Kiram Yonas
እስክንድር ነጋ አንዱአለም አራጌ ርዮት አለሙ በቀለ ገርባ አበበ ቀስቶ የሀይማኖት ጥያቄ ያነሱ ሙስሊም ወንድሞች እና ሌሎችም አንዳቸውንም በአካል አይቼ አላውቅም በፅሁፋቸው በፖለቲካዊ ተሳትፏቸው አሊያም በሰብአዊ መብት ተሞጋችንታቸው ብቻ ከማወቅ ውጪ: በተለይ በተለይ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ከጀመረ በሆላ አንድም ሳላስቀር ስከታተል ቆይቺያለው:: አሳሪው እውነት ሊኖረው ይችላል በሚል የዋህነትም ጉዳዩን በነፃ ህሊና ለመከታተል ሞክሪያለው እያደር ግን ሊሆን አይችልም የሚባለውን የምታደርግ ሀገር ውስጥ መኖሬን የሚያረጋግጥልኝ እጅግ አይን ያወጣና ፍፁም ተስፋ የሚያስቆርጥ ትርጉም ከሚሰጠው የህፃን ጨዋታ ጋር እንኳን የማይስተካከል የአቃቤ ህግና የዳኝነት ስርአትን አይቼበታለው: በሀገሬ ምንም ተስፋ የለኝም ምክንያቱም ግለሰብ ቢበድለኝ ፍርድ ቤት ነፃ ያወጣኛል የሚል እምነት የለኝም ባለስልጣኑ ፓርቲ በፖለቲካ አቋሜ ቢወነጅለኝ ፍርድ ቤት ንፅህናዬን አይመሰክርልኝም ንፅህናዬን ሊመሰክርልኝና ነፃ ሊያወጣኝ የሚችለው ብቸኛው ተቋም ላይ እምነት ከሌለኝ ሀገሬ ለኔ ምኔ ነች? ታላቁን ግድብ ብትገድብ የቦሌን መንገድ ብታሳምር ኮንዶሚኒየም ከየቤቱ እየጠራች ብታድል ገቢዬ በእጥፍ ቢያድግ ነዳጅ ብታገኝ ባታገኝ ተፈጥሮ የሰጠችኝን ህሊናዬን ተጠቅሜ ያመንኩበትን አስቤ ለሰዎች አካፍዬ በሀገሬ ነፃ ሆኜ መኖር ካልቻልኩ ሰውነቴ ምኑላይ ነው? ጭንቅላታቸውን በማሰራት አገዛዝን ስለሞገቱ ብቻ እዚህ ግባ በማይባል ማስረጃ የመኖር እጣ ፈንታቸው እስርና እንግልት የሆነባቸው ሰዎች ፍትህን በማጣታቸው ብቻ ቤተሰቦቼ ናቸው::
ቤተሰባቸው አመት ባህልን ፍፁም ተስፋ ቢስ በሆነ ጨለማ ውስጥ በሀዘን እና በለቅሶ ሲያሳልፍ ልብን ይሰብራል እራሴን በእያንዳንዱ ታሳሪ ቤተሰብ ውስጥ አድርጌ ስመለከተው ፋሲካው ትርጉም አልባና ጨለማ ነው። የታሳሪ ቤተሰቦችን እውነት ነፃ ያወጣቸዋል አይዟችሁ አልልም እውነት አይኔ እያየ ስንቴ ተቀብሯል እውነት ነፃ የሚያወጣው ኢፍትሀዊነትን የማይኸከም ማህበረሰብ እና ተቋም ሲኖር ብቻ ነው:: በዛሬው እለት የእስክንድርና የአንዱአለም ባለቤት የሚያሳልፉትን ለሊት ማሰብ ብቻውን ሀገር ያስጠላል በቤተሰቡ ውስጥ የሚኖረውን ድብርት እንዲሰማኝ እዛቤት ነዋሪ መሆን የለብኝም: ይህንን ስፅፍ ፍፁም በብስጭት ውስጥ እና በድብርት ውስጥ ሆኜ ነው….. አዲዮስ አንቺ ሀገር በምድርሽ ብኖርም ግፍሽ ስላስጠላኝ ተፋትቼሻለው ለግንባታ ሳይሆን ቀድሞ ለተገነባው የሰው ልጅ ክብርና ዋጋ ስትሰጪ እንታረቅ ይሆናል።እስክንድር ነጋ አንዱአለም አራጌ ርዮት አለሙ በቀለ ገርባ አበበ ቀስቶ የሀይማኖት ጥያቄ ያነሱ ሙስሊም ወንድሞች እና ሌሎችም አንዳቸውንም በአካል አይቼ አላውቅም በፅሁፋቸው በፖለቲካዊ ተሳትፏቸው አሊያም በሰብአዊ መብት ተሞጋችንታቸው ብቻ ከማወቅ ውጪ: በተለይ በተለይ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ከጀመረ በሆላ አንድም ሳላስቀር ስከታተል ቆይቺያለው:: አሳሪው እውነት ሊኖረው ይችላል በሚል የዋህነትም ጉዳዩን በነፃ ህሊና ለመከታተል ሞክሪያለው እያደር ግን ሊሆን አይችልም የሚባለውን የምታደርግ ሀገር ውስጥ መኖሬን የሚያረጋግጥልኝ እጅግ አይን ያወጣና ፍፁም ተስፋ የሚያስቆርጥ ትርጉም ከሚሰጠው የህፃን ጨዋታ ጋር እንኳን የማይስተካከል የአቃቤ ህግና የዳኝነት ስርአትን አይቼበታለው: በሀገሬ ምንም ተስፋ የለኝም ምክንያቱም ግለሰብ ቢበድለኝ ፍርድ ቤት ነፃ ያወጣኛል የሚል እምነት የለኝም ባለስልጣኑ ፓርቲ በፖለቲካ አቋሜ ቢወነጅለኝ ፍርድ ቤት ንፅህናዬን አይመሰክርልኝም ንፅህናዬን ሊመሰክርልኝና ነፃ ሊያወጣኝ የሚችለው ብቸኛው ተቋም ላይ እምነት ከሌለኝ ሀገሬ ለኔ ምኔ ነች? ታላቁን ግድብ ብትገድብ የቦሌን መንገድ ብታሳምር ኮንዶሚኒየም ከየቤቱ እየጠራች ብታድል ገቢዬ በእጥፍ ቢያድግ ነዳጅ ብታገኝ ባታገኝ ተፈጥሮ የሰጠችኝን ህሊናዬን ተጠቅሜ ያመንኩበትን አስቤ ለሰዎች አካፍዬ በሀገሬ ነፃ ሆኜ መኖር ካልቻልኩ ሰውነቴ ምኑላይ ነው? ጭንቅላታቸውን በማሰራት አገዛዝን ስለሞገቱ ብቻ እዚህ ግባ በማይባል ማስረጃ የመኖር እጣ ፈንታቸው እስርና እንግልት የሆነባቸው ሰዎች ፍትህን በማጣታቸው ብቻ ቤተሰቦቼ ናቸው::
No comments:
Post a Comment