Friday, May 17, 2013

የምዕራባዊያንን ጋጠወጥ ፊልም ማየቱይሆን እንዴ ጋዜጠኞቻችንን እንዲህ እንዲባልጉ ያደረጋቸው?


የምዕራባዊያንን ጋጠወጥ ፊልም ማየቱይሆን እንዴ ጋዜጠኞቻችንን እንዲህ እንዲባልጉ
ያደረጋቸው? አዎን መጠርጠር ደግ ነው እኮ አንዳንዴ ምናልባትም ይሄ ማነው ኤሚኔም የሚባለውን ያበደ
ራፐር፡-
Mosh
Fuck bush...
Mr president
Mr senator
Fuck you all...
እያለ ‹‹mosh›› በሚል ቪዲዮው ላይ
ሲያቀነቅን ተመልከተውትና ይህን በማረጉም ሌላ
አንዳችም ነገር ሳይሆን American music award
(Amy)
Gramy እና MTV የሚሉ ዋንጫዎችን
ከረብጣ ሚሊዮን ዶላሮች ጋር ሲታቀፍና ወደ ቤቱ
ሲሄድ ጋዜጠኞቻችን ተመልክተው ይሆን ይሆናል
እንጂ ኋላ መች እንዲህ በዋዛ ከመንግስታችን ጋር
‹‹
መሰፋፈጥን›› ያበዙት ነበር።
እጁ የማያጥረው መንግሥታችን(የሚለው አምባገነኑ በሚለው ይስተካከልልኝ) እርግጥነው ቸር በመሆኑ በህገ-መንግሥቱ አንቀፅ 29
ላይ ጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆኑ ያሻው ዜጋ ያሻውን እንዲናገር ሀሳብን የመግለፅ መብት ‹‹እስከ
አፍንጫው›› እንዲጎናፀፍ ደንግጎ ይሆን ይሆናልብቻ ሳይሆን የግል ሚዲያዎች እንዲከፈቱ ፈቃድ
ሰጥቷል። በሌላም በኩል የመደራጀትና የመቃወም መብቶችም ለሰፊው ህዝብ ተሰጥተዋል። ይህ ማለት
ግን ጋዜጠኞች በዚህች ‹‹የህዳሴ ሀገር በምትባለው›› (ዘመኑየህዳሴ ነው አቦ) ላይ ልክ እንደ ኤሚኔም‹‹ጥሬ ካካቸውን ካካ ማድረግ›› እንደፈለጉ ይችላሉ ሊባልበፍፁም አይችልም።

ይህ ከመፈጠሩ በፊትና ነገሩ ሁሉ ጥሬ ካካ እንዳይሆን በሚል አልነበረም እንዴ መንግሥታችን
አዲሱ የፕሬስና የሲቪክ ማህበራት አዋጅ፣ አዲሱንየፀረ-ሽብር አዋጅ እንዲሁም በመገናኛ ብዙሀን ፈቃድ
አሰጣጥና አሰራር ላይ ጎታች ቅድመ ግዴታዎችን የማስቀመጡና በሀገር ደረጃ የማፅደቁን ስራ ልክ
ለእነዚህ ‹‹የቀበጡ ዕለት...›› ለሆኑ ‹‹ሞት እምቢ››ጋዜጠኞች ምሳቸውን መስጫ ፍቱን መድሃኒቶች
እንደሆኑ ሽንጡን ገትሮ የሚከራከረው። አዎንውይ ይህ ከሆነስ አይፈረድበትም መንግሥት ወዶ
አይደለምበቅኝ ግዛት የሚያስተዳድራት አገር ሆናለች እኮ የምር!!ስለጠኔአም ሚሊዮኖች ወገኖቻችን መርገፍንፍፁም ጀርባ ሰጥቶ ረስቶ ባለሥልጣናት ለውጪዲፕሎማቶች ስላደረጉት በሻምፓኝ ድግስ ስለታጀበ የአቀባበል ዝግጅት ጠዋት ማታ መዘገብ ማንን ገደለ?ባለሁለት ዲጂት የጥቂት ዓመታት እድገት እስከዓለምፍፃሜ ከአፅናፍ አፅናፍ በየሚዲያው ነጋሪት ማስጎሰም የሚችል ርዕሰ ዜና ሆኖ ሳለ በዚህች ሀገር ድህነቱ፣የኑሮ ውድነቱ፣ ስራ አጥነቱ ወይም ፖለቲካዊ ስነ-ምህዳሩ ከፋ ማለትን ምን አመጣው? (አዎን የዚህንዓ.ነገር ገሚስ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው ደግመነዋል)
ሌላው የሚዲያ ሰዎቻችን ግልጥልጥ ሊልላቸው የሚገባው ጉዳይ ባለፉት ትዝታዎች
መመሰጥን አቁመው ወደተጨባጩ ሀቅ መቅረብመቻል ያለባቸው መሆኑ ነው። አዎን ይህ ወቅት 97
. አይደለም ማንም ያሻውን የሚፅፈበትና ህዝብመረጃን በመፈለግና በማወቅ ማእበል እየተገፋ 1000
ኮፒ ሽያጭ ያላቸው የህትመት ውጤቶች በአንዴ 35እና 50 እትም እስኪደርሱ ድረስ ተነባቢ የሆኑበት
ደጉ ሊባል የሚችለው ጊዜ ላይመለስ (ይሁን አይሁንእንጃ ብቻ) ያለፈ ትዝታ ሆኗል።
ውዥንብሩ ሊጠራ ይገባል። እንደቀደመውጊዜ ‹‹ቀዩን መስመር›› አልፎ የሚገኝ ብእረኛ ሁላ ፀረ
መንግሥት /ህገ መንግሥት፣ ፀረ-ልማት/ ዲሞክራሲ፣የኒዮሊበራሊስት ኃይላት ወይም ሀገር አተራማሾች
በሚሉ የውርጅብኝ መአቶችና እንደገናም ድግግሞሹ በበዛ ይቅርታ የሚታለፉ ብቻ ሊሆኑ እንደማይችሉ
ግልፅና ግልፅ እየሆነ መጥቷል። የሚዲያ ሰዎቻችን‹‹ልማታዊ መንግሥት፣ በበሳል አመራር፣ በተሳኩ
ፖሊሲዎችና የልማት እቅዶች የሚመራ፣ ሀገሪቱን ወደ አደጉት አገራት ተርታ የሚያሰልፍ...›› ምናምን
የሚሉ ማቆለጳጰሻዎችን ወደዱም ጠሉ መከተብና መናገር እስካልቻሉ ድረስ እጣቸው መሰደድ፣ እስር
ወይም ጃሚንግ (የቦብ ዘፈን አይደለም) ይሆናልማለት ተራ ትንቢት ብቻ አልያም ውቃቢ የሚናገረው
ጉዳይ አይሆንም እናብቃ።አይ ወያኔ????????????????
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment