Wednesday, May 22, 2013

‹‹አድርባይነት›› የወያኔ/ኢህአዴግ መለያ ባህሪው ነው።‹‹አድርባይነት›› ምን ማለት ነው?


አንድ መልካም እድል ሲገኝ በዚያ ዕድል ቀዳሚ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያንቀዠቅዥ ልክፍት አለ። የዚህ ልክፍት መጠሪያም ‹‹አድር ባይነት›› (Opportunism) ይባላል።መልካም አጋጣሚ ወይም ዕድል (Opportunity) ሲገኝ በዚያች ለመጠቀም ያለምንም ይሉኝታ መሽቀዳደም፤በስተኋላ ሊከሰት የሚችለውን ጎጂ ውጤት እያወቁም ቢሆን ‹‹እንደ አመጣጡ እመልሰዋለሁ›› በሚል ድፍረት
መግባት፣ ከየት አመጣ? እንዴት አገኘ? በምን ዘዴእዚህ ደረሰ? የሚሉ የህዝቡ ምን ይላል ጥያቄዎችን ወደ
ጎን አሽቀንጥሮ ጥሎ ጥቅም ፍለጋ ሲል ብቻ ለመሰል አለቆቹ እየተሽቆጠቆጠና የእሱ ቢጤዎችን እያሰባሰበ
የሚንቀሳቀስበት አሰራር አድርባይነት ነው። ሰውሸንኮራ አገዳ አይደለም፤ እየተመጠጠ አይታይም። ከላይ
ስታየው የሚጣፍጥ የመሰለህ አገዳ ገዝተህ ስትቀምሰው ሊጎመዝዝህ ይችላል። የአድርባይም ጉዳይ እንዲሁ ነው።አድርባይነት የተገኘውን መልካም አጋጣሚ ሁሉየግል ጥቅምና አላማን ለማስቀደም የሚደረግ የፖለቲካ
አቋምን ያመለክታል። ጥቅም የሚያስገኝ እስከሆነ ድረስ ማንኛውንም አቋም ለማራመድ (ለመደገፍ) ቆርጦ
መነሳትን፣ ለግምገማም ሆነ ለህጋዊ ተጠያቂነት ንቀት ማሳየትን፣ የህዝብን ውክልናና ስልጣን አሳንሶ ማየትን፣
አይንን በጨው አጥቦ ለጥቅም ሲሉ ብቻ የድርጅቱን ራዕይመመሪያና ደንቦችን የህዝብን ትዝብትና ሃይማኖትንጭምር ጨፈላልቆ ለመሄድ ያለንን ውስጣዊ የጠባይ(የባህርይ) ዝግጁነት የሚያሳይ ክፉ አመለካከት ነው።አድርባይ ሰው በድርጅቱ የፖለቲካ አቋምአያምንም። ያመነ የሚመስለውና ከእሱ በላይ ተቆርቋሪ የሌለ እስኪመስል ድረስ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ለመሪዎቹ(አለቆቹ) ፍቅር ያለው ይመስል የሚሽቆጠቆጠው ያቺን ያሰባትን ጥቅም በእጁ እስኪያስገባና ተጨማሪ ጥቅምለማግኘት የሚያስችል እድል (አጋጣሚ) Opportunity እስካለ ድረስ ብቻ ነው። ‹‹የራስ ጥቅምን መፈለግና ለዚህም ተግቶ መንቀሳቀስ ምን ችግር አለው?›› የሚልጥያቄ ሊነሳ ይችላል።
ሁላችንም የምንሰራው ለመጠቀም
ነው። ራሳችንንና ቤተሰባችንን ለማስተዳደር ሰው የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ነው። መሬት፣ መኪና፣
ቤት፣ ኢንቨስትመንት፣ አካውንት፣ ደህና ዕቁብ ጥሩዕድር ቢኖረንና የጣፈጠ በልተን ያማረ ለብሰን ብንኖር
አንጠላም። ይህ ደግሞ ኃላፊነት በሚሰማውና በእውቀትና በጉልበት ተሳትፎ ተሰርቶ የሚገኝ ሲሆን ደስ ይላል።እንደ ምርጫና ወዘተ... በመሳሰሉት አጋጣሚዎች በተገኘእድል ከህዝብ በተሰጠ አደራ የራስን ጥቅም ለማስቀደም የሚደረግ የፖለቲካ እሽቅድድም ግን አያዋጣም።አድርባይነት በፓርቲና በመንግስት ተቋማት ኃላፊዎችና ሠራተኞች አማካይነት ሲፈፀም ከፍተኛ ችግር ያስከትላል።ታማኝነት (Loyalty)... ግልፅነት (transparency)...ምስጢር ጠባቂነት (Confidentiality)... ሀቀኝነት(Honesty) ተጠያቂነት (Accountability) አለማዳላት(Impartiality)...ምላሽ ሰጪነት (Responsiveness)አርአያ መሆን (Exemplary) የህዝብ ጥቅም (Public
Interest)
ወዘተ... የሚባሉት መሰረታዊና ስትራቴጂክ የዕድገት እሴቶቻችን በሙሉ ጥንጣን እንደበላው የበረሃዛፍ ውስጥ ውስጡን እየተቦረቦሩ ያልቁና ራዕያችንን ገንድሰው ይጥሉብናል። ከዚያ ኋላማ ‹‹የማን ቤት ጠፍቶየማን ሊበጅ... የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ›› እያልን እርስ በርስ ከመጨካከንና ከመተራረድ በቀር የሚተርፈን ነገር የለም።ይህ ማለት ደግሞ ሰዎችን ስንጠረጥራቸውእንኑር፣ ወይም በየጆሯቸው ስር መረጃ እናቁምባቸው፣ስህተታቸውን የሚያሳብቅ ቃጭል እናንጠልጥልላቸው ማለት አይደለም። ወደንና ፈቅደን እንደሰው መጠን አገናዝበን የመረጥናቸው ወኪሎቻችንና አገልጋዮቻችን ስለሆኑ አዲሶቹ በአድርባይነት በሽታ እንዳይለከፉና የተለከፉትም ከዚህ የአድርባይነት አስተሳሰብ እንዲወጡ በተቻለን አቅም እንርዳቸው፣ እናግዛቸው ማለት ብቻነው። አድርባይነት የስብዕና (Personality) ምስክርነው። የአመለካከት ችግር ነው። የሰዎች ስብዕናና አመለካከት የሚቀረፀው ደግሞ አንደወጡበት ቤተሰብና እንደ አደጉበት ማህበረሰብ ነው። ሌብነትን ከሚፀየፍ ቤተሰብና ማህበረሰብ የተገኘ ልጅ ሌብነት ውስጥ ሊገባ አይችልም። ወይም የመግባት እድሉ በጣም ጠባብ ነው።ስለዚህ የሰውዬውን ቤተሰብና ያደገበትን ማህበረሰብ ዳራ ማወቅ ይጠቅማል። አድርባይነትን ከሚያስፋፉ ባህርያት አንዱ ስኬታማ የመሆን ጥማት ነው።ከሌሎች ሰዎች ተሽሎ የመገኘት፣ የማሸነፍ፣ በውጤት፣በዝና በሀብት በልጦ የመገኘት (‹‹ወንዳታ›› የመባል)ውስጣዊ ፍላጎት ነው። ይህን ፍላጎት ለማርካት (ከግብለማድረስ) ሰውዬው ስልጣኑንና የተገኘውን መልካም አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም እስከየትኛውም ጫፍ ድረስ ይጓዛል። ከድርጅቱ (ከፓርቲው) እና ከሚሰራበት ተቋም መርሆዎች ጋር ፈጽሞና ፈጽሞ የማይጣጣሙ ዘዴዎችን(አሰራሮችን) እየተጠቀመና ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቀ
ይሟሟታል። ይህ ደግሞ ለአድርባይነት ይዳርገዋል።ለአድርባይነት ከሚዳርጉ ምክንያቶች ሌላኛው የሰው ልጅያለው የስጋት (ስጋታምነት) ተፈጥሮ ነው። ለትንሹም ለትልቁም መስጋት ይወዳል። በሰላም አገር ‹‹ይገመግሙኝይሆን? ከደረጃ ዝቅ ያደርጉኝ ይሆን?... ይጠረጥሩኝይሆን?... ከቤተሰቤ ወደራቀ ቦታ ያዛውሩኝ ይሆን?ያባርሩኝ ይሆን?... ዕድገት ይከለክሉኝ ይሆን? እያለይጨናነቃል። ከዚያች ከያዛት ቦታ ቢለቅ ወይም ከዚያመስሪያ ቤት ቢወጣ ሰማይ የሚደፋበት ይመስለዋል።በራስ መተማመኑ ብን ብሎ ይጠፋበታል። ስለዚህ ህዝብ የጣለበትን አደራና ተቋሙ የሰጠውን ኃላፊነት እርግፍ አድርጎ ትቶ የጥቅመኛ አለቃው ሽቁጥቁጥ አሽከር(ባሪያ) ሆኖ ያርፈዋል። ‹‹ቢጭኑት አጋሰስ፤ ቢጋልቡት ፈረስ›› ይሆንና ሀሳብ አመንጭነትና ተነሳሽነት የጎደለው አስመሳይ ተራማጅ ሆኖ ይቀራል። ለድርጅቱም (ለተቋሙ)
ሳይጠቅም ህዝቡ የጣለበትን አደራ ሳይፈጽም የትውልድ መዛበቻና የዘመን መሳለቂያ ሆኖ ያርፈዋል። ሌላው ጉዳይ ደግሞ አድርባይነት የሚያስገኘውን ጥቅም (pay off) ከፍአድርጎ የማሰብ አመለካከት ነው። ድርጅቱ ቢያባርረኝ፣ህዝቡ ቢታዘበኝ፣ ህግ ያለውን ቢለኝ አድርባይ ሆኜ አንድ ዝግ ከዘጋሁ ይካካስልኛል። የተቀጣሁትን ሁሉ ያህል ብቀጣ በአድርባይነቴ ባገኘሁት ጥቅም አጥበዋለሁ።ጉድ አንድ ሰሞን ነው። የኛ ሰው እንደሁ ማውራት ልማዱ ነው፤ ስለዚህ ያለውን ይበል... በዚህ ላይ ደግሞ የሚኮንነኝ ሰው የመኖሩን ያህል የሚደግፈኝ ሰውም አለ። ያሉትን ቢሉ ምን ያመጣሉ... ለዚያውስ ለየትኛው ህግ ነው? አንድ ሚሊዮን ዘግተህ ሁለት ዓመት ታስረህ ለምትወጣው ምን ችግር አለ። ሁለት ዓመት እንደሁነገ ናት.. እያሉ የሚያበረታቱ ሞልተዋል። ሌላው ጉዳይ አድርባይነት ‹‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ›› በሚለው መርህ
መሰረት የሚመራ በመሆኑ ጥሩ ውጤት የተገኘ ጊዜ ነጥቡን ለራስ እየወሰዱ መጥፎ ውጤት በተመዘገበና
ጉዳት በደረሰ ጊዜ ኪሳራውን በሌሎች ላይ ማላከክ(Shifting the costs, blame and disadvantages toothers) የሚቻልበት አሰራር በመኖሩና ይህም በሰዎች አመለካከት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር መሆኑ ነው። ሌላውን ተጠያቂ ማድረግ ጣትን በሌላው ላይመቀሰር ሁል ጊዜም ቀላል ስራ ነው። ለችግሮች ውጫዊ ምክንያት መስጠት ቀላል ነው። የአድርባይነትን ጠባይ ከሚያበረታቱ ነገሮች መካከል መነሳት ያለበት የሰውዬው ወይም የዚያ ቡድን የስልጣን መጠን ነው። ስልጣን ሲባል
