Tuesday, March 24, 2015

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ቢፍቱ በሲያትል በስለት ተወግታ ሕይወቷ አለፈ

biftu
(ዘ-ሐበሻ) ስሟ ቢፍቱ ዳዲ ይሰኛል:: የተወለደቸው እዚሁ ሰሜን አሜሪካ ውስጥ ይሁን እንጂ ቤተሰቦቿ ከኢትዮጵያ ናቸው:: እንደ ሲያትልፒ ድረገጽ ገለጻ ከሆነ ቢፍቱ ዳዲ በስለት የተወጋችው ማርች 9 ቀን 2015 ነው::
በሲያትል ዋሊንግፎድ መኖሪያ ሰፈር አካባቢ ገና በ24 ዓመቷ በስለት የተወጋቸውና ሕይወቷ ያለፈው ቢፍቱ ከቆመ መኪና ጀርባ ነው::
የወጡት ዜናዎች እንደሚጠቁሙት ይህች ወጣት እዚያው ሲያትል ዋሽንግተን ውስጥ በስትሪፕ ክለብ (በምሽት ዳንስ ቤት) ትሰራ ነበር::

የኪንግ ካውንቲ ፖሊስ የጠረጠረው የቢፍቱ ገዳይ ነው የተባለው ተከሳሽ ሪቻርድስ ቢፍቱን ከመግደሉ በፊት በምትሰራበት ስትሪፕ ክለብ (የምሽት ዳንስ ቤት) አካባቢ ሲጨቃጨቁ ነበር ብሏል:: የሚያውቋት ሰዎች ለፖሊስ እንደገለጹት ቢፍቱ ወደ ሥራዋ ዳንስ ቤት በምትሄድበት ወቅት ብዙ ጊዜ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ትወስድ ነበር::
ፖሊስ ከሪቻርድ ጋር ትጨቃጨቅ እንጂ በምን ምክንያት ሊገድላት እንደቻለ የሰጠው መግለጫ የለም:: ለሟች ነብስ ይማር እንላለን::

No comments:

Post a Comment