(ነገረ ኢትዮጵያ) በደቡብ ክልል በምርጫ አስፈፃሚነት የተመደቡ ግለሰቦች የዴኢህዴን አባላት እንደሆኑ ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ በላኳቸው ሰነዶች አረጋገጡ፡፡ ለአብነት ያህልም አረካ ከተማ የምርጫ ክልል በአስፈጻሚነት እየሰሩ ከሚገኙትን አቶ ግዛው ቴማ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባል መሆናቸው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ የተላኩት ሰነዶች ያሳያሉ፡፡ አቶ ግዛው ለፓርቲያቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) በነሃሴ ወር 2006 12 ብር ከ87 ሳንቲም፣ እንዲሁም በ2007 መስከረምና ጥቅምት የሁለት ወር 25 ብር ከ74 ሳንቲም መዋጮ የከፈሉበት ደረሰኝ የደኢህዴን አባልነታቸውን ያረጋግጣል፡፡

በቀን 07/05/ 2007 ዓ.ም ወ/ሮ መሰለች በ173ኛ እና 147ኛ ቁጥር፣ እንዲሁም ባለቤታቸው አቶ ህዝቁኤል ቱጫ ቱፋ በተመሳሳይ ቀን 172ኛ እና 151ኛ ተራ ቁጥር ላይ ተመዝግበው ሁለት ሁለት የምርጫ ካርዶችን እንዲወስዱ ተደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ነዋሪዎች መምረጥ ለማይችሉት የቤተሰብ አባላት ጭምር ‹‹ካርድ ውሰዱላቸው›› እየተባሉ በአንድ ሰው በርከት ያለ ካርድ መውጣቱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡
No comments:
Post a Comment