ሁሌም ለሙስና ይጋብዛል። ፍፁማዊ ስልጣን ደግሞ ለፍፁማዊ ሙስና አይን ላወጣ አድርባይነት ይዳርጋል።
(All power corrupts, and absolute power corruptsabsolutely)
ሰውዬው ከፍ ያለ ስልጣን ያለው ከሆነ ተቆጣጣሪ ስለሌለበት ያገኘውን መልካም አጋጣሚ ሁሉ ለግል ጥቅሙ የሚያውልበት ሰፊ እድል አለው። ስለዚህ አድርባይ ይሆናል። ለአድርባይነት መኖር በር የሚከፍተው
ሌላኛው አመለካከት ደግሞ ‹‹እኔ ባላደርገው ሌላው ያደርገዋል... ስለዚህ ለምን እኔ አላደርገውም›› የሚለው አመለካከት ነው። ሌላው መጥቶ አጋጣሚውን ለራሱ ጥቅም የሚያውለው ከሆነ እኔስ እጄ ባለው አጋጣሚ ብጠቀም ሃጢአቴ እምኑላይ ነው ብሎ ያስባል።የበላይ አለቆቹንም ያያል። ሁሉም በአድርባይነት
በሽታ የተለከፉ ይሆኑበታል። ያላቸውን ቤት፣ መሬት፣መኪና፣ ኢንቨስትመንት... የአኗኗር ሁኔታ ሲመለከት
እኔስ ከማን አንሳለሁ ይላል።እነሱ ምን ተደረጉ ይላል። ለእነሱ ያልሰራ ህግ ለእሱም እንደማይሰራ ያምናል። ይገባበታል፤ በመጨረሻም ከእነሱ ጋር ተለቃቅሞ ይገባታል። እስከዚያው ድረስ ግን ጥቅም ነውና ይሟሟትበታል። አድርባዩ በበዛበት ድርጅት ውስጥ ሆኖ አድርባይ አልሆንም ማለት ይከብዳል።ሁሉም አብዶ ጨርቁን በጣለበት ሀገር ልብስ ለብሶ የሚሄድ ሰው ከተገኘ ዋናው እብድ የሚባለው እሱ
ይሆናል። የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ የሚለውም የአድርባዮች መገለጫ ነው። ሰዎችን አድርባይ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው ሌላው ምክንያት የመረጃ፣ የእውቀት፣የግንዛቤ እጥረት ነው። ሰዎቹ በአድርባይ ጠባያቸው የተነሳ በፓርቲውና በመንግስት ስራ ላይ፣ በህዝብ ላይ፣ በሀገርላይ በመጨረሻም በራሳቸውና በቤተሰባቸው ህይወት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ካልተረዱ አድርባይ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። አንዳንዶች በዚህ ረገድ ማግኘት ያለባቸውን መረጃና ግንዛቤ እንዳያገኙ ወይም የተዛባመረጃ ሆን ተብሎ እንዲያገኙ deliberate disinformation የሚደረጉበት ሁኔታ አለ። ሌሎች ደግሞ አድርባይነት
በሚያስከትለው መዘዝ ላይ መረጃውና ግንዛቤው እያላቸው ሆን ብለው ራሳቸውን የሚያታልሉና በአጉል ድፍረት በልቼ (ተጠቅሜ) የመጣው ይምጣ ብለው የሚገቡ ፈጣጦች አሉ። ሲሾሙ ካልበሉ ሲሻሩ እንዳይቆጫቸው።ከዚህ በላይ ያነሳናቸው በአድርባዩ ሰውዬ በራሱ አማካይነት ተኮትኩተው ስለሚፋፉ የአድርባይነት ባህርያት ነው። ለእነዚህ ተከታታይ ስልጠና ያስፈልጋል።የአመለካከት ለውጥ፣ የግንዛቤ ዕድገት እንዲያመጡ ማድረግ ያስፈልጋል። ካደጉበት ‹‹እንብላው›› ብሂል የሚወጡበትን እድል ጥልቅ በሆነ ስነአዕምሯዊ ስልጠናና ክትትል ከውስጣቸው ለመንቀል መስራት ያስፈልጋል። ማስተማር
