Thursday, October 4, 2012

እውነት ይነገር! ውሸት ይቁም!




የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ዜና
ረፍትን ተከትሎ የታክስ ከፋዩ ሕዝብ ንብረት በሆነው
የመንግሥት ብዙሃን መገናኛ የሚነገሩትን የፕሮፓጋንዳ
ውርጅብኝ እየተከታተልን ነው፡፡ ኢትዮጵያን የምድር ገነት
የማስመሰሉ ጥረት የተሳካላቸው የሚመስላቸው ካሉ
ተሳስተዋል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን አገራችንን እየኖርንባት
ነው፡፡ የምናውቃት ነች፡፡ ከውጭ አገር አልመጣንም፡፡
ያለየነውን እዩ፣ ያልሰማነውን ስሙ አትበሉን፤ እውነቱን
እንነጋገር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ማመስገንና
ማወደስ መፈለጋችሁ በራሱ ችግር የለውም፡፡ ችግሩ
የሚመነጨው እውነትን ስትደፈጥጡና ሀሰትን ስታነግሱ
ነው፡፡ ኢህአዴግ ላለፉት ሃያ አንድ ዓመት ሲመራት ስለ
ቆየው አገራችን ኢትዮጵያ የምናውቀውንና በጥናት ላይ
ስለተመሰረተው እውነታዎች እንንገራችሁ፡፡
‹‹Forging Policy Magazine and Fund for
Peace›› የተባለ ድርጅት እ.ኤ.አ በ2ዐ11 ዓም በ177
አገሮች ላይ ያካሄደው ጥናት ውጤት እንደሚያሳያው
ከሆነ ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠል አደጋ ከሚያሰጋቸው
አገሮች መካከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት መካከል አንዷ
መሆኗን ይገልፃል፡፡ ለዚህም ምክንያቶቹ በሥልጣን
ላይ ያለው መንግሥት፡-
 በህዝብ መካከል ሠላም መረጋጋትና የጋራ
መግባባት መፍጠር ስለተሳነው፣
 በሕዝብ ተቀባይነትን አመኔታንና አክብሮትን
ስላጣ ፤
 ፍትሕን፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን
ስላልቻለ እንዲሁም
 የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ስለ
ተንሰራፉ ነው፤
‹‹ለቀባሪው አታርዱት›› አትሁኑብን አገራችንን
እናውቃታለን፣ እየኖርንባት ነው፡፡ እናንተ
አታውቋት ከሆነ ተጨበጭ ሀቆችን እንንገራችሁ፡
- Galoop የተባለ የድምጽ አሰባሳቢ የዓለም አቀፍ
ተቋም በ148 አገሮች ከሚገኙ እድሜያቸው 19
ዓመትና ከዚያ በላይ ባሉ ሰዎች ላይ በአደረገው
ጥናት በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ጎልማሶች
መካከል 46% የሚሆኑት ከአገራቸው በመሰደድ
ወደ ሌላ አገር ሄደው መኖር የሚፈለጉ ናቸው፡
፡ ይህም ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሥራ
አጥነት በእጅጉ የተንሰራፋ በመሆኑ ጭምር
ነው፡፡ በአዲስ አበባ ብቻ የሥራ አጡ ቁጥር
ለሥራ ከደረሰውና ሠርቶ ለመብላት ከሚፈልገው
የከተማው ሕዝብ አንፃር ሲታይ 5ዐ% ይሆናል፡
፡ ዛሬ ዛሬማ ከዚህም ይበልጣል፡፡
በሌላ በኩል ኢህአዴግ የአገራችን ኢኮኖሚ በየዓመቱ
11.2% እያደገ ነው ቢልም እውነቱና ሀቁ በቀን
አንድ ጊዜም ጠግቦ ለመብላት አለመቻሉ ነው፡፡ በዚህ
አጋጣሚ እንደ ቀልድ የሚነሳ የአኗኗር ዘይቤን መጥቀሱ
ሁኔታውን የሚያስረዳ ነው፡፡ ሰው በቀን አንድ ጊዜ
ስለሚበላ አመጋገቡን ‹‹ ቁምራ›› ይለዋል፡፡ ቁርስ፣ ምሳ፣
ራት ለማለት ነው፡፡
 የፕሬስ ነፃነትን በሚመለከት ከ188 አገሮች
በ139ኛ ደረጃ ትገኛለች ይህ ከሁለት ዓመት
በፊት ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ የነፃ ፕሬስ ሕልውና
ሙሉ በሙሉ በሚያሰኝ መልኩ እየጠፋ ነው፡
፡ ለዚህ ደግሞ እንደማስረጃነት ‹‹የአዲስ ነገር፣
አውራምባ እና ፍትሕ›› ጋዜጣን መዘጋት
መጥቀስ ይበቃል፡፡ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
ተመስገን ደሳለኝም በትላንትናው እለት የዋስ
መብት ተከልክሎ ታስሯል፡፡
በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩት
ዶናልድ ያማማቶ የተናገሩትና በዊኪሊክስ በኩል የወጣው
ሚስጥር የሚከተለው ነው፡፡ ‹‹ከ2005 ወዲህ በኢትዮጵያ
መንግሥት ዘንድ እየተጠናከረ የመጣው አድራጊ ፈጣሪነት
ተቃውሞን ያለማስተናገድ ዝንባሌና በኢኮኖሚው ውስጥ
የአይዲዮሎጂ›› (አብዮታዊ ዴሞክራሲ ለማለት ነው)
መንግስት በአገሪቱ መረጋጋት ላይ እና በአሜሪካ ጥቅም
ላይ ከፍተኛ ሥጋት ሆኗል›› ይላል፡፡ ይህ የዛሬ ሰባት
ዓመት ሲሆን ከ1997 ምርጫ በኋላ ኢህአዴግ በሕዝብ
ፍቃድ በስልጣን ላይ መቆየት የማይችል መሆኑን
በእርግጠኝነት በማወቁ ሁለንተናዊና አስከፊ የአፈና
ሥርዓት ዘርግቶ በሥራ ላይ አውሏል፡፡ ነፃ የሙያና
የሲቪክ ማህበራት እንዲፈርሱ ወይንም የእሱ ተለጣፊ
እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
ታዲያ ዛሬ በአገራችን ስለ ሰፈነው ዴሞክራሲ
የሚነገረን ከየት መጥቶ ነው? የአውሮፓ ህብረት ምርጫ
2ዐዐ2ን “ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ያላሟላ፣ በጫና
የተካሄደ፣ እኩል የመጫዎቻ ሜዳ ያልነበረው፣ የምርጫ
ሂደቱም ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ቆጠራ ችግር የነበረበትና
በአጠቃላይ ግልጽነት፣ ተዓማኒነት የጎደለው ፉክክር
በአልተካሄደበት የተደረገ ምርጫ” ብሎታል፡፡ እንዲሁም
የአሜሪካ ብሔራዊ ካውንስል ምክር ቤት ‹‹ያለ ነፃነት
የተካሄደ ምርጫ›› ብሎታል፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ
ስለየቱ ዴሞክራሲ ሥርዓት ነው ዛሬ የሚነገረን?
የኢህአዴግ አገዛዝ ኢትዮጵያን የምታክል
አገር ወደብ አልባ አድርጎ ‹‹ወደብ ሸቀጥ ነው›› ብሎ
የሚያፌዝ ነው፡፡ እኛ ደግሞ ወደብ የአገር ደህንነትና
ሕልውና ማስጠበቂያ፣ የኢኮኖሚ አውታር ነው እንላለን።

የኢህአዴግ ሥርዓት መገለጫዎች የሕግ የበላይነት
እጦት፣ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መደፍጠጥ፣
የመልካም አስተዳደር መጥፋትና የሙስና መንሰራፋት
ናቸው፡፡ ይህ በአለበት ሁኔታ በአገሪቱ እየተፈጠሩ
ያሉትን ችግሮችና ቀውሶችን ከሀቀኛ ተቃዋሚዎችና
የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ከሚሉ ባለድርሻዎች ጋር
በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይትና ድርድሮችን በማድረግ በሰከነ
አእምሮ ለመፍታት ጥረት ማድረግ ሲገባ ‹‹ጠቅላይ
ሚኒስትሩ የቀየሱት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች ወዘተ
ይቀጥላሉ፡፡›› ማለት አዋጭም ጠቃሚም አይደለም፡፡
የልማትና የእድገት መሠረቱ ሥራና እውነት ናቸው፡፡
እውነት ነው ብዙ ውሸቶች አንድ እውነት አይወጣውም፡፡
                                        
                             ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
                                                                 ከዘካሪያስ

No comments:

Post a Comment