Sunday, May 19, 2013

ሁላችንም ለሀገራችን ጉዳይ ያገባናል።


 ለጎረቤት ኤርትራ ሰላማዊ ሰልፍ  ተፈቅዶ ለኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ መከልከል! ምን የሚሉት የእብደት ስራ ነው።
ትንሽ ስለ ሰላማዊ ሰልፍ መከልከል እናውጋ።
 የሰላማዊ ሰልፍ መብታችን ይመለስ ስንል ምን ማለታችን ነው? መብት ተፈጥሮ የሚያድለን በመሆኑ መብቱን የሚቀሙን ይኖራሉ እንጂ የሚሰጡን አይኖሩም፣ ስንቀማ ይመለስልን ብለን እንጠይቃለን። ይህን ከምናደርግባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ ራሱ ሰላማዊ ሰልፍ ነው። ባለፉት 22 ዓመታት ደግሞ ጥቂት የማይባሉ ሰላማዊ ሰልፎች በመንግሥት ኃይሎች ታግደዋል/ተበትነዋል። ሕገ መንግሥቱ ግን "መሣሪያ ሳይዙ ሰልፍ ማድረግ" መብት መሆኑን ያረጋግጣል። ሰልፍ ለማድረግ ደግሞ ህጋዊ ቅድመ ሁኔታው ተገቢውን ጥበቃ ለተሰላፊዎቹ እንዲያደርግ የሚመለከተውን የመንግስት አካል ማሳወቅ ብቻ ነው። አሁን ሰልፍ የመውጣት ፍላጎት /ወይም የምወጣበት ምክንያት/ ይኑረኝም አይኑረኝ መብቴ ግን ተጠብቆ መኖሩን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። ስለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እንዲሁም የመሰብሰብ መብታችን ይመለስ!

ኢትዮጵያ የጥቂት አምባገነኖች ሳይሆን የዘጠና ሶስት ሚሊዮን ዜጎች ሀገር ናት። የህግ የበላይነት ተከብሮ ሰዎች እኩል የሚዳኙብት ፍትሐዊ ሥርዓት፣ በፈለጉበት ቦታ የመኖር ህልውናቸው ፣ሀብት የማፍራትና በማንነታቸው ሳይሸማቀቁ የመኖር ሰብዓዊ መብታቸው እንዲኖር እፈልጋለሁ። ዜጎች ብሶታቸውን ለመግለጽ የሚያስችላቸው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና የመሰብሰብ ህጋዊ መብታቸው ሳይሸራረፍ እንዲከበር አጥብቄ አታገላለሁ።

ስለዚህ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 30 ይከበር። ዴሞክራሲን በተግባር እናውል፣ ደርግና ወኔን አንድ የሚያደርጋቸው የሰላማዊ ሰልፋና የመሰብሰብ የሚከለከለው በሟች አምባገነን መለስ ዜናዊ ግንቦት ሰባት ቀን 1997 . የተገፈፈው የሰላማዊ ሰልፍ መብታችን ይመለስ! ደግመን እንላለን መብታችን ይመለስ!!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!!!!!!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment