Saturday, May 17, 2014

የዳላስ ኢትዮጵያውያን ዳግመኛ ችግር ሳᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ

ዘረኛው አገዛዝ የመጨረሻ የሚመስል ከልክ ያለፈ የዘረኝነትና የፍጅት ተግባሩን ቀጥሏል። ሕዝብን ከሕዝብ ማባላቱ የስርአቱ አይነታ ስልት መሆኑን እስካሁንም ያልተረዱ መኖራቸው ያሳዝናል። በአለፉት ፪፫ አመታት ተወልደው ያደጉና በሰላሳወቹ ውስጥ ያሉ ዜጎች ብዙወች የስርአቱ ሰለባወች ሆነዋል። አገርና ሕዝብ ለወያኔ ደናቁርት ምንም ማለት አይደለም። በመሆኑ የአገር ልሂቃን፤ የፖለቲካና የሰበአዊ መብት ተሟጋች የሆኑ ዜጎች ክንዳቸው እንዲጠነክር መተባበርን ይጠበቅባቸዋል።
ወያኔ በአገር ውስጥ ዜጎችን ያለርህራሄ በሚጨፈጭፍበት በዚህ ጊዜ፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በባእድ አገር የመሰረቷቸውን ትቂት ተቋማት ለመቀማትና ተቀናቃኝ የሚላቸው ወገኖች ጨርሶ መገናኘት እንዳይችሉ ለማድረግ መላ ዘይዶ ከተንቀሳቀሰ አመታት አስቆጠረ። መቸም ቢሆን በየሄደበቱ የሚነጠፉ አገልጋይ ማግኘት አልገደደውምና ስልት አድርጎ የሚጠቀምበት ቤትና መሬት እሰጣችኋለሁ። በልማት ስም ተሰባሰቡ በማለት እያደራጀ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል።

ከሁሉም የሚያሳዝነው ለዚህ ዘረኛ ስርአት ለማገልገል በወዶገብ የተደራጁት ዘመናቸውን አጠናቀው ለመሄድ አንድ ሐሙ የቀራቸው ናቸው። እግራቸው ወደገደል እየሄደ መሬትና እቤት እናገኛለን በሚል ደጅ የሚጸኑት ቁጥር ቀላል እየሆነ አይደለም። በአዲሱ የወያኔ ስልት መሰረት ተሰሚነት አላቸው የሚባሉትን በተለያየ ጥቅማጥቅም በመቅረብ በሚያሳፍርና በሚዘገንን ሽምግልና አዋቂነት የምንልውን ትተው በመሰረቷቸው አቢያተክርስቲያናትና በአደራጇቸው የኮሚውኒቲ ስብስቦችን ሲሆን በሰላም ለወያኔ ዘረኛ ፖሊሲ መገልገያ እንዲሆኑ አልሆን ሲል ምእመናን እርስ በእርስ ማባላትና ሰላም መንሳትን ተያይዘውታል።
በሰሞኑ የደብረሰላም መድሐኒ አለም ሚኒሶታን ቤተ ክርስቲያን መተያያ ለማድረግ የተሞከረው በጠንካራ ዜጎች ትብብር መክሽፉንና። የዘረኞች አባሪና ተባባሪወች የማፈራቸውን ቸር ወሬ ስምተናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደዋናው መልእክቴ ልግባ።
በዳላስ ኢትዮጵያውያን ላይ የቀጠለው ጸረ ሰላም የወያኔ ተግባር
ድሮ ስለምንኖርበት ከተማ ተናግረን አንጠግብም ነበር። በሌሎች ከተሞች እንሰማው የነበረው የወያኔ ቫይረስ ስለሌለ በከተማው የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንደአንድ ቤተሰብ ይቆጠር ነበር። በሐዘንም ሆነ በደስታ ሁሉም በአንድ ተሰብስቦ ተካፋይ ነበር። ዛሬ ያሁሉ ተለውጦ ክፍፍልና መራበሹ እስከ ወዳጆች ዘልቋል። ለዚህ መንስኤ ሕወሐት በከተማው የዘረጋው መዋቅር ለመሆኑ በተከታታይ ሕዝብ እንዲያውቅ ተደርጓል። አጥቢያ ቤተክርስቲያናችንን ለመንጠቅ የተሞከረው ሁሉ ቢከሽፍም ሙሉ ሰላም እንዳይገኝ ግን አጥብቀው የሚደክሙ እንዳሉ ተገንዝበናል። በምእመናን የብዙሐን ድምጽ ተመርጠው የሚያስተዳድሩ የቦርድ አባላትን ለሚሰሩት የአስተዳረ ተግባራትና ውሳኔወች እስከ ኮሚቴ ስብሰባ ለመቆጣጠር የሚሞክረው ክፍል። ያልተባለን ተባለ፡ ያልተሰራን ተሰራ በሚል ያላቋረጠ ጭቅጭቅ ከቶናል። ይህ ደግሞ በግልጽ እራሳቸውን የዚህ መንግስት ደጋፊ ነን በሚሉ ግለሰቦች የሚመራ ኮሚቴ በማደራጀት ነጋ ጠባ በመሰብሰብና አመል በማውጣት ዜጋን እርፍት መንሳታቸው ግልጽ ነው። ይህን ሲያደርጉ ግን ንጹህ እምነት የሚያራምዱ ዜጎችን ሊያታልሉበት የሚችሉ የተለያዩ ሰብቆችን በማዘጋጀት ነው።
• አንዳንድ ቀሳውስትን በተለየም መነኩሳት በነሱ ስር በማድረግ። በአሁኑ ጊዜ የሚወጡ አብዛኛወች በመንግስት የሚላኩ በመሆኑ ወይንም ሙሉ ልቦናቸው ውስጥ ካለው አስተዳደር ጋር የተቆራኙትን በመጠቀም ማራበሽ።
• እራሳቸውና እነዚሁ ቀሳውስት የነሱን ሰላም እናስታርቅ በሚል ሰበብ በየጊዜው አስታራቂ ኮሚቴ በመሰየምና ያው አስታራቂ ተብሎ የተቋቋመ ኮሚቴ ትንሽ ቆየት ብሎ ከሳሽ፤ አስተባባሪና የመንግስት (የውስጥ ሲኖዶስ) ወኪል ሆነው መቅረብ።
• በሁሉም ስብስቦች የነሱ ሰወች ተመራጭ ሆነው ቦታ ካልያዙ ማውገዝ፤ አሉባልታና የተዛቡ መረጃወች ለህዝብ ማሰራጨት። ግለሰቦችን እየመረጡ ጸያፍ ስም መለጠፍ። የሚለጠፍባቸው ግለሰቦች ለአገር ለወገን ተቆርቋሪ ከሆኑ አንገት እንዲደፉ ለማድረግ ሲሆን
• ይህን ሁሉ ካደረጉ በኋላ የነሱ ስም የማይገባበት ክስ መመስረት። አንዳንዴ እራሳቸው የከሰሱበት ወቅትም አለ።
• ከሳሽንና ተከሳሽን እናስታርቅ የሚል ሌላ ኮሚቴ ሌላ አጀንዳ ይከፍቱና ከሳሽም ሰላም አስጠባቂም አስታራቂም እነሱው ሆነው ይሰየማሉ። በየጊዜው ካላነጋገራችሁን በሚል አሉባልታና ሐሚት ይነዛሉ።
ለአለፈው አንድ አመት ጊዜያዊም ቢሆን አንጻራዊ ሰላም ታይቷል። ሆኖም ለእነሱ ያገለግሉ በነበሩ አንድ አባት በስነ ምግባር ከስራ ስለተነሱ ሆሳእና አንድ ሳምንት ሲቀረው አንቱ የተባሉ ትቂት የዚሁ ዘረኛ መንግስት ሰለባወች ስርአተ ቅዳሴ ተባርኮ ሳይጠናቀቅ ባደረጉት እረብሻ ብዙ መእመናን፡ ባልቴቶችና መነኩሳትን አሳዝነዋል።
ነገረ ስራቸው ማመስና ማፍረስ፤ ሰላም መንሳትና መበጥበጥ በመሆኑ። እኒሁ ከቅዱስ ሚካኤል በስርአት አጉዳይነታቸው የተነሱት መነኩሴ ይዘው በውስጥ ሲኖዶስ ስር ያሉ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስትን ወደ አንድ ሁኑ የሚል የማስማማት ስራ ሲሰሩ ሰንብተው ባለፈው እሁድ ሜይ 11 ቀን 2014 በገለልተኝነት የቆየውን የጊወርጊስ ቤተክርስቲያን በእርቅ ስም ግማሽ የሚሆኑ አባላት ሳያውቁትና ሳይመክሩ። በድብቅ ሲሰበሰቡ ሰንብተው ከዚህ ቀደም ተመራጭ ሆኖ ግን በድካም ከተመረጠበት እራሱን አግሎ የቆየን ሰው መሪ አድርገው ግለሰቡ ከዛሬ ጀምሮ አባ ማትያስ አባታችን ናቸው በማለት አስታውቋል። በድንጋጤ እና ሳያውቁ በጀርባ በወያኔ የድብቅ ስብሰባ ያለቀና የተጠናቀቀ ሰነድ አንቀበልም ያሉትን አባላት ትቂት ናችሁ እናንተም ለምን ትግሬ ገዛን ባዮች ናችሁ። ነገ ኦሮሞ ሲገዛ ምን እንደምትሉ አናውቅም የሚል ዘረኛና ልክ ዛሬም በኢትዮጵያ ከተሞችና መንደሮች እየተደረገ ያለውን ጸያፍ ንግግር ከዱላ ቀረሽ ስድብ ጋር በመሰንዘር አብረው ለአመታት በአንድ የጸለዩ ወገኖቻቸውን አሳዝነዋል። ተመልሰውም እንዳይደርሱባቸው አስጠንቅቀዋል።
የዳላስ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ሰላም ከተነፈጋቸው አመታት ተቆጥሯል። ይህን መሸከም ያቃታቸው ወገኖች ዛሬ እቤት መዋልንና ከወገን መለየትን አንደ መድሀኒት ቆጥረውታል። በእርግጥም የዚህ ዘረኛ መንግስት አላማም ይኸው ነው። በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ለወገኖቻችን እንዳንጮህ። ትቂትም ቢሆን የትብብር እጅ አንዳንዘረጋ ለማድረግ የዘየደው እየተሳካ ነው ብንል ስህተት አይሆንብንም።
የዚህ መልእክት አላማ የተወናበዱ የተታለሉ። መስሏቸው በእጅ አዙር ከዘረኛው የድብቅ ተባባሪወችና አስፈጻሚወች ጋር የቆሙ ወገኖቻችን አይናቸውን ከፍተው እንዲያዩ ለማሳሰብ ነው። ዛሬ ዳላስ ብቻ አለመሆኑን በየዜናው የምናየው የምንሰማው ነው። ብሩህ አዕምሮ ያለው ወገን ለምን የለንደን ወገኖች የእምነት ቤታቸውን አጡ፧ ለምን በሚኒሶታ ይህን ያክል ድፍረት ተሞከረ፡ እንዲሁም በሌሎች ሁሉ ለምን ሆነ የሚለውን መጠየቅና ነቅቶ ከወገን ጋር መቆም ይጠበቃል።
ወያኔ መንታ አማራጭ ይዞ ነው እረብሻውን የሚጀምር። በሁለቱም ጎዳና አይጎዳም። መራበሽ ሲነሳ ተጠቃሚው እርሱ ነው።፡ይህ የአናሳ ስርአት ሊቀጥል የሚችለው በውስጥም ሆነ በውጭ ዜጎች በተለያየ እርሱ በሚፈጥራቸው ተግባራት ተወጥረው እርስ በእርስ ሲጋጩለት ብቻ ነው። ኢትዮጵያውያን ውስጥና ውጭ ሳይሉ። የእከሌ የፖለቲካ ድርጅት ሳይሉ። በአንድ የቆሙ እለት ይህ ስርአት

No comments:

Post a Comment