Wednesday, May 1, 2013

በፌዴራል መ/ቤቶች - ወደ 1.4 ቢሊየን ብር አልተወራረደም


-   ወደ 1.4 ቢሊየን ብር አልተወራረደም
-   30 /ቤቶች 353.6 ሚሊየን ብር ደንብና መመሪያን ያልተከተለ ግዥ ተፈጽሟል
-   9 /ቤቶች 3.5 ቢሊየን ብር ባልተሟላ ሰነድ ወጪ ሆኗል፣3.2 ቢሊየን ብሩ የመከላከያ ወጪ ነው
-   27 /ቤቶች ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ ብር 212.5 ሚሊየን ተጠቅመዋል
በፍሬው አበበ
የፌዴራልና ዋና ኦዲተር /ቤት 2004 በጀት ዓመት በፌዴራል መንግስት /ቤቶች የኦዲት ሥራ አከናውኗል። በትላንትናው ዕለት ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ 58 ገጽ የያዘውንና 116 የፌዴራል መንግስት ባለበጀት /ቤቶችና 283 የወረዳና ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ /ቤቶች ላይ /ቤታቸው ያካሄደውን የኦዲት ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች /ቤት አቅርበዋል። በዚህ ሪፖርት ውስጥ የተጠቀሱ ዋናዋና ግኝቶች እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል።
በፌዴራል መንግሥት የልዩ ልዩ /ቤቶች
የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት ወቅት የታዩ ዋና ዋና ግኝቶች
/ቤታችን ምክር ቤቱ ያፀደቀው በጀት የፋይናንስ አስተዳደር ሕጉ፣ ደንብና መመሪያ በሚፈቅደው መሠረት በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ 2004 በጀት ዓመት ሂሳብ ላይ ባከናወነው ኦዲት በርካታ የሂሳብ አያያዝ ግድፈቶች እና የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶች፣ እንዲሁም አፈፃፀማቸው ከደንብና መመሪያ ውጪ የሆኑ ሁኔታዎች የተገኙ ሲሆን፤ የም/ቤቱን ትኩረት ሊያገኙ ይገባል ተብሎ የታመነባቸው አንኳር ግኝቶች ብቻ ተለይተው እንደሚከተለው ቀርበዋል።

የጥሬ ገንዘብ ጉድለት
የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ አያያዝና አጠባበቅ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ 3 /ቤቶች ብር 247 210 ብር 19 ሳንቲም የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ተገኝቷል። በመሆኑም በጉድለት የታየው የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ እንዲተካ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ለየመ/ቤቶቹ በላክነው የስራ አመራር ሪፖርት አሳስበናል።
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በሂሳብ መግለጫ ሪፖርት የተደረገውና በቆጠራ የተገኘው ጥሬ ገንዘብ መካከል ልዩነት 2 /ቤቶች ቆጠራው በብር 133466 ብር 99 ሳንቲም በማነስ እና 9 /ቤቶች በብር 3 ሚሊየን 433 156 ብር 03 ሳንቲም በመብለጥ የታየ ሲሆን፤ በአጠቃላይ 24 /ቤቶችም የተለያዩ የጥሬ ገንዘብና የባንክ ሂሳብ አያያዝ ድክመቶች እንደሚታዩ በኦዲታችን ወቅት አረጋግጠናል።
የጥሬ ገንዘብና የባንክ ሂሳቦች ላይ ተገቢ ቁጥጥር አለማድረግ ለገንዘብ ጉድለትና ምዝበራ የሚያጋልጥ በመሆኑ፤ የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ በየወቅቱ ተቆጥሮ ከመዝገብ ጋር እንዲመሳከር፣ በሂሳብ መግለጫ ሪፖርት ላይ የተመለከተው የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ በቆጠረ ከተገኘው ጋር ሊመዛዘንና ትክክለኛነቱ ሊረጋገጥ እንደሚገባ፤ በማነስና በመብለጥ የታየው ልዩነትም ተጣርቶ እንዲተካ ወይም ተገቢው ማስተካከያ እንዲደረግ እና 24 /ቤቶችም የታዩ የተለያዩ የጥሬ ገንዘብና ባንክ ሂሳብ አያያዝ ድክመቶች እንዲስተካከሉ አሳስበናል።
የውዝፍ ተሰባሳቢ ሂሳብ
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ ቁጥር 190/2002 አንቀጽ 32 እስከ 35 በተደነገገው መሠረት ተሰብሳቢ ሂሳብ በወቅቱ መወራረዱ ሲጣራ 57 /ቤቶች ብር 1 ቢሊየን 369 ሚሊየን 377 900ብር 98ሳንቲም በደንቡ መሠረት በወቅቱ ሳይወራረድ ተገኝቷል። ከዚህ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት የትምህርት ሚኒስቴር ብር 401 ሚሊየን 757 697 ብር 18ሳንቲም፣ የግብርና ሚኒስቴር 64 ሚሊየን 602 005ብር 48 ሳንቲም፣ የግብርና ቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ 155 ሚሊየን 597 701 ብር 70ሳንቲም፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 173 ሚሊየን 756 807 ብር 75ሳንቲም፤ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ብር 159 ሚሊየን 455 023 ብር 31ሳንቲም፤ የሀገር መከላከያ / ብር 86 ሚሊየን 367 964 ብር 14ሳንቲም፤ በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ ብር 83 ሚሊየን 081 758 ብር 27ሳንቲም፤ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ብር 69ሚሊየን 022 422 ብር 95ሳንቲም፤ የፌዴራል ፖሊስ 29 ሚሊየን 778 302 ብር 26 ሳንቲም እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ብር 21 ሚሊየን 399 805 ብር 70 ሳንቲም ይገኝበታል።
በተጨማሪም በተሰብሳቢ ሂሳብ አያያዝ የሚታዩ ዋና ዋና የአሰራር ችግሮች፤ ዕዳው ከማን እንደሚፈለግ ዝርዝር ማስረጃ ባለመኖሩ ከሰራተኛው የሚፈለገውን ቀሪ እዳ ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉ፤ በአንዳንድ /ቤቶች ገንዘቡ ወጪ ተደርጎ ለመሰጠቱ ማስረጃው ባለመቅረቡ የተሰብሳቢ ሂሳቡን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አለመቻሉ፤ የተሰብሳቢ ሂሳቡ ያልተለመደ ሚዛን /Abnormal Balance/ ማሳየቱ፤ በአንዳንድ /ቤቶች የተሰብሳቢ ሂሳብ ሰነዱ ለኦዲት ያልቀረበ መሆኑና ከመቼ ጀምሮ የሚፈልግ ሂሳብ እንደሆነ የሚገልጽ ማስረጃ እና ተቀጽላ ሌጀር ያልተቋቋመ በመሆኑ የሂሳቡን ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉ ናቸው።
ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳቡ በየመ/ቤቶቹ የሥራ ማስኬጃ ላይ ተፅዕኖ በማሳደር የሥራ እንቅስቃሴ የሚያዳክምና የበጀት አጠቃቀም ላይ ተጽዕኖ ከመፍጠሩም በላይ ለምዝበራና ለብክነት በር የሚከፍት በመሆኑ /ቤቶቹ የፋይናንስ ደንብና መመሪያዎችን ተከትለው እንዲያወራርዱ አሳስበናል።
የገቢ ሂሳብ
የመንግሥት ገቢ በአግባቡ መሰብሰቡን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ ቀጥሎ የተመለከቱት ሁኔታዎች ተገኝተዋል።
በገቢ ግብር፣ ቀረጥና ታክስ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት
ሳይሰበሰብ የተገኘ የገቢ ሂሳብ
