የጠለቀ ጥላቻ በዚች ታላቅ ሃገር ላይ ያለው ዘረኛው የህውሃት ቡድን ኢትዮጲያዊ መንፈስን ከሕዝብ ለመንጠቅ አንዱን ከአንዱ ለመለየት፣ በጎጥና በዘር እንዲሁም በእምነት ለመከፋፈል ሌት ከቀን ዘመኑን ሙሉ ለፍቷል፡፡ ሕዝብ አንድነትና ሕብረት እንዳይኖረው ውስጥ ውስጡን ሲያበጣብጥ፣ በዘር በተለከፉ ጀሌዎቹ አንዱን በአንዱ ላይ ለማስነሳት የሽብር ተግባር ሲከውኑ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መጠሪያው የኢትዮጲያ ሕዝብ የሆነ ግን ደግሞ በሆድ አደር ካድሬዎች በሚመራው የሕዝብ ሃብት በሆነው ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅትና ልማታዊ ጋዜጠኞች
በኩል የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ በመፈብረክ
የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበሩን ለማሳየት የሀሰት ፕሮባጋንዳ ሲደልቅ ይታያል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ መረዳት ያለበት!
1. የ ስርአቱን አዘናጊ አጀንዳ ጠንቅቆ መረዳት፤
2. ይህ ያንተ አጀንዳ እንጂ የሕዝቡ አይደለም ማለት፤ አለማጀብ፤በመንገዱም አለመሔድ፤ማምከን፤
3. ትኩረት ባለው የሕዝብ አጀንዳ ላይ መንቃሰቀስ፤
4. የህዝብን የመሰረታዊ የዲሞከራሲ፤የነጻነት፡የመብት ጥአቄዎችን፤የአገርን ሉአላዊነት አንድነትና ዘላቂነት የሚመለከቱትን ጉዳዮች በማጉላት-የለውጥን ባቡር ጉዞ ማፋጠን።
ከዚህ -ከምናውቀው ከተማርነውና ካስተዋልነው አንድ ተጨማሪ ግንዘቤ እንደወሰድን ይገመታል። በዚህም የስርአቱን የወደፊት አጀንዳ አስቀድም መተንበይ ይቻላል። በሚገርም ሁኔታ የ2015 ምርጫን አንስተው ሕዝን ሊያንጫጩ እንደሚሞክሩ መገመት አያዳግትም። አንድ ታምር -እንበለውና- አንድ ነገር ካልመጣ ስርአቱ እንዲሁ በድኑን እየተንቃሰቀሰ፤ ሙቱን አየተንገዳገደ፤ አደጋ አያንዣበበበት እዚያ ሊደርስ አንደሚሞክር መገመት አያዳግትም። ለነገሩ መሰሪነት ጨርሳ ባትጠፋም ሳትሞት አልቀረችም። ለእነርሱም ሰዎች -ጊዜአቸው
አስቀድሞ ያበቃ፤ በተዋሰ ጌዜ እንደሚንቀሳቀሱ፤ ጊዜና ሕዝብ እንደከዳቸው ሀይልም ትምክህትም ሸፍጥም አንደማያዋጣ ቢረዱና መንገዳቸውን ቢፈልጉ ከባሰ ሁለገብ ቀውስ መዳን ይሆናል ።
ይህም ሆኖ በየወቅቱ አዘናጊና አደናቃፉ አጀንዳዎች ቢደቀኑበትም -ሕዝቡ እንደተባለውም፦
በሰራው ወጨፎ በሰራው እርሳስ፤
ጥልያን ጠፈጠመ ዳግመኛ እንዳይደርስ!
ብሎ በገዛ አጀንዳው እተመታና እፍረትን ውርደትን እየተከናነበ እዚህ የድል ምእራፍ ላይ እንደደረሰ መጠቀስ አለበት። ሕዝቡ ምንጊዜም ባለድል ነው። ሕዝብን ዘለአለም ለማታለል መሞከርና -ለጊዜውም ቢሆን- ተላላነት ነው።
ለማጠቃለል-የኤርትራ ጦርንተ ተባለ ትረፉ እልቂት፤ውርደት። የአልጄርስ ስምምነት ድለ ነሳን ተባለ ባዶ ኳካታ ውርደት። ምረጫ ተባለ ሽንፈት። ወደእስር በሐሰት ክስ የገቡትመም ተፈቱ–ውርደት። የሶማሌ ጦርነትም ትረፉ እልቂት-ያለቀው ቁጠሩ እነኳ ሳይነገር-አሊ-ሽባውም አግር አውጠቶ ተጠናከሮ ጦርነቱን ቀጠለ። ድርቅ ተከሰተ-ድርቅና ረሃብ የቋንቋ አቃቂር መጣ-አንድም ሰው አልሞተም-ተባለ በቅርቡ በሶማሊያ ከ260፣000 ሕዝብ በላይ ማለቁን ተነገረ። አሁንም የምስራቁ ኢትዮጵያ ጉድ ተዳፍኖ አለ-ትልቅ መጪ ውርደት። ዳግም ምርጫ ተባለ-99.6% ውርደት። ሰውየው በሕይወት አለ ሲባል ተከረመ-ሰውየውም ሞተ። የሕዝብ ማፈናቀል ተሸረበ-የባሰ ውርደት የዘረኝነት ሴራ መጋለጥ። አሁን ደግሞ ሙስና ተባለ-ሲወተወት የነበረው የስርአቱ በዝርፊያ መንቀዝ በራሱ ኮሚሽን ይፋ መውጣት የባሰ ዝቅተት። ብዙ ሊጻፍ ሊነገር ይቻላል። ሕዝቡ ስርአቱን በአጀንዳው ካጠናቀቀው፤በራሱ አጀንዳ ቢራመድ ምንኛ የመከራው ጊዜ ባጠረች። ይህም ሲባል በሕዝቡ አጀንዳ ላይ ሳያሰልሱ ሲታገሉ በመጨረሻም የተናገሩት እውነት መሆሉን በተግባር በብቃት ያስመሰከሩ ብዙዎች እንዳሉ መጠቀስ አለበት።
ለቀባሪው አረዱት አይሁንና-ቁምነገሩ ሕዝቡ በስርአቱ አጀንዳ ሳይሆን በራስ አጀንዳ ስር መንቃሰቀስ አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን ማመልከት ተገቢ ነው። ስርአቱ ከእንግዲሕ የቀረው የቅዠት አጃንዳ ብቻ ነው። በዚህ መሄድ ደገሞ -በሌላው ቅዠት መቃዠት ነው የሚሆነው! ከእንግዲህም ቀልጠፍ ብሎ -አጀንዳህ ምድረ ነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል። አግባብነት ያለው ተመራጭ አጀንዳ-የተባበረ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ነው ቢባል ተገቢ ይሆናል! አጀንዳዎችን አጥንቶ መጓዝ ተገቢ ነውና!! እንቅስቃሴውም -ሲፈለግ የነበረውን አንድነት ቅንጅትና ሕብረት ሊያመጣ ይችላል።አንድነት ለእንቅስቃሴ፤እንቅስቃሴም ለአንድነት።
አጀንዳን እያስቀደሙ ማዘናጋት ከተጠያቂነት አያድንም!!!
ኢትዮጵያ በእግዚአብሔርና በጠንካራ ታጋሽ በሕዝቧ ተጠብቃ ትኑር!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment