Monday, October 1, 2012

ኃይለማሪያም ደሳለኝን ተስፋ አታድርጉ




ኃይለማሪያም ወይም ኃይለ ወያኔ ክፍት ወንበር ላይ ቂጢጥ ማለቱ አይገርመንም:: ድሮም
አውታንቲ ሾፌር ይሆናል  :: ግን መኪናውም መንገዱም ያው ነው :: ምኑ ላይ ነው
ዓሥራትነቱ ወይም ተስፋነቱ ?  እስቲ  እንግዲህ እንዴት እንደሚያፋድስ  እናየዋለን::
ዘንድሮ ጉድ እኮ ነው ! የአገር ቤቱ አዘንተኛ ሲገርመን ለካስ በተቃዋሚው ሰፈርም ነጠላ
ያዘቀዘቁ ነበሩ :: አገር የማዳኑ ጉዳይ  ቀረና እንታረቅ፤  እንቻቻል ሆነ ለቅሶው ።

ኃይለማሪያምን  እንደ ኃይለ እየሱስ  አርገው ቤዛችን_መድሃኒታችን ነው እያሉም አሸረገዱ ::
ገልጃጃው ችኩሉ ምሁር ዓለማየሁ ገ/ማሪያም ደግሞ አዲስ ጠ/ሚኒስትር  አዲስ ዓመት
በማለት ኃይለማሪያምን ፈገግ በል እያለ ይመክራል :: አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ
ታሸታለች ይባላል !
ኃይለማሪያም የወያኔ  ሸፋን የሆነ መጋረጃ  ወያኔ ነው :: ነገር ግን የወያኔን ትዕቢት
የሚያንፀባርቅ መልክ የለውም:: ለሚያየው ስው እንደ መለስ በትዕቢት የሚያስብና የሚሰራ
አይመስልም:; ሞኛ ሞኝ ገጽታው፦ጴንጤቆስጤነቱና አናሳነቱ ብዙ ነገሮችን ሸፍነውለት
ለሚመለከተው ሰው ሁሉ ነሁላላ መስሎ ይታያል:: እውነተኛው ኃይለማሪያም ግን ከዚህ
በስተጀርባ ያለው በመለስ ክሎን የተደረገ ገፅታ ነው ::
እውነተኛው ኃይለማሪያም ከትግራይ ያልበቀለና በሕውሓት የታቀፈ ስንግ ወያኔ ነው :: የልቡ
ሀሳብና ምኞቱ ሁሉ ከወያኔ ጋር ልክክ ብሎ አንድ የሆነ  ክፉና መሰሪ ነው :: መለስ
የመረጠውና  ያቀፈው  በዚህ ተገዥ ባህሪውና ሰውነቱ ነው ::
በክርስትና እምነቱ ወደ አምላኩ የቀረበና የእግዚአብሔርን ሞገስና ምህረት ያገኘ ሰው
እንዳይመስላችሁ ::
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ጌታን ከተቀበላችሁ በኃላ ተለዪና ለብቻችሁ ሆናችሁ የሥጋን ነገሮች
ከድታችሁ በመንፈስ  በመመላለስ  በጎ ሥራ ሥሩ ነው የሚለው :: ኃይለማሪያም ግን ኃይለ
ወያኔ በመሆኑ ጌታን ከተቀበለ በኃላ እንደ ውሻ ወደ ትፋቱ ተመልሶ እንደ አሳማ ጭቃ ላይ
እየተንደባለለ ወያኔን ሲያመልክና ሲያገለግል የኖረና ያለ መናፍቅ ነው ::
በድርጊቱ ከወያኔ ፀረ_ ኢትዮጵያ  እቶንና ፀረ_ ሕዝብ በደል የፀዳ ፦ከዝርፊያና ከቅሚያ
የራቀ:  በሃሰት የማይምልና የተፀፀተ እንዳይመሳላችሁ :: ለግለሰብ መለስና ለወያኔ የቆመ
እንጂ ለአገርና ለሕዝብ ወዳጅም አይደለም::
መለስ በእሱና በተቃዋሚዎች መካካል ተክሎት ያለፈውን ጠላትነትና አገር ያፈረሰ ራዕይ
ለመቀጠል ኃይለማሪያም ቃል ስለገባ ሰው ያስፈጃል ተብሎ ነው የሚፈራው ::
ኃይለማሪያም  እንደ አህያ ፈሪ ስለሆነ ከያዘ አይለቅም ነው የሚባለው፡: መቆራረጥና
መዘልዘል ሳይሆን በጥርሱ መንጨት ነው የሚቀለውና  እንዳይነጭህ በጊዜ ነቅቶ መታገል
ብቻ ነው የሚያዋጣው ::
ኃይለማሪያም የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ባለቤት ባለመሆኑ አቀማመጡ ሁሉ ዘራፍ ለማለት
ይመስላል እያሉ ሱዳኖችና ግብጾች የቡና መጠጫ አድርገው እየዶለቱበት  ነው ::
ኃይለማሪያም_ዘመም የሆናችሁ ሁሉ ተስፋ ዘርታችሁ ከሆነ ኃላ ሰደድ ሆኖ የሚያጠፋችሁን
ገለባ እንዳታፍሱ ከመቁነጥነጥና  ከመቁለጭለጭ መቆጠቡ ይበጃል ::
ከሕዝብ ትግል ጋር ተስፋና የተስፋ ምንጭ አሀዱ አምላክ ብቻ ነው :: ከዚህ ውጭ ተስፋና
መመኪያ ፈፅሞ የለም::
ኃይለማሪያምን ትተህ
ከሕዝብ ጋር ዘብ ቁም !!
                                              ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር !!!

No comments:

Post a Comment