Saturday, May 18, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለምን?


1. የታሰሩ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ይፈቱ
2. የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ጥያቄዎች ባግባቡ ይመለሱ

3. ዜጎችን ከቀዬአቸው በታጠቁ ሃይሎች አስገድዶ ማፈናቀል ይቁም

4. መንግስት ሙስናን የሚቆጣጠሩ ትክክለኛ ፖሊሲዎችን በማዉጣት ሐገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ ያድን

የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘር ጎሳ ሃይማኖት እንዲሁም ሌሎች ልዩነኦቻችን ሳይገድቡን በአንድነት ምላሽ ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው:: ለህዝብ ጥያቄዎች በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ የማይሆኑ ተቃዋሚ ድርጅቶች ለህዝብ እየታገሉ ሳይሆን የህዝብን ትግል እያዳከሙ እንደሆኑ ሊረዱ ይገባል:: 
ፓርቲው ያቀረበው ጥሪ የኢትዮጵያ ህዝብ እየደረሰበት ያለው ከፍተኛ ችግር እንዲፈታ የተቀደሰ አላማ አንግቦ እንደሆነ ይታወቃል:: ይህንንም መሰረት በማድረግ የቀረበው ጥሪ አሸዋ ላይ ተበትኖ እንዳይቀርና ከኢትዮጵያውያን ጆሮ እንዲደርስ ቀናይነት ባለው ሁኔታ ላሉት ሚዲያዎች ሳሳስብ እንደነበር ይታወቃል:: ስለሆነም ሚዲያዎቻችን ይህ ህዝባዊ ጥሪን ለህዝብ ለማዳረስ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉና ቢያንስ በቀን 5 እና 10 ደቂቃ ጥሪውን ማንሳት እንደሚያስፈልጋቸው በተደጋጋሚ ለመግለፅ ሞክሬአለሁ::
 
በዚህ አጋጣሚ የኢሳት ራዲዮ በዛሬው ፕሮግራሙ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርንና የኢትዮጵያ ሙስሊም ተወካይን አነጋግሮ ላነሳውት ሃሳብ ጅማሮ በማሳየቱ እጅግ አድርጌ ላመሰግን እወዳለሁ:: ይህም ሃላፊነትን የመወጣት ተግባር በሌሎችም ሚዲያዎች እንደምናየውና እስከመጨረሻው እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ:: 

ይህ የዩቱብ ምስል እነኝህን ሁለት ቃለመጠይቆች ያካተተ መሆኑን በመግለፅ እንዲያዳምጡት በአክብሮት እጋብዛለሁ:: 

ስላዳመጡ አመሰግናለሁ::

http://www.youtube.com/watch?v=VO_9JJDyNZs&feature=youtu.be

http://www.youtube.com/watch?v=VO_9JJDyNZs&feature=youtu.be

No comments:

Post a Comment