልብ መግዛት ባለመቻላቸው ጊዜ ጠብቀውም ቢሆን ተሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ ኢህአዴግ አሸነፍኩት የሚለውን የመንግስቱ ሀይለማሪያም ደርግ ጨምሮ ህዝባቸውን በሀይል ጨምድደው የኖሩ ስርዓቶች የኋላ ኋላ ተሸንፈዋል፡፡ እነዚህ አካላት የተሸነፉት ህዝብን በሀይል እንጂ በሀሳብ ማሳመን ባለመቻላቸው ነው፡፡ ሰውን በሆዱ አሊያም በግድ ለዘላለም መግዛት አይቻልም፡፡ አንድም የሚፈልገው ነገር በየጊዜው ስለሚጨምር ይህን በየጊዜው የሚጨምርን ነገር ማሟላት አይቻልም፡፡ ማሟላት ቢቻል እንኳ ሰው የመጨረሻ ፍላጎቱ ነጻነት ነውና ዳቦ ጠግቦም ሆነ ሳይጠግብ ነጻነቱን መጠየቁን አያቆምም፡፡

Tuesday, May 28, 2013

የኢህአዴግ የታሪክ ሽሚያ አሁንም ቀጥሏል፡፡

የኢህአዴግ የታሪክ ሽሚያ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ኢህአዴግ ታሪክን በራሱ አስተሳሰብ ከመተርጎም ባለፈ የራሱ ለማድረግ በርካታ ሙከራዎችን አድርጓል፡፡ ኢህአዴግ መለስ ይህን ያህል ባላበረከቱበት አሊያም ተቃራኒውን ሚና በተወጡበት ‹‹መለስና የብሄር ጥያቄ›› የሚል መጽሐፍን በትዕዛዝ አጽፏል፡፡ ታዲያ በትዕዛዝ ካልሆነ ጤነኛ ሰው ደግሞም ‹‹ምሁር›› ያውም ብቸኛው አለማቀፍ ዩኒቨርሲቲ በሆነው የቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዴት እንዲህ አይነት መጽሐፍ ይጽፋል? አንዳንዶቹ እንደሚሉት ደግሞ ኢህአዴግ በዚህ ከቀጠለ ‹‹መለስና የአድዋ ድል!›› የሚል መጽሐፍም በቅርቡ ሊታተም ይችላል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በዚህ ርዕስ ስም በትዕዛዝ ለመጻፍ የማያንገራግሩ ምሁራን ሞልተውታል፡፡ መቼስ ቢሆን አቶ መለስ በጊዜው ባይኖሩም ጣሊያን ኤርትራን ቆርጦ ባስቀረበት ጦርነት የመሪያችን አያት ከጣሊያኖች ጎን ሆነው መዋጋታቸው ከብሄር ጥያቄው በተሻለ ከአቶ መለስ ታሪክ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ይኖረዋልና በአድዋ ጉዳይ መጽሐፍ ቢጻፍበት የሚያስገርም አይሆንም፡፡ የአቶ አስረስ የልጅ ልጅ ደግሞ ይችውን ኤርትራን ‹‹የኤርትራ ህዝብ ከየት ወደ የት?›› በሚል ‹‹የአብዮታዊ ዴሞክራሲ›› መጽሐፍ አጋዥነት ዳግም ከኢትዮጵያ እንድትለይ አድርገዋል፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ‹‹ሌጋሲ›› ማለት! ያውም አቶ ኃይለማሪያም አስቀጥለዋለሁ እንደሚሉት ‹‹ባዳ›› ሳይሆን የአያት!
አሁንም የኢህዴግ የታሪክ ሽሚያ ቀጥሏል፡፡ የአባይ ግድብ የኢህአዴግ ግድብ አይደለም፡፡

“አባይ ይገደብ፤ ኢህአዴግም ይገደብ፤ አባይ ይቀየስ ኢህአዴግም ይቀየስ!”

አቤ ቶክቻው
“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ጉንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አለ ታጋዩ…
“የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ከዚህ በፊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዮ ጣቢያ አሁን ደግሞ ለራሱ ጥቅም ተቆጣጥሮታል፡፡ ቆጣጥሮታልም፤ ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ መህረት!” አልኩ እኔ…
“ኢህአዴግ ደርግን ደመሰሰ እና ሌላ ቀዳበት” አለ ልጅ ያሬድ! ”ኢህአዴግ ደርግን ደምስሶ በደርግ ዜማ ሌላ ቀዳበት” አልኩ እኔ
ዛሬ ግንቦት ሃያ ነው፡፡Abe Tokichaw (Abebe Tolla) the Popular Ethiopian Political Satirist
አነዛ ፀጉራቸውን አሳድገው አዲሳባ የገቡ ሰዎች ዲሞክራሲን እና መልካም አስተዳደር ያሳድጉልናል… ብሎ ተስፋ የጣለባቸው ሁሉ በቴስታ ብለው ከጣሉት እነሆ ሃያ ሁለት አመት እንደዋዛ ሆናቸው፡፡
መልካም አስተዳደሯንም ለራሳቸው እያደሯት፤ ዴሞክራሲዋንም ራሳቸው እየኮመኮሟት ህብረተሰቡን እንቁልጭልጭ አሉት፡፡
ዛሬ የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር የአባይ ወንዝን የማስቀየስ ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ ወንዙ ተቀይሶ ምን ላይ ሊሆን ነው… እንዴት ነው ነገሩ በሳፋ ነው እንዴ ግድቡ የሚሰራው… ብዬ ልጠይቅ ወይስ አልጠይቅ…!
አስታውሳለሁ፤ “አባይ ይገደብ በቃ” ብለው ጠቅላዩ የወሰኑት ከሁለት አመት በፊት “በቃ” በሚል ሀይለ ቃል …ኢህአዴግ ይበቃዋል ግንቦት ሃያን ዘንድሮ ለመጨረሻ ጊዜ እናከብራለን ከዛም ለድጋፍ ሰልፍ ወጥተን በዛው እንቀራለን፡፡ ኢህአዴግ እስካልወረደ ድረስም እቤታችን አንገባም…. የሚል እንቅስቃሴ በፌስ ቡክ በኩል ተጀምሮ የነበረ ጊዜ ነው፡፡

Monday, May 27, 2013

ደርግን በደርግ የተካው ግንቦት 20

ዳዊት ሰለሞን
በአስራ ሰባት መርፌ
በጠቀመው ቁምጣ
ለለውጥ ያጎፈረው
ስልጣን ላይ ቢወጣ
አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ
(
ቴዲ አፍሮ)
ግንቦት 20/1983 በኢትዮጵያ የመንግስት ለውጥ የተደረገበት በመሆኑ ቀኑ በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ህይወት ውስጥ ያሳደረውና በሂደትም የሚያሳድረው ተጽእኖ ለውጡን በፈጠሩት አካላት ዲስኩር ብቻ ተተንትኖ ያበቃል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ለውጡን የማይደግፉትና በለውጡ አቀንቃኞች ‹‹የቀድሞው መንግስት ናፋቂዎች›› የሚሰኙት ጭምር በአንድም በሌላም መንገድ ቀኑ ይነካቸዋልና ድምጻቸውን ሊያሰሙ ይገባቸዋል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግንየኢትዮጵያቴሌቪዥን 1984 ግንቦት ሃያ ጀምሮ ስለ ቀኑ እንዲናገሩ ሰፊ የአየር ሰዓት የሚቸራቸው ለተጋዳላዮቹ ብቻ ነው፡፡