Tuesday, March 24, 2015

የአባይ ግድብ በግብጽ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ መገንባቱ ወያኔ ምን ያህል አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባ ያሳያል::

Image
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የአባይም ግድብ እንደ ባድመ ድል ለጭፈራ አቀባብሎ እንዳይሰጠን .. መቸም ወያኔ በሰው መቀለድ ለምዷል::የአባይ ቦንድ የገዛህ የገዛሽ ሁሉ ነገሮች ሁሉ ባዶ ጭብጨባ ሆነዋል:: ለሕዝብ የማይጨነቀው ወያኔ በኢኮኖሚ ከደቀቀው የመንግስት ሰራተኘው ጀምሮ እስከ ጎንበስ ቀና ብሎ ደክሞ እስከሚሰራው ምስኪን ኢትዮጵያዊ ድረስ በአባይ ቦንድ ስም ከፍተኛ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቷል::በውጪዉም አለም ቦንድ ለመሸጥ ቢዘምትም ሳይሳካለት ቀርቷል::ሻእቢያ እና በአከባቢው ያሉ ጉዳዮች ወያኔን ውጥረት ውስጥ ጨምረውታል::ይህ የትግሉ አንድ አካል የሆነ የድል ጥርጊያ መንገድ ለፖለቲካ ድል ልንጠቀምበት ይገባል::የአባይ ግድብ ትከትሎ የመልስን መሞት አስታኮ ግለሰቡን አባይን የደፈረ መሪ በማለት እስከማላዘን ተደርሷል::የቅርብ ጊዜ ታሪክ እንደሚያሳየን ከሆነ የኢትዮጵያ የመጨረሻእ ንጉስ ሃይለስላሴ አባይን ለመገደን ይህንኑ የግድብ ዲዛይን አሰርተው ነው ዲዛይኑ በገንዘብ ኖቶች ላይ ሳይቀር ታትሟል; በጊዜው..ወያኔ ያንን ዲዛይን በዘመናዊ መሃንዲሶች አሻሻለው እንጂ አዲስ ነገር አልፈጠረም::



አሁን እየሰማንው ያለነው ደሞ አባይ የሚገደበው ሱዳን እና ግብጽ በፈለጉት መንገድ መሆኑ እየተነገረን ነው:: አስቀድመን እንደተናገርነው የህዝብ መብቶች ሳይረጋገጡ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሳይገደቡ ህዝብን በግዳጅ ከጉሮሮው በቦንድ ስም እየነጠቁ ሕዝብ ያተዋጠለትን ሕዝብን ያላሳተፈ ግድብ እገነባለሁ ብሎ መነሳት ከባት የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል ይህንንም ኪሳራ እያየነው ነው::ወያኔ ከሱ በላይ አዋቂ እና ከሱ በላይ ልሃገር ለህዝብ ጠበቃ የልማት ቡድን አድርጎ ቢንጠራራም ራሷን ከፍ ከፍ ያደረገች ማሽላ አንድም ለወንጭፍ አንድም ለውፍ .. የሚለውን ያስታውሰናል::

ወያኔ የሰበሰበው ቦንድ ለንግድ ድርጅቶቹ ካፒታል ማሳደጊያ ካደረገው በኋላ እየተሰራ ያለው ስራ ሁሉ በእኩይነት የተከበበ ከመሆኑም ባሻገር በውስጡ ያለውን መፈረካከስ ሙስና እና የፓርቲ ካድሬዎች መበስበስ እንዲሁም የተቃዋሚው ጎራ መጠናከር በጣም ስላሰጋው በተጨማሪም የኤርትራ ጋር ያለው አለመግባባት እየሰፋ መምጣቱ በአባይ ግድብ ላይ ያለው ልፍስፍስ አቋሙ የባሰ ሽባ በመሆኑ እጁን ለግብጽ እና ሱዳን እንዲሰጥ ተገዷል::ከኤርትራ ጋር ጦርነት ብንገጥም ሱዳን እና ግብጽ በተዝዋዋሪ ሊያጠቁን ይችላሉ የሚለው የወያኔ ጭንቀት እንዲሁም ለአባይ ግድብ ያሰበው ሁሉ ሳይሳካ በባዶ ስላስቀረው በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የገነባው ኢኮኖሚም በባዶ ካዝና ስለቀረ መጣፊያው ያጠረው ወያኔ አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ የአባይን ግድብ ለግብጽ እና ሱዳን አስረክቧል::አሁንም የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ከአባይ ግድብ በፊት የሰብአዊ መብት ጥሰት ይገደብ::የሰባዊ መብት እና የህዝቦች ነጻነት ባሌለበት አገር በልማት ስም ራስን መቆለል እንደምናየው ውርደቱ በአደባባይ ያጋልጣል::ኢትዮጵያውያን ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን በወያኔ መቃብር ላይ ነጻነታችንን ማረጋገጥ አለብን::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment