ኣንድ ሰው ኣማራን ጠልቶ ትግራይን ሊወድ ኣይችልም፤ጉራጌን ጠልቶ አፋርን ሊወድ አይችልም ትግራይ ጠልቶ ኦሮሞ ወይ ሌላ ህዝብ ሊወድ ኣይችልም።
አንድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሰው የፖለቲካ ፓርቲ ፣ድርጅት በተለያየ ስም ሊያደራጅ ይችላል ችግር የለውም ግን በብሔር ተደራጅቶ ብሔሬን ነፃ ላውጣ ሲል ብሔር ከኢትዮጵያ የተመሰረተ ነው እኮ እረስተውት አይመስለኝም ማላገጥ ካልሆነ በስተቀር! የፖለቲካ ideology ላይቀበለው ይችላል ግን ለብሔሬ ፣ለሕብረተሰቤ ሲል ግን ለትልቋ ኢትዮጵያ አይመስልም ! ከኢትዮጵያ ህዝብ ሌላ የሚወደው ህዝብ ሊኖረው ኣይችልም።
ህዝብን መውደድ የኣስተሳሰብ ዉጤት ነው፣ ህዝብ መጥላትም እንዲሁ። ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ መውደድ ካልቻልን የዘር ሓረጉ ማጣቀስ የመውደዳችን ምንጭ ሊሆን ኣይችልም። ምክንያቱም እኛ (ሁላችን) በወላጆቻችን በኩል ስንወለድ በፍቃዳችን ወይ ያለፍቃዳችን ኣይደለም። ከሆኑ ሰዎች ከሆነ ቦታ በሆነ ግዜ ተወለድን ፣ወደዚች ዓለም ተቀላቀልን። ከዛም መወለዳችን ፣መምጣታችን ወደድነው፤ ምክንያቱም የኛ መወለድ የተፈጥሮ እንጂ የምርጫ ጉዳይ ኣይደልም።
ተፈጥሮኣችን ሰው ሁነን መገኘታችን ያልወደደልን ሰው ወይ ድርጅት ‘ከማንና የት’ እንደተወለድን እንደ መስፈርት ተጠቅሞ ቢወደን ለፖለቲካ ፍጆታ መመፃደቅ እንጂ እውነት ሊሆን ኣይችልም። ምክንያቱም እኛነታችንን (ተፈጥሮኣችንን) ያልወደደልን ሰው እንዴት ሁኔታችንን (የተወለድንበት ቦታና የመጣንበት ብሄር) ሊወድ ይችላል?
ስለዚህ ኣንድ (ወይ ብዙ) ብሄር ጠልተን ሌላው እንደምንወድ ስንገልፅ ከማላገጥና ከግብዝነት ዉጪ ሌላ ትርጓሜ ሊሰጠው አይችልም። መውደዳችን ካልቀረ ሰው እንደ ብሄር ሳይሆን እንደ ሰው እንውደደው። ሰው እውነትና የተፈጥሮ ስጦታ ሲሆን ብሄር ግን የማሕበራዊ (ሰው ሰራሽ) አስተሳሰብ ውጤት ነው።
አንድ አገር በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ዘር የማጽዳት ወንጀል (Ethnic
Cleansing) መፈጸም ከተጀመረ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪም መጪ እጣ ምን እንደሆነ በየግድግዳው ላይ ተጽፎለታል ማለት ነው። በየግድግዳው
ላይ የተጻፈለትን ማንበብ የቻለ ፈጠን ብሎ አካባቢውን መልቀቅ ማሰቡ አይቀርም። ምናልባትም ተወልዶ ያደገበትን ወይንም ለረጅም ጊዜ
የኖረበትን የሚወደውን ቀየውን ለቆ ወደ ቀድሞ ዘመዶቹ ትውልድ ስፍራ መሄድን አሊያም ሌሎች እንዳደረጉት ወደ አረብ አገሮች ወይንም
ወደ ምዕራቡ ዓለም ለመሰደድ ማውጣት ማውረድ ይጀምራል። የቀረው ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ደግሞ ጊዜው ሲደርስ (ለህውሃት ሁኔታው የተሟላ
ሲመስለው ማለት ነው) ቀደም ሲል በሌላ ላይ የተፈጸመው የዘር-ማጥራት ወንጀል ይፈጸምበታል። ያም ሆነ ይኽ በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ
ላይ የተጀመረው የዘር ማጥራት ወንጀል የዜጎችን ኑሮ ቀጣይነት ያናጋል። ዜጎች እንደቀድሞው ባሉበት አካባቢ ተስፋ አይኖራቸውም።
ልማት እና እድገትን ይቆማል። ለምሳሌ በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በጎረቤቱ አማራ ህዝብ መካከል መቃቃር እየፈጠርክ እንዴት አድርገህ
ነው በህዝብ ትብብር የአባይን ግድብ በቤንሻንጉል እየገነባሁ ነው የምትለኝ!? ባጭሩ የአቶ መለስ ራዕይ አብሮት እንዲቀበር ካልተደረገ
በኢትዮጵያ ሁሉም በያለበት በተራ የዘር-ማጽዳት ወንጀልን እንደጽዋ መጎንጨቱ አይቀሬ ነው። ምርጫ 97ን ተከትሎ ድምጽ ይከበር የሚል
ጥያቄ በተነሳበት ወቅት ይመስለኛል በአገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ከሚጫወተው እጅግ ጠቃሚ የፖለቲካ ሚና ባሻገር ቀልዱም የሚጥመኝን
አቶ ጉዲናን አንድ ጋዜጠኛ “ለምን ድርጅትህ (ኦብኮ) ፈረሰ?” ብሎ ሲጠይቀው “የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ህውሃት/ኢህአዴግ የሁልሽንም
በር ያንኳኳል” ማለቱ በወቅቱ ቢያስቀኝም ሃቁን የገለጸበት አባባል ግን እስከዛሬ ድረስ ከአዕምሮዬ አለ። በቃ እንደዚያ ማለት ነው።
ዛሬ በጅጅጋ፣ በደቡብ ህዝቦች እና ቤንሻንጉል ጉምዝ በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ የተጀመረው ዘር የማጥራት ወንጀል ነገ የሌሎችን
በር ያንኳኳል። የሚገርመው ግን ዛሬ በሚሊዮኖች የሚቆጠር አባቱ አሜሪካዊ እናቱ ፊሊፒኖ ወይንም ኢትዮጵያዊት የሆነ አለም-አቀፋዊ
የሰው ዘር እየተፈጠረ ባለበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ይኽን አይነት የዘር ማጥራት ወንጀል መፈጠሩ ነው። ስለሆነም ይኽ ዘር የማጥራት
ወንጀል ፍጹም ተቀባይነት ሊኖረው አይገባ።
ሌባ ቀጪ አጥቶ ለሕዝብ አገልግሎት በሚውል ገንዘብ ደልቦ ሲንጎማለል ይውላል። ተጠቂው ሰፊው ሕዝብ አቧራ ለብሶ ለዕለት ጉርሱ ይማስናል። ፍትሕ የናፈቃት ዓለም። በየጥጋጥጉ ዲስኩር ብቻ ተለጥፎ ይነበባል!‹‹በመፈክር ውስጥ የተሸጎጡ በርካታ ውሸቶች አሉ፤››
“ነጻ ስለመሆን የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም። ሰው በሰውነቱ የሚከበርበትአገር እስከምንመሰርት ድረስ እንታገላለን። የብሶታችንና የትግላችን መነሻለናንተ ለኔ አዲስ ትግል አይደለም” መብታችን ይከበር ነው የምንለው፣ ነፃነት ያስፈልገናል፣ማንም እንዳሻው
ተነስቶ ህወሃትን አምልኩ እንዲለን አንፈቅድም! ግን ለምንድን ነው እርስ በእርስ እየተሻኮትን ለወያኔ እድሜ የምንጨምርለት? ፖለቲከኞቹሰ
ብንሆን የምንታገለው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ካልን ልዩነታችንን አጥበን አንድ ላይ ማበር ያልቻነው ለምንድን ነው?
ህዝቡ አንድ በሆነበት ሰዓት በፖለቲካው ድርጅቶች ርዕዮተዓለም መከፋፈል ምክንያት ህዝቡን ከጨቋኝ ስርዓት መታደግ ያልተቻለበት ግዜ
ላይ መሆናችንን አስተውለናል ካላስተዋልን እናስተወል እንጂ! ዛሬ በዚህ ወሳኝ ትግል ምዕራፍ በሆንበት ወቅት ላይ ሆነን አንድነታችን
ካልታየ ነገ ደግሞ እንደፈራነው ስንታገል የነበርነው ድርጅት እራስ በራሳችን መሻኮት ልንጀምር ነው ማለት ነው አረ ጠንቀቅ እንበል!!
ለፖለቲካ ድርጅቶች እውነት
ለኢትዮጵያ ህዝብ ቆመናል ካልን አንድ የሚያረገን፣ የምናብርበት ግዜ አሁን ነው። ከዚህ የከፋ የጭቆናና የአፈና ዘመን አታሳዩን!
ለህዝባችን በአንድ ላይ እንቁም !ዛሬ ህውሃት በወንዝ ላይ የወደቀ ዛፍ በሆነበት ግዜ እኛ የወንዙን ውሀ መልቀቅ ሲገባን የሀሳብ
ልዩነት ገደለን። የነፃነት ጉዞ መጨረሻው ያማረና ጣፋጭ ነች። ድል ነፃነት ለናፈቀው ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም
ትኑር !!!
No comments:
Post a Comment