የገቢ ሰብሳቢ /ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በገቢ ግብር፣ ቀረጥና ታክስ እንዲሁም በሌሎች ገቢ መሰብሰብን በሚፈቅዱ አዋጆች፤ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት የመንግሥትን ገቢ የሰበሰቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ በናሙና በታዩት 4 /ቤቶችና 6 የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን //ቤቶች በድምሩ ብር 29 ሚሊየን 205 484 ብር 95ሳንቲም  በገቢ ግብር፣ ቀረጥና ታክስ እንዲሁም በሌሎች ገቢ መሰብሰብ በሚፈቅዱ አዋጆች መሠረት ያለተሰበሰበ የገቢ ሂሳብ መኖሩ ታውቋል።
በአዋጁ መሠረት ገቢ ካልሰበሰቡት /ቤቶች መካከል ምስራቅ አዲስ አበባ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን //ቤት ብር 25 ሚሊየን 090 951 ብር 15 ሳንቲም እና ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ብር 1 ሚሊየን 066 483 ብር 48 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
በመሆኑም /ቤቶች ለወደፊቱ የመንግሥት ገቢ ሕግና ደንብ በሚፈቅደው መሠረት መሰብሰብ እንዳለባቸው፣ በተለያዩ ምክንያቶች ያልተሰበሰበውም ገቢ እንዲሰበሰብ በላክነው ሪፖርት አሳስበናል።
ያልተሰበሰበ ውዝፍ የገቢ ሂሣብ
ገቢ ሰብሳቢ /ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በወጣው ሕግና ደንብ መሠረት የመንግሥት ገቢ በወቅቱና በአግባቡ መሰብሰባቸውን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና /ቤትና በስሩ ባሉ ስድስት ቅርንጫፍ /ቤቶች ከውዝፍ ግብር፤ ወለድ እና ቅጣት መሰብሰብ የሚገባው ብር 853 ሚሊየን 920 158 ብር 83 ሳንቲም እና በሌሎች 6 /ቤቶች ብር 12 ሚሊየን 250 953 ብር 19 ሳንቲም በድምሩ ብር 866 ሚሊየን 171 112 ብር 02 ሳንቲም ያልተሰበሰበ ውዝፍ ገቢ መኖሩ ተረጋግጧል።
በመሆኑም የሚሰበሰበው ገቢ መንግስት ለሚያከናውናቸው የልማትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋት እንዲሁም ለሀገሪቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሳካት ወሳኝ በመሆኑ፤ ለገቢ አሰባሰቡ ትኩረት ተሰጥቶት የመንግሥት ሕግና ደንብ ተከብሮ እንዲሠራ፣ ያልተሰበሰበውም ውዝፍ ገቢ እንዲሰበሰብ በሪፖርታችን አሳስበናል።
በገቢ ሂሳብ ሪፖርት ውስጥ ያልተካተተ ገቢ
በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የመንግሥት /ቤቶች የተሰበሰበው ገቢ በትክክል ተመዝግቦና በሂሳብ ሪፖርታቸው ተካቶ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መቅረቡን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ 5 /ቤቶች የሰበሰቡት የውስጥ ገቢ ብር 24 ሚሊየን 606 079 ብር 30 ሳንቲም ባቀረቡት ዓመታዊ የገቢ ሂሳብ ሪፖርት ውስጥ ሳይካተት ተገኝቷል።
በሌላ በኩል 15 /ቤቶች ከልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ምንጮች ገቢ የሚሰበስቡ ቢሆንም፤ የገቢ ሪፖርት የማያዘጋጁ በመሆኑ ሂሳቡን ኦዲት ማድረግ አልተቻለም። በተጨማሪም 5 /ቤቶች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት / ሳያስፈቅዱ የገቢ ደረሰኝ አሳትመው ገቢ እንደሚሰበስቡ ታውቋል።
ይህ አሰራር በመ/ቤቶች የሚዘጋጁት የሂሳብ መግለጫዎች ትክክለኛውን የገቢ ሂሳብ እንቅስቃሴ የማያሳይና የመንግስት አጠቃላይ ገቢና ወጪም ትክክለኛውን ገጽታ እንዳያሳይ ስለሚያደርግ /ቤቶች የሚሰበስቡትን ማንኛውም የመንግስት ገቢ ሕጋዊ በሆነ መንገድ በታተሙ ደረሰኞች ብቻ በመጠቀም እንዲሰበስቡና በሂሳብ መግለጫዎቻቸውም በመካተት ለገ//// ሪፖርት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበናል።
የወጪ ሂሳብ
/ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎች መሠረት በአግባቡ መጠቀማቸውን፣ ተገቢው ማስረጃ መቅረቡንና ሂሳቡም በትክክል መመዝገቡን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ ቀጥሎ የተመለከቱት ሁኔታዎች ተገኝተዋል።
የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በውጪ ተመዝግቦ የተገኘ ሂሳብ
በወጪ ለተመዘገቡ ሂሳቦች የተሟላ ማስረጃ መቅረቡን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ 13 /ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ ብር 132 ሚሊየን 364 911 ብር 31 ሳንቲም በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።
ተሟልተው ካልቀረቡት ማስረጃዎች መካከል፣ የተከናወነውን ሥራ በሚያሳይ ዝርዝር ማስረጃ ሳይደገፍ በቀረበው ጥያቄ ብቻ የተፈፀመ ክፍያ፤ በባንክ በኩል ገንዘቡ ተልኮ ሥራ ላይ መዋሉን የሚገልጽ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ የተመዘገቡ ሂሳቦች ጎላ ያሉት ናቸው።
ማንኛውም ሂሳብ በወጪ ከመመዝገቡ በፊት በፋይናንስ አስተዳደር አዋጁ፣ ደንቡና መመሪያ መሠረት ማስረጃዎች መሟላታቸው እንዲረጋገጥ፣ ያልተሟሉት ማስረጃዎች እንዲሟሉና ለወደፊቱም ተገቢው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አሳስበናል።

የወጪ ማስረጃ ያልቀረበለት ሂሳብ
በወጪ የተመዘገቡ ክፍያዎች ሕጋዊ ማስረጃ የቀረበላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ 22 /ቤቶች ብር 13 ሚሊየን 803 411 ብር 08 ሳንቲም ማስረጃ ሳይኖረው በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።
በመሆኑም የወጪ ማስረጃ ያልቀረበለት ሂሳብ በቂ ማስረጃ እንዲቀርብለት፣ አለበለዚያ ገንዘቡ ለመንግስት ካዝና ተመላሽ እንዱደረግ፤ ለወደፊቱም ማንኛውም ወጪ ከመመዝገቡ በፊት ተገቢው ማስረጃ መቅረቡን በማረጋገጥ እንዲመዘገብ አሳስበናል።
የግዢ አዋጅ፤ ደንብና መመሪያ ሳይከተሉ የተፈፀሙ ግዢዎች
የዕቃና አገልግሎት ግዢ በመንግሥት ደንብና መመሪያ መሠረት የተፈፀመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፣ 30 /ቤቶች ብር 353 ሚሊየን 568 759 ብር 15 ሳንቲም የመንግሥትን የግዢ አዋጅ፤ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ ግዢ ተፈጽሞ ተገኝቷል።
ከደንብና መመሪያዎች ውጭ ግዥ ከፈፀሙ /ቤቶች መካከል ጅማ ዩኒቨርሲቲ ብር 240 ሚሊየን 221 573 ብር 63 ሳንቲም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ብር 36 ሚሊየን 198 641 ብር 27 ሳንቲም፤ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ብር 20 ሚሊየን 341 230 ብር 59 ሳንቲም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ብር 14 ሚሊየን 082 063 ብር 07 ሳንቲም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ብር 8 ሚሊየን 755 250 ብር 38 ሳንቲም፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ብር 6 ሚሊየን 745 462 ብር 35 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ካልተከተሏቸው የግዥ ደንብና መመሪያዎች ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት ሊፈፀሙ የሚገባቸው ግዥዎች ያለጨረታ ማስታወቂያ በመግዛት፣ በዋጋ ማወዳደሪያ /ፕሮፎርማ/ መፈፀም ያለበትን ግዥ ውድድር ሳይደረግ መፈፀም እና በውስን ጨረታው የግዥ ዘዴ በቂ አቅራቢዎች ሳይጋብዙ ግዥን ማከናወን የሚሉት ይገኙበታል።
የግዢ መመሪያን ሳይከተሉ ግዢ መፈፀም ለምዝበራና ለጥራት መጓደል የሚያጋልጥ በመሆኑ የመንግሥት ግዢ ደንብና መመሪያን አክብረው በማይሰሩ /ቤቶች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።
ደንብና መመሪያን ሳይከተሉ ያለአግባብ የተፈፀሙ ክፍያዎች
ኦዲት በተደረጉት /ቤቶች ደንብና መመሪያ ተጠብቆ ክፍያ መፈፀሙ ሲጣራ 21 /ቤቶች ብር 137 ሚሊየን 363 575 ብር 83 ሳንቲም ከደንብና መመሪያ ውጭ ተከፍሎ ተገኝቷል።
በግንባታ ቦታ ላይ ላሉ ዕቃዎች materials on site) ከሚመለከተው አካል ሳይፈቀድ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በመፈፀም፤ ሰራተኞች መስክ ሳይወጡ የውሎ አበል በመክፈልና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሳይፈቅድ የኃላፊነት አበል ለዩኒቨርሲቲ የስራ አመራሮች ክፍያ በመሳሰሉት ምክንያቶች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ብር 77 ሚሊየን 611 944 ብር 97 ሳንቲም፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ብር 34 ሚሊየን 771 018 ብር 34 ሳንቲም እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ብር 10 ሚሊየን 825 188 ብር 84 ሳንቲም ወጪ ያደረጉ መሆናቸው በኦዲቱ ተረጋግጧል።
በተጨማሪም የቀድሞው የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቁጥር 30//13137/820 በቀን 5/13/2001 . በተፃፈ ሰርኩላር የትርፍ ሰዓት ክፍያ ተግባራዊ እንዳይሆን መመሪያ ያስተላለፈ ቢሆንም፤ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሳያስፈቅድ በሁሉም ቅርንጫፍ /ቤቶች 2004 በጀት ዓመት ለትርፍ ሰዓት ክፍያ ፈጽሞ ተገኝቷል።
በመሆኑም ከደንብና መመሪያ ውጪ ያለአግባብ የተከፈለው ሂሳብ ተመላሽ እንዲሆንና ለወደፊቱም ደንብና መመሪያዎች ተከብረው መሰራት እንዳለበት ኦዲት ለተደረጉት /ቤቶች አሳስበናል።
በተሰብሳቢ ሂሳብ መመዝገብ ሲገባው በወጪ የተመዘገበ
የቅድሚያ ክፍያ ሂሳብ የተገኘባቸው /ቤቶች
በበጀት ዓመቱ በመንግሥት /ቤቶች በወጪ የተመዘገበው ሂሳብ በደንብና በመመሪያ መሠረት መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ 12 /ቤቶች ለልዩ ልዩ ኮንትራታዊ አገልግሎቶች የተከፈለ ቅድሚያ ክፍያ ብር 546 ሚሊየን 599 723 ብር 27 ሳንቲም በተሰብሳቢ ሂሳብ መመዝገብ ሲገባው በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።
ቅድሚያ ክፍያን በወጪ ከመዘገቡት /ቤቶች መካከል ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ብር 302 ሚሊየን 924 907 ብር 46 ሳንቲም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ብር 123 ሚሊየን 905 491 ብር 52 ሳንቲም፣ ትምህርት ሚኒስቴር ብር 47 ሚሊየን 988 495 ብር 21 ሳንቲም እና ማዕድን ሚኒስቴር ብር 28 ሚሊየን 630 317 ብር 74 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
መሆኑም የመንግሥት ሂሳብ አያያዝ በሚያዘው መሠረት አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ፤ ቅድሚያ ክፍያው ሥራው ተጠናቆ በቂ ማስረጃ እስከሚቀርብለት ድረስ በተሰብሳቢ ሂሳብ እንዲመዘገብ በሪፖርታችን አሳስበናል።

በብልጫ የተከፈለ ወጪ
በወጪ የተመዘገቡት ሂሳቦች በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ እና ደንብ መሰረት በአግባቡ የተፈፀሙ፤ እንዲሁም /ቤቶቹ ላገኙት አገልግሎት የተፈፀመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፤ 7 /ቤቶች ለተለያዩ ግዢዎች ብር 542 220 ብር 60 ሳንቲም እና ለውሎ አበልና ሌሎች ክፍያዎች 4 /ቤቶች ብር 851 589 ብር 66 ሳንቲም  በድምሩ ብር 1 ሚሊየን 393 810 ብር 26 ሳንቲም በብልጫ ተከፍሎ ተገኝቷል።
በብልጫ የተከፈለው ሂሳብም በግዢ ሂደት ያለበቂ ምክንያት ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረቡ እያሉ ከፍተኛ ዋጋ ከቀረቡት ድርጅቶች ግዢ በመፈፀም፤ በድጋሚ ወጪ በማድረግ ወይም ከተገባው ውል ውጭ በመክፈልና ከውሎ አበል ተመንና የትርፍ ሰዓት ክፍያ በላይ በመክፈል የሚሉት ይገኙበታል።
በመሆኑም /ቤቶች የግዢና ፊይናንስ አስተዳደር ስርዓቱን ተከትለው መፈፀም እንደሚገባቸውና በብልጫ የተከፈለውም ገንዘብ ለመንግስት ካዝና ተመላሽ እንዲሆን አስፈላጊ እርምጃ እንዲወሰድ በሪፖርታችን አሳስበናል።
የንብረት ገቢ ደረሰኝ ያልቀረበለት
የመንግስት ገንዘብ ወጪ ሆኖ የተገዛው ንብረት ለመ/ቤቱ ገቢ ለመሆኑ የንብረት ገቢ ደረሰኝ የተቆረጠለት መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ 6 /ቤቶች በብር 20 ሚሊየን 240 407 ብር 36 ሳንቲም የተገዙ ዕቃዎች የንብረት ገቢ ደረሰኝ ሳይቆረጥላቸው ሂሳቡ በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።
ከዚህም ውስጥ ጂማ ዩኒቨርሲቲ ብር 18 ሚሊየን 870 460 ብር 03 ሳንቲም እና መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ብር 1 ሚሊየን 325 755 ብር 75 ሳንቲም ለተገዛው ዕቃና ንብረት የንብረት ገቢ ደረሰኝ ካልቆረጡት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከውጪ ሀገር በድምሩ በአሜሪካን ዶላር 832 255 80ሳንቲም ተገዝተው የመጡ የተለያዩ ማሽነሪዎች ገቢ ያልተደረጉ መሆኑ ታውቋል።
የዚህ ዓይነት አሰራር ለንብረት ብክነት ስለሚያጋልጥ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ሊደረግና የንብረት ገቢ ደረሰኝ ያልቀረበላቸው ንብረቶች ለየመ/ቤቶቹ አገልግሎት ለመዋላቸው በማስረጃ እንዲረጋገጥ ለመ/ቤቶቹ በላክነው ሪፖርት አሳስበናል።
የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያልተቻለ ሂሳብ
በበደች ዓመቱ /ቤቶች የፈፀሙት ክፍያ ትክክለኛነቱን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፣ 9 /ቤቶች በተለያየ ምክንያት ማስረጀ ባለመቅረቡ የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያልተቻለ ሂሳብ ብር 3 ቢሊየን 507 ሚሊየን 062 927 ብር 60 ሳንቲም ተገኝቷል።
የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ካልተቻለው ሂሳብ ውስጥ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ብር 3 ቢሊየን 169 ሚሊየን 110 595 ብር 13 ሳንቲም፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ብር 187 ሚሊየን 857 058 ብር 5 ሳንቲም፤ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ብር 41 ሚሊየን 288 852 ብር 19 ሳንቲም፤ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ብር 29 ሚሊየን 790 947 ብር 40 ሳንቲም እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ብር 14 ሚሊየን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ማንኛውም የመንግስት ባለበጀት /ቤት የፌዴራል መንግስት የፋይናንስ አስተደደር አዋጅ ደንብና የመንግሥት የሂሳብ አያያዝ መመሪያዎችን ተከትሎ ሂሳቡን መያዝና ኦዲት ማስደረግ ስላለበት እነኚህ /ቤቶች ለወደፊቱ ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ የተሟላ ሰነድ በማደራጀት ሂሳባቸውን እንዲያስመረምሩ አሳስበናል።
በወጪ ሂሳብ ሪፖርት ያልተካተተ
ከውስጥ ገቢ እንዲጠቀሙ የተፈቀደላቸው /ቤቶች ከውስጥ ገቢያቸው ያወጡትን ወጪ በወጪ ሂሳብ ሪፖርት አካተው ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የሚያቀርቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ 6 /ቤቶች የብር 159 ሚሊየን 482 075 ብር 35 ሳንቲም ወጪ በወጪ ሂሳብ ሪፖርት ተካቶ በሕጉ መሠረት ለሚኒስቴር /ቤቱ ሪፖርት ያልተደረገ መሆኑ ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ የውስጥ ገቢ ሂሳባቸውን በገቢ ሂሳብ ሪፖርት የማያካትቱ 15 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በገንዘብ መጠን ያልታወቀ ወጪ በወጪ ሂሳብ ሪፖርት የማያካትቱ በመሆኑ ሂሳቡን ኦዲት ማድረግ አልተቻለም።
ይህ አሰራር የዘመኑ የፌዴራል መንግስት ዓመታዊ ገቢና ወጪ ሂሳብ መግለጫን የሚያዛባ ከመሆኑም በላይ ሕገወጥ በመሆኑ እንዲስተካከል ባለፉት ዓመታት ሪፖርታችን ብናሳስብም ሊስተካከል አልቻለም። ስለሆነም ሊሰበሰብ የሚገባው የመንግሥት ገቢ በአግባቡ እንዲሰበሰብ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ለተከበረው /ቤት ሪፖርት እንዲያቀርብ ሊደረግ ይገባል።

የተከፋይ ሂሣብ
በወቅቱ ያልተከፈለ ተከፋይ ሂሳብ
በገ//// መመሪያ መሠረት በበጀት ዓመቱ በተከፋይ ሂሳብ የተያዙት ሂሳቦች በተገቢው ጊዜ ውስጥ መከፈላቸውን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ 29 /ቤቶች ብር 491 ሚሊየን 128 467 ብር 58 ሳንቲም በወቅቱ ያልተከፈለ ተከፋይ ሂሳብ ተገኝቷል።
በወቅቱ ያልተከፈለ ተከፋይ ሂሳብ ከታየባቸው /ቤቶች ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ብር 173 ሚሊየን 824 549 ብር 10 ሳንቲም፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ብር 159 ሚሊየን 330 268 ብር 77 ሳንቲም፤ ትምህርት ሚኒስቴር ብር 64 ሚሊየን 327 615 ብር 57 ሳንቲም፤ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ብር 25 ሚሊየን 010 347 ብር 22 ሳንቲም እና የግብርናና ቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ማስተባበሪያ ብር 23 ሚሊየን 125 504 ብር 24 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሰኔ 30/2004 ከሠራዊት ደመወዝ ተመላሽ ተብሎ ሪፖርት የተደረገው ብር 163 ሚሊየን 504 599 ብር 94 ሳንቲም የሠራዊቱ አባላት ደመወዝ ባለመውሰዳቸው ለረጅም ዓመታት በተከፋይ ሂሳብ የተያዘና መጠኑም እያደገ የመጣ ከመሆኑም በላይ ክፍያው ሳይፈፀም ሂሳቡ በወጪ የተመዘገበ ሲሆን፤ ቀሪው ብር 10 ሚሊየን 319 949 ብር 16 ሳንቲም ለበርካታ ዓመታት በተከፋይ የተያዘና ለማን እንደሚከፈል የማይታወቅ መሆኑ ታውቋል። አሰራሩ ከመንግሥት የሂሳብ አሰራር ውጭ በመሆኑ እንደማንኛውም የፌዴራል መንግሥት /ቤት ያልተከፈለ ደመወዝ በቀጣዩ ወር መጀመሪያ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ፈሰስ መደረግ እንዳለበት ደመወዝ ካልተከፈላቸው አባላት ጥያቄ ሲቀርብ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እየተጠየቀ እንዲከፈልና ሌሎችም /ቤቶችም በወቅቱ ያልተከፈለውን ተከፋይ ሂሳብ የፋይናንስ አስተዳደር ሕጉን ተከትለው ለሚመለከተው አካል እንዲከፍሉ አሳስበናል።
በተጨማሪም 12 /ቤቶች የተለያዩ የተከፋይ ሂሳብ አያያዝ ችግር ያለባቸው፤ ያለበቂ ማስረጃ በተከፋይ ሂሳብ የተመዘገቡ፤ ለማን እንደሚከፈል የሚያመለክት ዝርዝር ማስረጃ ባለመቅረቡ ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ ያልተቻለ፤ በተከፋይ ሂሳብ መግለጫ ያልተካተቱ፤ እንዲሁም ያልተለመደ የሂሳብ ሚዛን የሚያሳዩ ተከፋይ ሂሳቦች ተገኝተው አስፈላጊው ማስረጃ እንዲቀርብና ተገቢው ማስተካከያ እንዲደረግላቸው ለየመ/ቤቶቹ በላክነው ሪፖርት አሳስበናል።

የበጀት አጠቃቀም
ከተደለደለው በጀት በላይ ወጪ የሆነ ሂሳብ
/ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በአግባቡ መጠቀማቸውን ለማረጋገጥ በተደረገው ኦዲት 27 /ቤቶች ለልዩ ልዩ የሂሳብ መደቦች ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ በደንቡ መሠረት ሳያስፈቅዱ ሥራ ላይ የዋለ ብር 212 ሚሊየን 476 799 ብር 01 ሳንቲም ተገኝቷል።
ከበጀት በላይ ወጪ ካደረጉ /ቤቶች ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ብር 40 ሚሊየን 976 939 ብር 3 ሳንቲም፣ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ብር 30 ሚሊየን 910 509 ብር 49 ሳንቲም፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ብር 28 ሚሊየን 217 838ብር 81 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ብር 22 ሚሊየን 225 409 ብር እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቆላ ዝንብ ማጥፊያ ፕሮጀክት ብር 21 ሚሊየን 636 005 ብር 12 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
በመሆኑም /ቤቶች በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅና ደንብ መሠረት የተፈቀደላቸውን በጀት በተገቢው መንገድ የበጀት ዝውውር በማድረግ አስፈቅደው ሥራ ላይ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበናል።

No comments:

Post a Comment