Wednesday, October 31, 2012

አገርን መከፋፈል አይቻልም አይሳካም !!!



የተከበሩት ኔልሰን መንዴላ እንዲህ ይሉናል ”….. ፍቅር አብሮን የተወለደ በተፈጥሮ ያገኘነው ነው። ጥላቻ ግን በትምህርት ያገኘነው ነው። ስለዚህ ጥላቻን በትምህርት ልናስወግደው እንችላለን።….”። ግን በ’ኛ ሀገር ለወያኔ ገዥዎቻችን ጥላቻና ክህደት አብሮ’ቸው የተፈጠረ ይመስላል። ያለፈው አልበቃቸው ብሎ አሁንም የጥላቻንና የዘረኝነትን መርዝ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ ይረጫሉ። ”ለምን?..” ያለውን ደግሞ ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይገላሉ፣ ያስገድላሉ። እንደ’ነሱ ጠበንና አንሰን፣ ሀገራዊነትን አውግዘን፣ ስብእናችን ሁሉ ”ጎጠኝነት” አንዲሆን ሌት ተቀን ይደክማሉ። ለመሆኑ ከዘመናት በፊት ”ዘሬ የሰው ልጅ ነው፤ ሀገሬም ዓለም ነው።” ያለው ደራሲ (ስሙን ማስታወስ ስላልቻልኩ ይቅርታ።) በዚህ ዘመን ወያኔወችን እጅ ቢጥለው ምን ይል ይሆን? እነሱስ ምን ያደርጉት ይሆን?

