Tuesday, March 31, 2015

ቆራጥ ጀግና ማነው? (ወለላዬ ከስዊድን)

አንድነት ይፈጠር – ሀገር ነጻ ትውጣ
ንብረትም ይቅርብኝ – ምንም ነገር ልጣ
ዳሩ መሀል ሳይሆን – ድንበሩ ተደፍሮ
ርቱዕ አንደበት – እንዳይቀር ተቀብሮ
ጋዜጠኝነትም – እንዲኖር ተከብሮ

ቸነፈር ረሀብ – ሙቀቱን ሳይፈራ
ውሎ የከረመ – ከታጋዮች ጋራ
ጽናቱ ጠንካራ – ወገኑን የሚወድ
ጌትነት የጠላ – ጭቆናን ለመናድ
ነጻነት ናፋቂ – በደል የመረረው
ውነተኛ ታጋይ – ቆራጥ ጀግና ማነው?

No comments:

Post a Comment