Saturday, March 21, 2015

ሁላችንም ልናቀዉ የሚገባ ወያኔ ሰራሽ ሴራ

የህዝብ መሰረትና ተቀባይነት የሌለዉ ጫካ በቀል የወያኔ ደመኛ ቡድን ከሰሞኑ ማህበራዊ ሚድያዉ ላይ ብሔር ተኮር ዘመቻ ለማካሄድ በርካታ የብሄር ጭምብል የለበሱ ተሳዳቢዎችን እያሰማራ መሆኑ ታዉቋል።
እራሳቸዉን የተለያየ የአማራ ስም በመስጠት፤ ኦሮሞ፣ ትግሬና ሌሎችን ብሄሮች ሆነ ቡድኖች የሚያንኳስሱ የወያኔ ካድረዎች ባህርዳር ሰልጥነዉ በማህበራዊ ድህረ ገጾች በመጠቀም ከፋፋይና ህብረተሰቡን እርስ በእርስ ያሚያጣላና አጽያፊ ተግባሮችን እንዲፈጽሙ ተሰማርተዋል፤ ሌሎችም አሁን በኮተቤ እየሰለጠኑ ይገኛሉ። ሁላችንም ከነዚህ ለወያኔ ጌታ ያደሩ ዉሾች ተግባር ሰለባ በመሆን ያልሆነ ነገር ማድረግ የለብነም።

ወያኔ ስልጣን የሚቆየዉ የኢትዮጵያን ህዝብ መከፋፈልና እርስ በእርሱ ማነካከስ እስከቻለ ድረስ ነዉ፤ ለዚህም ነዉ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ተመድቦላቸዉ እነዚህ ጌታ አደር ዉሾች አጽያፊ ነገር የሚሰሩት፣ሁላችን እነዚህን ዉሾች ማባረርና አይናችሁን ላፈር ማለት አለብን።
የማህበራዊ ሚድያ ድረገጾች ተጠቃሚዉን በተለይም የወጣቱን ቀልብ የሚስብና ሚዛናዊ የሆነ መረጃ የሚያገኝበት ብቸኛ መንገድ ከመሆኑም በላይ ለህሊናቸዉ ያደሩ ካድሬዎቹም እዉነታን በመገንዘብ እየኮበለሉበት በመሆኑ “የጨነቀዉ እርጉዝ ያገባል” እንዲሉ ወያኔ ሆድ አደር ተሳዳቢዎችን በይፋ በማሰልጠን ግብዓት አሟልቶ በማህበራዊ ሚድያዉ ማስረጉ ይህ የበከተ ተልካሻ ስርዓት በኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጆች ይፋዊ ፀረ ወያኔ አቋም ወደ ማይቀርለት ዉድቀቱ መቃረቡን ያሳያል።

ስለዚህ ለዚህ የወያኔ ደባ እምቢ በማለት ለአስነዋሪ ስራው ድጋፍ በመንፈግ አንድነታችንን ማስጠበቅና ለተተኪው ትውልድ ማስረከብ ይጠበቅብናል ለዚህም የወያኔን ስርሃት ከስሩ ነቅሎ መጣል የሁላችን ግዴታ ነው

No comments:

Post a Comment