Saturday, March 21, 2015

የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ሌንጮ ለታ አገር ቤት መግባታቸው ተሰማ

የኦነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ሌንጮ ለታ የስደት ህይወታቸውን ቋጭተው አገር ቤት ስለመግባታቸው እያደመጥን ነው፡፡በዚህ መቼም ደስ የማይሰኝ የአገሬ ልጅ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ደስታውን ሙሉ የማያደርገው በፖለቲካ አመለካከታቸው የተነሳ ብዙዎች አሁንም ከቀያቸው ተፈናቅለው፣አልያም ለእስር ተዳርገው በመገኘታቸው ብቻ ነው፡፡
በዚህች አገር ሁሉም አመለካከቱን እያራመደ መኖር የሚችልበት የፖለቲካ ሰርዓት ባለመፈጠሩ የሌንጮን ወደ አገር ቤት መመለስ እንደ ትንግርት እየቆጠርነው ነው፡፡
ምናልባት የሌንጮ የፖለቲካ ቁመና እንደ ቀድሞው ላይሆን ይችላል፣ጦር መዝዞ የነበረው ኦነግም የተቃዋሚዎች ዕጣ ደርሶት ተሰነጣጥቆ ይሆናል፡፡ሌንጮ ግን ድርጅቱን ለረዥም አመታት በመምራት ትልቅ ስም ገንብቷል፡፡እናም ኦነግ ሲባል ሌንጮ ሌንጮ ሲሰኝ ኦነግ ብቅ ይልብናል፡፡

የሌንጮ ኦነግ በዘመነ የሽግግር መንግስት በአሩሲ፣በአርባ ጉጉና በበደኖ ዘር ተኮር የሆነ ጥቃት በማድረስ ብዙዎችን ለህልፈተ ህይወት ስለመዳረጉ በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው የቀድሞው ኢቴቪ መዘገቡ አይዘነጋም፡፡የኦነግ አመራር በበኩሉ ከአገር ከወጣ በኋላ ባወጣቸው መግለጫዎች ለጭፍጨፋው ተጠያቂ መሆን የሚገባው የህወሓት ኦህዴድ ስለ መሆኑ ተናግሯል፡፡
የተፈጸመው ጭፍጨፋ አለም አቀፍ ወንጀል በመሆኑና በጊዜ ይርጋ ስለማይታገድ ዛሬም ለመናገር አልረፈደም፡፡በጭፍጨፋው ወላጆቻቸውን፣የትዳር አጋሮቸቸውን፣ልጆቻቸውን በግፍ የተነጠቁ ዜጎች በመኖራቸው ሌንጮ የሚሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ትርጉም እንደሚኖረው ይሰማኛል፡፡
ምናልባት ከመስኮት በስተጀርባ በተደረገ ድርድር ይህ ጉዳይ እንደማይነሳ ስምምነት ተደርሶ ወደ አገር እንዲገቡ መደረጋቸውን መጠርጠር ባይከፋም ክቡር የሆነውን የሰውን ህይወት ስላጠፋ ክስተት አለመነጋገር የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት ከመርገጥ አይተናነስም ፡፡
ሌንጮ ይመሩት የነበረው ድርጅት ድርጊቱን አለመፈጸሙን እንደ ቀድሞው መመስከር ቢችሉ ይህንን የማስረዳት ሸክም በህወሓትና ኦህዴድ ላይ ይወድቃል፡፡ኦነግ በእርግጥ ድርጊቱን ፈጽሞ ከነበረም የድርጅቱ ሊቀ መንበር ኦቦ ሌንጮ የእጁን ማግኘት ይኖርበታል፡፡
———- ያው ትምክህተኞች ፣አማራዎች የጻፉት በሉና ስም አውጡለት ———-
"ኦቦ ሌንጮና ያልተወራረደው ሂሳብ

----------        ያው ትምክህተኞች ፣አማራዎች የጻፉት በሉና ስም አውጡለት ----------"ዳዊት ሰለሞን

No comments:

Post a Comment