የሰው አገር የሰው ነው ማንም ሰው ከአገሩ ተሰዶ ቢኖር እንደራስ አገር መቼም አይሆንም ! ሰው በአገሩ፣ ሰው በወንዙ ተብሎ የለ? ሰው በአገሩ ላይ ቢጣላና ያለመግባባት ቢፈጠር፣ በዚያው በመንደሩ፣ በአካባቢውና በአገሩ ይዳኛል፡፡ እርቅም ይወርዳል ከዚያም የተለመደው ማኅበራዊ ግንኙነታቸው እንደነበር ይቀጥላል፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘው በጋራ ማደግና መበልፀግ ዕጣ ፈንታቸው ይሆናል፡፡
ሰሞኑን ከአሜሪካን የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ውድድር የቀሰምነው ትልቅ ቁም ነገር ዲሞክራሲ በተወለደበት ቀየ ምን ያህል ክብርና ሞገስ እንዳለውና ዲሞክራቶችን ምን ያህል እንዳረካ የተገነዘብን ይመስለኛል፡፡ ሁለቱ እጩ ተወዳዳሪዎች አሜሪካንን ለመምራት፣ ለሕዝቡ ራሳቸውን ለማስተዋወቅና የሕዝብ ድምፅ ለማግኘት ባደረጉት ዱላ ቀረሽ የቃላት ጦርነት ብዙ ብዙ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በሁለቱም ተፎካካሪዎች መካከል የነበረውን የቃላት ጦርነት በሚገባ ተከታትለናል፡፡ ዘለፋ፣ ስድብ፣ ወቀሳና ከዚያም አልፎ እስከማዋረድ የተቃጣ የቃላት ምልልሶች ነበሩ፡፡ ከሁለት አንደኛው ተወዳዳሪ በሥልጣን ላይ እንደመሆናቸው፣ አሜሪካን አገር ባይሆንና የዲሞክራሲን ጽንሰ ሐሳብ የተረዳ አገር ባይሆን ኖሮ ቢያንስ በሥልጣን ላይ የተቀመጡት ለዘለፋው ዱላ መምዘዛቸው አይቀሬ ነበር፡፡
በተቃዋሚው ተፎካካሪ ላይ ሲሰነዘር የነበረው የቃላት ውርጂብኝ ዲሞክራሲ በቀጨጨበት አገር ላይ ቢሆን ኖሮ፣ መዘዙ ምን ያህል እንደሚከብድ ሩቅ ሳንሄድ ከዚሁ ከአገራችን መልሱን ማግኘት ይቻላል፡፡ ዲሞክራሲ ለሰላም፣ ለብልፅግና፣ ለዕድገትና ለአንድነት እንደሚውል ከአሜሪካ ሕዝብና መንግሥት ቢቀዳ ኃጢያት የለውም፡፡
የተፎካካሪዎቹ ዓላማ ለአገር አንድነት፣ ለልማት፣ ለብልፅግናና ለደኅንነት ብቻ መሆኑን በግልጽ አሳይተዋል፡፡ ተቃቅፈው ወደ ንትርክ ይገባሉ፤ ከንትርክ በኋላ ተቃቅፈውና ተሳስመው ይለያያሉ፡፡ ውድድሩ ተጠናቅቆ አሸናፊው ሲታወቅ በሕዝብ ድምፅ የወደቀው ተወዳዳሪ አሸናፊውን አቅፎ ስሞ አሜን ብሎ መቀበሉን በማረጋገጥ በሰላም ይሰናበታል፡፡
እንዴት ያስቀናል? ምን የታደለ አገር ነው? መቼ ይሆን የአገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች ከግል አመለካከት ወጥተው ወደ አገር አንድነት የሚመለሱት? እባካችሁ ስለኢትዮጵያ አምላክ ብላችሁ እስቲ ከአሜሪካን ሕዝብ ትምህርት ውሰዱ፡፡ ውድ የአገራችን ህዝቦች የዲሞክራሲን ጉዞ ለመጀመር በመጀመሪያው የመወጣጫ እርከን ላይ ትገኛለች፡፡ ረዥም ጉዞ ይቀራታል፡፡ መንገድ የመምራት ኃላፊነት አለባችሁ፡፡ ስለዚህ ጐዳናው የተቃና ይሆን ዘንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ዓላማ ለሕዝብ አቅርባችሁ አወያዩ፤ አስተምሩ በርቱ ተበራቱ፡፡
‹ኢትዮጵያን አምላክ ይጠብቃት›
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!
ከዘካሪያስ

No comments:
Post a Comment