Saturday, May 31, 2014

ዓባይ እንደዋዛ፤ ግድቡን ከጥላቻ አንጻር ማየት አደገኛ ነው (ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፣ ክፍል አራት)

አክሎግ ቢራራ ዶ/ር (ክፍል አራት)

Click here for PDF

የዚህ ተከታታይ ፅሁፍ መሰረታዊ ሃሳብና ትንተና፤ ኢትዮጵያ ዓባይንና ሌሎች ወንዞቿን የራሷን ኢኪኖሚ ዘመናዊነት፤ ለሕዝቧ የምግብ ዋስትና ስኬታማነት፤ እያደገ ለሄደው ወጣት ትውልድ የስራ እድል የመፍጠር ወዘተ መብት ያላት መሆኑን የሚያጠናክር ነው። The Nile is African and Ethiopia is its hub በሚል አርእስት ለአለጀዚራ ያቀረብኩት ፅሁፍ ይኼን ይገባኛልነት በማስረጃ ተደግፎ ያሳያል። በአረብኛ የተተረጎመው ትንተና የብዙ አንባቢዎችን አስተሳሰብ እንደቀሰቀሰ ሰምቻለሁ፤ አሉታዊና ነቀፋ ያለበት ትችት አልደረሰኝም። የኢትዮጵያን ይገባኛልነት ሌሎች የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች እንደሚደግፉም አሳይቻለሁ።

ኢትዮጵያ እውነተኛ ልጇን አጣች

በልጅግ ዓሊ – ፍራንክፈርት

ብዙ የውጭ ሃገር ሰዎች ሃገራችንን ይወዳሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የኦስትርያ ተወላጅ የሆነው ካርልሃይንዝ ቦይም(Karlheinz Böhm ) ነበር። ነገር ግን ካርልሃይንዝ የዓለም ዜጋ(Weltbürger) ነኝ ብሎ ነበር የሚያምነው። ቢሆንም ካርልሃይንዝ 2003 የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ተቀብሏል።Karlheinz Böhm1
ይህንን ታላቅ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ኢሊባቡር ውስጥ ጉመሮ ሻይ ተክል መጥቶ በነበረበት ወቅት ነው። በዚያ ወቅት የተነገረን የፊልም ተዋንያን መሆኑን ብቻ ነበር። ጀርመን ከመጣሁበት ቀን ጀምሮ ስለዚህ ሰው ደግነት በሰፊው ልረዳ ችያለሁ።
ካርልሃይንዝ በተወለደ በ86 ዓመቱ ያለፈው ሐሙስ ሌሊት ሳልዝቡርግ – አውስትሪያ ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ለውጥን ፈልገን ለውጥንም ፈርተን በጭራሽ አናመጣውም

ዳዊት ዳባ
የለውጥ አስፈላጊነት ላይና ወያኔ መራሹ መንግስት ይበቃው ዘንድ ባብዛኛው ዜጋ ከተቻለ የሚለው እንዳለ ብዥታ የለም። ይህ ፍላጎት የብዙ ስረአቱ ውስጥ ያሉ ዜጎችም ጭምር መሆኑን የተለያዩ መረጃዎችን ጨምቆ ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል። በርግጥ የለውጡ አስፈላጊነት ላይ የሚስማሙና አይቀሬነቱን የሚያውቁ ነገር ግን ለውጡ የተረጋጋና ችግሮች ያልበዙበት እንዲሆን ይረዳል ብለው አገዛዙ ድርሻ በሚያደርግበት እንዲከወን የሚመኙ አሉ። ፈራ ተባ እያሉ ሀሳቡን አንዳንዴ ያነሱታል። ይህ ሀሳብ ክፋት ባይኖረውም ጥሩ ምኞት ብቻ ነው የሆነው። በትንሹ እንኳ ተቀባይነት እንዲያገኝ አይደለም እንዲሰማ ለማድረግ አገዛዙ ጉልብት አልሰጠው እያለ ብለጭ ድርግም ይላል።

Thursday, May 29, 2014

ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን

ከሮበሌ አባቢያ
በአምቦ ከተማና በሌሎች የኦሮምያ ክልል ውስጥ የዩኒቭርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያቀረቡት ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ በጨካኙ የአግዓዚ ጦር አልሞ ተኳሾች በጥይት መደብደብን ስለሆነ፣ ይህንን አሰቃቂ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ ያውም ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰብአዊ መብት መከበር ግምባር ቀደም መመሪያ ሆኖ በዓለማችን ላይ በገነነበት ጊዜ በመፈፀሙ፣ ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም። ይህንን የተገነዘበው የባእዳንን ዓላማዎች ለማስፈፀም በጫንቃችን ላይ የተኮፈሰው የወያኔ መንግሥት አገልጋዮቹ ለፈፀሙት ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ወንጀሉን በመሸፋፈን የሕዝብ ትኩረት ወደ እርሱ ሙገሳ እንዲዞር እነሆ 23ኛውን የወረራ በዓሉን ሲያከብር በመፍጨርጨር ላይ ይገኛል። ነገር ግን ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን ተብሎ መዘከሩ አይቀርም።

የቅድመ ምርጫ አፈናው በውይይት እንዲተካ እንጠይቃለን!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

እንደሚታወቀው የግንቦት 2ዐን 23ኛ ዓመት ለማክበር ጉድ ጉድ እያለ የሚገኘው ገዥ ፓርቲ ወደ ጠቅላይ አምባገነን ፓርቲነት ከተለወጠ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በ1983 ዓ.ም ሀገሪቱን ከመቆጣጠራቸው በፊት በርካቶች ስለ ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሰብአዊ መብት መከበርና ዴሞክራሲ ሥርዓት መስፈን ክቡር ህይወታቸውን እንዲገብሩ ተደርጎ በተገኘ የዜጎቻችን መስዋእትነት መንበረ ሥልጣኑን ቢጨብጡም በተግባር ዋጋ የተከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት አልቻሉም፡፡ እንዲሁም የህዝቦችን ነፃነት በጉልበት በመቀማት፣ ሰብአዊ መብትን በመጋፋት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ለማስመሰያነት በንድፈ ሃሳብ አስፍረው በተግባር በዜጎችዋ ግፍ በመፈፀም ነፃነውን ፕሬስ እንደጠላት በማየት፣ ተቀናቃኝ ኃይሎችንና የፖለቲካ መሪዎችን በማሰርና በማፈን፤ በነፃነት የመደራጀት መብትን በመጨፍለቅ በአጠቃላይ ፍፁም አምባገነን የሆነ ስርዓት በመዘርጋት ላይ ነው፡፡

ውሸት ሲደጋገም ዕውነት እንዳይመስል፣ ስንናገርም ሆነ ስንጽፍ ልንጠነቀቅ ይገባል!

ተክሌ የሻው
ዛሬ ከአገራችን አውራ ችግሮች መካከል ዋናው፣ የተደጋገሙ ውሸቶች ዕውነት የመሰሏቸው ቡድኖች የሚያጎኑት በጥላቻ ላይ የተመሠረተ የዘር ፖለቲካ እና አንድን ነገድ፣ በኢትዮጵያ ተፈጠሩ ለሚባሉ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርገው ነው ብዬ አምናለሁ። አይደለም የሚለኝ ከመጣም የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ነኝ። የተደጋገሙ ውሸቶች ሀውልት ሲያስቆሙ እያዬን ነው። የአኖሌን ሀውልት ለአብነት መመልከት ነው። የከተሞችን ስም ሲያስለውጥ እያዬን ነው። አዲስ አበባን ፊንፊኔ፣ ናዝሬትን አዳማ፣ ደብረዘይትን ቢሸፍቱ፣ አዋሣን ሀዋሣ፣ ዝዋይን —ሌላ ሌም አለ። ወደ ኋላ እንይ ከተባለ ወለጋ፣ ቢዛምን፣ ኢሉባቡር እናርያ፣ አርሲ ፈጠጋር፣ ወሎ ላኮመልዛ ወዘተ ማለት ይቻላል። ይህ ግን አይጠቅምም። የኋሊት ጉዞ ያስከትላል። ይህ ደግሞ ወደ አንጋዳ በራስ ኃይል መውደቅን ያመጣል። ይህ ሁሉ የሆነው ውሸት በመደጋገሙ ነው።

Tuesday, May 27, 2014

አቶ ስብሃት ነጋ – የእንደራደር ጥያቄዎን በታማኒ ተግባር ይጀምሩት!

ከአቢቹ ነጋ
ከዚህ በፊት የግንቦት ሰባት ድርጅት የንደራደር ጥያቄ ከኢትዮጵይ መንግሥት አንደደረሰው በአፅኖት አውርቶናል። ብዙ ሕዝብ የግንቦት ሰባትን ዜና በማድቤት የተፈበረከ እራስን የመካቢያ ወሬ አድርጎት አንደነበር አይዘነጋም። እኔ ግን ዜናውን አንደወረድ መቀበል ብቻ ሳይሆን ደስተኛም ነበርሁ። ኢትዮጵያን አግዚአብሔር አንደሚጠብቃትም ያመንሁበት ወቅት ነበር ማለት ይቻላል። የዋህ ላገር ቅን አሳቢ ስለሆንህ እንጅ ከእባብ የርግብ አንቁላል እንዴት ትጠብቃለህ ብባልም የባብ መርዝም መዳህኒት ሊሆን እንደሚችል ይታወቅ ብያለሁ።TPLF power broker, Sibehat Nega
ከሁልም ያስደስተኝ ግን ግንቦት ሰባት ጥያቄውን በሕዝባዊ መግለጫው ያስተናገደበት ዘዴ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ድርጅቱ በኢሃዴግ ተጠይቆ ከሆነ ጉዳዩን በምስጢር ይዞ ማካሄድ ነበረበት ብለዋል።

Thursday, May 22, 2014

አኖሌ…..የባህር ዳር ነውር….አምቦ እና ግምቢ

ኢትዮጵያችን አደጋ ላይ ነች። የአደጋዋ ምንጭ ህወሃት እና ህወሃት ነው። ህወሃቶች በአገራችን ላይ የመዘዙት የበቀል ሰይፍ ወደ ሰገባው የሚመለስ አልሆነም። ከበቀል ስሜታቸው ጋር መቶ ዓመት የመንገስ ምኞት አላቸው። ምኞታቸውንም እውን ለማድረግ የንፁሃን ደም ለህወሃቶች መስዋዕት ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል። እስከ ዛሬ ብዙ ኦሮሞዎችና አማሮች መሥዋዕት ሁነዋል። የመስዋዕቱ ምንጭ እንዳይደርቅ አሩሲ ላይ አኖሌ ቁሟል።እርሱን ተከትሎ ባህር ዳር “አማራና ኦሮሞ” ኳስ እንዲጫወቱ ሁኖ ነውር የሆኑ ስድቦች እየተነቀሱ ወጥተው በኢቲቭ እንዲተላለፍ ተደረገ። ይሄን ተከትሎ የመሬት ቅርምቱ ተከሰተ። አምቦና ግምቢ ላይ በህወሃት-ኦህዴድ ፊታውራሪነት የንፁሃን ደም በከንቱ ፈሰሶ ህወሃት የለመደውን ምሱን አገኘ።

ኢትዮጵያዊነት – ክፍል አንድና ሁለት (ሄኖክ የሺጥላ)

flag ethio

ኢትዮጵያዊነት በተቃርኖ የተሞላ የግሳንግስ ስብስብ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የወጪት ሰባሪዎች ትግል፣ ለኔ በገሌ ነው ባዮች ምክር አይደለም። ኢትዮጵያዊነት በበግ ጸጉር ቡክርናውን እንደቀውማው ያዕቆብም ( “አታላይ ማለት ነው”) አይነትም አይደለም። በጎሳ አሽክላ ተተብትበን፣ በቂም ቆመን፣ ጭረት አመርቅዘን ቁስል አርገን ፣ የዛሬ ውድቀታችንን ፣ የዘምን ምክነት አስመስለን፣ ላለመቻላችን መወጣጫ፣ ላለመቆማችን የ ምክንያት መቆናጠጫ ብንፈልግ ፣ ካለፈ ጥፋትም ሆነ ሕዝብ ካለፈለት እውነት ጀርባ መዶለታችንን እስካልተውን ፣ የድርሻችንን ለመወጣት ታጥቀን እስካልተነሳን ድረስ ፣ ትግላችን እንደ እስከ ዛሬው “ለ አፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል” ሆኖ ስለመቀጠሉ አዋቂ መሆን አይጠይቅም።

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ "ወንጀል በዘር አይተላለፍም"


gereb babu and beggars

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ “የለሁበትም!” እያለ ነው።

የእርቅ ቀመር/ፎርሙላ

(ያዬ አበበ - 65Percent.org)

recon22

የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ለዚህ ተተኪ ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርዓያነት ማውረስ አስፈላጊነት ስላመንኩበት ስለ እርቅና መግባባት ለመሟገትና ፋና ወጊ ሚና ለመጫወት የዜግነት ሃላፊነቴን ጀምሬያለሁ።

የኢህአዴግ የ23 ዓመት “ፌዴራላዊ የዘር አወቃቀር” ውጤት

ዘረኝነት - በኢትዮጵያ እግር ኳስ!

tok

የጋምቤላ ምርጥ “ቶክ” አንገቱን ደፋ
የኢትዮጵያው ቡናው እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ የጋምቤላ ምርጥ ውጤት ቶክ ጀምስ ይርጋለም ላይ በአንዳንድ የሲዳማ ደጋፊዎች በዝንጀሮ ድምፅ በቆዳ ከለር ተሰድቧል።
በቦታው የነበሩ እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊው ቶክ በድንጋጤ ከሜዳው ወጥቶ የተቀያሪ ወንበር ላይ አንገቱን አቀርቅሮም ታይቷል። በአዲስ አበባ ስታዲየም የግለሰቦች ስም እየጠሩ የሚሳደቡ እንዳሉ ይታወቃል።

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ


tplf addis

ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::
ደርግ
የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::
ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::

Monday, May 19, 2014

የ አንበጣ ምድር (ሄኖክ የሺጥላ)

እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው ” ወደ ፈርዖዎን ግባ ፣ እኔ የ ፈርዖዎንን ና የሹሞቹን ልብ አጽንቼአለሁና፣ ተአምራቴ በነሱ ላይ በትክክል ይመጣ ዘንድ፣ በግብጻውያንም ላይ የተዘባበትሁትን ሁሉ፣ ያደረጉሁባቸውንም ተአምራቴን በልጆቻችሁና እና በልጅ ልጆቻችሁ ጆሮዎች ትነግሩ ዘንድ፣ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። ሙሴና አሮንም ወደ ፈርኦን ገቡ ፣ አሉትም ፣ ” የእብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እምቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፣ ህዝቤን ለመልቀቅ እምቢ ብትል ግን፣ እንሆ ነገ በዚህ ጊዜ በተራራዎችህ ላይ አምበጣ አመጣለሁ ፣ የምድሩንም ፊት ይሸፍናል፣ ምድሩንም ለማየት አይቻልም፣ ከበረዶውም ተርፎ በምድሩ ላይ የቀረላችሁን ትርፍ ሁሉ ይበላል; ያደገላቹን የእርሻ ዛፍ ሁሉ ይበላል; ቤቶችም፣ የሹሞችህም ሁሉ ቤቶች፣ የግብጻውያን ሁሉ ቤቶች በእርሱ ይሞላሉ፣ አባቶችህ ፣ የዓባቶችህም አባቶች በምድር ላይ ከተቀመጡበት ቀን ጀምሮ እስቀዝ ቀን ድረስ እንደ ርሱ ያለ ያላዩት ነው። ሙሴም ተመልሶ ከፈርዖን ዘንድ መጣ። እናም እግዚአብሔር አምላክ ቃሉን ጠብቆ መጣ። እኔም ይሄንን አየሁ ያየሁትንም እናገራለሁ። አንደበቴ ያንተን ትልቅነት ያወራል፣ በቃልህ ትገኛለህ፣ ከቀጠሮህ አትዛንፍም፣ ሃጣን ከጥፋት ውሃው አይተርፍም የተረፉ ምስክሮች ያንተን ትልቅነት ተናጋሪዎች ይሆናሉ።

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ

የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።

አማራውን በሁለንተናዊ መልኩ አዳክሞ መግዛት ወይም ማጥፋት

በጌታቸው ፏፏቴ
ራስ ስሁል(ራስ ስዑል) ሚካኤል መቀመጫውን በጐንደሩ ቤተ-መንግሥት በማድረግ በሥሩ ንጉሶችን በማንገስ ከላይ ሆኖ የሚቆጣጠራት በመሳፍንቶች የምትመራና አንድ ማዕከላዊ የሆነ ግዛቷ ለተወሰነ ጊዜ ተዳክሞ የነበረች ኢትዮጵያችን ይገዛ ነበር። በኋላ በመይሳው ካሣ(አፄ ቴዎድሮስ) የተገነባ ማዕከላዊ መንግሥት ተመስርቶ እነሆ እኛ እስካለንበት ዘመን ደርሷል። የኛው ሞራልና ኢትዮጵያዊነት ወኔ ደግሞ የት እንደሚያደርሰን እናየዋለን።ወደ ራስ ስሁል ልመለስና ራስ ስሁል ሚካኤል ጨካኝና ተንኮለኛ መሆናቸውን የሚያሳይ አንዱን ንጉሥ ከምግብ ጋር መርዝ በመጨመር አንደኛውን ንጉሥ በሻሽ አሳንቀው መግደላቸውን የሚገልጽ አንድ ጹሑፍ አንብቤ ስለነበር የህወሃት ድርጅታዊ ፕሮግራም ከዚህ የተቀዳ ይሆን ? በማለት አንዳንድ የቀደምት ጸሓፍትን መመልከት እንዳለብኝ የግድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

Saturday, May 17, 2014

አገራችን በሕወሃት ምርጫ ዋዜማ

እንደተለመደው ዘወትር በየቀኑ እንደማደርገው ሁሉ – ማክሰኞ ምሽት አካባቢ (ግንቦት 5፣ 2006) የኢትዮጵያን ጠረንና ሙቀት በመሻት፡ የሃገር ቤት ወቅታዊ ዜናዎች ገጾችን ሳፈላልግ/ሳገላብጥ – በቤት ማስተላለፍ ሂደት የሚታየውን የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር ለማስወገድ እርምጃ እየተወሰደ ነው የሚለው በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የተጻፈው አርዕስት ላይ ዐይኔ በድንገት አረፈ።
አገራችን ምርጫ ዋዜማ ላይ ስለሆነች፡ በየመሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣኖች ያልሆነውን ሆነ፡ አገሪቱ ያለችበት ተጨባጭ የፖለቲካና ኤኮኖሚ ሁኔታ እንደሌለና እንዳልነበር ተደርጎ፡ በዕድገትዋ ወደ ህዋዕ መተኮሷ የሚፈበረኩበት ወቅት በመሆኑ፡ ተናዳፊ እባብ ያየሁ ይመስል፡ ከኔ ትዕዛዝ ውጭ ሰውነቴ ክስክስ ብሎ፡ ዜናውን ማንበብ ጀመርኩ።

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ክለላ ዛሬ በድብቅ ሊፈረም ነው! – አብርሃ ደስታ

የኢትዮ ሱዳን ዳር ድንበር በግልፅ የተከለለ እንዳልሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የሚጠቀሙት መሬት የኢትዮጵያ እንደሆነ ሲወሰድ ሱዳናውያን የሚገለገሉበትም የሱዳን ነው ተብሎ ይታሰባል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያውያን አርሶአደሮችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ለሱዳን ማስረከቡ ይታወቃል። ብዙ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች ተፈናቅለዋል፣ የተወሰኑ ተለዋጭ መሬት ሲሰጣቸው ምንም ያላገኙም አሉ።
ድንበሩ ብዙ ዉዝግብና ተቃውሞ ያለው ሲሆን የኢህአዴግ መንግስት ከሱዳኖች ጋር በመተባበር በድብቅ ለመከለል ተስማምቷል። እንዲህ ነው የተደረገው፥ በድንበሩ አከባቢ የሚገኙ ኗሪዎች (የኢትዮጵያና የሱዳን) ድንበራቸውን አይተው ክለላውን ይፈፅማሉ፣ ይፈራረማሉ። ለሱዳን የተሰጠው መሬት ታውቋል። ሁሉም ነገር በኢህአዴግና የሱዳን መንግስት አልቋል። አሁን “የሀገር ሽማግሌዎች” እንዲፈርሙ እየተደረገ ነው። የሀገር ሽማግሌዎች እንዲፈርሙ የተፈለገበት ምክንያት የድንበር ክለላ የተከናወነው በኗሪዎች ነው እንዲባል ነው። ለሌላ ግዜም ምስክር ሁነው እንዲቀርቡ ነው።

የዳላስ ኢትዮጵያውያን ዳግመኛ ችግር ሳᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ

ዘረኛው አገዛዝ የመጨረሻ የሚመስል ከልክ ያለፈ የዘረኝነትና የፍጅት ተግባሩን ቀጥሏል። ሕዝብን ከሕዝብ ማባላቱ የስርአቱ አይነታ ስልት መሆኑን እስካሁንም ያልተረዱ መኖራቸው ያሳዝናል። በአለፉት ፪፫ አመታት ተወልደው ያደጉና በሰላሳወቹ ውስጥ ያሉ ዜጎች ብዙወች የስርአቱ ሰለባወች ሆነዋል። አገርና ሕዝብ ለወያኔ ደናቁርት ምንም ማለት አይደለም። በመሆኑ የአገር ልሂቃን፤ የፖለቲካና የሰበአዊ መብት ተሟጋች የሆኑ ዜጎች ክንዳቸው እንዲጠነክር መተባበርን ይጠበቅባቸዋል።
ወያኔ በአገር ውስጥ ዜጎችን ያለርህራሄ በሚጨፈጭፍበት በዚህ ጊዜ፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በባእድ አገር የመሰረቷቸውን ትቂት ተቋማት ለመቀማትና ተቀናቃኝ የሚላቸው ወገኖች ጨርሶ መገናኘት እንዳይችሉ ለማድረግ መላ ዘይዶ ከተንቀሳቀሰ አመታት አስቆጠረ። መቸም ቢሆን በየሄደበቱ የሚነጠፉ አገልጋይ ማግኘት አልገደደውምና ስልት አድርጎ የሚጠቀምበት ቤትና መሬት እሰጣችኋለሁ። በልማት ስም ተሰባሰቡ በማለት እያደራጀ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል።

በምእራብ ኢትዮጵያ ቤንሻንጉል /አሶሳ እና አከባቢው/ የሚደርሱ ጥቃቶች የስድስት ወር ሁኔታዎች መረጃ እውን አማጺ ቡድን በቦታው አለን ? ሃላፊነቱን ማን ይውሰድ? ‪- ምንሊክ ሳልሳዊ

የቤንሻንጉል ጉምዝን የምናውቃት በለምለምነቷ እና በአከባቢው አገራችን ነው ብለው ለረዥም ዘመናት ሰፍረው ሲኖሩ በአንድ ጀንበር ተፈናቅለው በገዛ አገራቸው በተሰደዱ ዜጎች እና በተፈጠሩ ሁኔታዎች ነው። አከባቢውን በተመለከተ የጸጥታ ሁኔታዎች አስተማማኝ ከመሆናቸውም በላይ ህዝቡ ሰላማዊ እና ሰራተኛ መሆኑ የተረጋገጠ ነው።
ከተወሰኑ አመታት በፊት በሱዳን እና በአማጺ ጄኔራል መካከል በተደረገ ጦርነት ሸሽተው የገብ ወታደሮች ወደ ደቡብ ሱዳን ተላለፉበት እንጂ ….እንዲሁም ከደቡብ ሱዳን እየተነሱ ወያኔን የሚወጉ የጋምቤላ ክልል ተወላጆች ወደ አከባቢ ባይደርሱም የነሱ እንቅስቃሴ የተገደበ ሲሆን ለሰበብ የሚበቃ አይደለም እንዲሁም አማጽያኑ እንደተበተኑ መረጃዎች ፡ይጠቁማሉ በአሁን ወቅት ከጸጥታ ቁጥጥር አንጻር በሚል አከባቢው ከፍተኛ ጥበቃ እና የወታደራዊ ደህንነት መዋቅር ስለተዘረጋበት ይህንንም መዋቅር ከመሃል አገር አለቃ ጸጋይ እና ከምእራብ እዝ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በጋራ ተቀናጅተው ሲመሩት አስፈላጊውን መረጃ ከሁለቱ ሱዳኖች ጋር በመለዋወጥ ይቆጣጠሩታል። ለዚህ ቁጥጥሩ ጥብቅ መሆኑ ማርጋገጫው ባለፈው የተይዙትን የግብጥ ሰላዮችን እንደ ማስረጃ ማጣቀስ ይቻላል፡፤ እንድሁም ከደቡብ ሱድን ተፈናቅለው ከመጡ ኢትዮጵያውያን ጋር ተቀላቅልው ለመግባት የሞከሩ የሻ እብይ ስእላዮች ናቸው የተባሉ መያዛቸው የአከባቢውን የጽጥታ ቁጥጥር ያሳብቃል። ታዲያ ከዚህ መሃል እንዴት አማጽያን ሊሰርጉ ቻሉ ?

የኛ ነገር፤ የኛ ፖለቲካ፡ ግንቦት ሰባት ምን ነካው?ተክለሚካኤል አበበ

እንደመግቢያ፡ ግንቦት ሰባት ምን ነካው?
፩-ልረብሽ ነው፡፡ ልክ እንደኢሳት ሁሉ፤ “ግንቦት ሰባትም የኛ ነው” ( “የኔ ነው” የሚለው መፈክር አይመቸኝም)፡፡ የኛ ለሆነ ነገር ደግሞ ፍቅራችንን የምንገልጸው፤ በጭብጨባና በሽብሸባ ብቻ ሳይሆን፤ በተግሳጽና በትችትም ጭምር ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ለድርጅታቸው ካላቸው ጽኑእ ፍቅር የተነሳ፤ ድርጅታቸውም መሪዎቻቸውም ሲሳሳቱ፤ መተቸት የሌለባቸው ብጹአን አድርገው ይወስዱኣቸዋል፡፡ በዚህ አልስማማም፡፡ ስለዚህ፤ ግንቦት ሰባትን/የሊቀመንበሩን ቃለምልልስ ትንሽ ልተች ነው፡፡ ይህንን ነው ረብሻ ያልኩት፡፡
፪-በድጋሜ ግልጽ ለማድረግ ያህል፤ ግንቦት ሰባት በንጽጽር ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች የተሻለና የተሳለ ነው የሚል እምነት ስላለኝ/ስለነበረኝ፤ ከግንቦት ሰባት በኩል የሚመጡ መግለጫዎችን፤ መርሀግብሮችን፤ እርምጃዎችን በንቃትና በጥንቃቄ እከታተላለሁ፡፡ የሊቀመንበሩን ዲባቶ ብርሀኑ ነጋን ቃለምልልስም የተከታተልኩት በዚያ እምነት ነው፡፡ በዚህ በያዝነው ሳምንት፤ ሊቀመንበሩ በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ፤ ከኢሳቱ ሲሳይ አጌና ጋር ቃለ-ምልልስ አድርገዋል፡፡ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አብግን ቃለምልልስ ከሰማን ከወራት በኋላ፤ ከሊቀመንበሩ እንዲህ ያለ ተስፋ አስቆራጭ ቃለምልልስ ቶሎ ይመጣል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር፡፡

ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!! ከጥላዬ ታረቀኝ አለማየሁ

ለመረጃ ያህል አሁን እየተሰሙ ያሉ ነገሮች በጣም አስፈሪና አሳዛኝ ናቸው:: ለመሆኑም ይህንን በዝምታ ማለፍ አይቻልም፤ በጥቂቱም ቢሆን እየተሳካለት የሚገኘውን ህዋህት/ኢህዴግ ከመነሻው ጀምሮ ለሀገር ማሰቡ የሚባል ነገር ወደ ጎን በመተው የስልጣን ማርዘሚያ ዘዴዎችን በመቀየስ ይህው 23 ዓመት ሀገሪቱን በጎሳ፤ በጎጥ፤ በብሔር፤ በሀይማኖት ሲከፋፍል ከርሞአል። በመጀመሪያ እሱ በቀደደው ቁምጣ የቡሄር ብሔረሰቦች መብት፤ በማለት ሰራ ግን ከጭፈራ ያልዘለለ መብት ሰጠሁ ብሎ የተወሰኑ በጥቅም በሞቱ አንድ ብሔር እንወክላለን የሚሉ ግን ደግሞ ስራቸው የማይታወቅም ኢትዮጵያን ለመበታተን የተነሱ አካላት ጋር በመደገፍ የህዋህት አሽከር ሆነው ስንመለከት ወይ ሰው ብለን ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል፤ ለምሳሌ በ1997 ምርጫ ውጤት ከታወቀ በኋላ የትግራይን ህዝብ ለመለየት መሠረቱ እስካሁን የማይታወቅ ህዝብ ከህዝቡ የሚያጋጭ ንግግር ሰምተናል ”እቃ ወደ ቀበሌ ትግሬ ወደ መቀሌ” የሚል በመቀጠል ወጣቶችን በማደራጀት አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ በማለት ማህበር አቋቁሞ፤ እዚህ ላይ እና መሰል የተዘሩ የተንኮል ዘሮች ቀናቸውን ጠብቀው አቆጥቁጦ ከማቆጥቆጥም አልፈው ለምልመው ይህው ሀገሪቱ ባለ ብዙ ባንዲራ ባለ ብዙ ሀገር ሆነች። ሁሉም የራሱን ጥግ በመያዝ አንዱ አንዱን ሲጠበቅ ገዥው መደብ ሀገር ሲበዘበዝ ደስ ካለው ከህግ አግባቢ ውጭ ሲገድል ሲያስር ተመልክተናል፤ የፀረ ሽብር ህግ ብሎ አውጥቶ ንፁሃንን በእስር ቤት የሚታገሉ አካላትን እራሱ ሲያሸብር ተመልክተን፤ በፈለገው መጠን ባይባልም በጣም ብዙ ግን የብሔርተኝቶ አስተሳሰብ ያላቸው አፈራ፤ እነሱንም በየኃላፊነት ቦታ ላይ በማስቀመጥ የልቡን አደረሷል፤ በተመቸው ሁሉ ህዝቡ ወደ አንድነት እንዳይመጣ ታግሏ።

Thursday, May 15, 2014

እምዬ ምኒልክ ሲመጥቅ፣ ወያኔ ሲወድቅ

ከሮበሌ አባቢያ፤ 14/5/2014
ቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ
ወያኔ በ1983 አዲስ አበባ ሲገባ እግረ መንገዱን የገበሬውን ልጆች፣ ጋዳፊና የአረብ ሀገር ከበርቴዎች ባስታጠቁት ዘመናዊ ታንክና መሣሪያዎች፣ እያጨደ በሬሳቸውና በደማቸው ላይ እየተረማመደ እንደነበር መሪር የቅርብ ትዝታ ነው። በቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ይመራ የነበረው ጎጠኛው የወያኔ መንግሥት፣ የኢጣልያ ፋሺስት ያወጣውን በተለይ በአማራና በኦሮሞ ላይ ያነጣጠረውን የከፋፈለህ ግዛው ፖሊሲ ኮርጆ በመከተል፣ የአፄ ምኒልክ ሐውልት እንዲፈርስ ለማደረግ ሕዘቡን አነሳስቶ እንደነበር ይታወቃል።ሆኖም ሙከራው ወያኔ አስቦት በነበረበት ወቅት ባይሳካም፣ ሐውልቱን የማንሳት ሃሳብ አሁንም አለ። ስለዚህ ሕወሐት የሚመራው በውስጡ በሚስጥር በተሰገሰጉ ባንዳዎች እንደሆነ እያደር ሊታወቅ ስለቻለ የእምዬ ምኒልክ ወደጆች መዘናጋት የለባቸውም።

Wednesday, May 14, 2014

የጎሳ ፌዴራሊዝም፤ የአማራው ጎሳ የጅምላ መፈናቀልና አማራውን ለማጥፋት የሚደረገው ስልታዊ የወያኔ ትግሬዎች ዘመቻ



አሰፋ ነጋሽ (ዶ/ር)* (ሆላንድ – ጥቅምት 2006 ዓ. ም)
ምንጭ፦
ክፍል አንድ
የወያኔ ትግሬዎችና ስለ አማራ ህዝብ ያላቸው ግንዛቤና የቆየ ጥላቻ ምን ይመስላል?
የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎችም ሆኑ ተከታዮቻቸው የትጥቅ ትግላቸውን ሲጀምሩ ለትግራይ ህዝብ ችግርና ኋላ ቀርነት ተጠያቂዎቹ ከዳግማዊ ዐጼ ምንሊክ ጀምሮ እስከ ደርግ መውደቅ ድረስ በስልጣን ላይ የነበሩት ወያኔ «አማራ» ብሎ የሚጠራቸው መንግስታት እንደ ነበሩ በፖለቲካ ፕሮግራም ደረጃ ቀርጸው የትግራይን ህዝብ እንዳስተማሩ ቀድሞ የወያኔ ድርጅት አባል የነበረውና ዛሬ በስደት በሚኖርበት አውስትራሊያ ሆኖ የወያኔን እኩይ ዓላማ በቆራጥነትና በሃቅ እያጋለጠ ያለው አቶ ገብረ መድህን ዓርዓያ በቅርቡ “እነማን ነበሩ” በሚል ርእስ በመረጃ አስደግፎ አሳውቆናአል።

ተቃውሞ እና ጭፍጨፋ በኦሮሚያ (ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
ዕለተ-ሐሙስ፤ ሚያዚያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም የታሪካዊቷ አምቦ ከተማ ጀንበር አዘቅዝቃ ሰማዩ መቅላት ሲጀምር፣ ከወትሮው ለየት ያለ ጉዳይ በሰደድ እሳት ፍጥነት ጠቅላላ የዩንቨርስቲ ግቢውን አዳርሶ ተማሪውን ከባድ ሃሳብ ላይ ጣለው፡፡ ሌሊቱ ዕኩሌታ ላይ የግቢው ኦሮምኛ ተናጋሪ ተማሪ በሙሉ ስለጉዳዩ መረጃው እንደደረሰው ያረጋገጡ ጥቂት አስተባባሪዎች በተረፈችዋ ሰዓት ቢያንስ ጎናቸውን ለማሳረፍ ወደየመኝታቸው ሲያዘግሙ ተስተዋሉ፡፡ …ነገስ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን? አንዳቸውም ይህን አስቀድመው የማወቅ መለኮታዊ ፀጋ አልነበራቸውም፤ የሚያውቁት በግቢው ስታዲዮም ለመሰብሰብ ቀጠሮ መያዛቸውን ብቻ ነው፡፡ ከዚያስ? አንድ ስሙን መናገር ያልፈለገ የዩኒቨርስቲው ሁለተኛ ዓመት ተማሪ እና የተቃውሞው አስተባባሪ ክስተቱን በእኔ ብዕር እንዲህ ይተርክልናል፡-

ተስፋለም ሆይ ! ስላንተ ምን ልናገር ? ስለልጅነትህ ? ! (ኤልያስ ገብሩ ጎዳና )

 ሚያዚያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ንጋት ላይ ትንሿ ስልኬ አንጫረረጭ፡፡ ከእንቅልፌ ብንን ብዬ ስልኬን ተመለከትኩት፡፡ የደወለው ወዳጄከዚህ ቀደም በዚህ ሰዓት ደውሎልኝ አያውቅም ነበር፡፡ ስልኩን ሳላነሳው ‹‹ምን አንዳች ነገር ተፈጥሮ ይሆን?›› ብዬ ማሰላለሌን ተያያዝኩት፡፡ ከ20 ደቂቃ በኋላ ስልኩ በድጋሚ ተደወለ፣ አነሳሁት፡፡ ከደዋዩ ወዳጄ ጋርም ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ ‹‹ጓደኞችህ ታሰሩ አይደል?›› አለኝ፡፡ ‹‹እነማን?›› በማለት በችኮላ መለስኩለት፡፡ ‹‹ተስፋለም፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ዞን ዘጠኞች…›› ደንግጬ መረጃው እንደለሌለኝ ነገርኩት፡፡ …ተስፋለም ከመታሰሩ ሁለት ቀናት በፊት ደውሎ ከሥራ ጋር የተገናኘ መረጃ ጠይቆኝ ነበር፡፡

ኢትዮጵያዊነት ክፍል ሁለት ትግሬ ሆነህ አታንብበው (ሄኖክ የሺጥላ)



ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት ፣ ” መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የሚለው መጽሐፋቸው ላይ በሚደር ውይይት ካንድ ተሳታፊ ለቀረበላቸው ትያቄ ሲመልሱ፣
“አንዳን የሚያሳዝኑ ነገሮች ተነስተዋል እዚህ አካባቢ ነው መሰል ትግሬ ነኝ ያለ ልጅ አለ፣ ትግሬ ነኝ ብለሃል፣ እኔም ትግሬ ነኝ፣ ነገር ግን ልዩነታችን ትግሬ ሆነህ በማንበብህና ኢትዮጵያዊ ሆነህ በማንበብህ ላይ ነው። እውነት ነው፣ ትግሬነትን እያሰቡ እንደ ኢትዮጵያዊ መኖር አይቻልም፣ ኦሮሞነት ኢትዮጵያዊ ለመሆን ባሰበ ቁጥር የተበዳይነት እና የተገፊነት ስሜት የሚጭር ከሆነ በምንም መልኩ ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም። ፋሲለደስን ስንመለከት አማራ አደረሰብን የምንለው በደል ከሆነ ትዝ የሚለን ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም ፣ አክሱምን ስንመለከት የትግሬዎች ክፋት ከሆነ ትዝ የሚለን ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም፣ ሰንደቅ አላማችንን ስንመለከት አሁንም ሰንደቁ ከተሸከመው ምልክታዊ ትርጉም ውጪ የአማራነት መለኪያአንድን ጎሳ የጥፋት ብብሃር ታሪክ ካደረግነው አሁንም ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም። ስለ ብራና እና መሰንቆ ስናወራ ወደ አእምሮዋችን ቀድሞ የሚመጣው ቁሶቹ የኢትዮጵያውያኖች እሴት ስለ-መሆናቸው ካልሆነ ኢትዮጵያዊ መሆን ይከብዳል።

የምርጫ ሽር ጉድ በ2015ቷ ኢትዮጵያ (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በ2015 በሚካሄደው ፓርላሜንታዊ “ምርጫ” መቅረብና መወሰን ያለበት አንድ ጥያቄ ይህ ነው፤ “የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁን እ.ኤ.አ 2014 ያሉበት የኑሮሁኔታ ከቀድሞ 2010 ወይም 2005 ከነበሩበት የኑሮ ሁኔታ ይሻላል ወይ?” ህዝቦች ካለፉት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ ላይ የማይገኙ ከሆነ አንደ አሮጌ ሸማ መቀየር መቀየር ይኖርባቸዋል፡፡ የፖለቲካ ሰዎችና እንደ አሮጌ ሸማ ናቸው፡፡ በየጊዜው ካልታጠቡና ካልተለወጡ ይበሰብሳሉ ይገማሉም፡፡ በጣም የሚገርም ነገር ነው! ምስኪን ኢትዮጵያውያ አንድ የበሰበሰ የገማ ሸማ ለሌላ 5 ዓመታት በጠቅላላው ለ25 ዓመታት ስትለብስ አያሳዝንም?Ethiopian election 2015
እ.ኤ.አ. ጁን 2010 በቅርቡ ያረፉት የአቶ መለስ ዜናዊ ፓርቲ የሆነው “ኢህአዴግ” (“የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር”) 99.6 በመቶ ድምጽ በማምጣት ድልን ተቀዳጀሁ ያለበትን እርባናየለሽ ንግግር በመተቸት የተሰማኝን ሀዘን ገልጨ ነበር፡፡

እናስራችኋለን? ለካንስ የነአጅሬ ጋጠወጥነት ከድንበርም ተሻግሯልና!

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
በሀገራችን ባደመነው አጠቃላይ የሀዘን ድባብ ሳቢያ ፈገግታ እያማረኝ ፈገግ ለማለት ምንም ዕድል ሳላገኝ ብዙ ሰሞኖችን ባጀሁ፡፡ ዕድሜ ለዚህ ነገረኛ ኢሳት የሚባል ቴሌቪዥን ዛሬ ማታ ግና በሣቅ የሚያፈርስ ዜና ሰማሁና ምሽቱን ብቻ ሳይሆን ትዝ ባለኝ ቁጥር ሌቱን ሁሉ በሣቅ ስፈርስ አደርኩ – የግራ ጎን አጥንቶቼ ክፋይ ጉድ እስክትለኝ፡፡ ሣቅ ጥሩ ነው፡፡ አንዳንዴ በሣቅ የሚገድል ነገር ማግኘት የመታደል ያህል ነው፡፡ እውነተኛው ሣቅ ሞቶ ቢቀበርም ወያኔን መሰል ጅላንፎ ጉጅሌ የሚሠራቸው አንዳንድ ነገሮችን በመታዘብ ለጊዜውም ቢሆን ፈገግ መሰኘት ሲያስፈልግም ሆድን ያዝ አድርጎ በሣቅ መንፈርፈር ሰውነትን ያፍታታል፤ ወቅታዊ እፎይታንም ይሰጣል፡፡ እኔ – እውነቴን ነው – ለብዙ ጊዜ ያጣሁትን ሣቅ ዛሬ አገኘሁትና ከልቤ ተዝናናሁ፡፡ ወያኔ እኮ አልታወቀለትም እንጂ ደምበኛ የኮሜዲ መፍለቂያ ውድብ ነው፡፡ ልዩ የኢትዮጵያ ቻርሊ ቻፕሊን ሆነው የለም እንዴ!

Tuesday, May 13, 2014

ከኢትዮጵያዊነት የአንድነትና የፍቅር መንፈስ ጋር የሚጣሉ ሁለ ይደቃሉ!

በዲ/ን ኒቆዲሞስ (ምንጭ ፋክት) መጽሔት

“… ኢትዮጵያን አምላኬ ምትለው እግዚአብሔር ከኃያሉና ከብርቱ መዳፌ የሚያድናት፣ የሚታደጋት ከሆነ የእኔንም እግዚአብሔር ልጨምርላት እችላለሁ …፡፡” ቤኒቶ ሞሶሎኒ

ይህን ንግግር በሮማ አደባባይ የተናገረው ኢጣሊያዊ የፋሽስት መሪ ቤኒቶ ሞሶሎኒ ነው፡፡ ሞሶሎኒ ሮማውያኑ አያቶቹና አባቶቹ በዓድዋ የጦር ግንባር የተከናነቡትን ሽንፈትና ውርደት ከታሪክ መዛግብት እየቀፈፈውና እየዘገነነውም ቢሆን አንብቦ ነበር፡፡ ከዚህ ለማሰብ ቀርቶ ለማለም እንኳን ከሚከብድ የታሪክ ሐቅ ጋር የተፋጠጠው ሞሶሎኒ አምኖ ሊቀበለው የከበደውን ግን ደግሞ ሊፍቀው ያልቻለውን ይህን የታሪክ ውርደት፣ ይህን የታሪክ ስብራትና ክፉ ጠባሳ በሮማና በመላው አውሮጳ ምድር ይሻር ዘንድ ራሱን ታሪክን አዳሽ፣ ኃያልና ብርቱ የዘመኑ ጦረኛ ጎልያድ መሆኑን ለራሱም ለሕዝቡም አሳመነ፡፡

ኢትዮጵያዊነት (ሄኖክ የሺጥላ፣ ክፍል አንድ)

ሄኖክ የሺጥላ
ኢትዮጵያዊነት በተቃርኖ የተሞላ የግሳንግስ ስብስብ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የወጪት ሰባሪዎች ትግል፣ ለኔ በገሌ ነው ባዮች ምክር አይደለም። ኢትዮጵያዊነት በበግ ጸጉር ቡክርናውን እንደቀማው ያዕቆብም (“አታላይ ማለት ነው”) አይነትም አይደለም። በጎሳ አሽክላ ተተብትበን፣ በቂም ቆመን፣ ጭረት አመርቅዘን ቁስል አርገን፣ የዛሬ ውድቀታችንን ፣ የዘመን ምክነት አስመስለን፣ ላለመቻላችን መወጣጫ፣ ላለመቆማችን የምክንያት መቆናጠጫ ብንፈልግ፣ ካለፈ ጥፋትም ሆነ ሕዝብ ካለፈለት እውነት ጀርባ መዶለታችንን እስካልተውን፣ የድርሻችንን ለመወጣት ታጥቀን እስካልተነሳን ድረስ፣ ትግላችን እንደ እስከ ዛሬው “ለአፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል” ሆኖ ስለመቀጠሉ አዋቂ መሆን አይጠይቅም።henok yeshitla

የፕለቲካ ድርጅቶች መግለጫና ትርጉም
የ-ወያኔው ስርዓት እንደ ወየነ 40 ዓመት ሞላው። እኛም የዚህ ስርዓት አድማቂዎች መሆን ከጀመርን እንዲሁ። የተለያዩ ያልተቀናጁ፣ በማይረባ የትግል ቅርጽ የተጠረቡ ድርጅቶችም ይሄንን ስርዓት እሱን በሚመቸው መልኩ እየታገሉት (በጩኸት እያጫፈሩት) ተጉዘዋል፣ ብዙዎቹ መሰረት አልባ፣ የማይጨበጥ፣ የማይያዝ ትግል አድርገዋል። ባንጻሩ ደሞ ጥቂቶች ደማቸውን አፍስሰዋል፣ ጥቂቶች ራሳቸውን ባደባባይ ገብረዋል፣ ጥቂቶች ተሰውተዋል። እና በዚህ በማይረባ የትግል መስመር ውስጥ ባሉትና በቆራጥ አቁዋም ራሳቸውን በሰዉት መሃከል ግን በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ይህ ነው የማይባል በደል (እስር፣ እንግልት፣ ግድያ፣ አፈና፣ ስደት እና ወዘተ) ደርሶበታል እየደረሰበትም ነው፣ ገና ወደፊትም ይደርስበታል።

Wednesday, May 7, 2014

ወደ ህሊናችን እንመለስ

አንተነህ መርዕድ
የመሬት ጥያቄ ብዙ መስዋዕት የተከፈለበት ቢሆንም አሁን በባሰ ሁኔታ ወያኔ ከሁሉም ዜጋ ነጥቆ በግሉ አድርጎታል። ማንም ኢትዮጵያዊ የሃገሩ፣ የመሬቱ ባለቤት አይደለም። ከዚህ የባሰ ዜጎችን የማዋረድ ተግባር የለም። አባቶቻችን መሬታቸውን ለባዕድ አንሰጥም በማለት ህይወታቸውን ከፍለው አቆይተውናል። ዛሬ እኛ የራሳችን መሬት ባለቤት እንዳንሆን ሁላችንንም መሬት አልባ ያደረገን ስርዓት ዜጎችን አፈናቅሎ ካድሬዎቹን በመሬት ችብቸባ አሰማርቷል። ለባዕዳን ከመሸጥ አልፎ “እኛም የመሬት ባለቤት ልንሆን ይገባናል” ያሉትንና ይህንኑ የዜጎችን ህጋዊ መብት የጠየቁትን ሁሉ በጠራራ ፀሃይ ባደባባይ ይገድላል።

የኃይለማርያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች (ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ )

በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም “ጠቅላይ ሚኒስትር” ተደርጎ በኢህአዴግ ሲሾም፤ በፓርቲው ውስጥ አክራሪ ብሔርተኛ የአመራር አባላት ከመኖራቸው አኳያ፤ መቼም ቢሆን “ራሱን ችሎ ይቆማል” ብሎ መጠበቁ ተምኔት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ኃይል እንኳን እንደ ኃይለማርያም ላለ የድል አጥቢያ መሪ ቀርቶ፣ ከድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ እስከ ምኒሊክ ቤተ-መንግስትም ድረስ ታላቅ የተጋድሎ ታሪክ ለነበረው አቶ መለስም ቢሆን ክፍተት ካገኘ አለመመለሱን የ93ቱ ሣልሳዊ ህንፍሽፍሽ በግልፅ አሳይቶ ማለፉ አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም ራሱ መለስ ዜናዊ በድህረ ምርጫ 97 የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ዘብጥያ ወርደው የነበሩትን የቅንጅት አመራሮች “ከእስር እንዲፈቱ ብፈልግም አክራሪው ኃይል ተቃወመኝ” ማለቱን ዊክሊክስ የተሰኘው የመረጃ መረብ የአሜሪካ አምባሳደርን ጠቅሶ ይፋ ማድረጉ ይህንኑ ያስረግጣል፡፡ የአምባሳደሩ መረጃ የተጋነነ፤ አሊያም “ተጋግሮ የቀረበለት ነው” ሊባል ቢችል እንኳ “ጭስ በሌለበት…” እንዲሉ፤ በግንባሩ ውስጥ አክራሪ ኃይል ለመኖሩ በጠቋሚነት ሊወሰድ ይችላል፡፡

የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይሳተፉ መከልከል ብዙዎችን አስቆጥቷል

“የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አንድነት የጠራውን የሰላማዊ ሰልፍ እንደሚቀላቀሉ አስታወቁ” የሚለው ዜና ለውጥ ናፋቂዎችን በእጅጉ ያስደሰተ ነበር። ይሁንና አንድነት ፓርቲ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን” በሚል ባካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ትንታጎቹ የሰማያዊ ወጣቶች አልታዩም። ከሞላ ጎደል ከዚህ በታች የተለያዩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ስለሁኔታው የገለጹትን ለአንባብያን ለማካፈል ሞክረናል።
———————————–
በአንድነት ፓርቲ አዝኛለው
Brhanu Tekleyared, Semayawi party public relation
ብርሃኑ ተክለያሬድ
በጣም ከፍቶኛል በጣም አዝኛለሁ በፖለቲካ ህይወቴ ብዙ ነገር ደርሶብኛል እንደዛሬው ግን ከፍቶኝ አያውቅም፡፡ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ ያለቀስኩበት ቀን ከ2 ጊዜ አይዘልም ዛሬ ግን ጓደኞቼ እስከሚገረሙብኝ ድረስ ስቅስቅ ብዬ አልቅሻለሁ።
እንደ ሌባ “ከዚህ ሰልፍ ውጡ” ተብለን ስንወጣ የተሰማኝ ስሜት……ግን ይሄ መንገድ የት ያደርሳል?

ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰቀለ? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

በዚህ ርእስ ላይ የምጽፈው ሃይማኖትን ለመስበክ ፈልጌ አይደለም፤ ከውስጥ የሚኮረኩረኝን ነገር ለማውጣት ነው፤ በኢትዮጵያ የተስፋ ሕልም አይታየኝም፤ የሚታየኝ የጥፋት ቅዠት ነው፤ ከሃያ ዓመት በላይ በመለስ ዜናዊና በጓደኞቹ በኩራትና በእብሪት የተዘራው ጥላቻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልቡ የደም መግል እንዲቋጥር አድርጎታል፤ ይህንን የማይገነዘብ ያለ አይመስለኝም፤ ነገር ግን ባህል ሆኖብን አደጋ ማስጠንቀቂያን አንወድም፤ በአንጻሩ ግን በባዶ ሜዳ ለሽለላና ለፉከራ የሚጋብዘንን እንወዳለን፤ እኔ ማንንም የሚያስፎክር ነገር አይታየኝም፤ ማንንም የሚያሳብይ ነገር አይታየኝም፤ ክርስቶስ የተሰቀለበት ምክንያት ግን በድፍን ጨለማው ውስጥ ብልጭታን ያሳየኛል፤ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዋናው ምክንያት ‹‹ክፉን በክፉ አትመልሱ ስላለ ነው፤ የኢየሱስ ክርስቶስ አብዮት ይኸው ነው።

እሰይ! ድል ለወጣቱ ትውልድ!!!

ከሮበሌ አባቢያ
የአንድነት ፓርቲ ያቀረበውን እጅግ በጣም ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ፣ አይኖቼ እምባ እያቀረሩ፣ ልቤን ደስታ ፈንቅሏት ነው እኔም እንደ ሰልፈኞቹ መፈክር እያሰማሁ ከናት ሀገሬ ውጪ ከምኖርበት ከተማ በቴሌቪዥን ከመኖሪያ ቤቴ ተቀምጬ ነበር የተመለከትኩት።
እሰይ! ድል ለወጣቱ ትውልድ!!! በማለት ይህቺን መጣጥፍ ለመክተብ ተነሳሳሁ።
ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንደጻፍኩት ግትር ኢትዮጵያዊ ነኝ። ያ እንዳለ ሆኖ፣ አንድነት ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ የተገኙት ታዳሚዎች በኦሮሞ ተማሪዎችና በደጋፊዎቻቸው ላይ የደረሰውን ፋሺስታዊ ጭፍጨፋ አበክረው በማውገዘቸው በወገኖቼ ኢትዮጵያን ኮርቻለሁ፤ አድሮብኝ ከነበረው ጥልቅ ሀዘንም ተፅናንቻለሁ፤ ለሰብአዊ መብት ዓላማ ስኬት ለመታገል ቃልኪዳኔን አድሻለሁ።

ብአዴን ማን ነው? (ገብረመድህን አርአያ፣ አውስትራሊያ)

ገብረመድህን አርአያ፣ ከአውስትራሊያ

Click here for PDFAto Gebremedhin Araya is one of former Tigray People Liberation Front (TPLF) leaders

የአንድን ድርጅት ማንነቱን ከማቅረብ በፊት ቀደም ብሎ የተፈጸመውን ስህተት፣ ቀጥሎም ኢህአፓን ለማጥፋት በህወሓት እና በሻእቢያ የደረሰበትን ጥቃት አጠር ባለ መልኩ ማቅረብ አስፈላጊ ይሆናል።
የስትራተረጂ ስህተት ለከባድ ወድቀት ይዳርጋል።
ኢህአፓ ትግሉን የጀመረው ገና በ1960 መጀመሪያ ነበር። አብዮቱ እየተቀጣጠለ ሃገር አቀፍ ሆነ። ዘውዳዊ ስርዓት ወድቆ በማርክሲዝም ሌኒኒዝም ርእዮተ ዓለም የሚመራ ሶሻሊዝም የኢትዮጵያ ስርአት እንዲሆን ነበር። ይህ ግራ አክራሪ ስታሊኒዝም በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ ይማሩ በነበሩ የተሰባሰበ ቡድን፣ የወቅቱ አብዮተኞች ተገቢውን መልክ የያዘ አደረጃጀት ያልነበረው፣ አብዮተኛ የሚል ስም በማግኘታቸው ብቻ “ዲሞክራሲያ” ተብሎ የሚታወቀውን የኢህአፓ ልሳን በየሳምንቱ በመበተን አሁን ኢትዮጵያ የደረሰባትና እየደረሰባት ያለው ከባድ ችግር የከፈተው እነ ዋለልኝ መኮንን እና የኢህአፓ ግብረአበሮቹ የስታሊን ደቀ መዛሙርት ኢትዮጵያን አደጋ ወስጥ ጣሏት። በዚህ ወቅት ሰፊውን ትኩረት የሰጡት፤

Saturday, May 3, 2014

ቴሌፎኑ ‘ለግዜው’ ጥሪ አይቀበልም (ክንፉ አሰፋ)

“የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።…” የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልእክት ያላጋጠመው ቢኖር  ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ። አስር ለሚያህሉ አርሶአደሮች እና የሰራዊቱ አባላት ዘንድ ደውለው አልተሳካለቸውም። ለሁሉም ጥሪ ያገኙት ምላሽ “የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።” የሚል ሲሆንባቸው ራሳቸውን ነቀነቁ። ሰው ሁሉ የጨከነባቸው መሰላቸው። እንዲህም አሉ። “የሃገሬ ሰው እንኳን የስልክ ጥሪ፤ የእናት ሃገር ጥሪስ መች ተቀበለ።”
ለአመታት በተከታታይ በሁለት ድጅት እያደገች ያለች ሃገር የስልክ መስመር ችግር ይገጥማታል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ችግሩን በደንብ ላልተረዳው፣ ሰው የሞባይል ስልክ የሚገዛው እንዲሁ ይዞ ለመታየት ነው ያስብል ይሆናል። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ነው። ዘመናዊ ስልክ በመያዝ ለላንቲካነት ብቻ የሚጠቀሙበት ሰዎች አይጠፉም። የቻይናው ቀፎ ከሞዴል አርሶ አደሮች አልፎ ተራው አርሶ-አደር እጅ ላይም ገብቷል። አብዛኞቹ ግን ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን አይጠቀሙበትም።  ለዚህም ይመስላል በርካታ ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚይዙ ሰዎች እንዲሁ ለእይታ እና ለላንቲካ ብቻ የሚመስላቸው። አገልግሎቱን በተመለከተ ግን 99 በመቶ የሚሆነው ችግር የመዋቅር ችግር ነው።
ለዓውዳመቱ ወደ ኢትዮጵያ ስልክ የደወላችሁ ካላችሁ፤ ይህ ነገር እንደገጠማችሁ እርግጥ ነው። ዘንድሮ ደግሞ ቴሌ ከፍቷል። የሞባይሉ መስመርማ እንደ አይን እልም ብሎ ነው የጠፋው።  ከበርካታ ሙከራ በኋላ መስመር ያገኘ ሰው ካለ በደስታ ይዘልላል።  የተቀባዩም ስልክ ካቃጨለ ተዓምር ነው የሚባለው። ከርማ ብቅ እንደምትለው የአዲስ አበባ መብራት … ልክ እንደ ቧንቧ ውሃ፤ ስልኳም “መጣች – መጣች!” ብሎ መጨፈሩ አይቀርም።
(በመከራ መስመር ሲገኝ እንዲህ ያስደስታል)
(በመከራ መስመር ሲገኝ እንዲህ ያስደስታል)
“እንኳን አደረሳችሁ!” ለማለት እኔም ወደ ሃገር ቤት ስልክ መታሁ።
“የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።” የሚል መልስ ነበር ያገኘሁት። ለሁለተኛ ግዜ ስሞክር ደግሞ “የደወሉት ስልክ ለግዜው ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ነው።”  የሚል ምላሽ አገኘሁ።  ደቂቃ ባልሞላ ግዜ ውስጥ ጥሪ ያማይቀበለው ስልክ ከአገልግሎት መስጫ ክልል መውጣቱ አስገረመኝ። ተስፋ ሳልቆርጥ ደገግሜ ሞከርኩ።  ቢያንስ ከአስር ግዜ ሙከራ በኋላ፤ መስመር አገኘሁና ሎተሪ የወጣልኝ ያህል ተሰማኝ።
ደስታዬ ግን ብዙም አልዘለቀም። በመሃል እንግዳ ነገር ተፈጠረ። ስልኩን የተቀበለኝ የደወልኩለት ሰው አልነበረም። የተፈጠረው ክስተት – ባለንበት የመረጃ ዘመን እንደ 17ኛው ክፍለዘመን “ቴሌ በኦፐሬተር መስራት ጀመረ እንዴ?” ያሰኛል። ነገሩ ግን ሌላ ነው። ስልኩን ያነሳው የተለመደው የስልክ ጠላፊ ስለመሆኑ አንዳች ጥርጥር አልነበረኝም። ሶማሌያውያን መርከብ ሲጠልፉ ጸሃዩ መንግስታችን ደግሞ የስልክ ፓይረት መሆኑን ሂዩማን ራይትስ ዎች በዚያን ሰሞን ነግሮን ነበርና።
ውጭ ሃገር ያለ ኢትዮጵያዊ ዘመድ ለመጠየቅ መደወሉ አይቀርም። ተስፋ የማይቆርጥ፤ ደጋግሞ ይሞክራል። እንደ እድል የስልኩን መስመር ካገኘ ደግሞ ሌላ ችግር ይገጥመዋል። ዘው ብለው የሚገቡ የስልክ ጠላፊዎች መስመሩን ያውኩታል። ሌላው አማራጭ ደግሞ አጭር የጽሁፍ መልእክት ነው። በኢትዮጵያ ቴሌኮም አጭር መልእክት ከመላክ ይልቅ ደብዳቤ ጽፎ በፖስታ መላኩ እየፈጠነ መጥቷል። አጭር መልእክት የሚደርሰው ከቀናት ብኋላ ነው። ከላኪው ዘንድ መልዕክቱ መድረሱ ቢረጋገጥም ተቀባዩ ጋ ጨርሶ ላይደርስም ይችላል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሰጡት ጋዤጣዊ መግለጫ “የኢትዮጵያ ቴሌኮም ቴክኖሎጂ ከዴንማርክ፣ ከኖርዌይ እና በከፊል ከእንግሊዝ ቴክኖሎጂ ጋር አንድ ነው” ብለው ነበር። በዚህ መግለጫቸው አቶ ሃይለማርያም የኢትዮጵያን የኢንተርኔት አገልግሎት፣ እንዲሁም የስልክ መስመሩ ጥራት እና አስተማማኝነት በደንብ አድርገው ነበር “ለጋዜጠኞቹ” የገለጹላቸው። ይህን ተናግረው እንዳበቁ ግን የራሳቸውም ስልክ መጠለፉን ሰማን። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዲሉ አልሰሙት ይሆናል እንጂ፤ “እኛ ሲም ካርድ፤ አንተ ደግሞ ቀፎ ነህ!” ይሏቸዋል – ከላይና ከታች ያሉ አለቆቻቸው።
የኢትዮጵያን ስልክ አገልግሎት ከዴንማርክ፣ ኖርዌይ እና እንግሊዝ ጋር አወዳድረው ማወደሳቸው ግን ራሳቸው ካዴሬዎቹንም ሳይቀር ሳያሰፍራቸው አልቀረም።  ሰውየው የኢትዮጵያን ቴሌኮም እያወዳደሩ ያሉት 99.9 በመቶ ሳያቋርጥ አገልግሎት ከሚሰጠው አራተኛው ጀንሬሽን የምእራቡ ቴክኖሎጂ ጋር ነው። መቼም ሁሉም ይዋሻሉ። ነብሳቸውን ይመርና አቶ መለስ ዜናዊም ይዋሹ ነበር። ለዛ ያለው ውሸት አለ። እጅ፣  እግርና አይን የሌለው ውሸትም አለ። እንዲህ አይነት ያፈጠጠ ውሸት ግን እመራዋለሁ የሚሉትንም ሕዝብ እንደመናቅ ይቆጠራል። እኚህ ሰው የሞራል እሴታቸውን ሁሉ አሽቀንጥረው ሊጥሉት ይችሉ ይሆናል። ምሁራዊ ግብአታቸውንም ለተራ ፖለቲካ ጥቅም ሊያስወግዱት ይችላሉ።  እምነታቸውስ እንዲህ አይነቱን ቅጥፈት ይፈቅድላቸው ይሆን?
የቴሌ የኢንተርኔት አገልግሎት የመንግስት አልባዋ ሶማልያን አንድ መቶኛም። ኮሜዲያን ክበበው ገዳ እንደቀልድ የነገረኝ ቁም-ነገር የኢትዮጵያን ኢንተርኔት ፍጥነት በደንብ ይገልጸዋል።  ክበበው ሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝቱ ወቅት ፎቶ ተነስቶ ለቤተሰቡ በኢሜይል ይልካል። የላከው ፎቶ መድረሱን ለማረጋገጥ በነጋታው ወደ አዲስ አበባ ደወለ።
“ፎቶ ደረሰ?”
“አልደረሰም!”
ሌላ ቀን እንደገና ደውሎ የላከው ፎቶ እንዳልደረሰ ተነገረው። ለሶስተኛ ግዜ ደውሎ ኢሜይሉ እንደደረሰ ጠየቀ። አሁንም አልደረሰም ተባለ። እንዲህ እያለ ሳምንት ሞላው።
“በሳምንቱ እኔ ቀድሜ ደረስኩ።” ነበር ያለው ክበበው።
telecom tየኢሜይል መልእክቱ መድረሱ ከተረጋገጠ በኋላ – ሌላ ችግር ገጠመው። ኢሜይሉ ሲከፈት ግማሽ አካሉን ነበር የሚያሳየው። ፎቶው እስኪያወርድ (ዳውንሎድ እስኪያደርግ) ደግሞ ግማሽ ቀን መፍጀቱ ግድ ነበር።

ዜጎች በጎጃም መሬቸውን እየተነጠቁ፤ በወለጋ ደግሞ እየተፈናቀሉ ነው!

map

አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለካሳ እየተነጠቁ ነው

መራዊ፡- በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ያለ ፈቃዳችን መሬታቸውን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ አርሶ አደሮች እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በመራዊ አካባቢ ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ መንግስት የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ እናካሂዳለን በሚል ከ400 በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች ከመሬታቸው እንዲለቁ የተደረገውን እርምጃ አርሶ አደሮቹ በመቃወማቸው እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ኦሮሚያ ካለቀሰች በኋላ – ህዝብ ሃሳቡን ሊጠየቅ ነው

የኢህአዴግ ቴሌቪዥን የቅስቀሳ ዘመቻ ጀመረ
mothers

በአምቦ ህዝብ አዝኗል። የሟቾች ቁጥር ከ22 በላይ እንደሆነ ይገመታል። በድፍን ኦሮሚያ ከ36 ሰዎች በላይ ተገድለዋል የሚሉ መረጃዎች አሉ። ኢህአዴግ ባወጣው መግለጫ 11 ሰዎች መሞታቸውን አምኗል። ታዛቢዎች እንደሚሉት ኦሮሚያ እያነባች ነው። ህዝብ ለቅሶ ከተቀመጠ በኋላ ኢህአዴግ በቴሌቪዥን ቅስቀሳ ጀመረ።
አርብ ሚያዚያ 24፤2006 (2/05/2014) ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ባሰራጩት መረጃ በጉዳዩ ዙሪያ ህዝብ ሃሳቡን እንደሚጠየቅ አመላክተዋል። የዚሁ መነሻ እንደሆነ የተነገረለት የቅስቀሳ ዘመቻ ዛሬ በቴሌቪዥን ተላልፏል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ኩማ የድንበር ጉዳይ እንደማይነሳ በመጥቀስ ተቃዋሚዎችን ወቅሰዋል።

“አውሬነት” – ለማንም አይበጅምና ጠንቀቅ!!

(ርዕሰ አንቀጽ)
police brutality
አሁን ከኢህአዴግ ጋር ገድለሃል አልገደልክም የሚል ክርክር የለም። ራሱ ባንደበቱ “ገድያለሁ” ብሏል። ነፍስ ማጥፋቱን አውጇል። ያልገለጸው በጸጥታና በስም እንጂ አንጋቾቹ ህይወት መቅጠፋቸውን አረጋግጧል። ግድያው በዚህ ስለማብቃቱ ማረጋገጫ አልተሰጠም። ተቃውሞውም እየቀጠለ ነው። ከዚያስ? በደም እየታጠቡ፣ ወንጀልን እያባዙና የደም ጎርፍ እየጎረፈ “ህግ” ማስከበር እስከመቼ ያስኬዳል። ያዋጣልስ? የህዝብ እንባስ እንዲሁ ከንቱ ይቀራል?

Thursday, May 1, 2014

ወያኔ የሚፈራው ምርጫ ወይስ ሕዝባዊ እምቢተኝነት (አመጽ)

ተስፋዬ ዘነበ(ኖርዌይ በርገን)
በዚች አለም በሕዝቦቻቸው ላይ የሚፈነጩ አምባገነኖችን ለማስወገድ የሚደረጉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የወያኔ ዘረኛችን ለምን ሲያስደነብራቸውና በፍርሃት ሲያሸማቅቃቸው እንደሚኖር የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው፡፡ የህውሃት ዘረኛ ቡድን በሕዝብና በሃገር ላይ የሚያደርሰው መጠነ ሰፊ ጥቃት ወይም ውድመት በተለያየ መንገድ ሕዝቡ ቅሬታውን ቢያሰማም እራሱ ለፈጠረው ዘርፈ ብዙ ችግር መፍትሄ ከመሻት ይልቅ የሕዝቡን ብሶት ለማዳፈን ሀላፊነት የጎደለው ተግባራትን እየፈፀመ ሃገርን የመበተን ስራውን ቀጥሎበታል፡፡

ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!

Ginbot 7 Ethiopian opposition partyግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲንቅናቄ፣ ዘረኛው ወያኔ በኦሮሚያ ሕዝብና ወጣቶች ላይ እያካሄደው ያለውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ እስርና አፈናን በጥብቅ ይቃወማል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ያስገነዝባል።
የአሮሚያ ወጣቶች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም የድሀ ገበሬዎች መፈናቀልን መቃወማቸው ፍትሀዊ ነው። የወያኔ “ማስተር ፕላኖች” የወያኔ የዘረፋ እቅዶች መሆናቸው በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው። ነዋሪዎቹን ያላማከረ፣ ግንባር ቀደም ባለጉዳዮችን ባለቤት ያላደረገ፣ የሕዝብ ይሁንታ ያላገኘ ማስተር ፕላን ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም።

በቁሎን አባትህ ማን ነው ቢሉት፣ አጎቴ ፈረስ ነው አለ አሉ፤ ምንነትና ማንነት፡ የዘመኑ አንገብጋቢ ጥያቄ (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

ምጽዓት የቀረበ ይመስላል፤ ብዙ ሰዎች ሳይጠየቁ በቁሎው የተጠየቀውን ጥያቄ ራሳቸውን ጠይቀው አጎቴ ፈረስ ነው የሚለውን መልስ እየመለሱ ናቸው፤ ስለምንነታቸውና ስለማንነታቸው በውስጣቸው አንድ አስጨናቂ ነገር እንዳለባቸው ግልጽ ነው፤ የጎዶሎነት ስሜት ስለሚሰማቸው የድረሱልኝ ጥሪ በጩኸት እያሰሙ ነው፤ ግንባር ቀዳሚ መለከት ነፊም አለ፤ እውነት ግን አይደፈጠጥም፤ እየዘለለ ያፈጥባቸዋል፤ አጎቴ ፈረስ ነው ባሉ ቁጥር፣ አባትህስ እያለ ያፈጥባቸዋል! በፈረስ አጎትነት የአህያን አባትነት መደምሰስ አይቻልም፤ ነገር አፍጥጦ ከመጣ አፍጥጦ ከመግጠም የተሻለ መልስ አይገኝለትም፤ ተቅለስልሰው ሊያልፉት ሲሞክሩ በኅሊና ውስጥ ተቀርቅሮ ይደበቃል፤ ለራስም ለማኅበረሰብም ክፉና ዘላቂ በሽታ ይሆናል፤ ኢትዮጵያዊነት ማንነቱን የሚክድ ኢትዮጵያዊ ሲያቃዠው ያድራል እንጂ ፍቆ አያጠፋውም፤ አንድ ጊዜ በጀኒቫ በአንድ የአበሻ ምግብ ቤት ስበላ አንድ ዱሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዬ የነበረ የኤርትራ ተወላጅ ሲገባ ተያየን፤ እየሳቅሁ ደሞ እዚህ ምን ልታደርግ መጣህ ስለው፣ ከዚህ ማምለጥ እኮ አይቻልም፤ አለኝ፤ እንዴት ብሎ!

ሦስት ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት? (ፕ/ር መሰፍን ወ/ማርያም )

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የፖሊቲካ ድርጅቶች ገዢ የሚባለውንም ጨምሮ ስያሜአቸው እንደሚያመለክተው ከነጻነት ውጭ ናቸው፤ ሌላው ቀርቶ ለነጻነት የተዘጋጁ አይደሉም፤ ራሳቸው በባርነት ውስጥ በጀርባቸው ተንጋልለው ሌሎችን ከባርነት ለማውጣት ማሰባቸው አለማሰባቸውን እንጂ ሌላ አያመለክትም፤ ወያኔ ራሱ ገና ነጻ ያልወጣ የባሪያዎች አለቃ ነው፤ ወያኔ ለባርነት ደረጃ አበጅቶ ጠርናፊና ተጠርናፊ እያለ ከፍሎታል፤ ከወያኔ ጋር በደባልነት አገር ለመግዛት የተመለመሉት ከባርነት ሳይወጡ ካባ ለብሰው በአገልጋይነት የወያኔን ጉድለት ለማሟላት የሚሞከርባቸው መሣሪያዎች ናቸው፤ መሣሪያነታቸው የተሰማቸው ከብዙ ዓመታት ጀምረው በመኮብለል ላይ ቢሆኑም፣ ጭራውን እየቆላ በሞተ-ከዳ እግር ለመግባት የሚተናነቀው ብዙ ነው፤ ወያኔ ለአንድ ትልቅ አገር የሚበቃ ሠራዊት፣ ለአንድ ትልቅ አገር የሚበቃ የፖሊስ ኃይል፣ ለአንድ ትልቅ አገር የሚበቃ የአስተዳደር የሰው ኃይል በቁጥርም በጥራትም የለውም፤ በይድረስ-ይድረስ በብዙ ዶላር አስተማሪዎችን ከውጭ እያስመጡም ሆነ፣ ወይም በፖስታ፣ ወይም ከታወቀው ማምረቻ በሚወጡ የለብ-ለብ ምሩቆች እየተንገዳገደ እዚህ ደረሰ።