Tuesday, May 21, 2013

ከበደ ካሳ ጩኽትህ ከሲኦል ይውን !!



አንድ ልማታዊ የኢቲቪ ጋዜጠኛ ከበደ ካሳ ይባላል የፃፈውን ፅሁፍ ላካፍላችሁ እንዲ ይላል ተስፈኛዉ "መንግስት" የቦንድ ሽያጭን አወገዘ
በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በህመም ላይ ሳሉ ሃገራችን ገደል አፋፍ ላይ ቆማለችና እንታደጋት ብለዉ በአሜሪካ ምድር ኢትዮጵያን የሚገዛ አንድ ተስፈኛ መንግስት አቋቋሙ፡፡  ስመሙንም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት ምክር ቤት አሉት፡፡በማለት ይጀምራል የወሬ አራራው ለመወጣት!
ከበደ ካሳ በመለስ ዕራይ ካበዱና ከሰከሩ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም አዜብ መስፍን እንኳን እንደሱ በራዕይ ያበደች አትመስለኝም!
 ሲፅፍ እንዲ ብሎ ነው የጀመረው የደብዳቤው ይዘትየህዳሴ ቦንድ የሚባል ነገር በአሜሪካ መሸጡ ይቁም፡፡ የገዙትም ገንዘባቸው ይመለስላቸዉ የሚል ነዉ፡፡ምኑ ነው የገረመው የሚዋጣው ገንዘብ እኮ እያየን አይደለ እንዴ የባለስልጣኑን ኪስ እያዳበረ
እነሱን ባለፎቅ፣አስመጪና ላኪ፣ ወገኔ ድሃው የሚበላው አቶ በርሃብ አለንጋ ሲመታና በየስደቱ በርሃ ለበርሃ በመንከራተትና ባህር ሲበላው ምነው ይህ አልገረመውም ልማታዊው ከበደ?ሌላ ያለውን ደግሞ ስሙት በውጭ ያሉት ተቃዋሚዎች በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የኢትዮጵያ ህዝብ ምርር ብሎ ሲያዝን ቢመለከቱት ጭንጋፍ የሕዝብ ርኩስ፤ የርጉም ዘመን ልጆች፤ የሬሳጀግና፤ ወዘተ…እውነት ሲነገራቸው ስድብ ስለሚመስላቸው  የስድብ መዓት አወረዱበት ይለናል፡፡ የኛዉ አልበቃ ብሏቸዉ በፍርፋሪዋ የምታኖራቸውን ሀገር ከፍተኛ ዲፕሎማት ሱዛን ራይስን ዘለፉ፡፡ መለስን በተመለከተ በጎ የተናገሩትን ሁሉ ጥላሸት ለመቀባት ባለ በሌለ ሃይላቸዉ ተረባረቡ፡፡ ከበደ ለመለስ ያለቀሰው ህዝብ እኮ ተገዶ ነው ኑሮው ያስለቀሰው ህዝብ እኮ ለሰው ያለቀሰ ይመስላል ለራሱ ሲያለቅስ! በውዴታም በግዴታም ሰው ደግሞ ሊያለቅስ ይችላል! እንዳንተ አይነቱ በውዴታ ያለቅሳል ሌላው ደግሞ ከነጠቃ ፍራቻ ያለቅሳል! ቢሰደብም አትገረም አንተም በፍርፋሬ የምታኖራቸውን ሀገር ብልአል እኮ የሰው ልጅ በላቡ ሰርቶ የሚኖርበት አገር ነው! በማጎብደድ የሚኖርበት አገር አይደለም  እንደራስ አይምሰልህ። ባጠቃላይ አፋፍ ላይ ያለች አገር ናት እውነቱን እወቀው!

 ኢቲቪ የኢትዮጵያን ህዝብ በማደንቆር፣የውሸት ፋብሪካ እንደሆነ፣ በቱልቱላና አእምሮአቸውን በብር በሸጡ ባለሙያ ተብዬዎች ፕሮባጋንዳ እንደሚነፉ የኢትዮጵያ ህዝብ በደንብ ጠንቅቆ ያውቃል!
እውነታው ግን የአባይን መገደብ የሚቃወም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የለም  ነገር ግን አባይ የሚገደበው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀም ከሆነ  ህዝብ ይከበር ነው የምንለው  ከአባይ በፊት፦
ዘረኝነት ይገደብ !
ህዝብን ማፈናቀል ይቁም !
ሰብአዊነት ይቅደም !
በሃገራችን የአፓርታይድ ስርዐት ይወገድ !
የሃይማኖት ነጻነት ይከበር !
አባይን ለርካሽ ፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ይቁም !
በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች ይፈቱ !
የሙስሊም ድምጽ ይሰማ !
ታሪካዊ ገዳማችን ዋልድባ ይከበር !
በህዝብ የተመረተ መንግስት ይምራን !
የህዝብ ድምጽ ይሰማ !
ነብሰ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ !
እና ሌሎችን ተያያዥነት ያላቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ነው የተጠየቀው ።የሚገርመው ግን በቅርብ ጊዜ ገንዘብ ለመሰብሰብ ጀሌዎቹ የገጠማቸው በየአውሮፓው፣በአረብ አገራት፣በደቡብ አፍሪካ፣በአሜሪካ ትልቅ የመሰረታዊ ጥያቄ ማሳያ ነው።ተስፈኛው እራስ ነን እውነትንና እሊናህን በገንዘብ ለሽጥክ ተስፈኛው የኢትቪ ሎሌ ለወንከው* የሚቃወመውማ *እውነትን ተመርኩዞ ነው ሰው ሲገደል፣ሰው ሲታስር፣ ሰብኣዊ መብት ሲረገጥ፣ብሔርን ክብሔርን ሲያጣሉ፣ኢትዮጵያዊነትን መንፈስ አደብዝዘው አገር ለባዳ ሲሸጡ ዝም ብሎ ለተቀመጠው ለተስፈኛው ከበደ ካሳ ነው የማዝነው!
አሁንም ደግሜ እልሃለው ከበደ ካሳ ጩኽትህ ከሲኦል ይውን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

የፃፈውን ፅሁፍ ከዚህ በታች በመጫን ማንበብ ይቻላል።


  

No comments:

Post a Comment