Friday, May 3, 2013

መልመድ ፈሪ ያደርጋል!


አንዳንዴ ግን ማብራሪያ ጥሩ ነው- “ሚስአንደርስታንዲግ” ያስወግዳል። ባለመግባባት ስንት ችግር ይፈጠር መሰላችሁ! ትዳር የሚፈርሰው፤ ባልንጀሮች የሚጣሉት፤ አገራት ጦር መዘው የሚዋጉት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስ በእርስ የሚናጩት … ወዘተ በአለመግባባት እኮ ነው። አሁን ለምሳሌ ወያኔ/ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች እንዲህ አይጥና ድመት የሆኑት ለምን ይመስላችኋል? የርዕዮተ ዓለም ወይም የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነት እንዳይመስላችሁ፡፡ ወደድንም ጠላንም ሁለቱም የሶሻሊስት ልጆች ናቸው፡፡ ግን በአደባባይ ይሄን ማንነታቸውን መግለፅ ይፈራሉ፡፡ (ኢህአዴግ ሶሻሊዝምን መሳቢያ ውስጥ ከተነዋል ብሏል እኮ!) እንዴት አይፈሩ! (ኧረ ማፈርም አለባቸው) አንደኛ ሶሻሊስት ነን ካሉ የህዝብ ተቀባይነት ያጣሉ። ሁለተኛ ፋሽኑ ያለፈበት ርዕዮተ ዓለም ነው - ሶሻሊዝም!! ለዚህ እኮ ነውወያኔ/ኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነኝ ሲል ተቃዋሚዎች ደግሞ ሶሻል ዲሞክራት ነኝ የሚሉት (የቸገረው እርጉዝ ያገባል አሉ!) በነገራችሁ ላይ የህወሃት የጥንት መስራችና የልባቸውን ያለ ይሉኝታ በመናገር የሚታወቁት አቦይ ስብሃት፤ ባለፈው ሳምንት  በሰጡት ኢንተርቪው ተዝናንቼአለሁ፡፡ አንዳንዴ ሳስበው አቦይ ስብሃት አሁን ፖለቲካን እንደ “ሲርየስ” ሥራ ወይም ሙያ ሳይሆን እንደ መዝናኛ (Hobby) ዓይነት የያዙት ይመስለኛል፡፡ ከሚሰጡት መልስ ተነስቼ እኮ ነው፡፡ ምን ነበር ያሉት? “በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ካፒታሊዝምን እንገነባለን!” ከምራቸው ነው ወይስ ሙድ ሊይዙብን ፈልገው ነው?


“በአፍሪካ ኢህአዴግን የሚስተካከል ፓርቲ የለም” ያሉም መሰለኝ፡፡ ይህቺ እንኳን እሳቸው ብቻ ሳትሆን የፓርቲው የራሱ አቋም መሆን አለበት። ግን እኮ ከተመኙ አይቀር ለምን ትልቅ ትልቁን አይመኙም? “በዓለም ኢህአዴግን የሚያህል ፓርቲ የለም!” ቢሉም እኮ ይችላሉ፡፡ (ሁለቱም ምኞት ነው ብዬ ነው!) እኛ እንደሆነ እንኳን ከአፍሪካ ከማርስም ቢሉ ለምደነዋል - አይሞቀን አይበርደን፡፡ አንዳንዴ እኮ መልመድን የመሰለ ነገር የለም። ኢህአዴግንና ስድቡን እንደ ለመድነው ወይም ደግሞ የተቃዋሚዎች የእርስ በእርስ ሽኩቻ እንደማይገርመን፡፡ (ላያስችል አይሰጠው አሉ!) እውነቴን እኮ ነው … እንደኛ ከሁሉም ነገር ጋር የሚላመድ ህዝብ የትም አይገኝም፡፡ እስቲ አስቡት ባሻው ጊዜ እልም የሚለውን መብራት በደንብ ለምደነው ድምፃችችንን አጥፍተን እየኖርን ነው - በጨለማና በብርሃን መሃል፡፡ የቴሌኮምን የሞባይል “ኔትዎርክ አልባ” አገልግሎት እንዲሁም ቀርፋፋ (Slow) ኢንተርኔት ለምደነው እየኖርን አይደለ! በሶስት ቀን አንዴ … ያውም ከሌሊቱ 9 እና 10 ሰዓት የምትመጣውን ውሃ ለመቅዳት እንቅልፋችንን መሰዋት ብቻ ሳይሆን ውሃ ካለበት ሰፈር በጀሪካን ማምጣትና ማስመጣቱንም ለምደነው እየኖርን ነው፡፡
በወያኔ መበደልን፣መገፋትን፣መሰረቅን፣መዋሸትን፣መደብደብን፣መታሰርን፣መሰረቅን፣መገንጠልን በፍራት ለመድን ! ጎበዝ እስከ መቼ? መልመድ ፈሪ ያደርጋል።
ህዝቡ በአደራ የሰጣቸውን ሃብት (መሬትና ሌላም) ቸብችበው ራሳቸውን የሚያበለፅጉ ወያኔ/ኢህአዴግ ሙሰኛ ሹማምንትን ችለናቸው ለምደነው እኮ ነው የምንኖረው - ለመድናቸዋ! በቀደም ዕለት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የከተማዋ ነዋሪዎች በታክሲ ሹፌሮችና ረዳቶቻቸው ስለሚደርስባቸው በደሎች ተጠይቀው ሲመልሱ “ህዝቡ ሁሉ አንሳፈርም … ቢል እኮ …” ያሉ መሰለኝ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ እውነት ብለዋል፡፡ ችግሩ ግን እኛ አንልም! እንደሱ ከማለት ይልቅ መልመድ ነው የሚቀናው፡፡ ለዚህ እኮ ነው የሹፌሮችን ማቆራረጥና ተሳፋሪ ማንገላታት ብቻ ሳይሆን የታክሲ ወረፋን በአንዴ ለምደነው ቁጭ ያልነው (ወረፋን እንኳ ደርግም አስተምሮናል!) እንዲያ ባይሆንማ … መጀመርያ ችግር ውሰጥ የሚገባው እሳቸው የሚመሩት መንግስት ነበር፡፡ ለሁሉም ነገር ተጠያቂው እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች ነን ?
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment