Tuesday, March 31, 2015

ወያኔና ሽብርተኛነት ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም

terrorist-cat
ወያኔነትና ሽብርተኛነት ትናንት ምን ዓይነት ግንኙነት ነበራቸው? ዛሬ ምን ዓይነት ግንኙነት አላቸው?
ወደዚያ ከመሄዳችን በፊት የአሸባሪነት የተግባር መገለጫው ምንድን ነው? ብለን እንጠይቅ፤ አሸባሪነት፡-
• ያለውን የሥልጣን ሥርዓት የማፍረስ ዓላማ ያለው ነው፤
• ዓላማውን ለማሳካት ጉልበቱን የሚያፈረጥመው ከሥርዓቱ ጠላቶች በሚያገኘው፡–
• የመሣሪያ እርዳታ፣
• የእውቀት ድጋፍና ገንዘብ
• ዓላማውን ለማሳካት

በኢትዮጵያ ዝሆኖችም “ተሸብረዋል” ባለፉት 30ዓመታት 90በመቶ ዝሆኖች አልቀዋል

ivory
የዝሆኖችን ግድያ ለማስቆም በሚል የብአዴኑ ደመቀ መኮንን ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ስድስት ቶን የሚመዝን ጌጣጌጥ እንዲቃጠል እሣቱን በለኮሱበት ጊዜ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየበት 25 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዝሆኖች ቁጥር ከ90በመቶ በላይ ለምን ሊቀንስ እንደቻለ የተናገሩት ነገር የለም፡፡

ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ላይ ጀገነ “ከቀድሞው ስህተት” የተማሩት እነ ሌንጮ ለታ ተቀባይ አጡ

odf lencho

ቆራጥ ጀግና ማነው? (ወለላዬ ከስዊድን)

አንድነት ይፈጠር – ሀገር ነጻ ትውጣ
ንብረትም ይቅርብኝ – ምንም ነገር ልጣ
ዳሩ መሀል ሳይሆን – ድንበሩ ተደፍሮ
ርቱዕ አንደበት – እንዳይቀር ተቀብሮ
ጋዜጠኝነትም – እንዲኖር ተከብሮ

መለሰ ዜናዊ ናፈቁኝ – የለቅሶ አየር ሰዓት አማረኝ

meles funeral3
“የለቅሶ ማስተላለፊያ የአየር ሰዓት/ክፍለ ጊዜ ቢጀመር ጥሩ ነው። ምርጫውን ያደምቀዋል” የሚል አስተያየት ሟርተኞች ያቀርባሉ። ግን ምን አለበት የከፋቸው ቢያለቅሱ። በየጓዳው እያለቀሱ ነው። አደባባይ ወጥተው ቢያለቅሱ ምን ነውር አለው? ለመለስ ደረት እየተመታ ሲለቀስ የአየር ሰዓት ተፈቅዶ የለ? ለሞተ ሰው ከተፈቀደ በህይወት ላለው፣ ግብር ለማያጓድለው ለምን ይከለካል? ወይስ ነዋሪው በሟች ተበልጧል?

“የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል” ሲለኝ – ደነገጥኩ ህወሃት - የመርዝ ገበሬ፤ ጥይት ማጭዱ!!

tplf gun holders
“የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል ሲለኝ – ደነገጥኩ” የሚል አስተያየት የሰጠው ኳስ አፍቃሪ ከጎልጉል የአዲስ አበባ ወኪል ጋር የተገናኘው አዲስ አበባ ስታዲየም ነበር። ጉዳዩ ለሚዲያ ግብዓት እንደሚውል ባይረዳም ገጠመኙን ለመናገር የተገደደው ስለ ምርጫ አንስተው ሲወያዩ ነው። ድንገት ተገናኝተው ቆሎ በመገባበዝ የጀመሩት ጨዋታ ዘጋቢውን ወደ 1997 ምርጫ ትዝታ ወረወረው። ተግባብተው አወጉና ተለያዩ። የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል!! ለምን? መርዝ ዘርቶ በጥይት ለማጨድ?
የስታዲየሙ ሰው የመኪና ማስጌጫ ለመግዛትና ለማስገጠም ሰባራ ባቡር እንደሄደ ይናገራል። እዛም እንደ ደረሰ የሚፈልገውን ገዝቶ እያስገጠመ ሳለ አንድ ጎረምሳ ቢጤ ይጠጋቸውና ወሬ ይጀምራል። ጎረምሳው የትግራይ ተወላጅ ነው። አንዳንድ ማስጌጫዎች የሚፈልግ ከሆነ እሱ ዘንድ በርካሽ እንደሚያገኝ እየነገረው ቃላት መለዋወጥ ጀመሩ። በዛው የተጀመረው ጨዋታ ስር እየሰደደ ሄደና ስለምርጫ ማውጋት ጀመሩ።

Monday, March 30, 2015

“የስለት ልጅ ነኝ” – አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾው ጋር)

በቅርቡ ወገኔ የሚለውን ተወዳጅ ነጠላ ዜማ የለቀቀው አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ከታማኝ በየነ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ስለ ሙዚቃ ሕይወቱና ስለራሱ ሕይወት ተናገረ:: ብርሃኑ “የስለት ልጅ ነኝ” ብሏል:: ቃለምልልሱን ይከታተሉት::

“የስለት ልጅ ነኝ” – አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ (ከታማኝ ሾው ጋር)

መንግስቱ ንዋይ : መጋቢት 19 ፣ 1953 ዓ.ም የሞት ፍርድ ከተወሰነባቸው በኋላ የተናገሩት ንግግር

mengestu_neway_
እናንት ዳኞች የበየናችሁብኝን የሞት ፍርድ ያለ ይግባኝ ተቀብያለሁ፡፡ ይግባኝ ብየ ጉዳየን የሚመለከትልኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢሆን ኖሮ ይግባኝ ማለት በፈለግሁ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ እንደማይሆን አውቃለውና በይግባኝ የአፄ ኃ/ስላሴን ፊት ማየት አልፈቅድም፡፡ በእግዚያብሄር ስም ተሰይማችሁ ከተቀመጣችሁበት የፍርድ ወንበር ላይ ከመቀመጣችሁ በፊት በእኔ ላይ የምትሰጡትን የዛሬውን ፍርድ ታውቁት እንደነበር ሳስብና ፍርድ እስከዚህ መርከሱን ስታዘብ ሀዘኔ ይበዛል፡፡

የይቅርታ ደብዳቤ ለጃዋር መሐመድ (ሄኖክ የሺጥላ)

ውድ ጃዋር ፣ ሳልውቅ ፣ ጠነኝነቴ አሳስቶኝ ፣ አንተም ምንም የመረረ እና የተንዛዛ ዘረኛ ብትሆንም ቅሉ ፣ ጤነኛ ነህ ብዬ ፣ እንደ አንድ ሰው ልወቅስህ አስቤ ፣ ባንተ ላይ የጻፍኩዋቸው ጽሁፎች ፣ አሁን አንተን በደንብ ሳውቅ እና ስላንተ ስረዳ ፣ ይህንን የይቅርታ ደብዳቤ መጻፍ እናዳለብኝ ተረድቻለሁና ፣ ደብዳቤን አርቅቄ ይኸው ይደርስህ ዘንድ ይሁን።Jawar Mohamed Muslim fundamentalist
ውድ ጃዋር ሆይ ፣ እንደምን ከርመሃል ? መቼም መጻፍ አስቸግሮኝ አያውቅም ፣ ይህንን ጽሑፍ ግን ለመጻፍ ስዘጋጅ ያየሁትን ፈተና እኔና መድሃኒያለም ነን የምናውቀው ። በመጀመሪያ ፣ ስለ አንተ በደንብ ከተረዳሁ እና ካወቅሁ በሁዋላ ፣ እንዴት አድርጌ ብጽፈው ፣ ይቅርታዬ ሊገባው ይችላል ብዬ ተጨነኩ ፣ ቀጥሎ ከዚህ ሁሉ የእርማት እና ፊደል የመልቀም ሥራ በሗላስ በእውነት የጻፍኩት ይገባው ይሆን ብዬ ድጋሚ ተጨነኩ ።

Friday, March 27, 2015

“ጦር ሠራዊቱ ሕዝባዊ እምቢተኛነት ሲያይል የወያኔን መቃብር ይቆፍራል” – አርበኞች ግንቦት 7

የአርበኞች ግንቦት 7 ወቅታዊ መጽሐፍ
ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!
አለማችን አንባገነን ስታስተናግድ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። ዘረኛንም እንዲሁ …….. እኛም ስለነፃነት ብለን ለትግል ሰንነሳ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም …… አለማችን እንደየዘመኑና እንደ የወቅቱ አንባገነኖች ያለ የሌለ የመሳሪያና ወታደራዊ ሀይላቸውን በመጠቀም ህዝብን በፍርሀት አሸማቀውና ረግጠው ለመግዛት ሲውተረተሩ በተደጋጋሚ ታይተዋል። በዚያው ልክ ህዝባዊ ሀይልና መመከት ተስኗቸው ሲንኮታኮቱ በተደጋጋሚ የታየ ወደፊትም አናባገነኖች እስከተከሰቱ ድረስ በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገው መቀመቅ ሲወርዱ መታየቱ አይቀሬ ነው ። ህዝብ የወደደውን አስተዳዳሪ እንጂ ረግጦ ሊገዛው የሚፈልገውና አንባገነን ተቀብሎ አያውቅም ፤ዛሬም አልተቀበለም ፤ ነገም አይቀበልም ። ይህን በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚና በጉልህ የሚታይ ግዙፍ እውነት መቼም ተቀብለውና ከታሪክ ተምረው ስለማያውቁ አሳፋሪው ውድቀታቸው በተደጋጋሚ ሲታይ አለ።
ginbot 7
ሀገራችን የአለማችን አካል እንደመሆኗ አንባገነኖች ተፈራርቀውባታል። አንባገነኖችም በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገውባ ታል። ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ትልቅ ወታደራዊ ሀይል የነበረው የትናንቱ ደርግ እንደ እንቧይ ካብ ሲናድ ተመልክተናል። አንባገነኖችመናገር እንጂ መስማት የማ ችሉ፤ ማየት እንጂ ማስተዋል የተሳናቸው በመሆናቸው እነሆ ዛሬም የወያኔ ዘረኛው ቡድን ህዝባ ላነሳው የነፃነትና የፍትህ ጥያቄ ያለ የሌለውን ወታደራዊ ሀይል በጠራራ ጸሀይ በማሰለፍ መቼውንም ያልተቻለ ውን ህዝብን በሀይል አሸማቆ ለመግዛት መከራውን ሲያይ ይስተዋላል። ለዚህም ነው ….. ከሌላው የሀገራችን ክልሎች ከፍ ባለ ሁኔታ የህዝባዊ እንቢተኝነት እየታየ ባለበት ጎንደርና አካባቢው በሰራዊት ማጥለቅለቅ የተያያዘው።

መንግሥት ለምን ጩኸት ይወዳል? (ኤልያስ ገብሩ ጎዳና )

የየትኛውም ሀገር መንግሥት፣ ለሚመራው ህዝብ፣ እየሰራ ስለሚገኛቸው ሥራዎች የማሳወቅ ኃላፊነት እና ግዴታ ስላለበት ይናገራል፡፡ የአገላላጽ ደረጃ እና መጠኑ እንደየመንሥታቶቹ ባህሪ የሚወሰን ነው፡፡ መንግሥታት ሥለሚያከናውኗቸው ሥራዎች ለህዝቡ በግልጽ ዕውነቱን ሊናገሩ እንደሚችሉ ሁሉ፣ ለፖለቲካ ትርፋቸው ሲሉ ቀናንሰው እና ውሸትን አቀላቅለው ሊገልጹም ይችላሉ፡፡Elias Gibru
ይሄም ብቻ አይደለም፣ ከተሰራው በላይ በማጋነን፣ የፕሮፖጋንዳ ሥራን በፈጆታነት ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል ብዬ የማስበው ገዥው መንግሥት ኢህአዴግ ነው፡፡ መንግሥታችን ትልቅም ሆነ ትንሽ ሥራ ሲሳራ በግንነት መግለጽ አንዱ መለያው ማድረጉን ምርጫው ያደረገ ይመስላል፡፡

አርበኞች ግንቦት7 – ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyአለማችን አንባገነን ስታስተናግድ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። ዘረኛንም እንዲሁ …….. እኛም ስለነፃነት ብለን ለትግል ስንነሳ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም …… አለማችን እንደየዘመኑና እንደ የወቅቱ አንባገነኖች ያለ የሌለ የመሳሪያና ወታደራዊ ሀይላቸውን በመጠቀም ህዝብን በፍርሀት አሸማቀውና ረግጠው ለመግዛት ሲውተረተሩ በተደጋጋሚ ታይተዋል። በዚያው ልክ ህዝባዊ ሀይልን መመከት ተስኗቸው ሲንኮታኮቱ በተደጋጋሚ የታየ ወደፊትም አናባገነኖች እስከተከሰቱ ድረስ በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገው መቀመቅ ሲወርዱ መታየቱ አይቀሬ ነው ። ህዝብ የወደደውን አስተዳዳሪ እንጂ ረግጦ ሊገዛው የሚፈልገውን አንባገነን ተቀብሎ አያውቅም ፤ዛሬም አልተቀበለም ፤ ነገም አይቀበልም ። ይህን በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚና በጉልህ የሚታይ ግዙፍ እውነት መቼም ተቀብለውና ከታሪክ ተምረው ስለማያውቁ አሳፋሪው ውድቀታቸው በተደጋጋሚ ሲታይ አለ።

ወይ ቤን ድኩማኑ – አምላክ ፍርፋሪ ለቃሚ ከመሆን ያውጣን!

የጦቢያ ነጭ ለባሽ
ከካናዳ ግራ የተጋባ ኑሮው ቋንቋ እንኳን በወጉ ሳይማር አቶ ለገሰና አላሙዲንን አቆላምጦ ቋሚ የአሸርዳጅነት ስራ የተሰጠው ቢንያም ከበደ (ቀለለ)ደግሞ ብሎ ብሎ ሄሊኮፕተራችንን መልሱ እያለ ሃገር ቆርሶ ለሰጠ የሽፍታ ቡድን ቋሚ ጠበቃ ሆኖ ሳያፍር፡ ወያኔ ተቆርቋሪ ሆኖ ፋታ ሳይሰጥ ላስገነጠላት የኤርትራ ምድር ግድ ሳይለው፡ ስለ ትግራይ የአፓርታይድ ስርዓት ንብረት ዛሬ አንደበቱ ተከፈተ።Ethiopia first, benyam kebede
በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ አየር ሃይልን አፍርሰው፤ የኢትዮጵያ ባህር ሃይልን ከነባህር በሩ ቀብረው፤ የሃገራችንን መከላከያ ጦር በትነው፤ ዛሬ በትግራይ ክልል መናገሻውን ካደረገ ለቆየው የህወሃት አየር ሃይል፡ የኦህዲዱ ካድሬ ቢንያም ቀለለ ጥብቅና ሲቆም፤ በሺዎች የሚቆጠሩየኦሮሞ ተወላጆች እስርቤቶችን ባጨናነቁበተና እና በምሬት ብረት ያነሱት የኦሮሞ ለጆችና ሌሎች ኢትዮጲያዊያን ጀግኖች ደግሞ ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ባሉበት ሰዓት፡ ምን ያህል በወገኖቹ ህይወት ቁማር የሚጫወት ከሃዲ መሆኑም ለፍርድ እየተመዘገበለት ነው።

ምርጫ በኢትዮጵያ – ሰማያዊ ፓርቲ ከምርጫ ክርክር ታገደ

ሰማያዊ ፓርቲ በኢብኮ ከሚደረገው የምርጫ ክርክር ታገደ

• ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በኢብኮ ስቲዲዮ ከሚደረግው ቀረጻ ተባረዋል
(ነገረ-ኢትዮጵያ) ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ መጋቢት 18/2007 ዓ.ም ምሽት ኢብኮ (EBC) ላይ ከሚቀርበው የ‹‹ግብርና እና ገጠር ልማት›› ላይ ሊያደርገው የነበረው የምርጫ ክርክር ላይ እንዳይቀርብ መታገዱን የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ለቀረጻ ወደ ኢብኮ ስቲድዮ ባቀኑበት ወቅት የድርጅቱ ምክትል ስራ አስካሄጅ አቶ ተሻለ ‹‹ባለፈው ያላሰባችሁትን የምርጫ ክርክር እድል ሰጥተናችኋል፡፡ በመሆኑም ዛሬ መከራከር አትችሉም›› ተብለው መባረራቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Thursday, March 26, 2015

ያልመከተ ተፈነከተ፤ ያልተደራጀ ተፈጀ። – ጌታቸው ኃይሌ


  • 647
     
    Share
getachew
ጌታቸው ኃይሌ
አንዱን የዘመናችንን ትልቁን ብሔራዊ ችግር ለመፍታት ያስችል የመሰለኝን ሐሳብ ከጥቂት ቀናት በፊት “በኢትዮጵያ ሰላም የሚያመጣ የአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ያስፈልጋል” በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ በ ethiomedia ለሕዝብ አቅርቤ ነበር። በጽሑፉ ጥቂት ሰዎች የተወያዩበትን ወዳጆች ልከውልኝ አነበብኩት። በስልክ ያወያዩኝም አሉ። ትችቶቹን ሁሉ ስላላየኋቸው ይሆናል እንጂ፥ ያየኋቸውን ሳጠናቸው፥ ከዶክተር ፀሐይ ብርሃነ መስቀል በቀር ፍሬ ነገሩ ላይ ያተኮረ ሐሳብ የሰጠ አላጋጠመኝም።
የተቺዎችን ቀልብ የማረከው “አማራ የሚባል ሕዝብ አለ ወይስ የለም?” የሚለው ነው። ይኸንን መተቸት ደስ ይላል መሰለኝ፥ ተተችቶ ባለቀ በስንት ዓመቱ፥ ትችቱ እንዲያገረሽበት ጽሑፌ ምክንያት ሆነ። እኔ ግን ጽሑፌን የደመደምኩት እንዲህ ብየ ነበር፤
ለዚህ ድርሰት አስፈላጊነቱ ስላልታየኝ፥ “አማራ ማነው?” ከሚል፥ መልሱ ብዙ ገጽ ከሚፈጅ ጥያቄ ውስጥ አልገባሁም። ሁሉም ራሱን ስለሚያውቅ፥ “አማራ ነኝ” የሚል ሁሉ በሙሉ አባልነት፥ በድርጅቱ የዕርቅና የሰላም ዓላማ የሚያምን፥ ግን “አማራ ነኝ” የማይል ኢትዮጵያዊ ደግሞ በደጋፊ አባልነት መመዝገብ ይችላል።

"አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል"

አርኣያ ጌታቸው አርኣያ ጌታቸው 
2005 ዓ.ም. ከ1998 ዓ.ም. በኋላ በተግባር ሊታይ የሚችል የፖለቲካ እንቅስቃሴ የታየበት አመት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። በተለይ በግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. የሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ምንአልባትም ወደኋላ ይጓዝ የነበረውን የሀገር ውስጥ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከማስቆም በዘለለ ወደፊት እንዲጓዝ ያደረገው ይመስለኛል።
 ከዚህ እለት በኋላ ባሉት ቀናቶች ውስጥ በርካታ ፓርቲዎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። በተለይ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ለዚህ ማሳያ ነው። ድርጅቱ በደሴና በጎንደር የተሳኩ ሁለት ሰልፎችን በአንድ ቀን አድርጓል።

Wednesday, March 25, 2015

የጠቅላይ ሚንስትሩ እጅ እጅ ያለው ዶሮ ወጥና ፖለቲካ

በቅርቡ ተጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይለማሪያም ደስ አለኝ ዓረብ ሐገር ያዩትን ወገንና አዉሮፓ መጥተዉ ያዩትን የወገን ችግር፣በምፀት ሲገልፁ- ብዙ እንቶ ፈንቶ ተናግረዉ ነበር ፈረንጆቹ bla -bla ይሉታል ፣ ከዛ ዉስጥ ግን አንድ አነጋገራቸዉ ቀልቤን ስባ ሌላም ነገር አስታወሰችኝና ትንሽ ልበል ብዬ እኔም ብዕሬን አነሳዉ ።
ምን ሆነዉ ነው እንደዚህ በሰዉ ሐገር እሚሰቃዩት -ሐገራቸዉ ቢሆኑ ጠግበዉ መብላት እንደሚችሉ, ስደተኛዉን ኢትዮጵያዊም ሆነ ያገሪቷን ክብር በወረደ ቃላት ሲዘባበቱበት ከራሳቸዉ አንደበት ሰማሁና ፣ ታዲያ ይሔን ግዜ ምን አሰብኩ እኝህን ጠቅላይ ሚንስትር በዙሪያቸዉ ያሉ የድሮ ማርክሲስት ኤሊትሶች ይህን እንዲናገሩ እና እንዴት ከጨወታ እያስወጡዋቸዉ እንደሆነና መጨረሻቸዉም ከግዜሩም ከሰይጣኑም እንዳይሆኑ ተደርጎ የስርዓቱ የተሞላ አሻንጉሊት ሲሆኑ ማየቱ እንደዜጋም እንደሰዉም ስላሳዘንኝም ነዉ ።

Tuesday, March 24, 2015

ህወሀትን የማስወገዱ ትግል ወደ ከፍተኛ ደረጃ ደርሳል ( የጦርነት ወሎ ይመልከቱ)

ህወሀትን የማስወገዱ ትግል ወደ ከፍተኛ ደረጃ ደርሳል ( የጦርነት ወሎ ይመልከቱ) አርበኞች ግንቦት ና  ትህዴን(ዴሚት) በጋራ ህወሀትን ማጥቃት ጀምረዋል ትግሉ ወደ ከፍተኛ ምህራፍ ተሽጋግራል ህወሀት ኢአዴግ በሚፈልገው ትግል ለመግጠም የቆረጡት የነፃነት ታጋዮች ቁርጠኛ ትግል እያካሄዱ ሲሆን ትግሉንም በርካታ ኢትዮጵያውያን እየተቀላቀሉት ነው።

የአባይ ግድብ በግብጽ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ መገንባቱ ወያኔ ምን ያህል አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ያሳያል::

Image
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የአባይም ግድብ እንደ ባድመ ድል ለጭፈራ አቀባብሎ እንዳይሰጠን .. መቸም ወያኔ በሰው መቀለድ ለምዷል::የአባይ ቦንድ የገዛህ የገዛሽ ሁሉ ነገሮች ሁሉ ባዶ ጭብጨባ ሆነዋል:: ለሕዝብ የማይጨነቀው ወያኔ በኢኮኖሚ ከደቀቀው የመንግስት ሰራተኘው ጀምሮ እስከ ጎንበስ ቀና ብሎ ደክሞ እስከሚሰራው ምስኪን ኢትዮጵያዊ ድረስ በአባይ ቦንድ ስም ከፍተኛ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቷል::በውጪዉም አለም ቦንድ ለመሸጥ ቢዘምትም ሳይሳካለት ቀርቷል::ሻእቢያ እና በአከባቢው ያሉ ጉዳዮች ወያኔን ውጥረት ውስጥ ጨምረውታል::ይህ የትግሉ አንድ አካል የሆነ የድል ጥርጊያ መንገድ ለፖለቲካ ድል ልንጠቀምበት ይገባል::የአባይ ግድብ ትከትሎ የመልስን መሞት አስታኮ ግለሰቡን አባይን የደፈረ መሪ በማለት እስከማላዘን ተደርሷል::የቅርብ ጊዜ ታሪክ እንደሚያሳየን ከሆነ የኢትዮጵያ የመጨረሻእ ንጉስ ሃይለስላሴ አባይን ለመገደን ይህንኑ የግድብ ዲዛይን አሰርተው ነው ዲዛይኑ በገንዘብ ኖቶች ላይ ሳይቀር ታትሟል; በጊዜው..ወያኔ ያንን ዲዛይን በዘመናዊ መሃንዲሶች አሻሻለው እንጂ አዲስ ነገር አልፈጠረም::

‹‹ተወይኖብኛል›› … በዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ተልእኮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተባርሬአለኹ (ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ)

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከሦስት እሥርት ዓመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ በሚሌኒየሙ መባቻ ወደ አገራቸው ተመልሰው ላለፉት ሰባት ዓመታት በማስተማር ሥራ ላይ ቆይተዋል፡፡ ምሁሩ በዋናነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር ቢሆኑም በሕግ ፋክልቲ፣ በሴንተር ፎር ሂዩማን ራይትስ፣ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም፣ በአምስት ኪሎ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፋክልቲ፣ በቴአትሪካል አርትስና በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤትም አስተምረዋል፡፡ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች በተለያየ ጊዜ ሲያስተምሩ ቢቆዩም ከጠየቁት የዓመት ዕረፍት(sabbatical leave) ጋር ተያይዞ ከዩኒቨርስቲው መሰናበታቸው ተሰምቷል፡፡ በዚህ ዙሪያ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከዶ/ር ዳኛቸው ጋራ ተከታዩን አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡

ኑሮ በአዲስ አበባ (ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ)

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
ትናንት ሲያቀብጠኝ ከአንድ ጓደኛየ ሞባይል እነዚያ አይሲስ የሚባሉ ጉግማንጉጎች እነዚያን 21 ክርስቲያን የግብፅ ዜጎች በሊቢያ አንድ የባሕር ዳርቻ ላይ አንገታቸውን ሲቀሉ የሚያሣይ ቪዲዮ አየሁ – እስከመጨረሻው መዝለቅ አልቻልኩምና ግን ዋናው ባራኪ በግራ እጁ የያዘውን ጩቤ ወደ እኛ ወደተመልካቾቹ ዘርግቶ እያስፈራራ ሲዝት አጠፋሁት፡፡Ethiopia, Addis Ababa
የሰው ልጅ በሰው ልጅ ላይ እስከዚህ መጨከኑ የሚያመላክተን ዋና ቁም ነገር የዚች ምድር ሰዎች የደረስንበት አጠቃላይ መንፈሣዊና ኅሊናዊ ኪሣራ ሊቀለበስ ወደማይችል ከፍተኛ የመጨረሻ ደረጃ መድረሱን ነው፡፡ ለምግብነት የተፈቀዱልንን እንስሳት እንኳን ስናርድ የሚዘገንነንና በዚህም ምክንያት የማናርድ ብዙ እንስፍስፍ ሰዎች አለን፡፡ ሰውን የሚያህል ክቡር ፍጡር ሊያውም በሚከተለው ሃይማኖት ምክንያት ብቻ በስለት አንገቱን ቀንጥሰው ጀርባው ላይ ሲያስቀምጡ ሊሰቀጥጣቸው ይቅርና በደስታ የሚፈነጥዙ “ሰዎች”ን በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ስናይ በሰዎች ተፈጥሮ መለያየት እጅግ እንገረማለን፡፡

የጄት ድብደባ ወይንስ የአውሮፕላን መከስከስ?

አበበ ገላው (ከፌስቡክ የተወሰደ)
ወያኔ ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ አንድ የካናዳ የወርቅ ማእድን በአውሮፕላን መደብደቡን አፍቃሪ ወያኔ የሆኑ ድረ ገጾች “ወታደራዊ ምንጮችን” በመጥቀስ ዘግበዋል።
ይሁንና እንኳን ድብደባው የጥቃቱን ውጤት ያሳያል ተብሎ የተለቀቀውም ፎቶ የውሸት መሆኑ ተረጋግጧል። አውራንባ ታይምስ አስተማማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ድብደባውን ማረጋገጡን የዘገበ ሲሆን ዘገባውም በፎቶ ማስረጃ የታጀበ ነው። ይሁንና ፎቶው የሚያሳው ኤርትራ ውስጥ የተኪያሄደውን የአየር ጥቃት ውጤት ሳይሆን ቢቢሲ በኦገስት 9 2013 አንድ የወያኔ አየር ሃይል የእቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ሞቃዲሹ ውስጥ ተከስክሶ ሲጋይ የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃን ነው። ይህም ፎቶ የተነሳው በሮይተርስ ሲሆን በቢቢሲ ድረ ገጽ ላይ ከዜናው ጋር በክብር ታትሞ ይገኛል።
Ethiopian Air Force Jets Attack
አውራምባ ታይምስ ግን ዜናውን እውነት ለማስመሰል ከርክሞ እውነተኛውን ምንጭ ሳይጠቅስ ለታዳሚዎቹ አቅርቧል። በዚህም ጥፋት የሚያሳይ ፎቶ የተደነቁ በርካታ ወያኔዎች “አየር ሃይሉን” በማወደስ አስተያየት ሰንዝረዋል። የካናዳው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ ግን አንዳንድ ሰራተኞቹ የተወሰኑ ማሽኖች ሆን ብለው ማበላሸታቸውን እና ጥገና አድርጎ ስራ መቀጠሉን በይፋ ገልጿል።

ጎንደር ዝምታውን ሰብሯል – የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዋል

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል።Ethiopian soldiers in Barentu
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል  ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ ሰራዊትም ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች አቅንቷል።
ወታደራዊ ልምምዶችና አዳዳስ ምልመላዎችም እየተካሄዱ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።

ህዳሴም ሆነ ዉዳሴ ክህዝብ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም!


pg7-logoከሰሞኑ አገራችን ኢትዮጵያን በተለይም ብሄራዊ ጥቅሟንና ደህንነቷን በተመለከተ ሁለት አቢይ ዜናዎች የአገራቸን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጉዳዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸዉን አገሮች የአየር ሞገደች ተቆጣጥረዉት ነበር። ከእነዚህ ዜናዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ኢትዮጵያ፤ ሱዳንና ግብፅ የህዳሴዉን ግድብ አስመልክቶ ስምምነት ላይ ደረሱ የሚል ዜና ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች የህዳሴዉ ግድብ የሚሰራበት ቦታ ድረስ ሄደዉ ባካሄዱት ጥናት መሠረት የህዳሴዉ ግድብ ፕሮጀክት ባጋጠመዉ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት የተነሳ እንዲዘገይ መወሰኑን የሚያወሳ ዜና ነዉ። አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚሰሩ ምንም አይነት ስራዎችና በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከየትኛዉም አገር መንግስትና መንግስታዊ ካልሆነ ተቋም ጋር ለሚደረጉ ስምምነቶችና ዉሎች ሁሉ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነዉ ብሎ ያምናል፤ ስለሆነም አርበኞች ግንቦት ሰባት የኢትዮጵያን ህዝብ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ከሚመለከቱና በሚስጢር መጠበቅ አለባቸዉ ተብሎ ከሚታመኑ አንዳንድ ጉዳዮች ዉጭ ሌላ ምንም ስራ ወይም አለም አቀፍ ስምምነትና ዉል የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያዉቀዉና ሳይሰማዉ በድብቅ መደረግ የለበትም የሚል የጸና እምነት አለዉ።

በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዙ

ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል።
Ethiopian soldiers ride on an army truck on the road to Afgooye, south of Mogadishu
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል  ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ ሰራዊትም ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች አቅንቷል።
ወታደራዊ ልምምዶችና አዳዳስ ምልመላዎችም እየተካሄዱ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።
ማንነታቸው በውል ያልታወቀ የተቃዋሚ ሃይሎች ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚሊሺያ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር ተፈራን ገድለው  ካመለጡ በሁዋላ፣ እነሱን ለመያዝ መጋቢት 12 አርማጭ ልዩ ቦታው እንኮይ ተራራ ላይ በተደረገ ጦርነት ፣ ከተቃዋሚዎች በኩል ሻምበል ይርዳውና

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለህዝባዊ ሰልፍ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለህዝባዊ ሰልፍ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ ሰልፉ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም ይደረጋል የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ፡፡ ትብብሩ በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ዋና ዋና የሀገሪቱ ከተሞች ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ቀደም ብሎ አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዚህ መሰረት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር መጋቢት 20/2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት ሰልፉን የሚያካሂድባቸው ከተሞች የሚከተሉት ሆነዋል፡፡ እነርስም፡

የጦማርያንና ጋዜጠኞቹ አቤቱታዎች ውድቅ ተደረጉ

ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ሦስቱ ወዳጅ ጋዜጠኞች መጋቢት 15/2007 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡
zone 9 bloggers
መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው ተከሳሾች ባቀረቧቸው ሁለት አቤቱታዎች ላይ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡ በዚህም አንደኛ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ አለኝ ካለው ማስረጃ ዝርዝር ውስጥ 12 የኦዲዮ-ቪዲዮ ሲዲዎች አያይዞ ያቀረበ ቢሆንም፣ ሲዲዎቹ ለተከሳሾች እስካሁን ባለመድረሳቸው ተከሳሾች የቀረበባቸውን ማስረጃ ተመልክተው መልስ ለማዘጋጀት ሲዲዎቹ እንዲሰጧቸው ያቀረቡት አቤቱታ ሲሆን፣ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ 4ኛ ተከሳሽ ማህሌት ፋንታሁን እና 9ኛ ተከሳሽ ኤዶም ካሳዬ በቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር ላይ ከጎብኝዎቻቸው መከልከል ጋር በተያያዘ አቅርበውት በነበረው አቤቱታ ላይ ብይን መስጠት ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱም ሁለቱንም አቤቱታዎች ውድቅ አድርጓል፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ቢፍቱ በሲያትል በስለት ተወግታ ሕይወቷ አለፈ

biftu
(ዘ-ሐበሻ) ስሟ ቢፍቱ ዳዲ ይሰኛል:: የተወለደቸው እዚሁ ሰሜን አሜሪካ ውስጥ ይሁን እንጂ ቤተሰቦቿ ከኢትዮጵያ ናቸው:: እንደ ሲያትልፒ ድረገጽ ገለጻ ከሆነ ቢፍቱ ዳዲ በስለት የተወጋችው ማርች 9 ቀን 2015 ነው::
በሲያትል ዋሊንግፎድ መኖሪያ ሰፈር አካባቢ ገና በ24 ዓመቷ በስለት የተወጋቸውና ሕይወቷ ያለፈው ቢፍቱ ከቆመ መኪና ጀርባ ነው::
የወጡት ዜናዎች እንደሚጠቁሙት ይህች ወጣት እዚያው ሲያትል ዋሽንግተን ውስጥ በስትሪፕ ክለብ (በምሽት ዳንስ ቤት) ትሰራ ነበር::

Sunday, March 22, 2015

የሕወሓት ሰዎች በትግራይ ክልል ለፓርላማ ከመድረክ ዕጩዎች ጋር ይፎካከራሉ

አርከበ ዕቁባይ አይወዳደሩም
299d05d703691f17d2f061a06bf1f93c_Lዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የሕወሓት/ኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ከሆኑት መካከል አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ዶ/ር አድኃነ ኃይለ አድኃናና አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል በተለያዩ ዞኖች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመድረክ ዕጩዎች ጋር እንደሚወዳደሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከድርጅቱና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በዘንድሮ አምስተኛ ዙር ምርጫ አቶ ዓባይ ፀሐዬ በስለኽለኻ (ምዕራብ ዞን)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በብዘት (ምሥራቅ ዞን)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በአላማጣ (ደቡብ ዞን) ሕወሓት/ኢሕአዴግን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአረና ትግራይ (መድረክ) ተወካዮች ጋር ይፎካከራሉ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ባህር ዳር ቅርንጫፍ ቢሮው እንደተዘጋበት አስታወቀ

ሰማያዊ ፓርቲ በባህር ዳር ከተማ የከፈተው ቢሮው በአከራይ ላይ በተፈጸመ ከፍተኛ ወከባና ማስፈራሪያ ምክንያት እንደተዘጋበት በስፍራው የፓርቲው አስተባባሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡
በባህር ዳር የፓርቲው አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ እንደገለጹት ቅርንጫፍ ቢሮው ከትናንት ጀምሮ የፓርቲው ንብረቶች ውስጥ እንዳሉ ተቆልፏል፡፡ አቶ አዲሱ ቢሮውን ያከራዩት ሰው በተደጋጋሚ ከፖሊስ፣ ከኢህአዴግ ካድሬዎችና ከደህንነት ሰዎች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ በመግለጽ ቤቱን እንዲለቁላቸው ሲነግሯቸው እንደነበር አስታውሶ፣ ሆኖም ግን ፓርቲው የአንድ አመት ውል ስላለው መልቀቁን እንዳልፈለገ ገልጹዋል፡፡

ኢህአዴግ ጦረነት አማረኝ የምትለን ነፍሰ ጡር ሆና ወይስ ለኛ ነፍስ ቁብ አጥታ!

ዛሬ እየሰማን ያለነው ዜና እንደሚያስረዳን እና እንደሚያረዳን… ኢህአዴዬ አይኗን ጨፍና ወደ ጦር ሜዳ ልትወስደን አንድ ብላ ጀምራለች። ትላንት ከኢትዮጵያ የተነሱ የጦር አውሮፕላኖች በኤርትራ ጥቃት ፈጽመዋል አሉ። እወነት ይሄ ነገር ለኢህአዴግ ይጠቅማታል… ? ለምርጫ ማስቀየሻ ተብለው የሚተኮሱ አየር ሃይሎⶭ በዛው እንደማይቀየሱ ኢህአዴግ የትኛው አዋቂ ነግሯት ነው ጦርነት የለኮሰችው! እንጃላት…
ኢህአዴግ መስተፋቅር ያሰራችበት ቢኒያም ከበደ (ቤን) እንደነገረን ከሆነ ጦርነቱ የተጀመረበት ምክንያት ያቺ አቶ ኢሳያስ 8100A ብለው ሞልተው ደረሰቻቸው የተባለችው ኢሊኮፍተር ናት አሉ! ያቺ ኢሊኮፍተር ስንት ሰው ታወጣለች…!? ከዚህ በፊት በአንድ ባድመ የተነሳ ስድሳ ሺዎች ተሰውተው ጠብ ያለልን ነገር ምን ነበር… ምንም!!!

ሰበር ዜና በአንድ የኤርትራ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ዲፖ ላይ የደረሰውን የአየር ድብደባ ኢትዮዽያ ኃላፊነቱን መውሰዷን አንድ ከፍተኛ የመከላከያ ኦፊሰር አረጋገጡ።

High ranking Ethiopian military officer confirmed to Awramba Times, on condition of anonymity, that Ethiopian Air Force jets bombarded two key targets inside Eritrea.
According to the official, the airstrikes were conducted separately in two key targets, at a gold mine processing facility, near the capital Asmara and a military depot in Southern AkaleGuzai, Mai Edaga.

የኢትዮጵያ ተዋጊ ጄቶች፤ የኤርትራን የወርቅ ማዕድን ማውጫ፤ ሚሻን በቦንብ ደበደቡ

ኢ.ኤም.ኤፍ) የኤርትራ ኢኮኖሚ ዋልታ እንደሆነ የሚነገርለት፣ በማይ እዳጋ የሚገኘው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ በአየር ተደብድቧል። ተያይዞ የደረሰን ዘገባ እንዳመለከተው ከሆነ፤ የአየር ጥቃቱን ያደረሰው በወያኔ የሚመራው ወታደራዊ ኃይል ሲሆን፤ በጥቃቱም የወርቅ ማውጫው ክፉኛ መጎዳቱን ለማወቅ ችለናል። ከአስመራ 65 ማይል ርቀት ላይ የሚገኘው የወርቅ ማዕድን በአየር መመታቱ ከተሰማ በኋላ፤ በተለይ የአስመራ ነዋሪ ስጋት ላይ ወድቋል። የሰሞኑ የአስመራ ነዋሪዎችም መነጋገሪያ፤ “በመጀመሪያ ደረጃ የአየር ክልላችን ሲጣስ በራዳር ታይቶ፤ በጄቶቹ ላይ ቅጽበታዊ ምላሽ ለምን አልተሰጠም?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ይህንንም ጥያቄ ተከትሎ “እኛስ ምን ዋስትና አለን?” የሚሉ ይገኙበታል።
የኤርትራ ወርቅ ማዕድን የአየር ጥቃት ደረሰበት
ከአንድ ቀን በፊት በኤርትራ እንደሚንቀሳቀስ ይፋ ያደረገ ኃይል፤ በዚሁ የወርቅ ማዕድን ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልጾ፤ በትግርኛ የተጻፈ ወረቀት በከተማው ማሰራጨቱ ይታወሳል። በዚህ በራሪ ወረቀት ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት የኤርትራን አስተዳደር በመቃወም መሆኑን ገልጾ ነበር። የአሁኑም ጥቃት ይህንኑ ተከትሎ የተሰነዘረ ይመስላል።

ሦስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ


22 M
ሦስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ
‹‹ቤተሰቦቻቸው ምግብና ልብስ ማስገባታቸውን ሰምተናል››  ሰማያዊ ፓርቲ
የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ የምክር ቤት አባል የነበረችው ወ/ሪት ኢየሩሳሌም ተስፋውና የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል አቶ ፍቅረ ማርያም አስማማው ትክክለኛ ቀኑ ባይታወቅም፣ ከሁለት ሳምንታት በፊት ድንበር አቋርጠው ኤርትራ በመግባት ግንቦት ሰባትን ሊቀላቀሉ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ፡፡
የፓርቲው አባላት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው የ28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው መሆኑ እየተነገረ ቢሆንም መቼ፣ እንዴትና በማን ተይዘው የትኛው ፍርድ ቤት እንደቀረቡ ሪፖርተር ለማጣራት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ሊከሱ ነው

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ28 ዓመታት ያህል ያስተማሩት ታዋቂው ፖለቲከኛ ዶ/ር መረራ ጉዲና የሥራ ውሌ በሕገወጥ መንገድ ተቋርጧል በማለት ዩኒቨርሲቲውን ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡ 
ዶ/ር መረራ የጡረታ ማራዘሚያ ጥያቄ አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸው እንደነበር አስታውሰው፣ ነገር ግን ከዩኒቨርሲቲው ጋር ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ የኮንትራት ቅጥር ተፈራርመው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ 
‹‹አስተዳደሩ ወደ ታች መውረድ አለበት ተብሎ አዲስ አሠራር ተፈጥሯል፡፡ አሁን መቅጠርም ሆነ ማባረር የሚፈጸመው በኮሌጅ ደረጃ ነው፡፡ የቀጠረኝ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ ነው፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ቅጥሩ አይቻልም ተባልኩ፡፡ ምክንያቱ እስካሁን አልተገለጸልኝም፡፡ ዕድሜ እንዳይባል እኔን ያስተማሩኝ ሰዎች አሁንም እያስተማሩ ነው፤›› በማለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

‹‹ወጣቱ ትውልድ ፖለቲካውን መነገጃ እንዳያደርገው ሥጋት አለኝ››


ዶ/ር መረራ ጉዲና፣  የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ
ዶ/ር መረራ ጉዲና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ናቸው፡፡ ከመድረክ አራት አባል ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበርም ናቸው፡፡
ዶ/ር መረራ በፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያነታቸው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በርካታ የምርምር ሥራዎችን በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ‹‹የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች-ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢሕአዴግ›› በሚል ርዕስ በአማርኛ ቋንቋ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ከዚህ በፊት የሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ማሟያ ጽሑፋቸው ‹‹Ethiopia-Competing Ethnic Nationalisms and the Quest for Democracy, 1960-2000›› በሚል የታተመ ሲሆን፣ ይህንኑ መጠነኛ ማሻሻያ አድርገውበት ‹‹Ethiopia-From Autocracy to Reveolutionary Democracy 1960s - 2011›› በሚል ርዕስ ለአንባቢያን አቅርበውታል፡፡

Saturday, March 21, 2015

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለመጋቢት 20 ህዝባዊ ሰልፍ ጠራ

•ሰልፉ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም ይደረጋል
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ፡፡ ትብብሩ በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ዋና ዋና የሀገሪቱ ከተሞች ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ቀደም ብሎ አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አፋኞች የሚፈሩት የታፈነ ድምፅ በዓለም አደባባዮች ሲደመጥ፤


አፈና በማናቸውም መልኩ በሰብዓውያን ላይ ሲፈፀም የፀያፍ ድርጊቶች ጊዜያዊ ማሰንበቻ እኩይ ተግባር ነው። ይህ ደሞ ለራሱ የመንግስትን ገጽታ በሰጠ ቡድን ሲከወን መጠኑ እጅግ ይከፋል፤ ይገዝፋልም
የሚገለፀውም በተለያዩ ዓይነቶች የግፍ መሥፈርቶች ነው። ግፎቹም ባለብዙ ፈርጆች በመሆናቸው የማይነኩት የኀብረተሰብ ክፍል የለም። በሚፈሩትና በፈቃደኝነት እጃቸውን በሰጡትም ላይ እየቆየ ሲሄድ ትንሽ ሲያንገረሰግሩም ሲፈፀም ይስተዋላል።
ይህ ፀያፍ ተግባር እንደቡድን በህወሓት እንደ አገር እና ሕዝብ ደገሞ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያን ላይ እተፈፀመ ነው። ” ፍርድ ቤት አለ! ግን ዳኛ የለም፣
ሕግ አለ ግን ፍትህ የለም፣
አፈና አለ ግን አስተዳደር የለም፣

ደብረወርቅ የሰማያዊ ፓር ሊቀመንበር የኢ/ር ይልቃል ጌትነት የትውልድ ቦታ መሆኑን ተከትሎ የብአዴን ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ እንደሚገኙ ምንጮች ገለፁ

በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረወርቅ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 136 መምህራን ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓ.ም የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ መምህራን ላይ እየተፈፀመ ያለውን የአስተዳደር በደል ተከትሎ 92 መምህራን ‹‹እኛ በደል እየደረሰብን ቢሆን መምህራን ማህበር ችግራችን እየፈታልን ባለመሆኑ ከአሁን በኋላ አባል እንዳልሆንን እንዲታወቅ፣ በየወሩ ከደመወዛችን እንዳይቆረጥብን›› በሚል ፊርማ አስገብተዋል፡፡ ከመምህራን ማህበር በተጨማሪ በየወሩ ከደመወዛቸው ለአልማ የሚቆረጠው ገንዘብም እንዲቆም መምህራኑ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ሌንጮ ለታ አገር ቤት መግባታቸው ተሰማ

የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ሌንጮ ለታ የስደት ህይወታቸውን ቋጭተው አገር ቤት ስለመግባታቸው እያደመጥን ነው፡፡በዚህ መቼም ደስ የማይሰኝ የአገሬ ልጅ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ደስታውን ሙሉ የማያደርገው በፖለቲካ አመለካከታቸው የተነሳ ብዙዎች አሁንም ከቀያቸው ተፈናቅለው፣አልያም ለእስር ተዳርገው በመገኘታቸው ብቻ ነው፡፡
በዚህች አገር ሁሉም አመለካከቱን እያራመደ መኖር የሚችልበት የፖለቲካ ሰርዓት ባለመፈጠሩ የሌንጮን ወደ አገር ቤት መመለስ እንደ ትንግርት እየቆጠርነው ነው፡፡
ምናልባት የሌንጮ የፖለቲካ ቁመና እንደ ቀድሞው ላይሆን ይችላል፣ጦር መዝዞ የነበረው ኦነግም የተቃዋሚዎች ዕጣ ደርሶት ተሰነጣጥቆ ይሆናል፡፡ሌንጮ ግን ድርጅቱን ለረዥም አመታት በመምራት ትልቅ ስም ገንብቷል፡፡እናም ኦነግ ሲባል ሌንጮ ሌንጮ ሲሰኝ ኦነግ ብቅ ይልብናል፡፡

ሁላችንም ልናቀዉ የሚገባ ወያኔ ሰራሽ ሴራ

የህዝብ መሰረትና ተቀባይነት የሌለዉ ጫካ በቀል የወያኔ ደመኛ ቡድን ከሰሞኑ ማህበራዊ ሚድያዉ ላይ ብሔር ተኮር ዘመቻ ለማካሄድ በርካታ የብሄር ጭምብል የለበሱ ተሳዳቢዎችን እያሰማራ መሆኑ ታዉቋል።
እራሳቸዉን የተለያየ የአማራ ስም በመስጠት፤ ኦሮሞ፣ ትግሬና ሌሎችን ብሄሮች ሆነ ቡድኖች የሚያንኳስሱ የወያኔ ካድረዎች ባህርዳር ሰልጥነዉ በማህበራዊ ድህረ ገጾች በመጠቀም ከፋፋይና ህብረተሰቡን እርስ በእርስ ያሚያጣላና አጽያፊ ተግባሮችን እንዲፈጽሙ ተሰማርተዋል፤ ሌሎችም አሁን በኮተቤ እየሰለጠኑ ይገኛሉ። ሁላችንም ከነዚህ ለወያኔ ጌታ ያደሩ ዉሾች ተግባር ሰለባ በመሆን ያልሆነ ነገር ማድረግ የለብነም።

ምርጫ ማላገጫ መሆኑ ማክተም ይኖርበታል። ምርጫ ያጣ ትውልድ!

SC
ብሶት ወለደኝ የሚለውና ጫካ መወለዱን የማይክደው ህወአት መራሹ የወያኔ መንግስት በምርጫ ተመርጬ ነው አገር የምመራው እያለ በከንቱ ሲመጻደቅ የአንድ ትውልድ ዕድሜ መቆጠሩ ነው። ህገ-መንግስቱ ባማሩ ቃላት ያሸበረቀ ጥራዝ ከመሆኑ ባሻገር ለህዝብ የፈየደው ጆሮ አደንቋሪነቱ ብቻ ነው። በተግባር የማይተርጎም ገዢዎች እንደፈልጉ የሚተረጉሙት ህገ -መንግስት የደብተራ ድግምት ከመሆን አይዘልም። ስልጣን የህዝብ መሆኑን ያላሳየ ስግብግብ ስርአት የነገሰባት አገር በትርጉም አልባ ምርጫ የአገርና የህዝብ ገንዘብና ጉልበት እንዲሁም የማይተካው ወርቃማ ጊዜ ለካድሬዎችና አለቆቻቸው ዕድሜ መቀጠያ እየሆነ የዕውር ድንብር መጓዙ ማክተም ይኖርበታል። አዲሱ ትውልድ የራሱን ዕድል ራሱ የሚወስንበት ጊዜ ዛሬ ነው።አሁን።

ወያኔን በብዕር ሳይሆን በጠብመንጃ

ወያኔ ኢህአዴግ 24 አመታት ሊሞላው እነሆ የሁለት ወራት ገደማ አድሜ ብቻ ቀረው፡፡ by Aseged Tamene
በእነዚ 24 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ከላይ ለተዘረዘረው ችግር ሁሉ ምንጭ የሆነው ወያኔ-ኢህአዴግ በጉልበቱ የቀማውን ሉኣላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን ለማስመለስ ትግል አካሂዷል፡፡ በዚህም ምክንያት እልፍ አዕላፎች ወደ ወህኒ ተግዘዋል፤ በርካቶች የሚወዷት አገራቸውን ጥለው ተሰድደዋል፤ ብዙዎች ከቀያቸውና ቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ ስፍር ቁጥ የሌላቸው አካላቸው ጎድሏል መንፈሳቸው ተመርዟል፤ አለፍ ሲልም ህልቆ መሳፍርቶች ውድ ህይወታቸውን ከፍለዋል…
ከወያኔ-ኢህአዴግ ጋር የተደረጉት ልዩ ልዩ ትግሎች በአብዛኛው በሰላማዊ ትግል ስልቶች ማዕቀፍ ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ብቻ ናቸው፡፡

Friday, March 20, 2015

ወቅታዊና ተገቢ ትግል ወ.ተ.ት.!

ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል።
በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ።

መላው ኢትዮጵያውያን ብሶታቸውን በብር ኖቶች ላይ እየጻፉ እያሰራጩ ነው። – ፎቶዎችን ይመልከቱ

የኢትዮጵያ ህዝበ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ዘዴዎችን በመጠቀምም ለመብቱ መከበር የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል፤ ወጣቶች ብሶቶቻቸውን በብር ኖቶች ላይ ጽፈው ገበያው እንዲያዘዋውራቸው እያደረጉ ነው። ይህም “የወረቀት ገንዘብን ለተሠራበት ዓላማ ብቻ ተጠቀሙ” የሚለውን ህግ በመጣስ ለቅስቀሳ ሥራ መጠቀም በመሆኑ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በርካታ የወረቀት ገንዘቦች በምሬት መግለጫነት ይውላሉ ተብሎ ይገመታል። ምስሎቹ በማህበራዊ መድረኮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጩ ነው።

የምርጫ ክርክር አንድ፡ መድበለ ፓርቲ ሰርዓት እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት- በእኔ ዕይታ! – ግርማ ሠይፉ ማሩ

ተከራካሪ “ፓርቲዎች”
ኢህአዴግ፤ አቶ አሰመላሽ ገ/ስላሴ እና አቶ ሬድዋን ሁሴን (ዋና ተከራካሪ ማን እንደሆነ ባይነገርም ይታወቃል)
አትፓ፤ አቶ አሰፋው ጌታቸው
መድረክ፤ ዶር መረራ ጉዲና
ሰማያዊ፤ አቶ ይልቃል ጌትነት እና አቶ ዮናታን ተሰፋዬ
“አንድነት”፤ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ
ከዚህ በታች የማቀርበው አስተያየት የግል ምልከታዬን ሲሆን፤ ሰዎች በተለያየ አረዳድ ሊኖራቸው እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በዘንድሮ ክርክር አንድ ጥሩ ነገር የውይይት ቅደም ተከተል በተራ እንዲሆን መደረጉ ሲሆን ይህ ኢህአዴግ የተሳሳተ መረጃና መደምደሚያ ሰጥቶ አድማጭ እንዳያደናገር ቢያንስ እድል ፊቷን አዙራበታለች፡፡ የመጨረሻውን መልካም እድል ያገኘው “የድንኩ አንድነት” ተወካይ አቶ ትዕግሰቱ አወሉ ቢሆንም በሙሉ ልብ የሚያከራክር ልዕልና ባለመያዙ ይህን ዕድል አልተጠቀመበትም፡፡ ሁለም ፓርቲዎች ከዋና ተከራካሪ በተጨማሪ አንድ አማካሪ ይዘው የገቡ ሲሆን ከሰማያዊ ፓርቲ በስተቀር ሌሎቹ ዕድል ሳያገኙ ወጥተዋል፡፡ ምክር ስለመስጠታቸውም ተመልካቾች እርግጠኞች አይደለም፡፡

እናቶችን የሚያስለቅስ አገዛዝ – የፍርድ ድቤት ዉሎ (ለገሰ ወልደሃና)

የካቲት 10/2007 ዓም የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀበት የነዘመነ ምህረት ችሎት፣ በቀጠሮው መሠረት፣ ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓም ተሰይሟ። ዘመነ ምህረት፣ መለሰ መንገሻና ሌሎች ወደ 25 የሚጠጉ ወጣቶች በማእከላዊ ፓሊሶች ታጅበው 8:ሰአት 20 አካባቢ ፍርድ ቤት ግቢ ገቡ። እንደተለመደው በርቀት እጃቻችንን በማውለብለብ ሰላም አልናቸው። እነሱም ባልታሰረው እጃቸው አፀፋውን መለሱልን።
ዘመነ ምህረት ብዙም አልተጎሳቆለም። መለሰ መንገሻ ግን በጣም ከስቷል። ሰውነቱ ቢጫ ሆኗል። እንደዛም ሆኖ ፈገግታ ግን አልተለያቸው። ችሎት ከመግባታቸው በፊት የተቀመጡበት አግዳሚ ወንበር ላይ ሆነው፣ በምልክት ለመነጋገር ሞክረን ለመግባባት ችለን ነበር። ነገር ግን ፓሊሶች ከኛ ጋር የሚያደርጉት የምልክት መግባባት አይተው፣ ፊታቸውን አዙረው አስቀመጧቸው ። ተስፋ ሳንቆርጥ ሞከርን። አልተሳካም።

የሚሊዮኖች ድምጽ – መደመጥ ያለበት ክርክር በመድበለ ፓርቲ ዙሪያ – ክፍል 1 እና ክፍል 2

“ኢሕአዴግ አርጅቷል። የሐሳብ ድርቀት ደርሶበታል” ኢንጂነር ይልቃል
“ለኢትይጵጵያ ሕዝብ ጥልቅ ፍቅር አለን። ፣ ትልቅ አክብሮትት አለን”
ኢንጂነር ይልቃል
“ኢሕአዴግ የአሁኑ ትዉል የሚመጥን አይደለም”
አቶ ዮናታን ተስፋዬ
“በኢሕአዴግ ክራይቴሪያ ማግኘት ይሻላል፣ በአካዳሚክ ከማግኘት እየተባለ ነው “
“የካቢኔ የካድሬ ወንድምና እህቶች የጠለበ ሥራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ድንጋይ ነው የሚፈልጡት!
ዶር መራራ ጉዲና
ዶር መራራ መልእክት ለኢትዮጵይ ሕዝብ “የኢሕአደግ መሪዎች ሰበካ በቀን ሶስት ጊዜ እናበላሃለን እያሉ፣ ግን በቀን ሶስት ጊዜ እንደምታበላ አንተም ታውቃዋለህ።ኢሕአዴግ አንተን እያሳለፍኩልህ ነው እያለ ማንን እያበለጸገ እንዳለ አንተም ታውቀዋልህ። በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ጥረህ ግረህ ያስተማርካቸው ወጣቶች ዛሬ ምን እንደሚሰሩ አንተም ታውቀዋለህ። የካድሬዎችን የካቢኔዎች ልጆች ዛሬ እንዴት እንዳለፈላቸው አንተም ታወቀዋለህ። ኢሕአዴግ መንግስት ነጋዴም በሆነበት ስርዓት በየአመቱ ያለ አግባብ ግብር እየተጫነብህ፣ የማዳበሪይ እዳ እየተጫነበህ፣ እንደሚገኝ አንተም ታወቀዋለህ። ……… ታሪክ ሥራ”

ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው! በፍቅር

‹‹ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!›› በሚለው በዚህ የሰውን ክብርና ልእልና ከፍ ባደረገው ፍቅር፣ ሰብአዊነትና ርኅራኄ ልባቸው የተሸነፈ የመቄዶንያ መስራች ከሆነው ከአቶ ብንያም ጀምሮ በበጎ ፈቃደኝነት በማዕከሉ ውስጥ እያገለገሉ ያሉ ወገኖቻችን በየጎዳናው ላይ የወደቁ፣ እርጅና ተጫጭኖአቸው፣ ጉልበትና ጊዜ ከድቶአቸው፣ በመጦሪያቸው ዘመን የቀኑ ሐሩር የሌሊቱ ቁር እየተፈራረቀባቸው፣ አምስትና አስር ሳንቲም ፍለጋ የእኛን እጅ የሚጠባበቁ፣ መውደቂያና መጠጊያ የሌላቸውን ወገኖችን ሰብስበው ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ እፎይ እንዲሉ እያደረጉ ነው፡፡

በትግል ሒደት የሚከሰቱ እንቅፋቶችን በጥንካሬ ልናልፋቸው ያስፈልጋል:: – ‎ምንሊክ ሳልሳዊ‬

ኢትዮጵያውያን ለውጥ እንፈልጋለን:: ለውጥ እንፈልጋለን ብለን ለትግል ስንነሳ መንገድ ሁሉ አልጋ በአልጋ ይሆንልናል ማለት አይደለም::በትግሉ ውስጥ የሚከሰቱ እሾህ እና አሜኬላዎች እንቅፋት ሆነው ከስንዴው እኩል እንደ እሸት የሚያብቡ እንክርዳዶች እየሰረጉ በመግባት ትግሉን ለማኮላሸት አሊያም ደሞ ተያይዘው ለመጥፋት በሚያሴሩት ደባ የህዝብ ልጆች በሚያደርጉት ተጋድሎ እነዚህን እንቅፋቶች ማስወገድ እና በጥንካሬ ጋሬጣውን ማለፍ የሚጠበቅበት ወቅታዊ አጋጣሚዎች ሳንዘናጋ ልንጠቀምበት ይገባል:: በትግል ጊዜ የሚከሰቱ እንቅፋቶች ለነገ ትልቅ ትምህርት የሚሆኑ ወርቃማ ጊዜያት አድርገን ልንማርባቸው ይገባል::

United Ethiopian Muslims Peaceful Movement Support Group የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት

 በመስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ህወሃት የዘረጋውን የጥላቻና የበቀል ዘመቻ ለመከላከል የወጣ የአቋም መግለጫ የኢትዮጵያውያን ሙሰሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት ሰሜን አሜሪካ March 19, 2015
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የተጣሰውን ህገመንግስታዊ መብት በህግ ለማስከበር የጀመሩት ሰላማዊ ትግል ድፍን ሶስት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህ ትግል በመላው አለም ሰላማዊ ትግልን መታገል ለሚሹ አርአያ ከመሆኑም ባሻገር በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት እውቅናን ያገኘም ነው፡፡ በነዚህ መራራ ሶስት የትግል አመታት ህዝቡ በፊርማው የመረጣቸው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የእስር ብቻ ሳይሆን የድብደባ፣ የግርፋት፣ የማዋረድ፣ የሰብዓዊ መብትም መገፈፍ ሰለባ ሆነዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሲታሰሩ፣ ሲገረፉ፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ደግሞ ለመሰደድ በቅተዋል፡፡ሰላማዊ ዜጎች በግፍ ጥይት እየተደበደቡ ለሞት መዳረጋቸው ሊካድ የማይችል የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

Thursday, March 19, 2015

(የሳዑዲ ጉዳይ)… ለሃጅ ጸሎት መጥቶ ሳውዲ የቀረው ገበሬ እንግልት … (ነብዩ ሲራክ)

(ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ)
የማለዳ ወግ
ወንድም ራያ ጀማ የ5 ወንድ እና የ3 ሴት ልጆች ጎልማሳ አባት ነው። ወደ ሳውዲ የመጣው ድህነት ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የፖለቲካው ሙቀት አለያም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ገፍቶት አይደለም ። ሳውዲ የመጣው ፣ በእስልምና እምነቱ በሚያዘው መሰረት በህይወት ዘመኑ የሚጠበቅበትን ለማድረግ ከብቶቹን ሽጦ የሃጅ ጸሎት ለማድረግ ነበር … ዳሩ ግና የጅማው ገበሬ ራያው ጀማል እንደ ቀሩት ጓደኞቹ ጸሎቱን አድርጎ ለመመለስ አልቀናውም! ከሀጃጅ ጓደኞቹ ተለይቶ ከቤተሰብ እንደራቀ እዚህ ላለፉት ሁለት አመት ከመንፈቅ ገደማ ሳውዲ በእንግልት ጊዜውን ሊገፋ ግድ ብሎታል ። ምክንያቱም የሃጅ ጸሎቱን ከውኖ መካ ውስጥ መኪና አደጋ ደረሰበትና ነው !
raya jema
የራያ ጀማል ጉዳት …
ራያ ጀማል በደረሰበት የመኪና ግጭት የተለያየ የአካሉ ክፍል በጠና ስለተጎዳ በከፍተኛ ህክምና መካ ውስጥ ለሁለት አመት ተኩል ገደማ በሳውዲ የመንግስት ሆስፒታል ሲረዳ ቆይቷል። የመጓጓዣ የማረፊያና የኢንሹራንስ እስከ 55 ሽህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ከፍሏቸው ለጸሎት ያማጡት የሃጅ ኮሚቴዎችም ሆኑ የጅዳ ቆንስል ራያ ጀማልን ሊረዱት ቀርቶ ሊያዩት አልቻሉም! ይህ የሆነው ስለ ራያ ጀማል መረጃ ስላልነበራቸው አይመስለኝም ፣ ይህን ስል መረጃው እንደነበራቸው እኔም መረጃ አለኝና ነው!
ለሃጅ ጸሎት መጥቶ ስለደረሰበት የመኪና አደጋ በያዝነው ሳምንት የ50 ኢዩቬልዩ በአሉን ባከበረው የጀርመን ራዲዮ ዜናውን አቅርበነው ነበርና የቆንስሉ ም የሃጅ ኮሚቴ ኃላፊዎች ያውቃሉ ! ከዚህ ሁሉ በኋላም ልክ የዛሬ አንድ አመት ገደማ የጅዳ ቆንስል ተወካይ ራያ ጀማል በነበረበት የሽሻ ሆስፒታል ለሌላ ጉዳይ ሄደው አግኝተውትም እንደነበር ተገፊው ወንድም አጫውቶኛል ።

በአርበኞች ግንቦት 7 – ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ!

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል።
በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ።

ለምን ዝም እንላለን ??

የዘር ፖለቲካ ቡድነኝነት ነው:: በግለሰቦች ነጻነት ሞት ላይ የቆመ የጋርዮሽ ፖለቲካ ነው:: አንዱም ከመንጋው ክፉን ቢያስተውል በግሉ እንዳይናገር የጋርዮሽ ፖለቲካው መብቱን ይነፍገዋል:: መለስ "በማእከላዊው ኮሚቴ እንጂ በራሴ ፍላጎት ስልጣኔን መልቀቅ አልችልም" ሲል የተጋነነ ቢሆንም በባህሪው ግን እውነት ነው:: በፓርላማ ተቃውመህ እጅህን ብታወጣ ከመንጋው እንደተለየህ እወቅ::
ወደ ቁምነገሩ ልመለስ!!
"ተስፋዬ ገ/አብ (ገዳ ገ/አብን) የነካ እኛን እንደነካ ይወቀው" ብለው ነበር በሞጋሳ ስርአት የኦሮሞን ማንነት ሲቀበል:: ጥልቅ ፍልስፍናውን ባላገኝውም ሊብራል ነኝ ብዬ አምናለሁ.... እናም ከት ብዬ ሳኩ (ትዝ ይለኛል የሰማሁ ለት የሳኩት ሳቅ) ተስፋዬ ሲነካ ምን?? ወይ የጋርዮሽ ፖለቲካ... ይህ ሊብራል ለሆነ ዜጋምን ማለት ነው? አንድን ግለሰብ በመናገር ማህበረሰብን መናገር ነው ብሎ የመናገር/የመውቀስ ነጻነቱ ላይ መደራደር??

የኢትዮጵያ የ “ዲፕሎማቶች ቁንጮ” መሳለቅያ ቅጥፈት፣ -ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

የወባ ትንኝ ተመራማሪ የሆነ ሰው ስለዲፕሎማሲ ጥበብ እና ሳይንስ ምንድን ሊያውቅ ይችላል? ወይም ደግሞ እውነትን በመናገር እና ውሸትን በመናገር መካከል ያለው ልዩነት ምን ያውቃል? ወይም ደግሞ የለየለት ቅጥፈትን አምኖ በመቀበል እና ቅጥፈትን  በማውገዝ መካከል ያለውን  ልዩነት ምን ያውቃል? እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ያለምክንያት አላነሰዋቸሁም፡፡
ቴዎድሮስ አድኃኖም በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር new፡፡ ይፋ በሆነው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሕይወት ታሪክ አድኃኖም “ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላው የወባ ትንኝ ተመራማሪ” መሆኑን ተገልጿል፡፡ አድኃኖም ከለንደን የጤና አጠባበቅ እና ትሮፒካል ህክምና ትምህርት ቤት/London School of Hygiene & Tropical Medicine የሰው ልጅ ሰውነት በሽታዎችን በመቋቋም ችሎታዎች/immunology ላይ ጥናት በሚያደርገው የተላላፊ በሽታዎች የህክምና ሙያ ላይ የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም ለንደን ከሚገኘው ከኖቲንግሀም ዩኒቨርስቲ እ.ኤ.አ በ2000 በህብረተሰብ ጤና/community health የዶክትሪት ዲግሪ ተቀብለዋል እየተባለ ይነገርለታል ፡፡