ያስፈልጋል። በሌላ በኩል ደግሞ ተቋማት ራሳቸው ሰዎችን ወደ አድርባይነት ለመገፋፋት የሚያመቻቹበት
ሁኔታ አለ። አንዳንድ ድርጅቶች የአድርባይነት ጠባይ የማያስተናግድ በግልፅ የተቀመጠ ውልፍጥ የማያደርግ
ህግና ደንብ አላቸው። ሰውዬው ምን ቢያደርግ ምን እንደሚደርስበት በግልጽ ተቀምጧል። ይህ ይነገረዋል።
በጽሑፍም ይሰጠዋል። አድርባይ ሆነው የተገኙ ሰዎችንም የሚቆጠቁጥ ቅጣት ይጥሉባቸዋል። በስልጣን ላይ ሳሉባገኙት አጋጣሚ ያከማቹትን ሀብት እንዲያጡ፣ ለበርካታ ዓመታት በእስር እንዲቀጡ፣ ባዶ እጃቸውን እንደመጡባዶ እጃቸውን እንዲወጡ የሚያደርግ የፍትህ አሰራርም አላቸው። ሌሎች ድርጅቶች እንዲህ አይነት በግልፅ የተቀመጠ ህግ ስለሌላቸው የሚደርስባቸው ቅጣትም ከበሉት ገንዘብና ከተቀራመቱት ጥቅም አንፃር ሲታይ በእጅጉ አናሳ በመሆኑ ጓዶችን ሲያዩ እየተሽቆጠቆጡ፣ ዞርሲሉ ምላሳቸውን እያወጡ፣ በህዝብ ላይ እያላገጡ፣ ሰለሄመለሄ እየዋጡና ሙቅ ተበሪድ አማርጠው እየጨለጡ እንዲኖሩ እድል ይሰጣቸዋል። ከተቋማት አንፃር ሲታይ በርካታ ለአድርባይነት የሚገፋፉ አመቺ ሁኔታዎች አሉ።ሁሉንም ዘርዝረን አንችልም። አንድ ቦታ ላይ ማቆም አለብን። የሙስና የኪራይ ሰብሳቢነት የብልሹ አስተደደር
እናቱም አባቱም አድርባይነት (Opportunism) ነው።ልንዋጋውና ልንታገለው ይገባል። ‹‹አድርባይነት››የተባለውን ጽንሰ ሀሳብ በግልጽና በጥልቀት በተለያዩ አደረጃጀቶቻችን አማካይነት ልንገነዘበው ይገባል። በእከክልኝ ልከክልህ በአባልነት ስም እየተሳሳቡ ጥሩ ጥሩውን ውጤት
ወደራሳቸው እየሳቡና ጥፋት ሲገኝ በሌላው ላይ እያሳበቡ፣ምንም ሳይሰሩ እየደለቡ እንዲኖሩ መፍቀድ የለብንም።ይህን መታገል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ  ኃላፊነትብቻ ነውምክንያቱም ወያኔ‹‹አድርባይነት›› ሙያው ስለሆነ እንዲያውም በዋናነት የህብረተሰቡ የራሱ ኃላፊነት ነው። ከየት አመጣችሁ ብሎ መጠየቅ
አለበት፤ ድምፁን መንፈግና በምርጫ ካረዱ መቅጣት አለበት ከደሃ ትከሻው ልናስጥረ አሽንቀጥሮ መጣል አለበት።ታዲያ ይኽሁላ የምናየው የገዥው መንግስት ባህሪያት አይደሉምን?ለማንኛውም መልካሙን ሁላ ለህዝባችን ይስጥልን!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከዘካሪያስ አሳዬ

No comments:

Post a Comment