በመጀመሪያ ‘ራሳቸውን ከዱ፣ ከዚያም በጥላቻ ታውሩ፣ ከዚያም ኢትዮጵያዊነትን ኢትዮጵያን አምርረው ጠሉ፣ ከዚያም በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየተመሩና እየታገዙ፣ የገንዛ ወገናቸውን ‘ርስ-በ’ርስ እያበጣበጡና እያለያዩ፣ ኢትዮጵያን እያፈራረሱ፣ ለባዕዳንና ለታሪካዊ ጠላቶቻችን እየቸበቸቡ አሁን ካሉበት ደረጃ ደረሱ። ወያኔ/ኢሕአዴጎች።
በቅርቡ የወያኔው ”የበኩር አባት” አቶ ስብሐት ነጋ ”….. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾመው ኢሕአዴግ ዱሮም አስቦበት ወንበሩን ከአማራና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድ ነበር……..” ሲሉ ተሰምተውል። ይህ በ’ርግጥ የለመደነው ክህደትና ሸፍጥ ነው። ታዲያ አኒህ ሰው ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ያላቸው ጥላቻ ይበልጥ በሽበታቸው ዘመን ስር እየሰደደና እየተባባሰ መምጣቱን ያሳያል። ብዙውን ግዜ በሌሎች ላይ ጥላቻ ያለባቸው ሰዎች ለራሳቸው ከሚሰማቸው የበታቸነት ስሜት የሚመጣ ሲሆን መድረኩንና አጋጣሚወን ሲያገኙ ደግሞ እንደወያኔ ሀገረንና ህዝብን ከማዋረድና ይዘው ከመጥፋት ወደ ኋላ አይሉም።
የአቶ ስብሐት የክህደትና የጥላቻ የበኩር ልጃቸው የሆነው አቶ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን አፍርሶና ሕዝቦቿ ‘ርስ-በርስ አባልቶ ሳይጨርስና ሳይሳካለት ወደ ማይመለስበት ስለሄደ፤ እሱ ያላያትን ”የፈራረሰች ኢትዮጵያን” እሳቸው ለማየት ካላቸው ጉጉት አንጻር የሚያደርጉትን አ’ተው ግራ ተጋብተዋል። ምክንያቱም ”ታላቋን ትግራይ” የመመስረት “ቅዥት”፣ “ቅዥት” ሆኖ እንደቀረ ሁሉ፣ ኢትዮጵያን የማፈራረሱም እኩይ ምግባራቸው ደግሞ ‘’ቅዥት’’ ሆኖ ሊቀር መሆኑ እንቅልፍ ነስቷቸዋል።
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ይ’ች ዓለማችን አስከ አለች ድረስ እንኖራለን። ይህ ሚሊዮን ግዜ ተነግሮ’ል። መነገር ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ዜጎቿ መሰዋአትነት ሲከፍሉበት ኑረዋል፤ አሁንም የተፈለገውን ያህል ውጤት ባያመጣም እየከፈሉ ይገኛሉ። ግን የወያኔ ገዥዎች ከልጅነታቸው እስክዚች ሰዓት ድራስ አእምሮ’ቸው በጥላቻና በተንኮል አድጎ፣ በክህደትና በዘረኝነት ጎልምሶ፣ ከሀገራችን ጠላቶች ጋር በማበር የኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማጥፋት እኩይ ዓላማ፣ በሽበት ዘመናቸውም ሆነ ”በትምህርት” ሊወገድ አልቻለም። አቶ መለስ ከነ ጥላቻቸውና ከነ ዘረኝነታቸው ሄደዋል። ቀሪዎቹ እነ አቶ ስብሐት ደግሞ ”ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል!” እንዲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን እንደ ምክንያት እያደረጉ ያመላቸውን “ዳቦ ይልሳሉ”።
የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለጠ/ሚኒስተር ስልጣን መድረስ ዋናው ምክንያት እንደሚከተለው ነው፤….
1/አቶ መለስ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ምክትል ጠ/ሚኒስተር ያደረጓቸው ኦሮሞና አማራ ነኝ ባይ ተለጣፊዎን ለማራቅ ነበር። ምክንያቱም በውቅቱ ሁለቱም ተለጣፊዎች የምክትልነቱ ቦታ ይገባናል በማለት ”ከሚስቶቻቸው” ጋር አልጋ ላይ ያንሾካሹኩ ስለነበር ነው። ታዲያ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከደቡቡ ተለጣፊ ቡድን በመሆናቸው እንደ መፍትሄ የተውሰደ ነው።
2/ አቶ ሃይለማርያም ወያኔን ”እንድ ግል አዳኛቸው” የተቀበሉ በመሆናቸውና አቶ መለስ የተናገሩትን መልሰው እንደ በቀቅን የሚያስተጋቡ ከመሆናቸው በተጨማሪ፤ ምንም አይነት ችግር የማይፈጥሩ ”ተነጅ” መሆናቸው ሌላው ምክንያት ነበር። አሁንም ”የመለስ ራእይ” እያሉ እየደነፉብን ነው። ለነገሩ የ’ራሱ ራዕይ ያለው ሰው ከመጀመሪያውም ወያኔ አይሆንም ነበር።
3/ ከአቶ መለስ ሞት በኃላ እነ አቶ ስብሐት አቶ ሃይለማርያምን ጠ/ሚኒስተር ለማድራግ ማቀድ ቀርቶ አልመውተም አያውቁም ነበር። የጠ/ሚኒስተርነቱን ቦታ ለወያኔ ተወላጅ ”ተገዳላይ” ለመስጠት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ነገር ግን የ’ርስ በርስ ሽኩቻው የወያኔን ህልውና እስከመፈታተን ደረሰ። ታዲያ እነ አቶ ስብሐት ”’ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾመው ኢሕአዴግ ዱሮም አስቦበት ነው…” ማለታቸውን ስሰማ በልጅነቴ የሰማሁትን ተረት አስታወሱኝ። ተረቱ እንዲህ ነው፤……ሁለት አብረው የሚኖሩ ወንድና ሴት ፍዬሎች ነበሩ። አንድ ቀን ውንድዬው ፍዬል የወይን ዛፍ አየና ወደ ዛፏ አመራ። የወይኑን ፍሬ ለመብላት ቢሞክር ሊደርስበት አልቻለም። እናም ‘ራቅ ብሎ ሄዶ ጋደም አለ። ሴቷ ፍዬል በተረዋ ወደ ወይኗ ዛፍ አዘገመች። የወይን ፍሬውን ለምብላትም ሞከረች። ግን አልቻለችም። ወደላይ ዘለለች። አልቻለችም። የፊት እግሮቿን ተጠቅማ ወደ ወይን ፍሬው ለመድረስ ሞከረች። አልቻለችም። ምንም ማድረግ እንደማትችል ስታውቅ ምራቋን እየዋጠች ወደ ጓደኛዋ ሄደች። እሱም ከርቀት ይከታተላት ነበርና ” እንዴት ነው የወይኑ ፍሬ?” ሲል ጠየቃት። ” እባክህ… ልበላ ፈልጌ ስቀምሰው የወይኑ ፍሬ ይመራል።” አለችው። እሱም ” አይ ያንች ነገር!….. ዘለሽ ..ዘለሽ ሲያቅትሽ ይመራል ትያለሽ።” በማለት መለሰላት። ታዲያ ዛሬ ወያኔዎች ”ዘለው..ዘለው… ሲያቅታቸው፣ የተሻለ ነገር መናገር አይችሉምና “ስልጣኑን ከአማራና ከኦርቶዶክስ ለማጽዳት ነው…” ማለት ሳይብቃቸው ‘’የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲ የበቃ አይደለም።” በማለት መዘላበዱን ተያያዙት።
3/ ወያኔዎች አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሳይፈልጉ ጠ/ሚኒስተር መሆናቸውን አማራጭ አጥተው ሲቀበሉ በ’ርግጥ ቢሳካላቸውም ባይሳካላቸውም ሁለት ነገሮችን እሳቤ ውስጥ አስገብተዋል፤
- የመጀምሪያው ጠ/ ሚኒስሩን ለዚህ ስልጣን የበቁት ባላቸው አፍቅሮ ወያኔ ስለሆነ፤ ከወያኔዎች ፈቃድ ውጭ ምንም የሚያደርጉት ነገር እንደሌለና ላድርግ ቢሉ እንኳ’ በቀላሉ ማስወገድ እንደሚችሉ ስለአመኑ።
- ሁለኛው እስከ ሚቀጥለው ምርጫ ድረስ የ’ርስ በርስ ሽኩቻዎችን ስለሚያስወግዱ ጠ/ ሚኒስሩን እንደ ግዜ መግዥ ሊጠቀሙባቸው በማሰብና በማቀድ ነው።
4/ ሌላው ደግሞ የአቶ መለስ ሞት ያስደነገጣቸው ገዥዎቻችን ግራ ሲገባቸው፤ በሁለት እግራቸው የቆሙ ለመምሰልና ሁሉም ነገር በ’ነሱ ቀጥጥር ስር መሆኑን ለማሳየት ሲሆን፤ የተለመደው አሳፋሪ ፓለቲካ ግን ወያኔ ተወልዶ ያደገበትን የኢትዮጵያን ጥላቻና እርስ-በ’ርስ ህዝብን የማባላት እኩይ የተለመደ ምግባር ለመግለጽ የታሰበ ነው። ክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “አቶ ስብሐተና የተነኮል ፓለቲካ” በሚል ርዕስ እንደገለጹት “…..አነጋገሩ በሁለት በኩል ስለት ያለው ቂል የያዘው ሰይፍ ነው።….” ግን ፕሮፌሰር ይህ ስለት ያለው ቂል የያዘው ሰይፍ ላለፉት ዓመታት ወግቶናል! ቆርጦናል! ከፋፍሎናል! አሁንም በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የተሳለው የቂል ሰይፍ መገዝገዙን ለማስቀጠል ደፋ-ቀና እየተባለ ነው።
ወያኔዎች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፈራረሱና ትውልድን የማጥፋቱ እኩይ ምግባር ሙሉ በሙሉ አለመሳካቱን ከቀንደኛ መሪያቸው ሞት በኋላ እንኳ’ ለራሳቸው ሲሉ ካለፈው ለመማርም ሆነ ለመጸጸት አለማሰባቸው ፕሮፌሰር እንደሚሉት ”ያሳዝናል” ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን፤ ሀገራችን ለማጥፋትና ለማውደም፤ አስፈላጊ ከሆነም ህዝብን ከመጨረስ በምንም አይነት መንገድ ወደ ኋላ እንደማይሉ ነው ደጋግመው እየነገሩንና እያሰረዱን ያሉት። ይሁን እንጅ ትላንት ዛሬ አይደልም፤ ዛሬም ነገ አይደለም።
…….ይዘገያል እንጅ ታሪክ ውል አይስተም
በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም።……
ምንም ይበሉ ምን፣ ወያኔዎችና ተከታዮቻቸው እየመረራቸውም ቢሆን መዋጥ ያለባቸው ሀቅ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከየትም ጎሳ ይምጡ፣ ምንም አይነት ሀይማኖት ይኑራቸው፣ ኢትዮጵያዊ አስከሆኑ ድረስ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የግል ማንነታቸውን ጥያቄ ውስጥ አያስገባውም። መግባትም ሆነ መታሰብም የለበትም። ኢትዮጵያዊነታቸው ከምንም በላይ በቂ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ብሄራዊ ጥቅማችን ያስጥብቃሉ ወይ? መብታችንና ነጻነታችን ያከብራሉ ወይ? በአጠቃላይ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ክብርና ልዕና መሉ ስልጣናቸውን (በህዝብ ያለተመረጡ ቢሆንም) ተጠቅመውና ሕግን አክብረው ይሰራሉ ወይ? ከወያኒያዊ አመለካከት የጻዳ አስተዳድር ይመሰርታሉ ወይ? በሚለው ላይ ነው ህዝብ ማውገዝም፣ ማወደስና መታገል የሚፈልገው። በ’ርግጥ እስከ አሁን ድረስ እንደታዘብነው ሰውየው ገና ”ከተገዥነትና ከተነጅንት’’ ያለመውጣታቸውን እያረጋገጡ ነው። የ’ኛም ትግል ይቀጥላል።የህዝቡም አንድነት ይቀጥላል !! አገርን መከፋፈል አይቻልም አይሳካም !!!
                ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

2 comments:

  1. no body separete sweet country !!!!!!! good articles...........

    ReplyDelete
  2. manem likefafelate ayichelem kidest hagerachenene enewedatalen sweet countryyyyyyyyyyyyyyyyyyyyyyyyy

    ReplyDelete